Tuesday, July 15, 2014

አንዳርጋቸው ጽጌ ከአዲስ አበባ ውጪ ወዳልታወቀ ስፍራ ተዘዋወረ።


(ምንሊክ ሳልሳዊ)

የሕወሃት የደህንነት ቡድን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ወዳልታወቀ ስፍራ ከአዲስ አበባ ውጪ ወስዶታል ሲሉ ለቡድኑ ቅርብ የሆኑ የብአዴን ሰዎች ከአዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ሪቭው ተቁመዋል፡፤ ምናልባት አንዳርጋቸው ወደ መቀሌ አሊያም ከአዲስ አበባ ጫፎች ወዳሉ የደህንነት ምስጢራዊ እስር ቤት ወስደውት ሊሆን ይችላል የሚል ግምታቸውን ሰጥተዋል።


እንደ ምንጮቻን ከሆነ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የብአዴን አባላት የሕወህሃ አመራሮች የአንዳርጋቸውን መታፈን በምስጢር በግላቸው መፈጸማቸው በኢሕ አዴግ ድርጅቶች ውስጥ ያለውን አለመተማመን እና ብባዴን ሲፋቅ ግንቦት ሰባት ነው የሚለውን የሕወሃቶች አስተሳሰብ በገሃድ ያሳየ መሆኑን ተረድተናል ሲሉ ተናግረዋል።

በወያኔው ሚኒስትር በደብረጺሆን ገብረሚካኤል እና በደህንነት ሹሙ በጌታቸው አሰፋ የሚመራ የመሃል ሃገሩ የፕርትዎችን አባላት የሚሰልለው ቡድን በአሁን ወቅት የደመቀ መኮንን ጨምሮ የብአዴን ከፍተኛ አመራር እና ካድሬዎች የሆኑትን ግለሰቦችን የኢሜይል እና ኤስ ኤም ኤስ በመመርመር እና በመሰለል ላይ መሆኑ ሲታወቅ አቶ አንዳርጋቸው ከዚህ ቀደም ከኢሕዴን አመራሮች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው የሚል በሰፊው በሕወሓት ውስጥ ይታመናል።


http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=83091

No comments:

Post a Comment