Tuesday, September 2, 2014

የወገኔ ዓማራ ነገር!

ከ ቦጋለ ካሳዬ


በወልቃይትም ሆነ በተቀረው ኢትዮጵያ ወያኔ ካለማቁዋረጥ ላለፉት 23 ዓመታት የሚያካሄደው አማራን የማጽዳት ዘመቻ
በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ በሌላ አገር የሚወዳደረው እንዳለ አላውቅም። ህዝብን ማጽዳት ግን እጅግ የቆየ፤ ምናልባት በአሳርያን
የተጀመረ ድርጊት እንደሆነ ጻሕፍት ያስረዳሉ።

ኢትዮጵያውያን ደጎችም ቂሎችም ስለሆንን፤ ወያኔ የሚያደርገውን ጭካኔ ስንሰማ፤ ኸረ ይኼ እንዴት ተድርጎ! ብለን የሆነውንና እየሆነ ያለውን ነገር ለመቀበል እንቸገራለን። ውይ! ውይ! እምጽ! የሰይጣን ጆሮ አይስማ ብለንም በደሉን እንደ ቀላል ነገር የምናረግብ አድርባይ የህሊና ዱልዱሞችና የውሸት ቤተክርስቲያን ተሳላሚዎችም ብዙዎች ነን።

የወገናቸውን በደል እውነት መሆኑን አጣርተው፤ ግፉ ነገ በራሳቸው ላይ ሊደርሰም እንደሚችል አስበው፤ ለችግሩ የማያዳግም መፍትሄ ለመስጠት ጥቂቶች ቁርጠኝነት ማሳየት ቢጀምሩም ለእስር፣ስደትና ግድያ እየተዳረጉ ነው። ብዙሃኑ በተለይ መረጃ በቀላሉ የሚያገኘው ከተሜ፤ መቼ የራሱም ሆነ የወገኑ በደል አንገፍግፎት ይኼን ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በሕብረት ከትከሻው ላይ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል አምላክ ብቻ ነው የሚያውቀው ማለት ሳይሻል ይቀራል?

ኽረ ለመሆኑ የሕዝብ ጽዳት ምንድን ነው? ነገሩ በእቅድ ተይዞ፤ ሆን ብሎ በጎሳ/ነገድ/ ብሄር፣በሃይማኖት፣በዘር፣በመደብ፣ ወይም በጾታ የሚለይና የማይፈለግ ሕዝብን ከአንድ አካባቢ ማስወገድ ነው። አተገባበሩም፤ ሰፋ
ያለና የማያቁዋርጥ፣ በአንድ ጽንፍ የዘር ማጥፋት(ለምሳሌ፤ እንደ በደኖና አርባጉጉ) በሌላው ጽንፍ ደግሞ ተጽእኖ እያሳደሩ ሕዝብ የሚኖርበትን አካባቢ ለቅቆ(ለምሳሌ፤ ጉራ ፈርዳ፣ቤነሻንጉል) እንዲሰደድ ማድረግ ነው።
ዓማራ

ዛሬ በዓማራ ላይ እየተካሄደ ያለውን የሕዝብ ጽዳትን ለማስቆም እሪ ከማለት ይልቅ፤ ዓማራ አለ የለም በሚል ጉንጭ አልፋ ትንተና ውስጥ የተጠመዱም ሞልተዋል። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም የተናገሩትን እንዳሻቸው የሚመነዝሩ የዓማራ ነጉላዎችና ጠላቶቹ ሳያውቁም ሆነ አውቀው መደናበራቸው በዓማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ አይናቸውን ካልጨፈኑ በስተቀር ሊክዱት አይችሉም።

ዓማራ የለም የሚለው የፕሮፌሰሩ አባባል ልብ ብሎ ላዳመጠው፤ ዓማራ የሚባል የጎሳ ስሜት የለም ነው። ፕሮፌሰሩ ዓማራ እንደ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እንዳለ አልካዱም። ይኸ ደግሞ እንደ ክርስቲያንነቱ ከጎሳ በላይ የሚያስብ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብን የሚመለከት ነው። ፕሮፌሰሩ በአርባጉጉ ከተገደሉት ውስጥ ክርስቲያኖች የሆኑ ጎሳቸው ኦሮሞችም የሆኑ አሉ ብለዋል። ኢሰመጉ ያወጣው የስም ዝርዝር አጠገቤ የለም። በእርግጠኝነት የማውቀው ግን በአርባጉጉ የተካሄደውን እልቂት ዘግበው ለአዲስ አበባ ዩኒቬርስቲ ያስረከቡት ሰዎች፤ የጻፉት አማርኛ የአፍ መፍቻ ቁዋንቁዋቸው እንዳልሆነ ነው። ዘገባቸውም በተለይ እልቂቱ በክርስቲያኑ ሕዝብ ላይ ማነጣጠሩን አጽእኖት ስጥቶበታል። በተከታታይም እልቂቱን የሰሙት ከሸዋ የተነሱ ተቆርቁዋሪዎች የአጸፋ እርምጃ እንደወሰዱም በወቅቱ ይሰራጩ በነበሩ የነጻው ፕሬስ መጽሄቶች ተዘግቡዋል። ዞሮ ዞሮ ዓማራ እንደ ጎሳ ስሜት የለም ቢባል እንኩዋን፤ እንደ ክርስቲያን ተለይቶ መገደሉ በሃይማኖት ሰበብ እየተካሄደ ያለ ጽዳት ከመሆን አይለውጠውም። ፕሮፌሰሩ በዓማራ የለም ጉዳይ ላይ በተለያየ ጊዜ የሰጡት አስተያየት ይለያያል። ከመለስ ዜናዊ ጋር በቴሌቪዝን ቀርበው ከትነጋገሩ በሁዋላ፣ “ዓማራ የለም ያልኩት፤ አለ ተብሎ የታሰበው የለም ሲባል ኢላማ ያስታል ከሚል ነው”ማለታቸውን እርስተውት ወይም ወቅታዊ አልሆነም ብለው ትተውት ሊሆንም ይችል ይሆናል።

ዞሮ ዞሮ ዓማራ ማለት ክርስቲያን ማለት ብቻ እንኩዋን ቢሆንም፤ መሬት ይቅለላቸውና ፕሮፌሰር ዓሥራት ወልደየስ እንዳሉት፤ የወያኔ ትግሬዎች ዓማራ ብለው የሚያድኑትን ጠላት መለየተ ሲቸገሩ አናይም። ፕሮፌሰር መስፍን ዓማራ እንደ ሕዝብ የለም የሚል አባባላቸውን ለማጠናከር ከተጠቀሙበት ዋቢ አንዱ የሰምና ወርቅ መጻህፍ ነው።ይኽ እንዳለ ሆኖ፤ የደራሲውን የአማርኛ ችሎታ ማድነቃቸው እጅግ አስገርሞኛል። የሌቫይን/ሊበን የአማርኛ ቈዋንቁዋ ችሎታ እዚህ ግባ የሚባል እንዳልሆነ ራሱም በኢሳት ላይ ነግሮናል። ከፕሮፌሰሩ የበለጠ ስለ ሰብአዊ መብቶች ተከራካሪ መሆን ጣር ነው አሳር ካልሆነ። ይሁን እንጂ የእርሳቸው ፕሮፌሰራዊ ትንተና የሚፈጥረው ውዥንብር ዓማራን ከጥፍት ለመታደግ የሚደረገውን ትግል አያቆመውም። ዓማራ ምንም ይሁን ምን፤ ፍሺስት ኢታሊያ፣ወያኔ/ሻእቢያና ሌሎች ጎሰኞች ሊያጠፉት ሲፈልጉ አላጡትም። ዛሬ እንዳይጠፋ በቀንደኛ ጠላቱ በወያኔ ላይ ተቆጥቶ መነሳት አለበት። ደጉ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከጎኑ እንደቆመና እንደሚቆም ምንም ጥርጥር የለውም።

No comments:

Post a Comment