Sunday, February 23, 2014

ውሽት ልማዳቸው

    ውሽት ልማዳቸው 


በየዘመናቱ የዘመን ክፍተት ሆነው ያለፍ በርካታ ጀግኖችን ከታሪክ ለማወቅ ችለናል በዘመናችንም ለማየት በቅተናል በአመዛኙ የታሪክ ተመልካች እንጂ በታሪክ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ የሚደፍርም ጥቂት ቢሆን ከሁሉ የከፉው ደግሞ ከነኝህ ጥቂቱ አሻራ አሳራፊ ውስጥ
ለስልጣናአቸው ማራዘሚያ ሲሉ የታሪክ ጀግኞችን ስራ ሲደብቁ ህልምና ራዕያቸውን ሲሸፍኑ ማየት ከምንም በላይ ያሳምማል።

አሁን ባለንበት ዘመን መተኪያ የሌላ ነፍሳቸው ገብረው ለዛውም ከነ ህይወታቸው ራሳቸውን
አቃጥለው ለህዝቤ ነፃነቱን ስጡ ብለው ራሳቸውን መሰዋት ሲያደርጉ አንባገነኞች ግን የተለመደውን ስም እየለጠፉ ሲላቸው የአይምሮ በሽተኛ ነው ብቻ ደስ ያላቸው ስም ለጥፈው ራሳቸው እንዳሻቸው በሚያሻሩት ሚዲያ የጀግናው ስራ አፈር ከድሜ ያበሉታል።

እንዲህ አይነት ጀግንነት ከፈፀሙ በየአለማቱ ያሉትን ጀግኞች ትተን የራሳችንን ጀግና ለማንሳት ብደፍር እንዃን “የኔ ሰው ገብሬ” ከድንቅ ታሪክ ስራዎች አንድ ነው ግን የወያኔ ካድሬዎች የሰው ቤት ድረስ መግባት ያውቃሉና በገዛ እህቱ የአይምሮ በሽታ እንደነበረበት እንዲነገረን አድርገዋል እንዲህ ያለ የወንበዴ ስራ ለሚወደው ወያኔ አሁንም ስለወንድማችን ሀይለመድህ አበራ በተቻለው መንገድ ሕዝብን ለማሳመን ወደ ቤተሰቡ ደጅ እየጠና ይገኛል በ VOA እና በተለያዩ ሳሻል ሚዲያወች እንዳየነውና እንደሰማነው ሀሳብ የተሳካለት ይመስላል።

መቼም ወንድማችን የሚያደርገውን የሚያውቅ ነው ዋጋውን ገምቶ የወጣ ደፉር ጀግና ያሰበውን በተግባር ያሳየ ከሚኖርበት የድሎት ሕይወት  ይልቅ ለአላማው ሲል  የሚመጣውን ለመቀበል የተዘጋጀ ነው ። ከማንም ይልቅ ሁሉን በእውቀት የሚያደርግ ጀግና ነው ።

“የመጨረሻውን ቃል ለጀግናው ተውለት” እንደሚሉት ጥንታዊያን ፀሀፍት የእኔም ሀሳብ ከእንዲህ የዘለለ አይደለም አሁን ላይ ቤተሰቦች ነን ከሚሉ ወገኞች የሚገራረሙ ወሬወችን እየሰማን ነው ከሁሉ ያስገረመኝ አብራሪው በአይምሮ ጭንቀት ውስጥ እንደቆየ ተናግረዋል መቼም በአውሮፓና በአሜሪካ ጥገኝነት ለማግኘት መጥለፍ የሚያስፈልገው አይመስለኝ የሕዝብን ብሳትና ስቃይ ችግር መከራ ለመጠቆም ፈልጎ ሊሆን ይችላል እንጂል ።   የጀግናውን ስራ ለማበላሸት ወይም “ የኔ ሰው ገበሬ” ታሪክ ሊደግሙ አስበው እንጅ እውነት ለመናገ አይደለም  የወያኔ ስራ ራሱን ደገመ ይላችሗል ይሄ ነው።

እኔ ግን እላለሁ ! “ ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ” ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ይዘው የሀይመድህን አበራ አይነቱን ሰው መተቸት ይከብዳል።
እናም ጎበዝ የመጨረሻው ቃል ለጀግናው ተውለት !!!  

ኢትዮጵያ አገሬ ለዘላለም ትኑር !!!

                                              ምናሴ መስፍን
                                        almazmina@yahoo.com   


No comments:

Post a Comment