Wednesday, December 31, 2014

የመሰናዶ ተማሪዎች የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሙ አሰሙ

• በሶስት ከተሞች ረብሻዎች ተነስተዋል

(ነገረ-ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቁመው እንዲወስዱ የተደረገውን የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ምንጮን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በስልጠናው ወቅት የህዝቡ አስተሳሰብ፣ የግል ሚዲያ፣ ተቃዋሚዎች ለኢትዮጵያ እድገት ጠንቅ ተደርገው የቀረቡ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አቀራረብ ተቃውመውታል።  በአንጻሩ ከወራት በፊት ስልጠናውን የወሰዱት መምህራንም ዳግመኛ ስልጠናውን እየወሰዱ ቢሆንም ዝምታን መምረጣቸው ተገልጾአል። 

Tuesday, December 30, 2014

የኢንተርኔት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ


በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክን በመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። 


የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም የሕትመት ሚዲያውን የሚመለከት ነው።  በዚህ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንተርኔት ድረገጾች ፈቃድ ማውጣት የግድ መሆኑን ደንግጎአል።  


በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል የመረጃ መረብ አማካኝነት ለስርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ፕሮግራም በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል ፣በአገር ደህንነት፣ ክብርና ጥቅም ላይ ጉዳት የሚያደርስ ፣የአገር ሚስጢርን የሚገልጽ ፣ አመጽና ጦርነትን የሚቀሰቅስ፣ የሰው ልጆችን ስብዕና ፣ነጻነት ወይንም ስነምግባር የሚጻረር ፣የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ መሆን እንደሌለበት ደንግጎአል። 

Wednesday, December 24, 2014

ኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዘው የጠፉት አብራሪዎች ቤታቸው ተፈተሸ


ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል ደህንነቶች ወደ ጠፉት አብራሪዎች ቤት በድንገት በመሄድ ፍተሻዎችን ያካሄዱ ሲሆን፣ በቤቶች ውስጥ የተገኙ ሰነዶችን፣ የበረራ ማኑዋሎችን፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን፣ ትጥቆችንና ሌሎችም ቁሳቁሶች ወስደዋል።

ከደህንነቶች ጋር ምንም አይነት ፖሊስ ያልነበረ ሲሆን፣ ደህንነቶች ፍተሻውን ለማካሄድም የፍርድ ቤት ማዘዣ አላሳዩም። የመከላከያ ሰራዊት ባወጣው መግለጫ ሁለቱ አብራሪዎች በዋናው አብራሪ ተገደው መጥፋታቸውን ቢገልጽም፣ ከዋና አብራሪው ውጭ ያሉት ረደት አብራሪውና ቴክኒሻኑ ቤታቸው እንዲፈተሽ መደረጉ፣ ሚኒስቴሩ የሰጠው መግለጫ የተሳሳተ መሆኑን እንደሚያመለክት ምንጮች ገልጸዋል።

Tuesday, December 23, 2014

የፀጋዬ በርሔ ቪላ ተሸጠ – ከኢየሩሳሌም አረአያ


የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በኋላ የፌዴራል ደህንነት ዋና ባለስልጣን የሆኑት የሕወሐት ፖሊት ቢሮ ባል አቶ ፀጋዬ በርሄ በመቀሌ ልዩ ስሙ “አፕርታይድ መንደር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ያስገነቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አረጋገጠዋል። 10 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደፈጀ የሚነገርለት የአቶ ፀጋዬ ቪላ ለአንድ ባለሃብት 25ሚሊዮን ብር እንደተሸጠ ቢነገረም በትክክል የተሸጠበትን ዋጋ ማወቅ እንዳልተቻለ ምንጮቹ አስታውቀዋል። ፀጋዬ በርሄ የቅዱሳን ነጋ ባለቤት ሲሆኑ ቅዱሳን የስብሃት ነጋ ታናሽ እህት ናቸው።የመቀሌ ነዋሪ “አፓርታይድ መንደር” የሚል ስያሜ በሰጠው በዚህ ቦታ ከአቶ ፀጋዬ በርሄ በተጨማሪ አቦይ ስብሃት ነጋ በራሳቸውና በመጀመሪያ ልጃቸው ስም ሁለት ቪላዎችን ሲያስገነቡ ቴዎድሮስ ሃጐስ፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጎበዛይ ወ/አረጋይ፣ ተክለወይኒ አሰፋ ዘመናዊ ቪላዎችን ካስገነቡ የሕወሐት ባለስልጣናት ሲጠቀሱ ኪሮስ ቢተው በሰባት ሚሊዮን ብር ወጪ በዚሁ ስፍራ ያስገነቡትን ቪላ ከ9 ወራት በፊት መሸጣቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል። በሌላም በኩል የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበሩት የሕወሐት አባል ጄ/ል አበበ ተ/ሃይማኖት (በቅፅል ስማቸው ጆቤ) በቦሌ ያስገነቡትን ቪላ በ24 ሚሊዮን ብር መሸጣቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

Monday, December 15, 2014

ሕወሐት /ፂዮንን // ለማድረግ አቅዷል  የአዜብና የደህንነቱ ሹም ያልታሳካ እቅድ

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የጠ/ሚ/ር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ፣ ፀጋይ በርሔ፣ አርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ የሚመራው የሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ ቀደም ሲካሂዱት በነበረውና ህወሀት የጠ/ሚ/ ርነት ስልጣን መልሶ መያዝ ይኖርበታል፣ የሚለውን ምክክር ከዳር ለማድረስ አቋም መያዘያቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ በተለይ በቅርቡ የተካሄደው የአራቱ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በብአዴንና ኦህዴድ በኩል ቅሬታና ተቃውሞ እየበረታ በመምጣቱ የሕወሐት አመራሮች ስልጣኑን በእጃቸው ለማስገባት ቆርጠው መነሳታቸውን አስረድተዋል። 

በብአዴን በኩል የአቶ በረከት ስሞን ከስልጣን መገፋት በደጋፊዎችቻቸውና አመራሩ በኩል ቅሬታ መፍጠሩን የጠቆሙት ምንጮቹ በረከት ስሞን የጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም አማካሪ ተብለው ቢሾሙም ነገር ግን በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ እንዳልተሰጣቸውና የተሰጣቸው ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው የቀድሞ የደህንነት ቢሮ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀው በዚህ ቢሮ ኩማ ደመቅሳ እንደሚገኙና በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት አዲስ ቢሮ ተገንብቶ ይሰጣችኋል የተባለው ተግባራዊ እንዳልሆነ አያይዘው አስረድተዋል።

Wednesday, December 3, 2014

ዘጠኙ ፓርቲዎች ለቀጣይና ለቀሩ ስራዎቻቸው ያወጡትን እቅድ በተመለከተ መግለጫ ሰጡ።እንዲሁም የህዳር 27 እና 28 የተቃውሞ ሰልፉን እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።


ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን  ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል። 

“በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ ” ማስገባቱንም ገልጸዋል።

የፓርቲዎቹ መግለጫ አያይዞም “ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ በመሆኑ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና  ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28  ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን።” ብሎአል። 

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ኑ- ለነጻነታችንና ክብራችን ድምጻችንን በጋራ እናሰማ!

ከባርነትና ውርደት ለመላቀቅ ነውና በፍጹም አይቀርም፣ አይቀርም!

የ9ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ ››በሚል መርህ የመጀመሪያ ዙር ዕቅዱን ለህዳር ወር አዘጋጅቶ ወደ እንቅስቃሴ ከገባ ሦስት ሣምንታትን አሳልፏል።  

Monday, December 1, 2014

ህጋዊ ተቃዋሚዎችን በአክራሪነት ሰበብ ለመምታት የሚያስችሉ ሃሳቦች ቀረቡ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 መሰረት በህጋዊ መልኩ ተመዝግበው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቃስቃሴ የሚያደርጉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በሽብርተኝነት እና ጽንፈኝነት በመፈረጅ የጥቃት ኢላማ ለማድረግ መታሰቡን ኢሳት የፌደራል መንግስት የጸጥታ ጉዳዮች ሰሞኑን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር  ካካሄደው ውይይት ለመረዳት ተችሎአል።

የትግራይ፣ቤንሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል ሃላፊዎች ሰማያዊ ፣አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ጽንፈኞች በመሆናቸው በአክራሪነት ሲሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን በማሰባሰብ ለሽብር እያዘጋጁ ነው በማለት የገዢውን መንግስት ፖሊሲዎች በሰላማዊ መንገድ የሚቃዎሙትን ፓርቲዎችን በወንጀለኛነት ሲፈርጁ ተደምጠዋል። 

መልካም ተሞክሮ ነው በማለት በየክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ኃላፊዎች የቀረበው ሪፖርትና የወደፊት እንቅስቃሴ በመጭው ምርጫ 2007 የተፈረጁት ፓርቲዎች የህዝብ ድምጽ በማግኘት የገዢው መንግስት ስጋት እንዳይሆኑ ከማሰብ የተነሳ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። 

ተመስገን ደሳለኝን ተቀበልኩት (ሕገ-መንግስት ሆይ የት ነው ያለኸው?)

ከክንፈሚካኤል ደበበ በረደድ (አበበ ቀስቶ)
ከዝዋይ ወህኒ ቤት

ቀኑ ቅዳሜ በመሆኑ ቤተሰቦቻችን እኛን ለመጠየቅ /ፈርዶባቸው የለ/ ወደ ዝዋይ ወህኒ
ቤት የሚመጡበት ሰዓት ደርሶ፣ ተጠርተን እንደወጣን፣ ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ የጠየቅናቸው
ነገር ቢኖር፣ ምን አዲስ ነገር አለ የሚለውን የተለምዶ ጥያቄያችንን ነበር፡፡
በዕለቱም የመጣልን የምስራች ልበለው ዜና አሊያም መርዶ ጋዜጠኛ ተመስገን ሦስት
(3) ዓመት ተፈረደበት የሚል ነበር፡፡ በዜናው አልተደነቅንም፤ አልተገረምንም፤ ምክንያቱም
በሥልጣን ላይ ያለው የህወሓት /ኢህአዴግ/ አምባገነን መንግስት፣ ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ ሌላ ሊሸልመው
የሚችለው መልካም ሽልማት /ሜዳሊያ/ የለውምና፡፡ በነገራችን ላይ ዜናው ለኔ ፍጹም አልገረመኝም፤ እገረም የነበረው
አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ተመስገንን በነጻ ቢለቀው ነበር፡፡
የሆነው ሆኖ፣ ከቤተሰብ ጥየቃ ተመልሰን ገና ምሳ በልተን አረፍ እንዳልን ግን፣ የሰማነውን ዜና እውነታ በአካል
የሚያረጋግጥልን አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ፍራሹን ተሸክሞ እኛ አለንበት ጭለማ ቤት /የቅጣት ቤት/ ድረስ
መጣ፡፡ ዓይኔን ማመን እስቲያቅተኝ ድረስ ተጠራጠርኩ፤ ግን ሆነ፡፡ ተመስገን መጣ፡፡ እናም ውለን ሳናድር ተመስገን
ደሳለኝን ተቀበልኩት! እነሆ ተመስገን ዝዋይ ከመጣ ዛሬ 15 ቀን ሆነው! ... ሕገ-መንግስት ሆይ የት ነው ያለሽው!?
ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዳሉ፤ እግረ መንገዴን እስቲ አንድ ገጠመኜን ደሞ ላጫውታችሁ፡፡ ህወሓት
/ኢህአዴግ/ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ፣ በሁኔታው ያልተደሰትን ጓደኛማቾች ተሰባሰበን፣ ከኛ ቀድመው ከብላቴ
ወታደራዊ ማሰልጠኛ ተቋም ወደ ኬንያ የተሰደዱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችንና ሌሎች ወገኖቻችን ተቀላቅለን ለመታገል
በመወሰናችን ተሰባስበን፡፡ ወደ ኬንያ የስደት ጉዞ ጀመርን፡፡ ይህ የሆነው ግንቦት 23 ቀን 1983 ዓ.ም ከሃያ ሦስት ዓመት
በፊት ነው፡፡

Saturday, November 15, 2014

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ታሰሩ


በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ለእሁዱ የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የታሰቱትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄዱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታሰሩ። 
በቅስቀሳ ወቅት የነበሩት የሰማያዊ አባላትና አመራሮች መያዛቸውን ተከትሎ የእሁዱን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ለስበስባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ያሳወቁበትን ህጋዊ ደብዳቤ በመያዝ የአባላቱና አመራሩ እስራት ህገ ወጥ መሆኑን ለማስረዳትና አባላቱን ለመጠየቅ ወደ አራዳ መምሪያ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ የፋይንስ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወሮታው ዋሴ እና የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል። 

በቅስቀሳ ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እየታሰሩ ነው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር እሁድ ህዳር
7/2007 ዓ.ም ለሚያደርገው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ታሰሩ።

Tuesday, November 11, 2014

ግልጽ ደብዳቤ ”ለጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለማርያም ደሳለኝ : ከታሳሪ ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች


ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስታችንን ያክብሩ!

ሠላም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!? እንዴት ነዎት? ያስታውሱ ከሆነ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢከፊሉ የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች  ‘ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ’


“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እባክዎትን የተለያዩ የመንግስት አካላት የሕገ መንግስታችንን ድንጋጌዎች እየጣሱ ነውና እርስዎም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 74/13/ መሠረት ሕገ መንስቱን የማስከበርና የማክበር ግዴታ ስላለብዎት ሕገ መንግስቱን ያክብሩ” በማለት አንዲት አጭር ደብዳቤ ፅፈንልዎት ነበር፡፡


ድንገት በተለያዩ ምክንያቶች የጻፍንልዎትን ደብዳቤ ካላነበቡት ወይም ማስታወስ ካልቻሉ ዛሬ ይሄን ማስታወሻ ስለምንፅፍልዎት ግለሰቦች አንድ ሌላ ማስታወሻ እንስጥዎ፡ ከ6ወራት በፊት /በሚያዚያ 2006 ዓ.ም/ ሶስት ጋዜጠኞችንና ስድስት ጦማሪያንን ‘ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር ወንጀል ጠርጥሬያችኋለሁ’ በማለት መንግስትዎ ልማታዊ ርምጃ (አብዮታዊ ርምጃ እንደሚባለው) ወስዶ ነበር፡፡

Friday, November 7, 2014

እሥሩ ተጧጡፏል፣ አንድነት ምርጫ እንዳይወዳደር አገዛዙ ይፈልጋል


ግርማ ካሳ

ዜጎች መታሰራቸው እየቀጠለ ነው። በተለይም የአንድነት ፓርቲ አባላት (በጎንደር፣ በትግራይ፣ በመቱ፣ በአዲስ አበባ ፣ በወላይታ ….) ። ብዙዎች ከፍተኛ ደብደባ እየደረሰባቸው ነው። ሕወሃት ፣ በሕዝብ እንደተጠላ ስላወቀ የአንድነት ፓርቲ እንዲዳከም ወይም ከምርጫው ዉጭ እንዲወጣ እየሰራ ነው። አንድነት ሊያሸንፈው እንደሚችል ስላወቀ።

የድርጅቶች መተባበር አስፈላጊ በመሆኑ፣ አንድነት ከመኢአድ ጋር ተስማምቶ የቅድመ ዉህደት ስምምነት ፈርሞ ነበር። ሁሉም ነገር አልቆ ነበር። ሆኖም ምርጫ ቦርድ ወይንም አገዝዙ፣ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ዉህደቱን አስቁሞታል። ይኸው እስከአሁን ድረስ በአቶ አበባው ለሚመራው መኢአድ እውቅና አልሰጠም ብሎ መኢአዶችን ምርጫ ቦርድ እያጉላላቸው ነው።

የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ በድርጅቱ ሕገ ደንብ መሰረት፣ አዲስ አመራር መርጦ መንቀሳቀስ መጀመሩም ይታወቃል። ሆኖ ምርጫ ቦርድ/ ሕወሃት ፣ በንድነት ዉስጥ አስርጎ አስገብቷቸው ከነበሩን በአንድነት እንዲራገፉ ከተደረጉት 2፣ 3 ግለሰቦች ጋር በመመካከር፣ እንደገና ለአዲሱ የአንድነት አመራር እውቅና አልሰጠም እያለ ነው። (የዛሬዉን ሰንደቅ ያንብቡ) ምናልባትም መኢአድ እና አንድነት ከምርጫዉ ሊያግዳቸው፣ አሊያም የነርሱን ሰርተፊኬት፣ ቅንጅትን ለአየለ ጫሚሶ እንደሰጠው፣ ለነ ማሙሸትና እና ለነ ዘለቀ ረዲ ሊሰጣቸውም ይችልም ይሆናል።

Thursday, November 6, 2014

መልዕክት ከቃሊቲና ከቂሊንጦ


ነገረ ኢትዮጵያ

የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ የዝግጅት ክፍል አባላት ወደ ቂሊንጦና ቃሊቲ እስር ቤቶች በማቅናት እስረኞችን ጠይቀዋል፡፡ እስረኞቹ ያስተላለፉትን መልዕክት ነገረ ኢትዮጵያ እንደሚከተለው ጠቅለል አድርጋ አቅርባዋለች፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አይቀርም›› እስክንድር ነጋ

በማህበራዊ ድረ-ገጽም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች መልካም ልደት ለተመኛችሁልኝ ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ የቡርኪናፋሶው አምባገነን መውደቁን በመስማቴ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ይህ ለእኔ ውድ የልደት ቀን ስጦታየ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ለውጥ የሚቀር አይደለም፡፡ የእኛ ችግር ከማንም የባሰ ነው፡፡ ቱኒዚያ ላይ የተጀመረው አብዮት ሰሜን አፍሪካ አንቀጥቅጧል፡፡ ኢትዮጵያ ከሰሜን አፍሪካ አገራት ይልቅ ለእነ ቦትስዋና ትቀርባለች፡፡ የቦትስዋና ጉዳይ ሌሎቹንም ማነቃነቁ የማይቀር ነው፡፡ ይህ ለውጡ ቅርብ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አይቀርም፡፡
‹‹ቂሊንጦም ገደብ አለብኝ›› አብርሃ ደስታ

Monday, November 3, 2014

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር “የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ እራስህን ከወያኔ አሽከርነት(መጠቀሚያነት) ልታርቅ ይገባል” አለ


በህዝብ ላይ የሚደርሰው ጭቆናና እርዛት እስከመቼ?

ከኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ የተሠጠ መግለጫ

የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ዘወትር ስልጣናቸውን ለማራዘም ካላቸው ነቢራዊ ፍላጎት የተነሳ በህዝብ ላይ ግድያ እና እስር ከመፈፀም አልፈው ሐገራችን ኢትዮጵያን ከማትወጣበት ማጥ ውስጥ ለመክተት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ በቅርቡ እንኳን በአሶሳ ከተማ ንፁሀን የትግራይ ወጣቶች ማንነታቸው እስካሁን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል ይኸውም መንግስትእየተከተለው ብልሹ የዘውግ አስተዳደር ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ እየታየ ነው በሌላ በኩል ይህ ግድያ መንግስት እራሱ የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሠለፍ በማሠብ እንደገደላቸው ግምታቸውን አስቀምጠዋል እንደምክንያት የጠቀሱት ምርጫ 97ን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ መንግስት ተቃውሞውን ለማባባስ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከቀድሞዋ የትምህርት ሚኒስቴር ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ግቢ ወደውጭ ቦንብ በመወርወር 6 ፖሊሶችን በመግደል ፖሊሶችን ለማነሳሳት እና ህዝቡን ለማሳሳት ቢሞክርም በመጨረሻ ጉዳዩን የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋ ሲያወጣው የመንግስት ሴራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአሶሳው፣ የአምቦው፣ የጎንደሩ እና የወለጋው ግድያም ከዚህ የተለየ አይሆንም፡፡

Friday, October 31, 2014

ፕሬስ በዘመነ ወያኔ

ፕሬስ(Press) ራሱን ለመግለጥ ከተፈቀደለትና ከተመቻቸለት መንግሥት አገርን በአግባቡ እንዲመራ የሚያግዝ ታላቅ የመርጃ መሣሪያ እንጂ ፀረ-መንግሥት አቋምም ሆነ ሚና የለውም። ፕሬስ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን አስተዋጽዖ ከማድረጉም በላይ፤ የመንግሥትንም ሆነ የድርጅቶችን፤የግለሰቦችንና የአጠቃላይ ዜጎችን በጎ ጎን በማጉላት ለሕብረተሰቡ ይፋ በማድረግ ከፍተኛ ድርሻ አለው። ከብዙ በጥቂቱ ነጻ ፕሬስ ሙስናንና ስግብግብነትን በመዋጋት ኢሰብአዊ ድርጊቶችን ያጋልጣል፥የሕዝብን የበላይነት ያስረጋግጣል፥ እንዲሁ የሥልጣን ክፍፍልንና ሕዝባዊ የፖለቲካ ተሳትፎን ያዳብራል። ከዚህም ባሻገር በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት የአገሪቱ ሕገ መንግስ በሚደነግገው መሰረት ሕዝብን ያለምንም አድልዎና በደል እያስተዳደረ መሆን አለመሆኑን ለሕዝብ ያስተጋባል። የፕሬስ አገልግሎት ላወቀበትና በአግባቡ ለተረዳው አወንታዊው አስተዋጽኦ ብቻ ሳይሆን አሉታዊውና ነቀፋው እንኳን ሳይቀር ገምቢ ነው። ስህተትን እየጠቆመ፥ጠማማውን እያቀና መንግሥትንም ቢሆን ለአስተዳደር ጥራት ያሰናዳል እንጂ አንድም ጉዳት የለበትም።  

ስለዚህ ፕሬስ ማለት የሕዝብን ሰብአዊ መብቶች በአግባቡ እየጠበቀ የሚያስጠብቅ  የወቅቱን ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታዊ እውነትና ሂደት እየተከታተለ ለሕዝብ የሚያቀርብና ለዲሞክራዊ እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ተግባራዊ ተቋም ነው። እንዲህ ያለው ነባርዊ ሐቅ ለወያኔዎች ባይዋጥላቸውም ቅሉ፤ የተባለለትም ሆነ የሚባልለት ሁሉ የፕሬስን የከበረ ዋጋ የሚመጥን አይደለም።

Thursday, October 23, 2014

መልዕክት ስለተመስገን ደሳለኝ ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ



 ‹ ተመስገን፣ ጥሩ ታጋይ እና ሰው ሆኖ ለእስር ይወጣል››
‹‹ተመስገን፣ የህዝብ ልጅ ነው፤ ነገም ከነገወዲያም የህዝብ ልጆች ይፈጠራሉ››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ‹‹ስለተመስገን ደሳለኝ ሃሳቤን አስተላልፍልኝ›› ካለኝ የተወሰደ
ከትናንት በስትያ፣ ሰኞ ዕለት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆነውን አቶ አንዷለም አራጌን በ2007 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ላገኛቸው ችዬ ነበር – ለአቤል አለማየሁ ጋር፡፡ ባለፈው ሳምንት የ‹‹ባንዲራ ቀን››     በተከበረበት ዕለት ቃሊቲ ከወዳጄ እዩኤል ፍስሐ ጋር ሄጅ እነስክንድርን መጠየቅ ሳንችል ተመልሰን ነበር። 

Tuesday, October 21, 2014

ኤልያስ ገብሩ ዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተጠራ



ደስ ባለው ጊዜ ክስ የሚቀሰቀስ መንግሥት
እንግዲህ፣ ‹‹ማዕከላዊ ናና ክስህን ውሰድ›› ተብያለሁ

ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ሞባይል ስልኬ አቃጨለች፡፡ ከጎኔ ወዳጄ አቤል አለማየሁ ነበር፡፡ የመስመር ስልክ ነው፡፡ አነሳሁት፡፡ ‹‹አቶ ኤልያስ›› የሚል የሴት ድምጽ አደመጥኩ፡፡ ‹‹አዎን›› በማለት መለስኩላት፡፡ ‹‹ቆይ አንዴ መስመር ላይ ጠብቅ›› አለችኝ፡፡

ወዲያው አንድ ወንድ አነሳና ሰላምታ ሰጥቶ አናገረኝ፡፡ የሚደውለው ከፌዴራል ፖሊስ መሆኑን ጠቆመኝና ‹‹ባለፈው ተቋርጦ የነበረው ክስህ ስለተዘጋጀ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ቁጥር 76 መጥተህ ውሰድ›› አለኝ፡፡ ስለጉዳዩ ጥቂት ቃላቶች ተለዋወጥን፡፡ 

Friday, October 17, 2014

ሰማያዊ፣ መኢዴፓና ኢብአፓ የምርጫ ቦርድን ስብሰባ ረግጠው ወጡ


ከደቡብ ኅብረት ፕሮፌሰር በየነ ተመሳሳይ እርምጃ ወስደዋል


ምርጫ ቦርድ በጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመወያየት በጊዮን ሆቴል የጠራውን ስብሰባ “ጥያቄዎቻችን የሚመልስ አይደለም” በሚል የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ በተጨማሪም የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) ተወካዮች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል፡፡ ፓርቲዎቹ በትናንትናው ዕለት ከምርጫ 2007 ዓ.ም በፊት ውይይት ሊደረግባቸውና ሊፈቱ ይገባል ያሏቸውን ጥያቄዎች ለምርጫ ቦርድ ያስገቡ ቢሆንም በዛሬው ስብሰባ በደብዳቤ ካሳወቋቸው ችግሮች ይልቅ የጊዜ ሰሌዳ ቅድሚያ የተሰጠው በመሆኑ የምርጫ ምህዳሩን ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም ብለው ስብሰባውን ረግጠው መውጣታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ የጠራውን ስብሰባ ረግጦ ወጣ




• ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ምህዳር እንዲኖር እንስራ የሚለው ጥያቄ ተቀባይነት አላገኘም
ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ጥቅምት 7/2007 ዓ.ም በ2007 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀውን 5ኛው አገራዊ ምርጫ በተመለከተ ከአገራዊ ፓርቲዎች ጋር ለመወያየት በጊዮን ሆቴል የጠራውን ስብሰባ ረግጦ ወጣ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ስብሰባውን ረግጦ የወጣው የምርጫ ቦርድ ምርጫው ፍትሃዊ እንዲሆን መስራት ያለበትን ነገሮች ሳይሰራና ፓርቲዎችም ያሉባቸውን ችግሮች አቅርበው መወያየት ሳይችሉ ስለ ጊዜ ሰሌዳ ማውራቱ አስፈላጊ አይደለም በሚል መሆኑን ስብሰባውን ለመሳተፍ ሄደው የነበሩት ተወካዮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡



በስብሰባው ላይ የተገኙት የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ስለ ጊዜ ሰሌዳው ከመወያየት በፊት ለምርጫ የሚያበቃ ምህዳር እንዲኖር በመስራት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቁ ሲሆን በ1997 ምርጫ ወቅት ፓርቲዎች ያሉባቸውን ችግሮች በዝርዝር መወያየታቸው ቢያንስ ቅድመ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ማገዙን ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ከ1997 ምርጫ በኋላ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች ችግራቸውን በዝርዝር በመወያየት፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለማካሄድ ስለሚያስችሉ ጉዳዮች መነጋገር ባለመቻላቸውና ምርጫ ቦርድም በጉዳዩ በህገ መንግስቱና በአዋጁ የተሰጠውን ኃላፊነት ባለመወጣቱ የፖለቲካ ምህዳሩ እንደተዘጋም በመግለጽ ምርጫ ቦርድን ወቅሰዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በ2005 የአዲስ አበባ፣ የድሬዳዋና የአካባቢ ማሟያ ምርጫዎች በፊት ምርጫ ቦርድ ኃላፊነቱን ሳይወጣ አዳማ ላይ ‹‹ስለ ጊዜ ሰሌዳው እንወያይ›› ብሎ ስብሰባ በጠራበት ወቅት ‹‹መጀመሪያ ለምርጫ የሚያበቃ ምህዳር እንዲኖር መወያየት አለብን›› ብለው ጥያቄ ቢያቀርቡም ቦርዱ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከምርጫው ራሳቸውን ማግለላቸውን ገልጸው በዚህ አመትም ለምርጫ የሚያበቃ ምህዳር እንዲኖር እንደሚፈልጉ አሳስበዋል፡፡

Monday, October 6, 2014

የአዜብ ዱላ በሰሎሞን አስመላሽ ላይ…


ከአርአያ ተስፋማሪያም

ጋዜጠኛ ሰሎሞን አስመላሽ ለብዙዎች እንግዳ አይደለም። የ120 መዝናኛ አዘጋጅ ነበር። ከኢቲቪ ከወጣ በኋላ ሜጋ አመራ። (በ1989ዓ.ም ከሳምሶን ማሞ ጋር በታዋቂ አትሌት ላይ የሞከሩት የፔፕሲ ማስታወቂያ ማጭበርበር ድርጊት ነበር፤ ጉዳዩን ለጊዜው እንለፈው) የሜጋ ሃላፊዎች እግር ስር ወድቀው ከወጡ በኋላ ሰሎሞን አስመላሽ የራሱን ማስታወቂያ ድርጅት ከፍቶ መስራት ቀጠለ። በአደባባይ የገዢው ፓርቲ ደጋፊና አቀንቃኝ መሆኑን የሚናገረው ጋዜጠኛ ሰሎሞን ከአራት አመት በፊት በምሽት መዝናኛ ውስጥ መጠጥ እየተጐነጨ ነበር። በድንገት መብራት ድርግም ይላል።

Monday, September 22, 2014

ሕዝቡና ተማሪው በአገር ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር መግባባት አልቻልንም በማለት ስልጠናው እንዲቋረጥ ጠየቀ


ምንሊክ ሳልሳዊ

የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብሶታቸውን በከፍተኛ ቁጣ ገልጸዋል።

- ለወያኔ ባለስልጣናት የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም።

- የሃምሳ አመት እቅድ ለምን አስፈለገ የስልጣን ጥመኝነትን ያሳያል።

- ለሶስተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ እየተካሄደ ነው።

- በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይሁኑ አባላቶቹ የአስተዳደር ብቃት የላቸውም።

- ኢትዮጵያውያን በህግ ፊት እኩል የሚሆኑት እና ፍትህ የሚነግሰው ቀን እንናፍቃለን።

- በቫት ስም መንግስት ዘረፋ ይዟል በህጉ ቫት አይከፈልበትም የተባለው የጤና ዘርፍ ሳይቀር ቫት እየቆረጠ ነው።


በየአከባቢው እየተካሂደ ያለው ልማታዊነትን ሽፋን አድርጎ የስልጣን ማስረዘሚያ ሰበካ (ስልጠና) እንደቀጠለ ቢሆንም በህዝቡ እና በአሰልጣኞች መካክል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ከመከሰቱም በላይ ህዝቡና ተማሪው በአገራችን ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር ልንግባባ አልቻልንም ስለዚህ አበል ይቅርብን እና ስልጠናውን አቋርጡልን በማለት እየጠይቀ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። ሰልጣኞች እንደሚሉት እየተካሄደ ያለው ስልጠና ሳይሆን የፖለቲካ ሰበካ ነው ይህ ደሞ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸውን ህዝቦች ለማደናቆር ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ የያዛችሁን ስልት ቀይራችሁ ህዝብ መሃል ግቡና አናግሩን እንጂ በ አበል እና በቀበሌ ጥቅማጥቅም አታስገድዱን፡ አያዋጣችሁም ሲሉ ተናግረዋል።

Sunday, September 21, 2014

በጸረ ሽብር ህጉ የሚፈጸመው በደል እንዲቆም ተጠየቀ

በየተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት አማካሪ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር ህጉን ሰብአዊ መብትን ለመደፍጠጥ ከማዋል እንዲቆጠብ አሳሰበ፡፡ ይህ ማሳሰቢያ የመጣው የተለያዩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰትና አፈና እንዳሳሰባቸው መግለጻቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተግልጾአል፡፡ ማሳሰቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና በጸረ ሽብር ስም የሚወሰደውን እርምጃም ለመከላከል ያግዛል ተብሏል፡፡

‹‹ችግሩ እየተከሰተ እንደሆነ ከገለጽንበት ከሁለት አመት በኋላም ጸረ ሽብር ህጉ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችንና ተቃዋሚዎችን ሰለባ እያደረገ እንደሚገኝ ሪፖርት እየደረሰን ነው›› ያሉት ባለሙያዎቹ በተለይ በእስር ቤቶች ማሰቃየት፣ ኢሰብአዊ የሆኑ እርምጃዎች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ባለሙያዎቹ አክለውም ‹‹ሽብር መዋጋት ጠቃሚ ነው፡፡ ነገር ግን ውጤታማ ለመሆን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብትን በማክበር መከናወን አለበት›› ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጸረ ሽብር ህጎች በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ውስጥ በግልጸ መቀመጥና መጠቀሚያ መሆን እንደሌለበት መክረዋል፡፡

Tuesday, September 2, 2014

የወገኔ ዓማራ ነገር!

ከ ቦጋለ ካሳዬ


በወልቃይትም ሆነ በተቀረው ኢትዮጵያ ወያኔ ካለማቁዋረጥ ላለፉት 23 ዓመታት የሚያካሄደው አማራን የማጽዳት ዘመቻ
በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ በሌላ አገር የሚወዳደረው እንዳለ አላውቅም። ህዝብን ማጽዳት ግን እጅግ የቆየ፤ ምናልባት በአሳርያን
የተጀመረ ድርጊት እንደሆነ ጻሕፍት ያስረዳሉ።

ኢትዮጵያውያን ደጎችም ቂሎችም ስለሆንን፤ ወያኔ የሚያደርገውን ጭካኔ ስንሰማ፤ ኸረ ይኼ እንዴት ተድርጎ! ብለን የሆነውንና እየሆነ ያለውን ነገር ለመቀበል እንቸገራለን። ውይ! ውይ! እምጽ! የሰይጣን ጆሮ አይስማ ብለንም በደሉን እንደ ቀላል ነገር የምናረግብ አድርባይ የህሊና ዱልዱሞችና የውሸት ቤተክርስቲያን ተሳላሚዎችም ብዙዎች ነን።

የወገናቸውን በደል እውነት መሆኑን አጣርተው፤ ግፉ ነገ በራሳቸው ላይ ሊደርሰም እንደሚችል አስበው፤ ለችግሩ የማያዳግም መፍትሄ ለመስጠት ጥቂቶች ቁርጠኝነት ማሳየት ቢጀምሩም ለእስር፣ስደትና ግድያ እየተዳረጉ ነው። ብዙሃኑ በተለይ መረጃ በቀላሉ የሚያገኘው ከተሜ፤ መቼ የራሱም ሆነ የወገኑ በደል አንገፍግፎት ይኼን ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በሕብረት ከትከሻው ላይ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል አምላክ ብቻ ነው የሚያውቀው ማለት ሳይሻል ይቀራል?

ኽረ ለመሆኑ የሕዝብ ጽዳት ምንድን ነው? ነገሩ በእቅድ ተይዞ፤ ሆን ብሎ በጎሳ/ነገድ/ ብሄር፣በሃይማኖት፣በዘር፣በመደብ፣ ወይም በጾታ የሚለይና የማይፈለግ ሕዝብን ከአንድ አካባቢ ማስወገድ ነው። አተገባበሩም፤ ሰፋ

Thursday, August 21, 2014

አብርሃ ደስታ ሃብታሙ አያሌዉና እና ኤርትራ

 ( ግርማ ካሳ)


ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር እና ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በመገናኘት ፤ እንዲሁም ከባንክ በትዕዛዝ ብር በመቀበል የግንቦት 7 ተልዕኮና አላማ ለመፈፀም፤ ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ግለሰቦችን ለዚህ ጥፋት እንዲሰማሩ በማድረግ» የሚል ክስ ነው በወዲ ሃዉዜን/ትግራይ በሆነው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና ብሎገር ላይ ክስ የቀረበው። ሌላው አንጋፋና አንደበተ ርትኡ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ፣ ሃብታሙ አያሌውም፣ «የግንቦት ሰባት ተባባሪ ነው» በሚል ነው ለመክሰስ ነው ዝግጅት እየተደረገ ያለው።


አብርሃ ደስታ እና ሃብታሙ አያሌው ፣ «ግንቦት ሰባትን ይደግፋሉ» የሚል ክስ ከቀረበባቸው፣ በተዘዋዋሪ መንገድ «ከሻእቢያ ጋር ወዳጆች ናቸው» ማለት ነው። ታዲያ የሻእቢያ ወዳጅ የሆነ ሰው፣ የኤርትራን መገንጠል ተቃዉሞ፣ ወይንም የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤት መከበር እንዳለበት በማስመር ይናገራል ወይ ? እስቲ የጸረ-ሽብርና የአገር ደህንነት ተብዬው ምላሽ ይስጠን !!!
ሁላችንም እንደምናውቀው፣ በኤርትራ በኩል ትግል እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች፣ ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት ሊናገሩ አይችሉም። በሻእቢያ ሥር እስካሉ ድረስ ቀይ መስመር ተሰምሮላቸዋል። እነ ግንቦት ሰባቶች፣ ኦነጎች ...፣ እርዳታ የሚያገኙጥ ከሻእቢያ ማእከላቼ ደግሞ አስመራ እስከሆነ ድረስ፣ «ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል» ብለው የመናገራቸው ነገር ጭራሽ የማይታሰብ ነው።

የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የዞን9 ጦማርያኑን እና የጋዜጠኞቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ (ዞን 9)

ስድስቱን የዞን ዘጠኝ አባላት ማለትም በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ፣ ማኅሌት ፋታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና አጥናፍ ብርሃነ እንዲሁም በሌለችበት ክሷ እየታየ ያለው በሶልያና ሽመልስ እንዲሁም በጋዜጠኞቹ ኤዶም ካሳዬ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ በልደታ 19ኛው የወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት የተሰየመ ሲሆን ከሙስሊም ኮሚቴ አመራሮች ጋር በአንድ ችሎት እንዲታደሙ በመደረጉ የታሳሪዎችን ቤተሰቦችም ሆነ ወዳጆችን ለማስተናገድ ቦታ የለም በሚል ለጋዜጠኞች ብቻ የፍርድ ሂደቱ እንዲታይ በፖሊስ ተፈቅዶ ነበር፡፡

በሌለችበት የተከሰሰችው ሶልያና ሽመልስ መጥሪያ በጋዜጣ መውጣቱን ፍርድ ቤቱ ያረጋገጠ ሲሆን የዋስትና
መብትን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ተሰይሞ የነበረው ችሎት በጸረ ሽብር አዋጁ መሰረት በአንቀጽ 3 የሽብር
ተግባራት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ አንድም ወይም ሁለትም ከዚያም በላይ ወንጀል የፈጸመ መሆኑ
ወይም ለመፈጸም ያቀደ ለመሆኑ ተገልጾ ክስ ሲቀርብ ነው በተመሰረተባቸው ክስ ዋስትናን ሊያሳጣቸው
የሚችለው ብለው ጠበቆቻቸው የተከራከሩ ሲሆን ደንበኞቻቸው በአዋጁ መሰረት የሰሩት የሽብር ተግባር ክስ
አልቀረበባቸውም ስለዚህ በአዋጁ ተጠቀሰ ማለት በአዋጁ መሰረት ክስ ቀርቧል ማለት ስለማይቻል
የዋስትናው ጥያቄ በመደበኛ ስርዓት እንጂ በጸረ­ሽብር ሕጉ መሰረት ሊታይ አይገባም፤ በተጨማሪም አዋጁ

ዋስትና ይከለክላል ተብሎ ቢተረጎምም ከሕገ­መንግስቱ ጋር ስለሚጋጭ ዋስትና ሊፈቀድላቸው ይገባል
ቢሉም፤ ፍርድ ቤቱ አንቀጽ ተጠቅሶ መከሰሳቸውን እንጂ በዚህ መከሰስ ነበረባቸው ወይም አልነበረባቸውም ብሎ ለማየት ፍርድ ቤቱ አይገደድም እንዲሁም የጸረ­ሽብር አዋጁ ከሕገ­መንግስቱ ጋር አይጋጭም ብለዋል በዚሁም መሰረት የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ተደርጎ ለጥቅምት 5 ቀን 2007ዓ.ም ቀጠሮ በመስጠት የዛሬው ችሎት የተጠናቀቀ ሲሆን ጠበቆቻቸውም የዋስትና ጉዳይ በተመለከተ ለጠቅላይ ፍረድ ቤት ይግባኝ እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡

የወያኔ ጁንታ በግዳጅ እየሰጠ ባለው ስልጠና ከባድ ተቃውሞ ከሰልጣኞች እየገጠመው ነው ።

ምንሊክ ሳልሳዊ


የመንግስት ሰራተኛው እና የዩንቨርስቲው ተማሪዎች የከተቱት ስልጣና ላይ ወያኔ በጥያቄዎች ተወጥሯል፡፤

በሚቀርቡ የስልጠና ርእሶች ላይ ከፍተኛ አለመግባባት እና ጩኽት እየተከሰተ ነው፡፡


ከኑሮ ውድነቱ በባሰ ያቆሰሉን የሕወሓት አባላት ናቸው ።" የመንግስት ሰራተኛው


መልካም የልማት አስተዳደር በሚል ሽፋን ለመንግስት ሰራተኞች እና ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች በተከታታይ ለ15 ቀን እየተሰጠ ያለው ስልጠና የወያኔን አመራሮች እና ከፍተኛ ካድሬዎች አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው መሆኑን እና ተቀባይነት ማግኘት እንዳልቻሉ ከሰልጣኞች የሚመጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።

ሰራተኞቹ እና ተማሪዎቹ በየፊናቸው ያነሱት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ወቅታዊ ጥያቄዎች ወያኔዎች ፊታቸው ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ከመነበቡም በላይ ለመመለስ ሲደናበሩ እና እፍረት ሲሰማቸው የታየ መሆኑን እና መጭውን እንደማይችሉት ስሜታቸው ላይ ሲነበብ እንደነበረ የጠቆመው መረጃ ከወያኔ ካድሪዎች አከባቢ የተገኘ መረጃ እንደጠቆመው ይህን ያህል አስጨናቂ ነገር ይነሳል የሚል ግምት ስላልነበረ ለአሰልጣኝ ካድሪዎች ቀድሞ የተሰጠው ስልጠና ምንም ውጤት ላይ ባለማሳየቱ አዳራሾች በተማሪዎቹ በፉጨት እና በከፍተኛ ተቃውሞ እንደተሞሉ መሆኑ ታውቋል።

Tuesday, August 19, 2014

የፀጥታ ሃይሎች በጭፍን ታዛዥነት የሚጥሷቸው መሰረታዊ መርሆች

ድምፃችን ይሰማ!

በሃገራችን ኢትዮጵያ ህገ መንግስት መግቢያ ላይ በግልፅ እንደሰፈረው ሃገራችንን እንዲመራ የሚመሰረተው መንግስት በኢትዮጵያ ህዝቦች ነፃ ፍላጎት፣ በህግ የበላይነት እና በህዝቦች ፈቃድ የህዝቡን የጋራ ጥቅም፣ መብት እና ነፃነት እንዲያስከብር የሚመሰረት የፖለቲካ ተቋም ነው፡፡ ይህ የፖለቲካ ተቋምም ህዝባችንን በትጋት እና በህግ በታቀፈ አካሄድ እንዲያገለግል ተደርጎ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባው ህገ መንግስቱ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ በመቀጠልም ህገ መንግስቱ በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ህዝቦች የሃገራችን ኢትዮጵያ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ረጋግጣል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ማንኛውም የውስጥ ደንብም ይሁን መመሪያ ውድቅ መሆን ያለበት መሆኑን በማስገንዘብ ያሰፈረ ሲሆን በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 2 ደግሞ ማንኛውም የመንግስት አካልም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ለህገ መንግስቱ ተገዢ መሆን እንዳለበት በጥብቅ ያስገነዝባል፡፡

Wednesday, August 13, 2014

2007ን ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ ሲባል እስከ ምርጫ ወይስ እስከ ዴሞክራሲያዊ መንግስት

ዳንኤል ተፈራ — የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ

በጣም በቅርቡ አንድ ስላልነገርኩት ስሙን የማልጠቅሰው ጉምቱ የሚባል ጋዜጠኛ ወዳጄና ሌላ አንድ ጎልማሳ ጋር ኢ-ወጋዊ በሆነ መንገድ ስለተቃዋሚ ጎራው ማውጋት ይዘናል፡፡ የጨዋታችን መነሻ ደግሞ አንድነትና መኢአድ ከብዙ ውጣ ውረድና ድርድር በኋላ ከፍፃሜ ለማድረስ ደፋ ቀና እያሉበት ያለው ውህደት ነው፡፡ የተቃውሞ ፖለቲካውን በቅርበት እንደሚከታተሉ አንዳንድ ግለሰቦች አስተያየት ‹‹ውህደቱ መሳካት አዎንታዊ ጎን ቢኖረውም ዘግይቷል፡፡ በዚህ ጊዜ የውህደቱ ጣጣ አልቆ፣ የሚተባበሩት ተባብረው ወደ ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ የሚገቡበት ነበር›› ይላሉ፡፡ የውህደቱ መሳካት ጥሩ ሆኖ ውህደቱም ሆነ ትብብሩ ዘለቄታ ላለው ዴሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት ወይስ ምርጫ ስለደረሰ ብቻ? የሚል ጥያቄ አንስቶ መመለስ ተገቢ ነው፡፡

ጎልማሳው ሰው ቀበል አድርጎ ለተቃዋሚው ጎራ ቅርበት አለው ብሎ ስላመነ ይመስለኛል አይኖቹን እንደ ቆመህ ጠብቀኝ መሳሪያ ፊቴ ላይ ወድሮ ‹‹በተቃውሞ ጎራው በኩል ተቀራርቦ፣ ተባብሮና ተዋህዶ የመስራቱ ነገር እምብዛም ባለመለመዱ ወይም እስካሁን ባለመሳካቱ ይመስለኛል ውህደት እንዳንድ አደረጃጀትን የሚያጠነክር የፖለቲካ ስራ ሳይሆን እንደግብ ይታያል፡፡ ከፖለቲካ ጠቀሜታ አንፃር ሳይሆን ከምርጫ፣ ከግል ጥቅምና ዝና አንፃር ይታል፡፡ ውህደት እንዳንድ የለውጥ ማምጫ ስትራቴጅ ባለመታየቱ በህዝቡ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቅ ነው፡፡ መጠላለፍና ሴራ በብርቱ የሚያጠቃው የፖለቲካ ባህላችን ግን ‹‹እኔ ብቻ አዋቂ፣ እኔ ብቻ ንጉስ›› ከሚል ጨፍላቂ ሰርዓት ጋር ሲደመር ግራ ማጋባቱ ላይገርም ይችላል፡፡

የምተችብህ ነገር አለ

ወያኔ ኢህአዴግ የኢትዮጲያን ታሪክ አበላሸ ፣ ሃገሪቱን እየበታተናት ነው፣ትውልዱን ወኔ ቢስ አረገው፣የትምህርት ፖሊሲው ትውልድ ገዳይ ነው ፣ ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች እየተጣሱ ነው ወዘተ ወዘተ ግን እኛ በግለሰብ ደረጃ ያለን አስተዋጽኦ ምን እንደሆነ የዘነጋን ይመስለኛል። ብዙዎቻችንም ስንጠየቅ የምንሰጠው መልስ እኔ አንድ ግለሰብ ነኝ ምን ላረግ እችላለሁ? እንዴ እንደ እኔ ለሃገሪቱ አሳቢና ተቆርቋሪ የት አለና ? እራሴን ማስጠቆር አልፈልግም ! ኦ ኦ የልጆች አባት ነኝ ልጆቼን ላሳድግበት ፣ ሃገር ቤት G+ ምንትስ የሆነ ቤት እየሰራሁ ነው ወይም ኢንቨስት እያረጉ ስለሆነ ቢነጥቁኝስ ወዘተ

ሀገር ቤት የበርበሬና የጤፍ ዋጋ ሽቅብ ወቶ ሰው ቁም ስቅሉን ሲያይ ዲያስፖራ ከሃገር ቤት እያስላካ ማኛ ጤፍ በቀይ ወጥ ካልበላሁ ሞቼ እገኛለሁ ይላል።ኢትዮጲያ ላይ በምግብ እጥረት ስንቱ እንደሚያልቅ ወይም የበሽታ ተጠቂ እንደሆነ እያወቅን ምግብ ተርፎት ይጥላል ።ደሞ ለምን ጠግባቹህ በላቹሁ ልትለን እንዳይሆን እንዳትሉኝ እስቲ አስቡት ተርፎን ከምንጥለው የምግብ መግዟ ላይ እኮ ጥቂት ሳንቲሞችን ባስቀምጥ እኮ ቢያንስ አንድ ወገኔን ከርሃብ ወይም ከበሽታ ለታደገው እችላለሁ ደግሞ እኮ እስቲ አስቡት እንዲህ ፈልጦት እንዲህ ቆርጦት ብይ ገዢውን ፓርቲ የምንተች እኛ የበቀለን ገረባ ልጅ በምን ይማር ፣ የአንዶለም ልጅ በምን ይኑር ለኛ ብለው ስቃይ የሚቀበሉትን የማላሳብ እኔ በምን ሞራል ኢህአዴግን እተቻለሁ።

Tuesday, August 12, 2014

ኢንጅነር ይልቃል የአውሮፓ ህብረት እርምጃ እንዲወስድ አሳሰቡ

ዛሬ ነሃሴ 6/2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተወካይ ያላቸው 20 የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት ተወካዮች በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው የአውሮፓ ህብረት ቢሮ ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲያስረዱ የተጋበዙት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያ ወደባሰ ችግር ሳትገባ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

የአውሮፓ ሉዑካን ኃላፊ የሆኑት ሚስስ ባርባራ በመሩት ስብሰባ ላይ የተገኙት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲ ስለሚያደርገው አፈና፣ ሰብአዊ መብት ረገጣ፣ በሚዲያው ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ፣ ስለታሰሩት ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን አስረድተዋል፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ስለ ኢህአዴግ ሁኔታ በተጠየቁበት ወቅትም ‹‹ኢህአዴግ በራሱ ችግር፣ በርዕዮት ዓለም መደናበር፣ በአመራር ብቃት ማነስ ምክንያት ምርጫውን ክፍት በማድረግ ዴሞክራሲን መፍቀድ ዋጋ እንዲሚያስከፍለው ያውቃል፡፡ በሌላ ኩል ምርጫን ማጭበርበርም ጣጣ እንደሚያመጣበት ተረድቷል፡፡ በመሆኑም ምርጫ ማጭበርበርም ሆነ ምርጫውን ክፍት ማድረግ ችግር እንደሚፈጥርበት ስለሚያውቅ ከወዲሁ
አፈናን መርጧል›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የ”ብርቱው ሰው” መልዕክት – ከቃሊቲ እስር ቤት (በኤሊያስ ገብሩ)

‹‹ለእውነት መቆም ካልተቻለ ስብዕና ይወርዳል፣ ሕሊናህም ይሞታል››
‹‹የክስ እና የእስር መብዛት … የድል ጊዜ እየቀረበ መሆኑን ያሳያል››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ (ከቃሊቲ እስር ቤት)
‹‹እ… እስክንድር “The Iron man’’?››
የቃሊቲ ጠባቂ ፖሊስ

ጥቁር ሰኞ (Black Monday) ከሚሉት ወገን አይደለሁም፤ በአባባሉም አላምንም፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ በሁሉም ቀናቶች ጥሩም ሆነ ጥሩ ያልሆነ ሁነቶችን ሊያስተናግድ ይችላል፡፡ ይህንን ማለት የወድድኩት ዛሬ ሰኞ በመሆኑ ነው፡፡ ብዙዎች ዕለተ ሰኞ እንደሚከብዳቸው እና እንደሚጫጫናቸው ይናገራሉ፡፡ በቀናት መጥቆር እና መንጻት ማመናችንን ትተን፣ እያንዳንዱ ቀናቶችን ለሥራ እና ለመልካም ነገሮች በአግባቡ ብንጠቀምባቸው መልካም እያልኩ ወደዋናው ርዕሰ ጉዳዬ ላምራ፡-

18 ዓመት ተፈርዶበት በቃሊቲ ወህኒ ቤት ታስሮ የሚገኘውንና እጅግ የማከብረውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በቃሊቲ ከጠየኩት አንድ ወር ገደማ ሆኖኝ ነበር፡፡ ባለፈው ሳምንት ልጠይቄው አስቤ፣ በአዲስ የጋዜጣ ሥራ ተጠምቼ ስለነበር ሳልችል ቀረሁ፡፡ ዛሬ ግን፣ ከመኝታዬ እንደተነሳሁ የናፈቀኝን እስክንድርን ለመጠየቅ ወደቃሊቲ ማምራት እንዳብኝ ወሰንኩና ጉዞዬን ጀመርኩ፡፡

እውነት አብርሃ ደስታ አሸባሪ ነው? (ክብሮም ብርሃነ-መቐለ)

ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም የአረና ትግራይ ፓርቲ ስራ አስፈፃሚና የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር አብርሃ ደስታ በሽብር ተጠርጥሮ በተከሰሰበት ልክ በወሩ ፍ/ቤት እንደሚቀርብ በፌስ ቡክ አይቼ እኔም እንደ ዜጋና እንደ አድናቂው የሚቀርቡለትን የድራማ ክስ ለመስማት ጓጉቼ ፍ/ቤቱ ስደርስ እንደ እኔ አብርሃ ደስታን በአይናቸው ለማየትና የክሱን ድራማ ለማወቅ እንዲሁም ለቆራጡ ወጣት ፖለቲከኛ አብርሃ ደስታ የሞራል ድጋፍ ለመስጠት የተሰባሰቡ የተለያዩ የክልላዊና ሀገራዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ አባላት፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች እንዲሁም የወጣቱ ፖለቲከኛ አድናቂዎች ሽማግሌዎችና ወጣቶች ተደማምረው ያልገመትኩት የሕዝብ ብዛት በቡድን በቡድን ሰብሰብ ብለው የአብርሃ ቆራጥነትና የሀገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ሲወያዩ አገኘኋቸው፡፡

ከኢህአዲግ/ወያኔ መላቀቅ ማለት ከድንቁርና ነፃ መውጣት ነው!

ሰሞኑን የኢህአዲግ/ወያኔ የኮምንኬሽን ሚኒስትር ዴታ የነበሩት አሁን በስደት የሚገኙት አቶ ኤርምያስ ለገሰ የሰጡትን መግለጫ  በኢሳት ቴሌቭዥን እየተከታተልኩ ነበር።አቶ ኤርምያስ ከተናገሩት ውስጥ የኢህአዲግ/ወያኔ አመራሮችም ሆኑ ቡድኑ ባጠቃላይ የተማሩ ኢትዮጵያውያንን ለምን እንደሚያሳድድ ያስረዱበት መንገድ ሚዛን የሚደፋ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።አቶ ኤርምያስ ኢህአዲግ/ወያኔ በመመርያው ውስጥ የተማሩ አባላት ከ 1% እንዳይበልጡ ለምን እንደሚደረግ እና ባጠቃላይ ድርጅቱ የተማሩ ኢትዮጵያውያንን የሚጠላበትን መሰረታዊ ምክንያት ሲያስረዱ እንዲህ ነበር ያሉት (ቃል በቃል ባይሆንም ሃሳቡን እንዲህ ይገለፃል) -

  ”ማየት ያለብን ድርጅቱን የሚመሩት ሰዎች አነሳስን ነው።እነኝህ ሰዎች ገና የ 16 እና 17 ዓመት ልጆች ሆነው ከግብርና ተነስተው (ግብርና የተከበረ ሙያ መሆኑን ሳንዘነጋ) ወደ ውግያ ገቡ።ዋናውን የወጣትነት ጊዜ ማለትም እውቀት የሚቀሰምበት እና የህዝቡን ማህበራውም ሆነ ቤተሰባዊ ሕይወት በማወቅያቸው ጊዜ ሁሉ ለአስራ ምናምን ዓመት የሚያውቁት መተኮስ ነው።አሸንፈው ቤተመንግስት ሲገቡ የመማርያ ጊዜ አልፏል።እኛ ያለፍንበትን የቤተሰብ ሕይወት እና ምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተውን የዕውቀት መገብየት ዘመን አያውቁትም።ትምህርት ቤት አያውቁም፣ማህበራዊ ኑሮ አያውቁም።በመሆኑም  የተማረ ሰው አዲስ ሃሳብ ይዞ ከመጣ ይገለብጠናል ብለው ይሰጋሉ።” ነበር ያለው።ሚዛን የሚደፋ አገላለፅ ነው። 

የጸጋየ አየለ ገዳይ አሜሪካ ይገኛል

ደስታው አንዳርጌ (ዶ/ር)

ጸጋየ አየለ ይግዛው ይባላል። የ፴፬ ዐመት ባለትዳርና የልጆች አባት ነበር። ጎንደር ሆስፒታል ውስጥ በራዲዮሎጂስትነት ሲሰራ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር አባል ነህ በሚል ፖሊስ የሚያደርስበትን ወከባ ለመሸሽ ወደ ደብረማርቆስ ሄዶ በአንድ የግል ክሊኒክ ተቀጥሮ መስራት ይጀምራል። ነገር ግን የፈራው አላጣውም ታህሳስ ፱ ቀን ፩፱፻፺፱ (1999) ዓ.ም ከጠዋቱ ፪ ሰዐት ከ ፵፭ አካባቢ ወደስራ ሲሄድ ፖሊስ ያለፍርድቤት ማዘዣ ይይዘዋል። ደብረማርቆስና ባህርዳር እያመላለሱ ለጥቂት ሳምንታት ካንገላቱት በኋላ ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ተዛውሮ ታሰረ። ማዕከላዊ እንደደረሰ ለበርካታ ቀናት ከፍተኛ ድብደባና ማሰቃዬት ደርሶበታል። በደረሰበት ድብድባ እጅግ ሲደክም ራስ ደስታ ሆስፒታል ተወስዶ እንዲታከም ተደረገና ሲያገግም እንደገና ወደ ማዕከለዊ ተወስዶ ዘግናኝ ግፍ ተፈጸመበት። ጥፍሮቹ ተነቀሉ፤ የግራ ጆሮው፣ ሁለቱም እጆቹ፣ ብልቱ፣ አይኖቹ ሁሉ ከጥቅም ውጭ እስኪሆኑ ድረስ አሰቃዩት። እንዲህ አርገው ካሰቃዩት በኋላ በድብደባ ሽባ የሆኑትን እጆቹን በካቴታ ታስሮ ያድራል። ሲደክም እያሳከሙ ይደበድቡት ነበር። እንዲህያል ግፍም ይፈጸማል። ይህ ሁሉ አብረው ከሚሰቃዩት ታሳሪወችና ከቤተሰቦቹ ብቻ ሳይሆን ከጸጋየ ከራሱ ማረጋገጥ ተችሏል።

Monday, August 11, 2014

የከዱ የግንቦት 7 አባላት አቶ አንዳርጋቸውን እያሰቃዩ ነው ተባለ፤ * 2 መምህራንና 1 ዳኛ በአንዳርጋቸው ጉዳይ ታፍነዋል

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መያዝ ተከትሎ ለወያኔዎች ከአዲስ አበባ እስከ ደብረዘይት ትልቁን የምርመራ ስራ እየሸፈኑ ያሉት ከግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሃይል ጋር በኤርትራ የነበሩ እና ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር የፖለቲካ ስራ ሲሰሩ የነበሩ በኋላም ከድተው የገቡ ቅጥረኞች መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ቅጥረኞች ከመጀመሪያው ሰርጎ ገቦች እንደሆኑ ሳይጠረጠር ወደ ግንቦት ሰባት ከገቡ በኋላ ከአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቀደም ብሎ በመክዳት ወደ ወያኔ የተቀላቀሉ ናቸው ሲል ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ ዘገበ።

እንደ ምኒልክ ዘገባ ከሆነ በአዲስ አበባ እና በደብረዘይት ትልልቅ ሆቴሎች ተይዞላቸው በምርጥ መኪኖች እየተንሸራሸሩ አቶ አንዳርጋቸውን በማሰቃያ ክፍል ውስጥ በማምጣት እውነቱን አውጣ አንተ እንደዚህ ብለኸን አልነበረም በማለት በተለያየ ጊዜ በስብሰባ እና በውይይት ወቅት የተነጋገሩትን የፖለቲካ ኦፕሬሽኖችን እና የትግል ስትራቴጂዎችን በመጥቀስ ከፍተኛ ስቃይ እና ድብደባ እያደረሱብት ነው።

ለአንቺ ነው ኢትዮጵያ !

 ከእንግዳ ታደሰ


ከውሻ ተሻምቶ ለሚያድረው ህዝብሽ ነው ፣
ህዝብሽ እንዲጠግብ ሽቅብ ቁልቁል ያለው ፣ራሱን ረስቶ ህይወቱን የቸረው ፣
እድል እጣው ሆኖ በግፍ የታገተው፣
ለዚህ ነው ኢትዮጵያ ! ልጅሽ የታፈነው ፡፡
በማድያት የኳሉሽ – ፊትሽን ያጠለሹሽ፣
ዉብ መልክ ገጽሽን አመድ ያለበሱሽ ፣
በብተና ሴራ ከምድር ሊያጠፉሽ ፣
ታጥቀው ለተነሱት ቅጥረኛ ልጆችሽ ፣
በነው እንዲጠፉ ከመላዋ ምድርሽ ፣
ለዚህ ነው ኢትዮጵያ ! የባዘነው ልጅሽ ፡፡
ክራሞታችን እንዲህ ከሆነ – የወደዱትን አሳልፎ ፣
ምን ጠቀመ መማማሉ – አንገት ላንገት ተቃቅፎ ፡፡

‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ (ከቂሊጦ እስር ቤት)

[ከመቶ ሰባት ቀናት እስር በኋላ በፍቄ ሰለ እስሩ ስለ ምርመራው እና ስለ ወደፊት ተስፋቸው ከቂሊጦ እስር ቤት የሰደዳት መልዕክት ይቺትና። እኔ ጽሁፉን ሳነብ የመጣብኝ ሃሳብ እነዚህ ሰዎች በርካታ ንጹሃንን እስከዛሬ ማንም ሳያያቸው ሲያሰቃዩ የስቃዩ ሰለባዎች ዘጋቢዎች እና ጋዜጠኞች ካልሆኑ የስቃያቸውን መጠን የሚገልጹት በእንባ እና... ''ተወው... ተወው አይነሳ...'' በሚል ምሬት ብቻ ነበር። አሁን ግን በራሳቸው ጊዜ ዘጋቢዎችን ወደ ማዕከላዊ እያስገቡ እነሆ የኢህአዴግ ''አመራር ጥበብ''ን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ሰዕላዊ መግለጫ እየሰጡን ነው።
ኢህአዴግ ሆይ፤ በጥፊ በርግጫ አይገኝም ምርጫ፤ እያልን የበፍቄን ጽሁፍ ሁሉም ሰው ያነበው ዘንድ ይሄው...
‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በበፍቃዱ ሃይሉ.
‹‹ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!››፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ፡፡ በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ‹‹አባሪዎቼ›› ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል፡፡ ይኼ ነው እንግዲህ የምርመራችንን ሒደት የሚገልፀው ጥያቄ፡፡ 

ዋ! ወንድሜን! (ጌታቸው አበራ)

ጌታቸው አበራ


ይድረስ ለወንድሜ “ለማላውቅህ”፣ ባረመኔ ገራፊዎች እጅ ለወደቅኸው፣
በኮረንቲ ሽቦ ገመድ – መላው አካላትህ ለሚላጠው፤
ከጭለማው የግፍ “ቻምበር” – ከሰቆቃ መፈጸሚያው፣
የስቃይህ ጣር ዋይታ – ላለም ጆሮ ለተሰማው።

ከህመምህ ስታገግም – ላንዲት ቅጽበት ብጠይቅህ፣
ምንስ ይሆን “ሃጢያትህ”? በነሱ ዐይን “ጥፋትህ”?
እኔማ ምን አውቄ?
ስቃይህን ሰምቼ እንጂ መጨነቄ፤

ግን፣ ግን…፣
ከሚያቃትተው ድምጽህ ዋይታ፣
እስኪ ልገምት …”መላ-ልምታ”፣
(በመዝገበ-ማሕደር ተከትቦ- ዓለም የሚያውቀውን እውነታ)፤
…ቆዳህን ባኮርባች ሲልጡ – ስጋህን በብረት ሲያቃጥሉ፣
አጥንትህን ፍቀው ሲግጡ – በስ ብልት ጠርሙስ ሲያንጠለጥሉ፣

Sunday, August 10, 2014

ትላንትና መኢአድ ያወጣው የትግል ጥሪ መግለጫ ወያኔን ብቻ ሳይሆን አሜሪካንንም አደናበሯል።

“መኢአድ ጠንካራ ድርጅት ነው።” በድንገት መኢአድ ቢሮ የደረሱ የአሜሪካ ዲፕሎማቶች


 (ምንሊክ ሳልሳዊ)


በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ከኢሕአፓ ሕዋስ (ሴል) በመቀጠል በብቸኝነት ድርጅታዊ መዋቅሩን በማጥበቅ 
ታላቅ ስራዎችን የሰራው እና እየሰራ ያለው እንዲሁም በ97 ምርጫ የቅንጅት ማሸነፍ ታላቅ አስታውጾ 
የነበረው የፕሮፌሰር አስራት የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) በትላንትና እለት ለኢትዮጵያ 
ሕዝብ ባስተላለፈው የትግል ጥሪ የተደናገጡት ወያኔዎች ብቻ ሳይሆኑ የአሜሪካ መንግስት ዲፕሎማቶችም
 እንደሆኑ ከኤምባሲው የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል።
ethiopol

በትላንትናው እለት የመኢአድ እና የአንድነት አመራሮች በጋር በሰጡት መግለጫ መኢአድ ድርጅታዊ 
መዋቅሩን ተጠቅሞ የጎዳና ላይ አመጽ እንደሚጠራ እና ሕዝቡ በተጠንቀቅ እንዲጠባበቅ ለምርጫ ቦርድ
እና ለወያኔም ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ይታወቃል። ይህ ያሰጋው ወያኔ እንደለመደው ሲራወጥ ሁኔታው
እና የመኢአድ ጥንካሬ ያሰጋቸው የአሜሪካ ዲፕሎማቶች በዛሬው እለት የፖለቲካ  ጉዳዮች ሃላፊ የሆነችዋ የኤምባሲው ዲፕሎማት በመኢአድ ጽ/ቤት በመገኘት አመራሮቹን ማነጋገሯ ታውቋል።

Friday, August 8, 2014

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ


esatነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።
ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም የሰራዊቱ አባላት ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። አንድ የ3ኛ ሻለቃ አንደኛ ጋንታ አባል የሆነ ወታደር አመጹን መርተሃል ተብሎ ሊታሰር ሲል አምልጦ እስከነመሳሪያው ተከዜ ውስጥ ገብቶ መሞቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎ መጠናኛ ብጥብጥ መነሳቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰአት ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን፣ ከመከላከያ እየጠፉ የሚሄዱትም ቁጥራቸው እየጨመረ ነው።

ታዋቂው ፖለቲከኛና ደራሲ ወጣት አብርሃ ደስታ ዛሬ ፍ/ቤት ቀርቦ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀበት!!

በአራዳ መጀመሪያ ፍ/ቤት ችሎት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይቀርባል ቢባልም ዘግይቶ 10 ሰዓት ከ25 ላይ ቀርቧል፡፡

ፖሊስ ሀምሌ 3 ቀን ፍ/ቤት ቀርቦ ከግንቦት 7 ጋር በተያያዘ በሽፋን ትሰራለህ በሚል በቁጥጥር ስር አድርጎ ለምርመራ የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት የነበረ ሲሆን በ28 ቀን ውስጥም ምንም ማስረጃ ለችሎቱ አላቀረበም፡፡


 በችሎቱ ላይ የአረና አመራር አቶ ካህሳይ፣የአብርሃ እህት በችሎቱ እንዲታደሙ ተፈቅዶላቸው ገብተዋል፡፡ አብርሃ ደስታ በእስርቤት የደረሰበትን ለችሎቱ ሲያስረዳ እያስገደዱ ቃል ተቀብለውኛል፣ ተደብድቤያለሁ፣ ከውጪ የመጡ የደህንነት ኃይሎች ምርመራ አድርገውብኛል፣ ጨለማ ቤት ለቀናቶች ነበርኩ፣ የማላውቀውንና ያላነበብኩትን እንደፈርም ተደርጌያለሁ፣ የጨጓራ በሽተኛ ሆኜ በግድ እንጀራ እንድበላ ተደርጌያለሁ በማለት ለፍ/ቤቱ አስረድቷል ፡፡ 

ፖሊስ እነዚህ ድርጊቶች በፖሊስ ጣቢያው እንደማይደረጉና ማስረጃ የሌላቸው ውንጀላዎች ናቸው በማለት ያስተባበለ ሲሆን፣ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ደንበኛቸውን የሚመረምረውን መርማሪ ስም እንዲገለጽ ቢጠይቁም የመርማሪውን ስም አንናገርም ይዞ ፍ/ቤት የሚያቀርበውን ፖሊስ ስም ብቻ ነው የምንናገረው በማለት መልሰዋል፡፡ 

አቃቤ ህግ ለምርመራ ተጨማሪ የ28 ቀን ቀጠሮ ጠይቆ ፍ/ቤቱ የ28 ቀን ቀጠሮውን ፈቅዶ ለነሐሴ 29 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት እንዲቀርብ አዟል፡፡ የፍርድ ቤቱን ሂደት ለመከታተል አረና፣ የአንድነት፣ የሰማያዊ፣ የመድረክ፣የጌዴኦ የፓርቲ አመራሮችና አባሎቻቸው፣ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች በርካታ ሰዎች ተገኝተው አብርሃ ወደ ፍ/ቤት ግቢ በሚገባበትና በሚወጣበት ጊዜ በጭብጨባና አይዞህ በማለት አጋርነታቸውን ሲገልጹ ብርሃ ደስታም አንገቱን ዝቅ በማድረግ የታሰሩ እጆቹን ከፍ በማድረግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡
ፍኖተ ነጻነት

የአማራ ክልል አመራሮች ከግንቦት7 የኦህዴድ ደግሞ ከኦነግ ጋር እያበሩ ነው ሲል አቶ አዲሱ ለገሰ ያዘጋጁትና ለጠ/ሚ አማካሪዎች የተላከው ሰነድ አመለከተ

ነሃሴ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰነዱ ላይ ኢህአዴግ የአመራር ችግር እንዳጋጠመው፣ የትራንስፎርሜሽኑ እቅድ አለመሳካቱ እንዲሁም በጋምቤላ ተማኝ መሪ መጥፋቱ ተዝርዝሯል።
በሃምሌ ወር መጨረሻ የተዘጋጀው ሰነድ ግልባጭ ለጠ/ሚኒስትሩ አማካሪዎች ለአቶ በረከት ስምኦን፣ ለአቶ ደስታውና ለአቶ ኩማ ደመቅሳ ተደርጓል።

የቀድሞው ም/ል ጠቅላይ ሚኒስትርና የኢህአዴግ የፖሊሲ ስልጠና ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ ” የኢህአዴግን ተቃዋሚ ሃይላት ማንኮላሻ አቅም ግንባታ እና የአመራር ግንባታና የትራንስፎርሜሽን ጉዞ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የፖሊሲ አማካሪዎች የቀረበ የሚለው ባለ 39 ገጽ ጽሁፍ፣ ኢህአዴግ ከላይ እስከታች የአመራር ችግር እንደገጠመው በዝርዝር ያቀርባል።

ዜና በጨዋታ፤ ሬድዋን ሁሴን በአሜሪካ ልብስ ስብሰባቸው ተስተጓጎለ

የመንግስት አፍ የሆኑት ሬድዋን ሁሴን ለራሳቸው በህግ አምላክ ብሎ የሚጮህ አንደብት እንኳ አጥተው ሂሳቸውንም ውግዘታቸውንም ችለው በዝምታ ዋጥ አድርገው ተስተውለዋል።

አሜሪካ ለስብሰባ የጠራቻቸው ባለስልጣኑ ልብስ ስብሰባ ገበያ ቢወጡም ኢትዮጵያ ውስጥ በሚሰሩት ነውር ተበሳጩ ኢትዮጵያውያን ከባልስልጣን መደዳ ብቻ ሳይሆን ከሰው ተራ አውጥተው ውጉዝ ከማሪዮስ ብለዋቸዋል።
በዚህም የተነሳ የባለስልጣኑ ልብስ ስብሰባ ተስተጓጉሏል።

Wednesday, August 6, 2014

መከሰሳቸውን ከፖሊስ ሳይሆን ከሚዲያ የሰሙት የሎሚ መጽሔትና የአፍሮታምይስ ጋዜጣ አዘጋጆች ይናገራሉ

“ስለመከሰሳችን የምናውቀው ነገር የለም”                                ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ 

ጋዜጠኛ ግዛው ታዬ
አቶ ግዛው ታዬ
የሎሚ መፅሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር
                        
ክሱን በተመለከተ የምናውቀው ነገር የለም። ከዚህ በፊት ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ይደወልልን ነበር። እዚያ ሄደን ቃላችንን እንሰጥ ነበር።
እኛ አሁን መገረም ነው የፈጠረብን። ሕገ-መንግስቱን አከበራለሁ የሚል መንግስት በምን መልኩ ነው የክስ ዝርዝር ሳይደርሰን፣ መጥሪያ እጃችን ላይ ሳይገባ በመገናኛ ብዙሃን ክሳችንን የሚያሰማን።

“ስለእኔ አታልቅሱ!”

 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

“ዋይ ዋይ ከሚሉና ሙሾ ከሚያወጡ ሴቶችና ከሕዝቡ እጅግ ብዙዎች ተከተሉት፡፡ ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ዘወር ብሎ እንዲህ አለ፡- እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን፡-
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

መካኖችና ያልወለዱ ማኀፀኖች፣ ያላጠቡ ጡቶችም ብፁአን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ፡፡” (የሉቃስ ወንጌል ም. 23 ቁ. 27-30) ከቅዱስ መጽሐፉ ይህን የመሲሁ የመጨረሻ ምክር የመረጥኩት (ምንም እንኳ ረቢው የተናገረው ስለመለኮታዊው ትምህርት ቢሆንም) ዓለማዊው ፍች የኢትዮጵያችንን የወቅቱን መንፈስ ለመረዳት ከማስቻሉም በዘለለ፤ በየጊዜው እያየን፣ እየሰማን ያለነውን የፖለቲካ ተቃውሞው የጥምዝምዞሽ መንገድ በአርምሞ ለመመርመር መልካም ምሳሌ ይሆናል በሚል እሳቤም ነው፡፡

የአርባ ምንጭ ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎች ታሰሩ

ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዞኑ ፖሊሶች ትናንት ከሌሊቱ 10 ሰአት ላይ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አመራሮች መኖሪያ ቤት በመሄድ ፍተሻ ካደረጉ በሁዋላ ፣ አመራሮችን ወስደው አስረዋቸዋል።

የፍርድ ቤት ማዘዣ ይዘናል በማለት ፍተሻ ያካሄዱት ፖሊሶች በአንደኛው ቤት ውስጥ ሁለት ፍሬ ጥይቶችን ማግኘታቸውን ሲያስታወቁ፣ በሌሎች መኖሪያ ቤቶች ደግሞ
ቪዲዮ ካሜራዎችን፣ ፊልሞችንና የተለያዩ ወረቀቶችን ሰብስበው ወስደዋል። የአንደኛው አመራር የቅርብ ሰው የሆነ ለኢሳት ሲናገር፣ ፖሊሶቹ ጠመንጃ በሌለበት ሁለት
ጥይቶችን አገኘን ማለታቸው አስቂኝ ነው ካለ በሁዋላ፣ ሁለቱንም ጥይቶች ፖሊሶች ራሳቸው ይዘው መምጣታቸውንና አገኘን ብለው መናገራቸውን ገልጿል።

የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት

                                                 
                                                       "ኦባማ ዝምታው ይብቃ"
ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የተከፈተውንና በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ጉባኤ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

“በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲቆም አዎንታዊና ተጨባጭ ግፊት በማድረግ ፋንታ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አራማጆች በመደገፍ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ እያደረገ ነው፤” ሲሉ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡ መሆናቸውን ያስታወቁት የሰልፉ ተሳታፊዎች የኦባማን አስተዳደር ኮንነዋል።

ስብሰባውን አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ርዕሰ-ብሔርነቱ በዘለቁ ወቅት ሃገራቸው ከነበረችበት የምጣኔ ኃብት ድቀት አሁን እያገገመች በመሆኗ ትኩረታቸውን ለአፍሪካ እየሰጡ መሆኑን የሚያሳዩ ክንዋኔዎችን እያደረጉ ነው በማለት ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር የነበሩትና የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን መናገራቸውን ያሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዘግቦ ነበር፡፡

Tuesday, August 5, 2014

የሕወሓት ጄኔራሎች ሲታመሱ ዋሉ ። በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን ነግሷል።

ምንሊክ ሳልሳዊ


በጥርጣሬ/ግምት ካልሆነ በቀር አስራ አራቱ መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም።
ሁለት ከፍተና የጦር መሃንዲስች ዱካቸው ደብረዘይት ከሚገኘው እስር ቤት ተገኝቷል።
ወደ መቀሌ ከዲያስፖራው ጋር ለዘረፋ የንግድ ሽርክና ኢንቨስተሮች ለመመልመል ያመሩት ጄኔራሎች ሳይቀሩ በምን እንደመጡ በማይታወቅበት ሁኔታ አዲስ አበባ ደርሰው የመሃል አገር መኮንኖች መጥፋትን ተከትሎ ያመጣውን ውጥረት በስብሰባ ሲያሹት እና ከተለያዩ ወታደራዊ ደህንነቶች መረጃ ሲሰበስቡ እንደዋሉ ታውቋል።

በሰራዊቱ ውስጥ አለመተማመን የተፈጠረው ከምን የመነጨ ነው የሚል ጥናት በዚህ ሳምንት በተካሄደበት የመሃል አገር መከላከያ መምሪያዎች ውስጥ አጋጣሚ በተገኘ መረጃ 16 ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የት እንደገቡ አይታወቅም ሲል ሪፖርት ያቀረበው የወታ
ደራዊ ደህንነት ቡድን የቀረበለትን ጥቆማ ለበላይ አካላት ሪፖርት ሳያድርግ ፍተሻውን አጧጡፎት የነበረ ቢሆንም ምንም አይነት 
ፍንጭ ባለማግኘቱ ትላንትና የተነገረው የበላይ አካል በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጦ የዋለ መሆኑን ለጦር ክፍሎቹ ቅርብ የሆኑ ምንጮ
ቻችን ከመከላከያ ያደረሱን መረጃ ጠቁሟል።

ኢህአዴግ በድሆች ጉሮሮ ላይ ቁማር መጫወቱን ቀጥሎበታል፡፡ የደመወዝ ማሻሻያ ርካሽ የፓለቲካ ትርፍና ተግዳሮቱ

ምንሊክ ሳልሳዊ


***የደመወዝ ማሻሻያ ርካሽ የፓለቲካ ትርፍና ተግዳሮቱ….***
በድሆች ጉሮሮ ላይ ፓለቲካውን የሚያካብተው ኢህአዴግ በተቀጣሪዎቹ ላይ ቁማር መጫወቱን ቀጥሎበታል፡፡

ተቀጣሪው የኢትዮጵያ ህዝብም ባርነትን ወዶ መኖሩን ተያይዞታል፤ የሰውን ልጅ ከጫማህ ስር በባርነት ለማኖር ከፈለግክ ቤተሰብ መጦር ድሮ ቀረን እያዜመ በቤተሰብ የሚጦረው የዘመናችን የመንግስት ሠራተኛ አያድርሰው እንጅ ቢታመም ጉድ ፈላ! ያው ጤና አዳሙን፣ዳማከሲዩን፣ዝንጅብሉን አጥር ያፈራውን ሐረግ ሬሳ ይታጠናታል እንጅ እንኳንስ የግል ሆስፒታል በቀበሌው ያለ ጤና ጣቢያ ሔዶ በሐኪም ሊታይ አይችልም፤ በዓመት በዓል እንኳን ከመንግስት ሠራተኛ ቤት የልኳንዳ ፌስታል እንጅ የበግ ቆዳ የገባው በደጉ ዘመን ነበር፤ለመማር እራስን ለመለወጥ ገንዘብ ያስፈልጋል፤ከተማርክ ደግሞ ጥያቄ ማንሳትህ አይቀርም! የዛሬን ካልቸገረህ ስለ ነገህ ትሞግታለህ! ማኩረፊያ ካለህ ምሰህን አስከብረህ ለእራትህም ትተርፋለህ! ቅሉ ግን ከምሳ ባሻገር እንድትኖር አይፈለግም፡፡ ከምሳ ያለፈ እንድታስብ አይፈለግም! ሆድህ ከሞላ ቁንጣንህ ወንበር ያሰይሃል ተብሎ ይታመናል-በኢህአህዴግ ቤት! እራትህን እርግጠኛ ከሆንክ መታረዝህ ያሳስብሃል! ቁርሳቸውን ላላሟሹቱ ማሰብ ትጀምራለህ! ሌሎች መብቶችህም ትውስ ይሉህ ይሆናል! ከራስህ አልፈህ አገሬ ብለህም ትነሳ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሆድህ ይሞላ ዘንዳ አይፈለግም፡፡ ደንደስህ ከወፈረ ለማነቆ አይመችም! የኢትዮጵያ የተቀጣሪዎች የደመወዝ እስኬል ዝቅተኛ ነው ብለህ ማንሾካሾ አትችልም፤ አደሃሪ ጓደኛህ 
ይቺ አገር ከዚህ በላይ ደመወዝ ለመክፈል አቅሟ አይፈቅድም ብሎ በሐገርህ ፍቅርህ ስስ ጎንህ በኩል ዘልቆ ይሞግትና ዝም ያሰኝሃል!
 አዎ! ይኢ አገር የተትረፈረፈ ደመወዝ መክፈል ያቅታት ይሆናል፤ እነ እንቶኔ ከጓሯቸው እንደ ባህር ዛፍ የሚያበቅሉትን ህንጻ መስሪያ
 የሚያክል ደመወዝ አልተመኘህም! ከእርሀብና ከእርዛት፣ከጥማትና ድቆሳ የሚያላቅቅ ገንዘብ ግን ኢትዮጵያ መክፈል አይሳናትም፤
 ደግሞስ የመሬቷ ኢትዮጵያ ይፋ የምትሆነው ደመወዝ ላይ ብቻ ነው እንዴ? የኢትቪዋ ኢትዮጵያ የት ገባች?