Monday, November 3, 2014

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር “የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ እራስህን ከወያኔ አሽከርነት(መጠቀሚያነት) ልታርቅ ይገባል” አለ


በህዝብ ላይ የሚደርሰው ጭቆናና እርዛት እስከመቼ?

ከኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ የተሠጠ መግለጫ

የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ዘወትር ስልጣናቸውን ለማራዘም ካላቸው ነቢራዊ ፍላጎት የተነሳ በህዝብ ላይ ግድያ እና እስር ከመፈፀም አልፈው ሐገራችን ኢትዮጵያን ከማትወጣበት ማጥ ውስጥ ለመክተት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ በቅርቡ እንኳን በአሶሳ ከተማ ንፁሀን የትግራይ ወጣቶች ማንነታቸው እስካሁን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል ይኸውም መንግስትእየተከተለው ብልሹ የዘውግ አስተዳደር ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ እየታየ ነው በሌላ በኩል ይህ ግድያ መንግስት እራሱ የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሠለፍ በማሠብ እንደገደላቸው ግምታቸውን አስቀምጠዋል እንደምክንያት የጠቀሱት ምርጫ 97ን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ መንግስት ተቃውሞውን ለማባባስ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከቀድሞዋ የትምህርት ሚኒስቴር ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ግቢ ወደውጭ ቦንብ በመወርወር 6 ፖሊሶችን በመግደል ፖሊሶችን ለማነሳሳት እና ህዝቡን ለማሳሳት ቢሞክርም በመጨረሻ ጉዳዩን የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋ ሲያወጣው የመንግስት ሴራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአሶሳው፣ የአምቦው፣ የጎንደሩ እና የወለጋው ግድያም ከዚህ የተለየ አይሆንም፡፡

የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴም ለመንግስት እና ለህዝቡ የሚከተለውን መልዕክት ማስተላለፍ ይወዳል፡፡
የመምህራኑ መልዕክት ለመንግስት

ማንኛውም መንግስት ህዝቡን ማዳመጥ ይኖርበታል መንግሥት ሕዝብን የሚያዳምጠው በሕገ መንግሥቱ ስለሚገደድ ብቻ መሆን የለበትም፡፡ የሕዝብ ወገን ነኝ የሚል ሥልጣን የያዘ ፓርቲና መንግሥት፣ ሕዝብን ምረጠኝ የሚል ፓርቲና መንግሥት፣ የሕዝብ ከበሬታና አመኔታ ሊያገኝና ዓላማውን በተግባር ላይ ሊያውል የሚችለው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ሥልጣን ላይ የሚቆየው ሕዝብን ሲያዳምጥ ብቻ ነው፡፡ ሕዝብን ማዳመጥ ለራስ ተብሎም መደረግ ያለበት ነው፡፡ የማያዳምጥ መንግሥት የማይደመጥ መንግሥት ይሆናልና፡፡

የመምህራኑ መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ

የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ለሐይማኖትህ፣ ለሐገርህ እና ለቀጣይ ትውልድ አስበህ እራስህን ከወያኔ አሽከርነት(መጠቀሚያነት) ልታርቅ ይገባል፡፡ መንግስት ህዝቡ ፊቱን ካዞረበት እና ካልተገዛለት ማንንም ሊገዛ እንደማይችል የቅርባችን የጋዳፊ አገዛዝ ምስክር ነው፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ከኢህአዴግ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት መመስረት የለብንም ከዚያም አልፎ ከወያኔ ጋር ተለጥፈው ህዝባቸውን የሚያስወጉ ጎረቤቶቻችንን ጭምር ከማንኛውም ማህበራዊ ህይወት በማግለል ትምህርት ልንሠጣቸው ይገባል፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!!!!!!!!!!

የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

No comments:

Post a Comment