Sunday, July 20, 2014

ሽብርተኝነት በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ '' ሁለተኛው ክፍል''




ሁሉን የሚያውቀውና የሚናገረው ታላቁ መጽሀፍ መጽሀፍ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሽብር ምን ይለናል? መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ሽብር በብዙ ቦታ ተጽፎ እናገኘዋለን ነገርግን ለዛሬ ስለሽብር የተወሰኑትን ከመጽሀፍ ቅዱስ ቃል ለእዚህ ጽሁፍ በማዘጋጀት እግዚያብሔር ሁከትና ሽብርን እንዴት እንደገለጸውና ትርፋቸውንና ጉዳታቸውን አብረን በእዚህ ጽሁፍ እናየዋለን::
“ከዓመፃም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።” ማቴ 24:12
“ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ።ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።” ማቴ 4: 8_10
“ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።” ማቴ 5:43_45


“አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፥ ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።”
ማቴ 5:25_26


“ሰይፍ የሚያነሡ ሁሉ በሰይፍ ይጠፋሉና ሰይፍህን ወደ ስፍራው መልስ።” ማቴ 26:52
“ለቀደሙት። አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል።እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።” ማቴ 5:21_22
“ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።” ማቴ 10:28


“እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና።” ማቴ 10:26
“ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል::” ማቴ 24:6_7
“እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ ትዕቢትንና እብሪትን ክፉንም መንገድ ጠማማውንም አፍ እጠላለሁ። ምክርና መልካም ጥበብ የእኔ ነው፤ ማስተዋል እኔ ነኝ፥ ብርታትም አለኝ።” ምሳ 8:13_14
“የነገሩን ሁሉ ፍጻሜ እንስማ፤ ይህ የሰው ሁለንተናው ነውና፤ እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዙንም ጠብቅ። እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።” መክ 12:13_14
“ሰው ከሞት ወጥመድ ያመልጥ ዘድን እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው።” ምሳ 14:27
“የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።” ምሳ 1:7
“በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና።” ማቴ 24:21
“ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።” ፊሊ 2:12_13
“ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና። ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።” ሮሜ 12:9_21


“እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፤ ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።” ምሳ 6:16_19
“ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን እሻ ተከተላትም።” መዝ 34:14
“ ዓይን ስለ ዓይን ጥርስም ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት::” ማቴ 5:38_39
“ ነፍስ ሁሉ በበላይ ላሉት ባለ ሥልጣኖች ይገዛ። ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።ስለዚህ ባለ ሥልጣንን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ሥርዓት ይቃወማል፤ የሚቃወሙትም በራሳቸው ላይ ፍርድን ይቀበላሉ።ገዥዎች ለክፉ አድራጊዎች እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉምና። ባለ ሥልጣንን እንዳትፈራ ትወዳለህን? መልካሙን አድርግ ከእርሱም ምስጋና ይሆንልሃል፤ለመልካም ነገር ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። በከንቱ ግን ሰይፍ አይታጠቅምና ክፉ ብታደርግ ፍራ፤ ቍጣውን ለማሳየት ክፉ አድራጊውን የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና።ስለዚህ ስለ ቍጣው ብቻ አይደለም ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።ስለዚህ ደግሞ ትገብራላችሁና፤ በዚህ ነገር የሚተጉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።ለሁሉ የሚገባውን አስረክቡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ። ” ሮሜ 13:1_17

“ ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ። ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ። ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና።” 1ጴጥ 2:13_19
“እነሆ፥ ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን እንዴት ያለ ትጋት፥ እንዴት ያለ መልስ፥ እንዴት ያለ ቁጣ፥ እንዴት ያለ ፍርሃት፥ እንዴት ያለ ናፍቆት፥ እንዴት ያለ ቅንዓት፥ እንዴት ያለ በቀል በመካከላችሁ አደረገ። በዚህ ነገር ንጹሐን እንደ ሆናችሁ በሁሉ አስረድታችኋል።” 2ቆሮ 7:11
“የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ።የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም። ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።” ዕብ 10:26_31
“ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ፥ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ፥ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፤ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግንም ማድረግንም በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።” ፊሊ 2:12_13
“ከእናንተ ማንም ነፍሰ ገዳይ ወይም ሌባ ወይም ክፉ አድራጊ እንደሚሆን ወይም በሌሎች ጒዳይ እንደሚገባ ሆኖ መከራን አይቀበል፤ክርስቲያን እንደሚሆን ግን መከራን ቢቀበል ስለዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር።ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?ጻድቅም በጭንቅ የሚድን ከሆነ ዓመፀኛውና ኃጢአተኛው ወዴት ይታይ ዘንድ አለው?ስለዚህ ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራን የሚቀበሉ፥ መልካምን እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ አደራ ይስጡ።”
1ጴጥ 4:15_19
“እንደሚታዘዙ ልጆች ባለማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።ዳሩ ግን። እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ። ለሰው ፊትም ሳያደላ በእያንዳንዱ ላይ እንደ ሥራው የሚፈርደውን አባት ብላችሁ ብትጠሩ በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃት ኑሩ።” 1ጴጥ 1:14_17
“እግዚአብሔር የድሆችን ምኞት ሰማ፥ ጆሮውም የልባቸውን አሳብ አደመጠች፥ፍርዱ ለድሀ አደግና ለችግረኛ ይደረግ ዘንድ፥ ሰዎች በምድር ላይ አፋቸውን ከፍ ከፍ ማድረግ እንዳይደግሙ።” ሮሜ 10:17_18
“ በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።”
ኢሳ 2:4
“ተነሥተውም ሄዱ፤ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፥ የያዕቆብንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም።” ዘፍ 35:5
“መፈራቴንም በፊትህ እሰድዳለሁ፥ የምትሄድበትንም ሕዝብ ሁሉ አስደነግጣቸዋለሁ፥ ጠላቶችህንም ሁሉ በፊትህ ጀርባቸውን እንዲያዞሩ አደርጋለሁ።” ዘፀ 23:27
“ ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ወሬህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፥ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።” ዘዳ 2:25
“አምላካችሁ እግዚአብሔር በዓይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንደ ሠራው ሁሉ፥ በፈተናና በተአምራት፥ በድንቅና በሰልፍ፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ በታላቅም ማስፈራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ገብቶ ለእርሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ ሞክሮ ነበርን?” ዘዳ 4:34
“ ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል። ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥ ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው። ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም። እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።” መዝሙረ ዳዊት 1

ሽብርተኝነት በቁራን እይታ


በአለም ላይ ሽብርን በይፋና በግልጽ ለአለም ህብረተሰብ ያስተዋወቀው የሳውዲው ተወላጅና የዛሬ 3 አመት እኤአ 2, 2011በፓኪስታን የተገደለው የአልቃይዳው መሪ ኦሳማ ቢንላዲን እኤአ በመስከረም 11 2001 አማካኝነትና በዋና መጠሪያ 9/11 በመባል የሚታወቀው ታላቅ የሽብር ስራ በእሱ አማካኝነት ለአለም ህብረተሰብ አስተዋውቆአል::



ሟቹ የአልቃይዳው መሪ ኦሳማ ቢላዲን ከሌላው የሽብር ተቋማት የሚለየው የማትደፈረዋን ታላቋን አሜርካንን ማሸበሩ ደግሞ ኢጃኢብ ያሰኛል:: እንደ አሜርካ እስቴት ዲፓርትመንት የዘንድሮ 2014 ሪፓርት መሰረት በአለም ላይ ወደ 70 የተመዘገቡ የሽብር ተቋሞች ያሉ ሲሆን ከእነዚሁ ውስጥ 52 የኢስላምን ሀይማኖት ተገን ያደረጉ ናቸው:: ብዙ ግዜ የኢስላም የሽብር ድርጅቶች ከእጃቸው ሁለት ነገር አይጠፈም እነርሱም አንደኛው እጃቸው የጦር መሳሪያ ሲያነሳ ሌላው እጃቸው ደግሞ የእምነታቸውና የሀይማኖታቸው መመሪያ የሆነውን ቁራንን ጨብጦ ይዞ ብዙ ግዜ እናየዋለን:: ቁራን ስለሽብር ምን ያላል?
ጌታህ ወደ መላእክቱ እኔ “በእርዳታዬ” ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አፅናኑ:: በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሀትን በእርግጥ እጥላለሁ:: ከአንገቶችም በላይ “ራሶችን” ምቱ:: ከእነሱም የቅርንጫፎችን መለያሊይ ሁሉ ምቱ:: ሲል ያወረደውን አስታውስ::
“ሱራ 8:12”


እነዚያንም የካዱትን “በጦር ላይ” ባገኛችሁ ግዜ ጫንቃዎችን በሀይል ምቱ ባደካማችኋቸውም ጊዜ “አትግደሉዋቸው ማርኩዋቸው”:: ማሰሪያውኑም አጥብቁ ቡኋላም ወይም በነጻ ተለቃችዋላችሁ ወይም ትበዧቸዋላችሁ:: “ይህም” ጦሪቱ መሳሪያዋን እስከምትጥል ድረስ ነው:: “ነገሩ” ይህ ነው:: አላህም ቢሻ ከእነርሱ “ያለ ጦር” በተበቀለ ነበር:: ግን ከፊላችሁን በከፊል ሊሞክር “በእዚህ አዘዛችሁ” እነዚያንም በአላህ መንገድ ላይ የተገደሉትን ስራዎቻቸውንም ፈጽሞ አያጠፋባቸውም:: ሱራ 47:4
“አንተ ነብይ ሆይ ! ምእመናንን በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው::”
ሱራ 8:65


“እነዚያ ያመኑት ሰዎች በአላህ መንገድ ይጋደላሉ:: !”
ሱራ 4፡76
“እነዚያም ቅርቧን ህይወት በመጨረሻይቱ ህይወት የሚለውጡ በአላህ መንገድ ይጋደሉ:: በአላህም መንገድ የሚጋደል : የሚገደልም ወይም የሚያሸንፍ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጠዋለን::”
ሱራ 4:74


“በአላህም መንገድ (ሀይማኖት) ተጋደሉ:: አላህም ሰሚ አዋቂ መሆኑን እወቁ::”
ሱራ 2:44
“በአላህ መንገድ ላይ ይጋደላሉ:: ይገድላሉም : ይገደላሉም በተውራት በኢንጅልና በቁራንም (የተነገረውን) ተስፋ በእርሱ ላይ አረጋገጠ”ሱራ:9:111
“ከተማንም ለማጥፋት በፈለግን ግዜ ባለጸጋዎችዋን እናዛለን:: በውስጡዋም ያምጻሉ በእርሷም ላይ ቃሉ (ቅጣቱ) ይፈፀምባታል:: ማጥፋትንም እናጠፋታላን::” ሱራ 17:16


“ከሀዲዎችንም አትታዘዛቸው:: በእርሱም (በቁርአን) ታላቅ ትግል ታገላቸው::” ሱራ 25:52
“አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ሆናው በመንገዱ (በሀይማኖቱ) የሚጋደሉትን ይወዳል::”
ሱራ 61:4


እናንተ ያመናችሁ ሆይ ! አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ:: ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው:: ከእናንተም ውስጥ ረዳቶች የሚያደርጋቸው ሰው እርሱ ከእነርሱ ነው:: አለህ የአመጸኞችን ህዝቦች አያቀናም “ሱራ 5:51” እንተ ነብይ ሆይ ! ከሀዲዎችንና መናፍቃንን ታገል:: በእነሱም ላይ ጨክን መኖሪያቸውም ገሀነም ናት:: መመለሻይቱም ከፋች:: “ሱራ 9:73”
በእነርሱም ላይ ቁራን በተነበበ ግዜ የማይሰግዱት (የምንላቸው?) በእርግጥ እነዚያ የካዱት ( በትንሳኤ ) ያስተባብላሉ:: አላህም (በልቦቻቸው) የሚቆጥሩትን አዋቂ ነው:: በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው:: ሱራ 85:21_24
“ከዚያም አላህ እርጋታውን በመልክተኛውና በምእመናኖቹ ላይ አወረደ:: ያላያችኋቸውንም ሰራዊት አወረደ:: እነዚያን የካዱትንም በመግደልና በመማረክ አሰቃየ:: ይህም የከሀዲያን ፍዳ ነው::” ሱራ 9:26
“እነዚያ መጽሐፍ ከተሰጡት ሰዎች እነዚያን በአላህና በመጨረሻው ቀን የማያምኑትን አላህና መልእክተኛው አርሞ የማያደርጉትንና እውነተኛውንም ሀይማኖት የማይቀበሉትን እነርሱ የተዋረዱ ሆነው ግብርን በእጆቻቸው እስከሚሰጡ ድረስ ተዋጉአቸው::”
ሱራ 9:29
“እነዚያ በአላህ አንቀፆች የሚክዱ ነቢያትንም ያለ አግባብ የሚገድሉ ከሰዎችም ውስጥ እነዚያን በትክክለኝነት የሚያዙትን የሚገድሉ በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::” ሱራ 3:21
ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ግዜ አላህን የሚያስታውሱና ለሀጢያቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት ከአላህም ሌላ ሀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ:: (በስህተት በሰሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆን የማይዘወትሩ ለሆኑት ( ተደግሳለች )” ሱራ 3:135
“እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሀፉን ያወረደ ነው:: ከእርሱ ( ከመጽሀፉ) ግልጽ የሆኑ አንቀፆች አልሉ:: እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን ለመፈለግና ትችቱን ለመፈለግ ከእርሱ የተመሳሰለውን ይከተላሉ:: ( ትክክለኛ ) ትችቱንም አላህ ብቻ እንጂ ሌላ አያውቀውም:: በእውቀትም የጠለቁት “በእርሱ አምናናል ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው” ይላሉ:: የአእምሮ ባለቤቶችም እንጂ (ሌላው) አይገለፅም::” ሱራ 3:7
“(እነሱም ይላሉ) ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኅን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን ከአንተ ዘንድ የሆነን ችሮታም ለእኛ ስጠን:: አንተ በጣም ለጋስ ነህና” ሱራ 3:8
“ ጌታችን ሆይ አንተ በርሱ ( ለመምጣቱ ) ጥርጥር የሌለበት በሆነ ቀን ሰውን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ:: ምን ግዜም አላህ ቀጠሮውን አያፈርስምና” ሱራ 3:9
“እነዚያ በአላህ አንቀፆች የሚክዱ ነቢያትንም ያለ አግባብ የሚገድሉ ከሰዎችም ውስጥ እነዚያን በትክክለኝነት የሚያዙትን የሚገድሉ በአሳማሚ ቅጣት አብስራቸው::” ሱራ 3:21
“ጌታዬ ሆይ! ሰው ያልነካኝ ስሆን ለኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል አለች ነገሩ እንዳልሺው ነው:: አላህ የሚሻውን ይፈጥራል አንዳችን ባሻ ግዜ ለርሱ ሁን ይለዋል ወድያውኑም ይሆናል አላት::”ሱራ 3:47
“ወደ እስራኤልም ልጆች መልእክተኛ ያደርገዋል: (ይላልም) “እኔ ከጌታዬ ዘንድ በተአምር ወደ እናንተ መጣሁ:: እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርጽ እፈጥራለሁ :: በርሱም እተነፍስበታለሁ:: በአላህም ፈቃድ ወፍ ይሆናል:: በአላህም ፈቃድ እውር ሆኖ የተወለደን ለምፀኛንም አድናለሁ ሙታንንም አስነሳለሁ:: የምትበሉትንና በቤታችሁ የምታደልቡትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ:: የምታምኑ እንደሆናችሁ ለእናንተ በእዚህ ውስጥ በእርግጥ ተአምር አለበት” ሱራ 3:49
“ከከታማም ከጌታዋ ትእዛዝ ከመልክተኞችም ያመፀች ብርቱንም ቁጥጥር የተቆጣጠርናት መጥፎንም ቅጣት የቀጣናት ብዙ ናት::”
ሱራ 66:8
“የነገርዋንም ቅጣት ቀመሰች የነገርዋንም መጨረሻ ኪሳራ ሆነ::” ሱራ 66:9
ለጅብሪል ( ለገብርኤል ) ጠላት የሆነ ሰው (በቁጭት) ይሙት በላቸው:: እርሱ ( ቁርአኑን ) ከበፊቱ ለነበሩት ( መጽሀፍት ) አረጋጋጭ ለምእመናን መሪና ብስራት ሲሆን በአላህ ፈቃድ በልብህ ላይ አውርዶታልና:: ሱራ 2:97
ለአላህና ለመላእክቱ ለመልእክተኞችም ለጅብሪልም ለሚካልም ( ሚካኤል ) ጠላት የሆነ ሰው አላህ ( እነዚህ ) ከሀዲዎች ጠላት ነው::!
ሱራ 2:98


አላህና መልእክተኛውን ታዘዙ ብትሸሹም አላህ ከሀዲዎችን አይወድም በላቸው:: ሱራ 3:32
አላህ እነዚያን እነርሱ ልክ እንደ ተናሰ ግንብ የተሰለፉ ሆነው በመንገዱ ( በሀይማኖቱ ) የሚጋደሉትን ይወዳል:: ሱራ 61:4
እነዚያንም የሚጋደሉዋችሁን (ከሀዲዎች)በአላህ መንገድ ተጋደሉ:: ወሰንም አትለፉ አላህ ወሰን አላፊውን አይወድምና:: ባገኛችዋቸውም ስፍራ ሁሉ ግደሉዋቸው:: ከአወጧችሁም ስፍራ አውጡዋቸው:: መከራም ከመግደል ይበልጥ የበረታች ናት : በተከበረው መስኪድም ዘንድ በእርሱ ውስጥ እስከሚጋደሉዋችሁ ድረስ አትጋደሉአቸው:: ቢጋደሉአችሁም ግደሉዋቸው የከሀዲዎች ቅጣት እንደዚህ ነው:: ቢከለክሉም አላህ መሀሪ አዛኝ ነው::
ሁከት እስከማይገኝና ሀይማኖት ለአላህ ብቻ እስከሚሆን ድረስ ተጋደሉዋቸው:: ቢከለክሉም ወሰንን ማለፉ በበዳዮች ላይ እንጂ የለም ( ወሰን አትለፉባቸው ) ሱራ 2:190_193
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህ መንገድ ( ለመታገል ውጡ ) በተባለችሁ ግዜ ወደ ምድር የምትወዘፉት ለእናንተ ምን አላችሁ የቅርቢቱን ህይወት ከመጨረሻይቱ ይበልጥ ወደዳችሁን የቅርቢቱም ህይወት ጥቅም በመጨረሻይቱ ( አንጻር ) ጥቂት እንጂ አይደለም:: ለዘመቻ ባትወጡ (አላህ) አሳማሚ ቅጣት ይቀጣቸኋል:: ከእናንተ ሌላ የሆኑትንም ህዝቦች ይለውጣል:: በምንም አትጎዱትምም:: አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው:: ሱራ 9:38_39
እነዚያም የቅርቧን ህይወት በመጨረሻይቱ ህይወት በመጨረሻ ህይወት የሚለውጡ በአላህ መንገድ ይጋደሉ:: በአላህ መንገድ የሚጋደል : የሚገደልም የሚያሸንፍ ታላቅ ምንዳን በእርግጥ እንሰጠዋለን:: ሱራ 4:74
እነዚያ ያመኑት ሰዎች በአላህ መንገድ ይጋደላሉ:: እነዚያም የካዱትም በጣኦት መንገድ ይጋደላሉ:: የሰይጣንንም ጭፍሮች ተጋደሉ:: የሰይጣን ተንኮል ደካማ ናውና:: ሱራ 4:76



በእግዚያብሔር መንገድና ህግ የማይሄድ እንዲሁም እግዚያብሔርን የማይፈራ ባልም ቢሆን ሚስትም ብትሆን ልጅም ቢሆን ቤተክርስትያንም ብትሆን አገልጋይም ቢሆን መንግስትም ቢሆን ንጉስም ቢሆን ሌላም ቢሆን እርሱ ዋናው አሸባሪ ነው:: !
“ በአምላካችን ፊት ራሳችንን እናዋርድ ዘንድ፥ ከእርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ በዚያ በአኅዋ ወንዝ አጠገብ ጾም አወጅሁ።ንጉሡንም። የአምላካችን እጅ በሚሹት ሁሉ ላይ ለመልካም ነው፤ ኃይሉና ቍጣው ግን እርሱን በሚተዉ ሁሉ ላይ ነው ብለን ተናግረን ነበርና በመንገድ ካለው ጠላት ያድኑን ዘንድ ጭፍራና ፈረሰኞች ከንጉሡ እለምን ዘንድ አፍሬ ነበርና። ስለዚህም ነገር ጾምን፥ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን፤ እርሱም ተለመነን።” ዕዝ 8:21_23
ማራናታ !

No comments:

Post a Comment