Saturday, March 15, 2014

በአሜሪካ የሚኖረው የህወሓት ወንጀለኛ


በአሜሪካ የሚኖረው የህወሓት ወንጀለኛ 
(እየሩሳሌም አርአያ)


የሕወሐት አባል የሆነውና በአሜሪካ የሚኖረው ብስራት አማረ በርካታ ወንጀሎችን እንደፈፀመ የቅርብ ምንጮች አጋለጡ። ሕወሐት በረሃ እያለ የባዶ 6 እስር ቤት ዋና ሃላፊ የነበረው ብስራት አማረ
የኢ.ህ.አ.ፓ አባላት የነበሩት እነ ፀጋዬ ገ/መድህን (ደብተራው) ጨምሮ በሕወሐት የተያዙትን በሙሉ ወረኢ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በነበረ እስር ቤት በጅምላ አሰቃይቶ እንደገደላቸው ምንጮቹ አረጋግጠዋል።
በሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎች “ኢዲዩና ፊውዳል..” በሚል ባዶ 6 ተብሎ ይጠራ በነበረው እስር ቤት ተሰቃይተው እንዲገደሉ የተደረጉት በብስራት አማረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ ከዚህ በተጨማሪ የድርጅቱን በርካታ አባላት እንዳስገደለ አያይዘው ገልፀዋል። እነተክሉ ሃዋዝ በዚህ ወንጀለኛ ከተገደሉት
ይጠቀሳሉ ሲሉ ያክላሉ።
በ1983ዓ.ም ሕወሐት/ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ የሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን
ምክትል የነበረው ብስራት አማረ ከቤተ መንግስት የጃንሆይ የነበረ ከፍተኛ ወርቅ በመዝረፍ መውሰዱን
ያጋለጡት ምንጮቹ በዚህ የዘረፋ ወንጀል ሆለታ እስር ቤት እንዲገባ መደረጉን ያመለክታሉ። በነስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ ትእዛዝ እንዲፈታ ተደርጐ ወደ አሜሪካ የተሸኘው ብስራት አሜሪካ ሲጓዝ የዘረፈውን ወርቅ ይዞ እንደነበረ ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምንጮች በግርምት ይገልፃሉ።

ብስራት አማረ አሜሪካ ከመጣ በኋላ ቅርስ የሆኑትንና የዘረፋቸውን ወርቆች መሸጡንና አንዲት ሴት ለማሻሻጥ የተቀበለችውን 1 ኪሎ ወርቅ ከወሰደች በኋላ እንደካደችው ማወቅ ተችሎዋል። ብስራት አማረ ስለዚሁ ጉዳይ ተበሳጭቶ የነገራቸው ምንጮች ማረጋገጫ ይሰጣሉ። የብስራት ታናሽ ወንድም የሆነውና በደህንነት ቢሮ ይሰራ የነበረው ታጋይ ጠስሚ ( ጠስሚ - ትርጉሙ ቅቤ ማለት ነው) ከስራው በመልቀቅ የአስመጪና ላኪነት ትልቅ ቢዝነስ መክፈቱን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም፥ ድርጅቱ የተከፈተው ብስራት አሜሪካ ከገባ በኋላ በላከለት ገንዘብ መሆኑን አስታውቀዋል። (ስለዚሁ ጉዳይ በ1995 ዓ.ም በኢትኦጵ ጋዜጣ መረጃው ይፋ መደረጉና የብስራት ወንድም ቅቤ ኢትኦጵ ቢሮ ድረስ በመምጣት የጋዜጣውን አዘጋጅ በድንጋጤ ተውጦ “የራሴን ቢዝነስ ተቋም ነው፤ እነማን መረጃ እንደሚሰጧችሁ አውቃለሁ። እባካችሁ የእኔንም፣ የወንድሜንም ስም አታንሱ?” በማለት ተማጽኖ አቅርቦ ነበር)
ብስራት አማረ ከሽማግሌው ስብሃት ነጋ ጋር ባለው የጠበቀ ግንኙነት ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለስ መቆየቱን ያወሱት ምንጮቹ፣ ወንጀለኛውና ዘራፊው መቀሌ ሄዶ አስገደ ገ/ስላሴን እንደከሰሰ አስታውቀዋል። የደርግ ወንጀለኞች ከአሜሪካ በገዢው ፓርቲ እየተወሰዱ ነገር ግን የኢ.ህ.አ.ፓ አባላትንና ሌሎች ንጹሃን ዜጎችን በጅምላ የፈጀና የአገር ቅርስ የዘረፈ ወንጀለኛ ጠያቂ ማጣቱ አስገራሚ ነው ብለዋል ምንጮቹ። ጠያቂ አካል ካለ- በወንጀለኛው ብስራት አማረ ላይ ለመመስከር ፈቃደኛ መሆናቸውን አክለዋል። ይህን ምስክርነትና ማረጋገጫ ሊሰጡ የሚችሉና በአሜሪካ የሚኖሩ ሶስት የቀድሞ የሕወሐት ሹሞች እንዳሉና የብስራትን ወንጀል ጠንቅቀው የሚያውቁ መኖራቸውን አያይዘው ጠቁመዋል።

ኢትዮሚድያ -
                   

Wednesday, February 26, 2014

“ ነውራቸው ክብራቸው ”

          
    “ ነውራቸው ክብራቸው ”
                                                 
                                                 
        

በዚህ ሰሞን ከረዳት ካፕቴን ኀይለመድህን አበራ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶች ሳነብና ሳዳምጥ ነበር።  ካነበብኩት መካከል  አንዱ ላይ ድንገት አይኔን አሳረፍኩኝ። በርግጥ  በወያኔ ካድሬዎች የተፃፈው ነበር። ረዳት ካፕቴን ኀይለመድህን አበራ  የኢትዩጵያን ክብር አዋረደ የሚል አስተያየት። ግን  ኢትዮጵያ የተዋረደችው እውን  በኀይለመድህን ወይስ  እራሱ ወያኔ መንግስት ነኝ ብሎ አገራችንን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነው???

ህውሀት በአገራች ላይ የማይቆጠር በደልና ውርደት የፈፀመ አምባገነን መንግስት ለመሆኑ የማይረሳ ቢሆንም የቅርብ ጊዜውን በኢትዩጵያዊያን ህሊና ከማይረሳው ክፉ ትዝታዎች መካከል እስቲ ጥቂቶቹን ላስታውሳቸው።  መቼም እነርሱ አድርገውና አጥፍተው እንዳልተደረገ ሆነው መቅረብ  ጠባያቸው ነው       “ ታሪክ ይቅር የማይለው ውርደት” ነው ።

Sunday, February 23, 2014

ውሽት ልማዳቸው

    ውሽት ልማዳቸው 


በየዘመናቱ የዘመን ክፍተት ሆነው ያለፍ በርካታ ጀግኖችን ከታሪክ ለማወቅ ችለናል በዘመናችንም ለማየት በቅተናል በአመዛኙ የታሪክ ተመልካች እንጂ በታሪክ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ የሚደፍርም ጥቂት ቢሆን ከሁሉ የከፉው ደግሞ ከነኝህ ጥቂቱ አሻራ አሳራፊ ውስጥ
ለስልጣናአቸው ማራዘሚያ ሲሉ የታሪክ ጀግኞችን ስራ ሲደብቁ ህልምና ራዕያቸውን ሲሸፍኑ ማየት ከምንም በላይ ያሳምማል።

አሁን ባለንበት ዘመን መተኪያ የሌላ ነፍሳቸው ገብረው ለዛውም ከነ ህይወታቸው ራሳቸውን
አቃጥለው ለህዝቤ ነፃነቱን ስጡ ብለው ራሳቸውን መሰዋት ሲያደርጉ አንባገነኞች ግን የተለመደውን ስም እየለጠፉ ሲላቸው የአይምሮ በሽተኛ ነው ብቻ ደስ ያላቸው ስም ለጥፈው ራሳቸው እንዳሻቸው በሚያሻሩት ሚዲያ የጀግናው ስራ አፈር ከድሜ ያበሉታል።

Saturday, February 8, 2014

ጩኸታችን ለማን ? ለሀገራችን ወይስ ለፓለቲካ ድርጅታችን?

ጩኸታችን ለማን ? ለሀገራችን ወይስ ለፓለቲካ ድርጅታችን?     
                                                                                 
                                                               
ደርግ ውድቀት በኋላ አቆጥቁጦ የነበረውን ያንን የሕዝብ ተስፋና እምነት መለስ ብለን ስንቃኘው፣ ያ ብዙ የተጠበቀበት ተስፋውና እምነቱ ፍሬ አፍርቶ የታየበት ሳይሆን ቀርቷል። ይልቁንም ትግሉ ለዲሞክራሲና ለነጻነት የሚካሄደው ትግል አፍዝ አደንግዝ የተጠናወተው ሆኖአል። ሕዝቡ ያለ አንድነትና ሕብረት ነፃነት ሊኖረ አይችልም እያለ ቢጣራም፣ የሚደርስለት በማጣቱ ራሱን በራሱ በምቸገረኝነትና በግዴለሽነት እራሱን በተስፋ መቁረጥ አዘቅት ውስጥ ሊጥል ተገዷል።

ስለዚህ፣ ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስቃይና መከራ መልሰን መላልሰን ማላዘን ሳይሆን ከግፍና ከመከራ ማዕበል የመውጫውን    ብልሃት ማመንጨትና መተግበር ላይ ማትኮር ግድ ይለናል። በተለይም ‘በፓለቲካው መሪነት ላይ ያሉት’ ምን ማድረግና ማከናውን እንዳለባቸው ራሳቸውን መልሰው በዝርዝርና በጥልቀት መመርመር ግድ ይላቸዋል። አማራጭ በማይገኝበት በህብረት ትግል ውስጥ ሆኖ የዘረኛውን የወያኔን ስርአት መጣል የውዴታ ግዴታችን ነው። አለመታደል ሆኖ ግን በፓለቲካ ድርጅት መካከል ህብረት ሳይሆን መለያየት፣በጋራ አገር ማሰብን ሳይሆን የእኔ ብቻ ባይነት፣መገፋፋትና መነቃቀፍ በመሃላችን ነግሶ ይታያል።

Tuesday, January 7, 2014

“የራሷ እያረረባት የሰው ታማስላለች”

“የራሷ እያረረባት የሰው ታማስላለች”

“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” አለ ያገሬ ሰው ይህንን ማሳሌያዊ አነጋገር እዚህ ቦታ ላይ ያምክንያት አላመጣሁትም። ሰሞኑን የሰማሁት ነገር ገርሞኝ ነው። የወቅቱ የዓለም መነጋገሪያ ጉዳይ ያው እንደምታውቁት የደቡብ ሱዳን ጉዳይ ነው።  በሁለት የደቡብ ሱዳን ብሄረሰቦች መካከልየተጀመረው አሰቃቂ ጦርነት፣ የወቅቱ መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነበት በቂ ምክንያት አለ።

ካንድ ጎልማሳ እድሜ ያላነሰ ፍልሚያ ከሰሜኑ ሱዳን መንግስት ጋር ሲያደርጉ ቆይተው፣ ከብዙ የደም መፋሰስ ስቃይ በኋላ በተባበሩት መንግስታት፣ ባፍሪካ አንድነትና በመሳሰሉት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ያላሰለሰ ጠረት ሳቢያ ነጻነታቸውን ሊገኙ ችለዋል፡፡ ከዚያ ሁሉ እገዛ በኋላ ለዚህ ድል በመብቃታቸውና፤ ድፍን የአለም ህዝብ እሰይ አሁን የዚህ ህዝብ ስቃይ አበቃ ብሎ ትንሽ እንኳን ሳያገግም፣እንደገና ወደከፋ የደም መፋሰስ መግባታቸው እጅግ የሚዘገንን ሁኔታ ነው ።

ሌላ የውጭ ጠላት ሳይመጣባቸው እርስ በርሳቸው ብቻ በመባላት እንዲህ ያለውን አሳዛኝ እልቂት ሊፈጽሙት ችለዋል። ይህን ችግርም ማቆምም እጅግ በጣም ውስብስብ እንደሆነ እየተስተዋለ ነው። ለምን ቢሉ፣ ጦርነቱ የሚካሄደው ጎሳን መሰረት አድረጎ ስለሆነ፤ በሁለቱም ብሔር ወይም ጉሣዎች ዘንድ የሚጥለው ጠባሳ ትንሽ የሚባል አይደለም።

Sunday, January 5, 2014

ብሔርተኝነትና መዘዙ

ብሔርተኝነትና መዘዙ

መቼም ሁላችንም እንደምናውቀው አንድ ብሔር ሊወለድ የሚችለው ከአንድ ሰው ነው የዛን
ሰው የዘር ግንድ ይዘን ስንቆጥር መድረሻችን አንድ ሰው ወይም ሁለት ጥንዶች ጋር ያደርሰናል ። አዳምና ሄዋን እንዲሉ…

ለዚህ እንደምሳሌ ሊሆነን የሚችለው ሁላችንም የምናውቀው የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ነው፡፡ እሱን እንመልከት እስራኤል የሃገር ስም ሣይሆን የያዕቆብ ስም ነው፡፡ እርሱ የወለዳቸው አስራ ሁለት ልጆቹ ነገድ ወይም ብሔር ለመሆን በቁ፡፡ የኛንም ታሪክ ስንመለከት ልክ እንደዛው ነው፡፡ ለምሣሌ ስለ ኦሮሞ ብናነሳ ኦሮሞ የብሔር ስም አይደለም የሰው ስም እንጂ እርሱ የወለዳቸው እነ ሜጫና ቱለማ ሲወልዱ ሲዋለዱ በዙ ተባዙ ታላቅ ህዝብም ለመሆን በቁ፡፡ ለዚህም እንዴት እንደበቁ ለማወቅ አንድ በአንድ እንመርምር ቢባል በቂ የታሪክ ምስክርና አሻራ እናገኛለን ።  መነሻዬ ማን ማንን ወለደ የሚለውን መርምሮ ለማሳየት ሳይሆን የብሄርንና የጎሳን መዘዝ መጠቆም ነውና ወደ ተነሳሁበት ርዕስ ልመለስ፡፡