Monday, July 7, 2014

በሕወሃት አባሎችና እንዲሁም በኢትዮጵያም ሆነ በዲያስፖራ በሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ላይ ያነጣጠረ አንዳርጋቸዋዊ ዘመቻ




ሙሳ ሙሃባ

Andargachew Tsige 2
1.በየአገሩ በተለያዩ ሽፋኖች ተሰግስገው ያለት ወንጀለኞች የወያኔ ሹማምንትና ደጋፊዎችን ለፍርድ ማቅረብ፤

2.የወያኔ ኤምባሲዎች ሥራ መሥራት የማይችሉበት ሁኔታ መፍጠር፤

3.የወያኔ አባላትና ደጋፊዎችን ከያሉበት (በሰፈር፣ በዩኒቨርስቲዎች፣ በንግድ የተሰማሩ ..) በማደን ማስነወር፣ ማግለል፣ ማዋረድ፤ ከእነሱ ጋር አንዳችም የንግድም ሆነ የሥራ ትብብር አለማድረግ፤ በሥራዎቻቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳዎችን ማካሄድ። ይህ ኢትዮጵያም ውስጥ በስፋት በሥራ ላይ መዋል ይኖርበታል።


4.ለሥራ ወይም ለሽርሽር የሚዘዋወሩ ከፍተኛ የወያኔ ባለሥልጣኖችና የጦር መኮንኖችን እየተከታተሉ ማሸማቀቅ፣ ማስነወር፣ መገታተር፤

5.የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ በወያኔ መንግሥት የሚመሩ ቢዝነስች ላይ እቀባ ማድረግ፤ በእነሱ ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማድረግ። ይህ በኢትዮጵያም በውጭ አገራትም መደረግ ይኖርበታል።

6.በዌስተር ዩኒየን እና በወያኔ ደጋፊዎች በኩል ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ አለመላክ፤ በየአካባቢው አማራጭ መላኪያ መንገዶችን መፈለግ።

7.ከወያኔ ጋር የሚሠሩ የውጭ አገር ድርጅቶች ከወያኔ ጋር ያላቸውን ሽርክና እንዲያቋርጡ መወትወት፤ አልሰማ ካሉ በቢዝነሳቸው ላይ አሉታዊ ቅስቀሳ ማካሄድ።

8.የምዕራብ አገራት ዩኒቨርስቲዎች ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት እንዲመረምሩ ማሳሰብ። በወጉ ሳያስተምሩ ለወያኔ ሹማምንቶች ዲግሪ የሚያድሉ ዩኒቨርስቲዎችና ኮሌጆችን ማስጠንቀቅ፤ ተግባሮቻቸውን ለተማሪዎቻቸው ጭምር መንገር (ለምሳሌ University of Greenwich ከ International Leadership Institute ጋር ያለውን ግኑኝነት እንዲሰርዝ፣ እስከዛሬ የሰጣቸውንም የማስትሬት ዲግሪዎች እንዲመረመር የሚጠይቅ ደብዳቤ ጽፎ በብዛት በፋክስ መላክ፤ ተመሳሳይ ደብዳቤ Open University እና ከወያኔ ጋር ተሻርከው ለሚሠሩ ዩኒቨርስቲና ኮሌጆች መላክ)

9.ይህ ዘመቻ ለጊዜው በወያኔ ላይ ያነጣጠረ ቢሆንም፣ የሕዝቡን የነፃነትና የፍትህ ጥረት የሚያደናቅፉ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ አገር ዜጎች በሆኑ ቱጃሮች የተያዙ ቢዝነሶችም የዘመቻው ዒላማ ሊሆኑ ይችላሉ።

No comments:

Post a Comment