ሀገር ቤት የበርበሬና የጤፍ ዋጋ ሽቅብ ወቶ ሰው ቁም ስቅሉን ሲያይ ዲያስፖራ ከሃገር ቤት እያስላካ ማኛ ጤፍ በቀይ ወጥ ካልበላሁ ሞቼ እገኛለሁ ይላል።ኢትዮጲያ ላይ በምግብ እጥረት ስንቱ እንደሚያልቅ ወይም የበሽታ ተጠቂ እንደሆነ እያወቅን ምግብ ተርፎት ይጥላል ።ደሞ ለምን ጠግባቹህ በላቹሁ ልትለን እንዳይሆን እንዳትሉኝ እስቲ አስቡት ተርፎን ከምንጥለው የምግብ መግዟ ላይ እኮ ጥቂት ሳንቲሞችን ባስቀምጥ እኮ ቢያንስ አንድ ወገኔን ከርሃብ ወይም ከበሽታ ለታደገው እችላለሁ ደግሞ እኮ እስቲ አስቡት እንዲህ ፈልጦት እንዲህ ቆርጦት ብይ ገዢውን ፓርቲ የምንተች እኛ የበቀለን ገረባ ልጅ በምን ይማር ፣ የአንዶለም ልጅ በምን ይኑር ለኛ ብለው ስቃይ የሚቀበሉትን የማላሳብ እኔ በምን ሞራል ኢህአዴግን እተቻለሁ።
መቼም እኛ ኢትዮጲያውያን ሃይማኖተኛ ለመምሰል እማናረገው ጥረት የለም ግን በጣም በሚገርም ሁኔታ ማንን እንደምናመልክ እንኳን እረስተን ነጻነት ያለበት ሃገር ላይ ቁጭ እየኖርን ስንት ቤተክርስቲያን እንደፈጠርን ተመልከቱ አሳዛኙ ነገር ደግሞ እነዚሁ የተከፋፈሉት ቤተክርስቲያኖች ላይ ከሃይማኖቱ ይልቅ ፖለቲካው በጣም ከመንገሱ የተነሳ ሰው ተከፋፋሎ በምን አይነት ሁኔታ ቤተክርስቲያን ተብለው የሚቀደስባቸው ቦታዎች እንዳሉ ስናይ "የቤትህ ፍቅር በላኝ" የሚለውን ከመጽሃፍ ቅዱስ ያወጣንው እንምስላለን ለነገሩማ "ባልእንጀራህን እንደራስህ አርገህ ውደድን " "ባለእንጀራህን ባይነ ቁራኛ ተመልከት
" ወደሚል ስለቀየርንው ቤት በኩል ጸጋ ያላት ቤተክርስቲያን ይኖረናል።
የኢትዮጲያ ታሪክ እያዛባ ነው እያለ የሚጮኸው ዲታስፖራ ለታናናሾቹ በተለይ ደግሞ እድሜያቸው ከ30 አመት በታች ለሆኑት ገንዘብ ሲልክ እስቲ ሃገርህን| ሃገርሽን ጎብኝና|ጎብኚና ስለሃገርህ|ሽ እወቀት አግኝ|ኚ የምንል ስንቶቻችን ነን?እሱ እንኳን ቢከብድ የሃገርህን|ሽን ታሪክ ለማወቅ ይረዳሃል|ይረዳሻል ይህንን መጽሃፍ ገዝተህ|ሽ ብታነብ|ቢ የምንል? አሁን ደግሞ እድሜ ለቴክኖሎጂ የሃገራችንን ታሪክ በተመለከት የተጽፉ መጽሃፍትን በቀላሉና እንደ እውነቱም በርካሽ በምናገኝበት ሁኔታ እስቲ ማናችን ነን ለወንድሞቻችን እንደ ስጦታ የምንልክ ?ላፕቶፖችንና ኤሌክትሮኒክ እቃዎችን ስንልክላቸው የየሃይማኖቶቻቻንን መዝሙርና ማንዙማ ጭነን እንልካለን ፥ ሃገር አልባ ሃይማኖት እንዴት እንደሆነ እንጃ
? እንዴ ይሄማ ቅንጦት ነው እንዴት ሆኖ ትልኝ ይሆናል።እርግጥ ነው ሆድ ጠግቦ እንዴያድር ማረግ ነው ተቀዳሚው ነገር ግን ታዲያ በምን መልኩ ታሪኬ እንዳይዛባብኝ ብዬ ከኔ ከግለሰቡ የሚጠበቅብኝን ሳላደርግ ልቅር አለበለዚያማ ሌላውን በምን ሞራል እወቅሳለሁ?
ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች እየተጣሱ ነው ብዬ የምጮህ ፥ ግን እቤቴ ውስጥ ያለችውን ሰራተኛዬን ( ሙሉ ለሙሉ ሴቶች ስለሆኑ ነው ሃገራችን ላይ ) ለሰራችበት በቂ ክፍያ እየነፈግሁና እየደበደብኩ ፥ ጉልበተኛነቴን ለማሳየት የጎረቤቴን ሰላም እየነፈግሁ ፥ መብቴ እስከ ምን ድረስ እንደሆነ የማላውቅ እኔ ከኔው ማህበረሰብ በወጡ የምተዳደር እኔ ለሚያደርሱብኝ ግፍ ከማን ተምረውት እንደሆነ የረሳንው ይመስላል፥መቼም ወገናችን ላይ እናውእራሳችን እንዴት በደል እንደምናደርስበት እንኳን ለማሳየት፣ በጣም ትንሽዬ ስህተት በሌላ ሃገር ሰው ላይ ሰርተን ይቅርታ እንዴት ተሽቆጥቁጠን እንደምንጠይቅ ፥ ነገርግን ያሰው ወገናችን ከሆነ ግን እንደምንነፍገው የምናውቀው ሃቅ ነው።
ሰልፋችን ወሬ የበዛበት ፣ ያልተደራጀ እንኳን ለምዕራባዊያን መልክት ለናስተላልፍ ይቅርና ለኢህአዴግ እንኳን የሚያስፈራ አልሆነም በተለይ እዚህ አውሮፓማ ጫወታ ይመስላል።ለዛም ሳይሆን አይቀርም ነጮቹም አይተውን አይተውን እንደው ለይስሙላ ብቻ በየሰልፉ ፖሊስ የሚመድቡት። ይሄ ስህተት ነው የሚለኝ ካለ እንደኛ አያብዙት እንጂ ሰልፍ ሲወጡ እስከ ምን ድረስ ችግራቸውን ለማስረዳት እንደሚጥሩ የሌሎች አፍሪካዊያን ፣ፓኪስታኖ ችንና አፍጋኖችን ሰልፍ ማየት ነው።
ዲያስፖራዊ የፖለቲካ ድርጅቶችን ተመልከቱ እስቲ ኢህአዴግ ካድሬዎችን በየቦታው መልምሎ እንደ ጋሪ ፈረስ በራሱ መንገድ እንደሚያስጉዛቸው ሁሉ እነዚህም እንዲሁ እነሱ በሚፈልጉት መንገድ ብቻ አባሎቻቸው እንዲጓዙላቸው ይፈልጋሉ ፥ ምንም አይነት እነሱ ከሚፈልጉት ሃሳብ ውጭ ለመስማት አይሹም ። ኢህአዴግን 23 አመት ስልጣን አለቅ አለ ብለው እየጮሁ እነሱ ግን የያዙትን ወንበር ድርጅቱ ተበጣብጦ ካልተበተነ በቀር ለመልቀቅ ፍላጎቱም ዝግጁነትም አይታይባቸውም እንደውም አንዳንዶቹ ጥሩ የገንዘብ ማግኛ ዘዴ አርገውታል።
በተስፋዮ ገብረአብ የደራሲው ማስታወሻ ላይ እንደምናገኘው እኔና አጼ ቴዎድሮስ ያለ ጊዜያችን ነው የተፈጠርነው እንዳለን ኢትዮጲያዊ አይነት ሰዎች ይበዙብኛል።
በየሃገሩ ያሉትን ኤንባሲዎች የኢትዮጲያዊያን አይደሉም እያልን እይጮሃለን ፥ የኢትዮጲያ ኮሚኒቲ ተብለው የሚቋቋሙት ስራቸው ምን እንደሆን ግራ የሚያጋቡን ፥ አንዳንዶቹማ በስደት ያለውን ኢትዮጲያዊ ከመደገፍ ይልቅ የሀገር ቤት ባህላዊ እቃዎችና የምግብ ሸቀጦች መሸጫ ሆነዋል።አቶ አንዳርጋቸው በኢህአዴግ እጅ ሲገባ ምን አይነት ስቃይ ሊጠብቀው እንደሚችል እናውቃለን ፥ ግን ለኔ ሲል የምንል ስንቶቻችን ነን። እነ ኮለኔል አለበል፣ሪዮት አለሙ ፣ እስክንድር ነጋ ወዘተ ለበል እንጂማ ስንቱን ጠቅሼ እችለዋለሁ የዛሬዋንና የነገዋን ኢትዮጲያ ለማሻሻል ሲሉ መስዋዕትነት የሚከፍሉትን የምናስብ ስንቾች እንሆን ? ከነገሩ ጾም እደሩ ብለን ሃሜት ብቻ ስራችን ስለሆነ አይደለምን እራሱ አንዳርጋቸው ዲያስፖራዊ ኮምፕሌክስ(አማርኛው በምን መልኩ እንደሚገልጸው አላውቅም) ያለን።
ይኽን ሁሉ ስል ግን ዲያስፖራው እያረገ ያለውን በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በጎ እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ እረስቼ አይደልም ግን መስራት የሚጠበቅበትና የሚፈልገውን ለማግኝት እያረግ ያለው እንቅስቃሴ
በብዙ መልኩ ስለሚቃረንበት ነው።እርግጥ ነው እኛ ኢትዮጲያዊያን ከፍተኛ የሆነ የቅንነት ችግር ስለሚጎለን እንኳን ለፖለቲካችን ችግር መፍትሄ ለማግኘት ቀርቶ የእርስ በርስ ግንኙነታችንን እንኳን በመተማመን ላይ የተመሰረት ማረግ አቅቶናል።የሚከተለውን የሄኖክ የሺጥላግጥም በማስታወስ ልሰናበት
የሃበሻ ለቅሶ
ደከመኝ አመመኝ ምን ጉድ ነን የልም ዟት፣
እኛው ነን ፍረሃት እኛው ነን ጠንቆቹ፣
....ጠናቋይ ጣቶቹ
እኛ ነን እንጂ ህመም የሃገር ነቀርሳ፣
በዋይታ ዳቢሎስ ሙት የምናስነሳ
ይበለን ብያለሁ መርገምቶቹ እኛ ነን፣
ይህንን አይቶ ነው አምላክም የተወን
ነጻነትን ብሎ መሰዋቱ ይቅር ፣
አንገትም ቀና አይበል
ይሁና ግድ የለኝማ ዘንድሮም ይቀርቀር፣
ዘንድሮም ይቀበር
ዘንድሮም እናዳምናው ተረት ሆኖ ይቅር ፣
መድፈር ጀግንነቱም እምቢታውም ቢሆን፣
ይሁን ለምደንዋል በተዝታ እንኑር
ኢትዮጲያ ለዘላለም በክብር ትኑር!
አበበ ሃይሉ
No comments:
Post a Comment