Friday, August 8, 2014

ዜና በጨዋታ፤ ሬድዋን ሁሴን በአሜሪካ ልብስ ስብሰባቸው ተስተጓጎለ

የመንግስት አፍ የሆኑት ሬድዋን ሁሴን ለራሳቸው በህግ አምላክ ብሎ የሚጮህ አንደብት እንኳ አጥተው ሂሳቸውንም ውግዘታቸውንም ችለው በዝምታ ዋጥ አድርገው ተስተውለዋል።

አሜሪካ ለስብሰባ የጠራቻቸው ባለስልጣኑ ልብስ ስብሰባ ገበያ ቢወጡም ኢትዮጵያ ውስጥ በሚሰሩት ነውር ተበሳጩ ኢትዮጵያውያን ከባልስልጣን መደዳ ብቻ ሳይሆን ከሰው ተራ አውጥተው ውጉዝ ከማሪዮስ ብለዋቸዋል።
በዚህም የተነሳ የባለስልጣኑ ልብስ ስብሰባ ተስተጓጉሏል።

አስተያየት ፩
አንዳንድ ወዳጆች ኢትዮጵያውያኑ ያደረጉት ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት አይጠበቅም ሲሉ ይደመጣል፤ እኔ ግን ባለስልጣኖቻችን በሀገር ውስጥ ህዝቡን መቆሚያ መቀመጫ አሳጥተው እነርሱ በነጻነት መዘነጫ ልብስ ሊገዙ እጃቸውን ኪሳቸው ከተው ሲንጎማለሉ ማየት ሙድ የለውም ባይ ነኝ። እናም ዲሲዎች ያደረጉት ጥሩም ባይሆን እንኳ የሚበረታታ ተግባር ነው ባይ ነኝ። ባለስልጣኖቹም፤ ልብ ካላቸው ይሄኔ ቆም ብለው ለምን… ብለው ራሳቸውን ይጠይቁ እና በስራቸው ይጸጸቱ ይሆናል… ማን ያውቃል!
አስተያየት ፪
አቶ ሬድዋን ራሳቸው ልብስ ተራ ምን ያደርጋሉ… መንግስት ይሰብሰቡ ብሎ ላካቸው እንጂ ልብስ ሰብስቡ ብሎ ላካቸው እንዴ፤
አስተያይት ፫
ይሄኔ አቶ ሬድዋንም ሆኑ የባለፈው ንግድ ሚኒስቴር ሰውዬ በህዝብ ዘንድ ቅቡል የሆነ ደስ የሚያሰኝ ”ነውር ፍሪ” የሆነ ስራ ሰርተው ቢሆን ዜናው አቶ ሬድዋን ፈርሙልኝ በሚሉ ሰዎች ልብስ ገበያቸው ተስተጓጎለ፤ ወይም ደግሞ አቶ ሬድዋን ለመግዛት የሰበሰቡትን ልብስ አድናቂዎቻቸው ሂሳቡን ”ከቨር አድርገው አስደምመሟቸው” የሚል ይሆን ነበር።
ለማንኛውም እንሆ አቶ ሬድዋን ቪዲዮ በባለ ሃያ አራት ብር የሴቶች ልብስ መሃል እየተንጎማለሉ ውግዘታቸውን ሲቅሙ የሚያሳየው ቪዲዮ!
ለማንኛውም እንሆ አቶ ሬድዋን ቪዲዮ በባለ ሃያ አራት ብር የሴቶች ልብስ መሃል እየተንጎማለሉ ውግዘታቸውን ሲቅሙ የሚያሳየው ቪዲዮ!

No comments:

Post a Comment