Monday, October 6, 2014

የአዜብ ዱላ በሰሎሞን አስመላሽ ላይ…


ከአርአያ ተስፋማሪያም

ጋዜጠኛ ሰሎሞን አስመላሽ ለብዙዎች እንግዳ አይደለም። የ120 መዝናኛ አዘጋጅ ነበር። ከኢቲቪ ከወጣ በኋላ ሜጋ አመራ። (በ1989ዓ.ም ከሳምሶን ማሞ ጋር በታዋቂ አትሌት ላይ የሞከሩት የፔፕሲ ማስታወቂያ ማጭበርበር ድርጊት ነበር፤ ጉዳዩን ለጊዜው እንለፈው) የሜጋ ሃላፊዎች እግር ስር ወድቀው ከወጡ በኋላ ሰሎሞን አስመላሽ የራሱን ማስታወቂያ ድርጅት ከፍቶ መስራት ቀጠለ። በአደባባይ የገዢው ፓርቲ ደጋፊና አቀንቃኝ መሆኑን የሚናገረው ጋዜጠኛ ሰሎሞን ከአራት አመት በፊት በምሽት መዝናኛ ውስጥ መጠጥ እየተጐነጨ ነበር። በድንገት መብራት ድርግም ይላል።


ሰሎሞን ጮክ ብሎ « አዜብ መስፍን ያስገባቸው ጄኔሬተር ተቸበቸበ! ሆን ተብሎ ነው መብራት የሚጠፋው..የአዜብን ጄኔረተር ለመሸጥ!» እያለ ተናገረ። በሚገርም ፍጥነት ይህቺ ቃል አዜብ መስፍን ጆሮ ደርሳለች። አዜብ ወዲያው በቀጭን ትእዛዝ ወደ መዝናኛው ደህንነቶች አዘመቱ። በዛው ሰሞን ሰሎሞን በውድ ዋጋ እጅግ ዘመናዊ አውቶሞቢል ሸምቶ ነበር። በስፍራው የደረሱት ደህንነቶች የመኪናዋን መስተዋት በመሰባበርና ጐማዎቿን በማስተንፈስ ተልእኳቸውን ጀመሩ። ሰሎሞን አስመላሽ ከመዝናኛው ሲወጣ አንድም የሰውነት አካሉ ሳይቀር በዱላ ቀጥቅጠው መንገድ ዳር ዘርረውት ሄዱ።

አዜብ « እንዳትገድሉት ግን ሰባብራችሁ ጣሉት» በማለት አዘው ስለነበረ ያንን ደህንነቶቹ እንደፈፀሙ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቅ ከፍተኛ የደህንነት ምንጭ አጋልጦዋል።…በነገራችን ላይ መስከረም 1 ቀን 1995ዓ.ም ፒያሳ ትግራይ ሆቴል በገዢዎቹ ተቀነባብሮ የተፈፀመው የፈንጂ ጥቃት በአሰቃቂ ሁኔታ ከሞቱት 60 ንፁህ ሰዎች አንዱ የሰሎሞን አስመላሽ ታናሽ ወንድም ይገኝበታል። ይህ ዘግናኝ ድርጊት እንዴት እንደተፈፀመ ጋዜጠኛው ካወቀ በኋላ ሞቅ ሲለው ይናገር ነበር።..በ1990 ዓ.ም ሰሎሞን አስመላሽ እጅግ ውብ የሆነች ፍቅረኛውን ተነጥቋል። በአሜሪካ ትኖር የነበረችው ፍቅረኛውን አንድ ለባለሃብቱና ለገዢው ባለስልጣናት ቅርብ የሆነ ግልገል “ቱጃር” የግሉ አድርጓታል። .. ጋዜጠኛው አሁንም የገዢው ደጋፊ ነው።

No comments:

Post a Comment