Monday, July 28, 2014

በስቃይ ላይ ተመርኩዘው የሚወጡ ቃላቶች የአንዳርጋቸው እንዳልሆኑ መናገር ይቻላል።

አባይ ሚዲያ፡ እንደተለመደው ሁሉ ወያኔዎች የኢትዮጵያ ህዝብ እንደማያምናቸው በተረዱ ጊዜ በርካታ ዘዴዎችን እየፈጠሩ ማሀበረሰቡን እያዋረዱ ረግጠው ለመግዛት ያላቸውን ሃይል ሁሉ ተጠቅመው ለማሳመን ጥረት ማድረጋቸውን እያየን ነው። ይህም አንዳርጋቸው እኔ ደህና ነኝ በል ተብሎ ያለው እና “እንደምታዩት ነው” ያለው ትልቅ መልእክት አለው።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለሁለተኛ ጊዜ አወራ ያሉት ነገር ግን በየ 50 ሴኮንድና አንድ ደቂቃ ልዩነት በሆነ እየተቆራረጠ ኢዲት ተድርጎ መጀመሪያ አካበቢ የተቀረጸውን ምስል እንዲሁም የህዝቡን ቁጣ ለማብረድ የተጨመረበት መጨረሻው ደቂቃ ላይ ሌላ ልብስ ለብሶ የታየበት ምስል የወያኔን ጭንቀት የሚያጎላ እንጂ ከቶ የአቶ አንዳርጋቸው አንደበቶች  ሳይሆኑ መትረጌስና ሽጉጥ እንዲሁም ገዳይ ጅቦች ተደርድረው በማሰቃያ ቤት የተቀዳ ድምጽ እንጂ እንደሚሉት በፌድራል ምርመራ ጣቢያ አይደለም።

የህግን ስርአት ገድሎ የቀበረው ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን ሲቀርጽ የታፈኑ የሲቃይ እና የድረሱልኝ ጩኸቶች ይሰሙ ነበር። ምናልባትም አቶ አንዳርጋቸው ከዛ ድብደባ በኋላ እንደወጣ ይገመታል።
ይህን በማስመልከት ወደ አዲስአበባ ዘጋቢያችን በመደወል የህዝቡን ስሜት እንዲገልጽልን ጠይቀነው ነበር።
የአዲስ አበባ እና የተቀረው ማህበረሰብ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ቲቪ ምንም አይጠብቅም አንዳንዶቹ አቶ አንዳርጋቸውን በል የሚሉትን ቀድመው መናገር እንደሚችሉ ለምሳሌ ግንቦት 7 በሀገር ውስጥ ያሉ እነ እከሌ፣ ቦንብ ያስገባነው ብዛት ያቀድናቸው ታርጌቶች እኔ ይቅርታ እጠይቃለሁ ወዘተ የሚሉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመውኑ ይናገራሉ በማለት አብራርቶል። በርካታ ኢትዮጵያኖች አንዳርጋቸው ያለበትን ሁኔታ ስለሚረዱ አንዴ በጠላት እጂ ከወደቀ በሆላ የሚናገራቸውን እንደምንም እንደማይቆጥሩት ምክንያቱም ዜጎችን ለማዋረድ ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በርካታ ልምዶች ያሉት እና የሰራ በመሆኑ እንደማይደንቃቸው በርግጠኝነት ተናግረዋል።


    ስለዚህም ላስተዋለው ቪዲዮውን ሁለት የተለያየ ልብስ እንደለበሰ እና የተቆራረጡት ምስሎች ይህን እንደሚያስረዱ ያሳያሉ። በመሆኑም አዲስ ነገር መጠበቅ  እንደሌለብን አሳስቦል።

    No comments:

    Post a Comment