Monday, September 22, 2014

ሕዝቡና ተማሪው በአገር ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር መግባባት አልቻልንም በማለት ስልጠናው እንዲቋረጥ ጠየቀ


ምንሊክ ሳልሳዊ

የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብሶታቸውን በከፍተኛ ቁጣ ገልጸዋል።

- ለወያኔ ባለስልጣናት የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም።

- የሃምሳ አመት እቅድ ለምን አስፈለገ የስልጣን ጥመኝነትን ያሳያል።

- ለሶስተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ እየተካሄደ ነው።

- በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይሁኑ አባላቶቹ የአስተዳደር ብቃት የላቸውም።

- ኢትዮጵያውያን በህግ ፊት እኩል የሚሆኑት እና ፍትህ የሚነግሰው ቀን እንናፍቃለን።

- በቫት ስም መንግስት ዘረፋ ይዟል በህጉ ቫት አይከፈልበትም የተባለው የጤና ዘርፍ ሳይቀር ቫት እየቆረጠ ነው።


በየአከባቢው እየተካሂደ ያለው ልማታዊነትን ሽፋን አድርጎ የስልጣን ማስረዘሚያ ሰበካ (ስልጠና) እንደቀጠለ ቢሆንም በህዝቡ እና በአሰልጣኞች መካክል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ከመከሰቱም በላይ ህዝቡና ተማሪው በአገራችን ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር ልንግባባ አልቻልንም ስለዚህ አበል ይቅርብን እና ስልጠናውን አቋርጡልን በማለት እየጠይቀ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። ሰልጣኞች እንደሚሉት እየተካሄደ ያለው ስልጠና ሳይሆን የፖለቲካ ሰበካ ነው ይህ ደሞ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸውን ህዝቦች ለማደናቆር ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ የያዛችሁን ስልት ቀይራችሁ ህዝብ መሃል ግቡና አናግሩን እንጂ በ አበል እና በቀበሌ ጥቅማጥቅም አታስገድዱን፡ አያዋጣችሁም ሲሉ ተናግረዋል።

Sunday, September 21, 2014

በጸረ ሽብር ህጉ የሚፈጸመው በደል እንዲቆም ተጠየቀ

በየተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት አማካሪ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር ህጉን ሰብአዊ መብትን ለመደፍጠጥ ከማዋል እንዲቆጠብ አሳሰበ፡፡ ይህ ማሳሰቢያ የመጣው የተለያዩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰትና አፈና እንዳሳሰባቸው መግለጻቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተግልጾአል፡፡ ማሳሰቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና በጸረ ሽብር ስም የሚወሰደውን እርምጃም ለመከላከል ያግዛል ተብሏል፡፡

‹‹ችግሩ እየተከሰተ እንደሆነ ከገለጽንበት ከሁለት አመት በኋላም ጸረ ሽብር ህጉ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችንና ተቃዋሚዎችን ሰለባ እያደረገ እንደሚገኝ ሪፖርት እየደረሰን ነው›› ያሉት ባለሙያዎቹ በተለይ በእስር ቤቶች ማሰቃየት፣ ኢሰብአዊ የሆኑ እርምጃዎች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ባለሙያዎቹ አክለውም ‹‹ሽብር መዋጋት ጠቃሚ ነው፡፡ ነገር ግን ውጤታማ ለመሆን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብትን በማክበር መከናወን አለበት›› ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጸረ ሽብር ህጎች በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ውስጥ በግልጸ መቀመጥና መጠቀሚያ መሆን እንደሌለበት መክረዋል፡፡

Tuesday, September 2, 2014

የወገኔ ዓማራ ነገር!

ከ ቦጋለ ካሳዬ


በወልቃይትም ሆነ በተቀረው ኢትዮጵያ ወያኔ ካለማቁዋረጥ ላለፉት 23 ዓመታት የሚያካሄደው አማራን የማጽዳት ዘመቻ
በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ በሌላ አገር የሚወዳደረው እንዳለ አላውቅም። ህዝብን ማጽዳት ግን እጅግ የቆየ፤ ምናልባት በአሳርያን
የተጀመረ ድርጊት እንደሆነ ጻሕፍት ያስረዳሉ።

ኢትዮጵያውያን ደጎችም ቂሎችም ስለሆንን፤ ወያኔ የሚያደርገውን ጭካኔ ስንሰማ፤ ኸረ ይኼ እንዴት ተድርጎ! ብለን የሆነውንና እየሆነ ያለውን ነገር ለመቀበል እንቸገራለን። ውይ! ውይ! እምጽ! የሰይጣን ጆሮ አይስማ ብለንም በደሉን እንደ ቀላል ነገር የምናረግብ አድርባይ የህሊና ዱልዱሞችና የውሸት ቤተክርስቲያን ተሳላሚዎችም ብዙዎች ነን።

የወገናቸውን በደል እውነት መሆኑን አጣርተው፤ ግፉ ነገ በራሳቸው ላይ ሊደርሰም እንደሚችል አስበው፤ ለችግሩ የማያዳግም መፍትሄ ለመስጠት ጥቂቶች ቁርጠኝነት ማሳየት ቢጀምሩም ለእስር፣ስደትና ግድያ እየተዳረጉ ነው። ብዙሃኑ በተለይ መረጃ በቀላሉ የሚያገኘው ከተሜ፤ መቼ የራሱም ሆነ የወገኑ በደል አንገፍግፎት ይኼን ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በሕብረት ከትከሻው ላይ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል አምላክ ብቻ ነው የሚያውቀው ማለት ሳይሻል ይቀራል?

ኽረ ለመሆኑ የሕዝብ ጽዳት ምንድን ነው? ነገሩ በእቅድ ተይዞ፤ ሆን ብሎ በጎሳ/ነገድ/ ብሄር፣በሃይማኖት፣በዘር፣በመደብ፣ ወይም በጾታ የሚለይና የማይፈለግ ሕዝብን ከአንድ አካባቢ ማስወገድ ነው። አተገባበሩም፤ ሰፋ