Saturday, February 8, 2014

ጩኸታችን ለማን ? ለሀገራችን ወይስ ለፓለቲካ ድርጅታችን?

ጩኸታችን ለማን ? ለሀገራችን ወይስ ለፓለቲካ ድርጅታችን?     
                                                                                 
                                                               
ደርግ ውድቀት በኋላ አቆጥቁጦ የነበረውን ያንን የሕዝብ ተስፋና እምነት መለስ ብለን ስንቃኘው፣ ያ ብዙ የተጠበቀበት ተስፋውና እምነቱ ፍሬ አፍርቶ የታየበት ሳይሆን ቀርቷል። ይልቁንም ትግሉ ለዲሞክራሲና ለነጻነት የሚካሄደው ትግል አፍዝ አደንግዝ የተጠናወተው ሆኖአል። ሕዝቡ ያለ አንድነትና ሕብረት ነፃነት ሊኖረ አይችልም እያለ ቢጣራም፣ የሚደርስለት በማጣቱ ራሱን በራሱ በምቸገረኝነትና በግዴለሽነት እራሱን በተስፋ መቁረጥ አዘቅት ውስጥ ሊጥል ተገዷል።

ስለዚህ፣ ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስቃይና መከራ መልሰን መላልሰን ማላዘን ሳይሆን ከግፍና ከመከራ ማዕበል የመውጫውን    ብልሃት ማመንጨትና መተግበር ላይ ማትኮር ግድ ይለናል። በተለይም ‘በፓለቲካው መሪነት ላይ ያሉት’ ምን ማድረግና ማከናውን እንዳለባቸው ራሳቸውን መልሰው በዝርዝርና በጥልቀት መመርመር ግድ ይላቸዋል። አማራጭ በማይገኝበት በህብረት ትግል ውስጥ ሆኖ የዘረኛውን የወያኔን ስርአት መጣል የውዴታ ግዴታችን ነው። አለመታደል ሆኖ ግን በፓለቲካ ድርጅት መካከል ህብረት ሳይሆን መለያየት፣በጋራ አገር ማሰብን ሳይሆን የእኔ ብቻ ባይነት፣መገፋፋትና መነቃቀፍ በመሃላችን ነግሶ ይታያል።

ስለሆነም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለያዩ የፓለቲካ ድርጅቶች እርስ በርስ አለመተባበር ምክንያት ተስፋ ቆርጦ የባለጊዜዎች    መቀለጃ ሆኗል። በዚህ አይነት መንገድ እስከመቼ ይሆን የምንጓዘው? እያለ ውስጡ እየተቃጠለ በመኖር ላይ ይገኛል። ለዚሀ ተስፋ መቁርጥ ያበቃውም ይሄው በብዙዎቹ የፓለቲካ ድርጀቶች መካከል ያለው ባብሮነት ያለ መቆም ችግር ነው።

         መንስኤዎቹንም ዘርዘር አድርገን ማየት እንችላለን።

1 ጠባብ ብሔርተኝነት  ማለትም አጀንዳቸው  የራሳቸውን ብሄረ ሰብ ጥቅምና ሥልጣን የማስከበርና የማቆየት ዓላማ ብቻ  የለቸው የመሆናቸው አባዜ  አንዱ ነው።ይህንንም ተልዕኮ እውን ለማድረግ የሚከተሉት ፖሊሲና አካሄዶች አፍራሽ ነው።  በተለይም  የኢትዮጵያን ግዛታዊ አንድነትና ሉዓላዊነት የሚጻረሩ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ሆነው ይቆማሉ። ሁል ጊዜም እኛ ብቻ እንደመጥ የሚልም ስሜት አላቸው። በነፃነትና በኩልነት ላይ ያተኮሩ የፓለቲካ ድርጅቶች ሁነው ለመውጣት አለመፈለጋቸው ጠባብነትን መርሃቸው እንዲያደርጉ ያስገድዳቸዋል። በአገር ቤትም በውጭም በዘር ላይ የተመሰረተ የፓለቲካ ፓርቲ መኖሩ ትለቁ ችግር ነው። የአማራ ፥ የኦሮሞ፥ የትግራይ ፥ የደቡብ ወዘተ… እያሉ በመቧደናቸው ወደ ሕብረት ለመምጣት ያለውን እድል እንዲጠብ አድርገውታል።  

2 መደባዊነት  ሁለተኛወ ችግር ነው። በዚህኛው ስር የተሰባሰቡት የፓለቲካ መሪዎች ፍፀም በእኩልነት ላይ አያምኑም።  እኛ ይላሉ በኢኮኖዊም ፥ በአባላትም፥ በእውቀትም ትልቆች እኛ ነን ባዮች ናቸው ። ከነሱ ጋር ለመስራት የሚፈልጉትን የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በእኛ ስር ሁኑ እንጂ በጋራ እኩል ቦታ ይዞ መስራትን አንቀበልም ይላሉ። በኮሌክሽን ሊደር ሽፕ አያምኑም፣ አይቀበሉምም ። በተጨማሪም ዲሞክራሲያዊ ያልሆነ አወቃቀርና ሂደትን ይመርጣሉ። የፓለቲካ ድርጅቱን የመሰረቱት ሰዎች የዲሞክራሲ መድረኩን  አጥብበው ይይዙታል። እርስ በርስ በዝምድና፣ በጓደኝነት ወዘተ… ሥልጣኑን ተከፋፍለውት ከላይ ተቀምጠው የሚፈልጉትን እንጂ ለአባልና ለደጋፊ ብሎም ለሕዝብ የሚበጀውን አይሰሩም። ለጋራ የሕብረት ትግል ዝግጁም አይደሉም ።

3 የግል ጥላቻ ሌላው ችግር ነው። በአንድ ወቅት በአንድ ፓርቲ ውስጥ አብረው ይታገሉ የነበሩ፣ በኋላ ወደ ሌላ   ድርጅት ገብተው ሲገኙ እንደጠላት ይፈረጃሉ፣ ይታያሉ። የግል ጸባቸውንና ችግራቸውን በግል መፍታትን አያውቁበትም። ወደ ግል በፓለቲካ  አመለካከት አለመስማማት እንኳን ቢኖር፣ እዛው በጠረጴዛ ዙሪያ ተወያይተው መፍታት ሲገባቸው፣ የሌላውን ወገን ህይወትና አገርን በሚጎዳ መልኩ ወደ አጥፍቶ መጥፋት እርምጃ ይሸጋገራሉ።   
4 ዘላቂነት ያለው የበጀት ምንጭ አለማግኘት ሌላው የችግር ምንጭ ነው። ጠንካራ ከመሆን ይልቅ ደካማ        ስለሚሆኑ ማድረግ የሚፈልጉትን ከማድረግ ይከለከላሉ (ራዕያቸውን)ማስፈፀም ይቸገራሉ። ከሌላው ጋር ተባብረው
ለመስራት ሲፈልጉ ከበታች ሁኑና ስሩ ይባላሉ። ከዚህ የተነሳ ከጨዋታ ይወጣሉ።

5 የእኛ ድርጅት ብቻ ነው የሚለው እምነት ሌላው ችግር ነው። ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠቅመው የእኛ እንጂ የሌላው አያስፈልግም የሚለው የተሳሳተ አመለካከት እጅግ ትግሉን ጎድቶታል። ከሌላው ጋር ከመስራት ይልቅ ይህኛው ከተገኘ አልገኝም እያሉም የሚንቀሳቀሱና ለለውጥ ዝግጁነት የሌላቸው  የሕብረት ጸር ድርጅቶች አሉ ።  

6 ዲሞክራሲያዊ የሆነ አወቃቀርና ሂደት አለመኖር = የፓለቲካ ድርጅቱ የመሰረቱት ሰዎች የዲሞክራሲ መድረኩን  አጥብበውታል ይይዙታል ራሳቸው በራሳቸው ሥልጣኑን ተከፉፍለውት ከላይ ተቀምጠው
የሚፈልጉትን እንጂ ለአባልና ለደጋፊ ለሕዝብ የሚበጀውን አይሰሩም ለጋራ የሕብረት ትግል ዝግጅ አይደሉም ።

7 የጋራና ጠንካራ የሚያስተዳድር እሴቶች አለመኖር አንዳንድ እንኮን ቢኖሩ ጠንካራ ሆነው መውጣት አልቻሉም ለዲሞክራሲ ያለን አመለካከት ደካማ መሆን ያመለክታ በነፃነትና በኩልነት ላይ ያተኮሩ የፓለቲካ ድርጅቶች አለመኖራቸው በአገር ቤትም በውጭም በዘር ላይ የተመሰረተ ፓለቲካ ፓርቲ መኖሩ ነው የአማራ ፥የኦሮሞ፥የትግራይ ፥የደቡብ ወዘተ እያሉ ወደ ሕብረት ለመምጣት ትልቅ ችግር ሆኖል

ከብዙ በትንሹ ለህብረት ጠንቅ የሆኑትን ምክንያቶች ለመጥቀስ ሞክሬያለሁ። ሌሎች እንዳይነት የሚጠቀሱ ምክንያቶች ደግሞ  ቅንንት መጥፋት ፥ አለመተማመን ፥ ትምክተኝነት ፥ ከእኔ ሌላ ላሳር ባይነት፥ የስልጣን አምሮትና ወዘተ… ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው። እነዚህንም ልናስወግድ ይገባል። የህብረት ጠላት የሆነውን ነገር ከተቃዋሚዎች አስወግደን ለአንዴና ለዘላለሙ ወያኔን በማስወገድ በነፃነትና በኩልነት ላይ የተመሰረተች  ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት በጋራና በሕብረት እንታገል።  

አገራችንንም ህዝባችንንም እፎይ የሚያደርግና የጠነከረን ህብረት ለመፍጠር ሁሉም የፓለቲካ ፓርቲዎች የተወከሉበት ከመቼውም ጊዜ በተሻለ መስራት የግድ ነው። የተቃሚያችም ጉልበት መውደቅ የሚጀምረው ያኔ ነው። ሁሉን የሚያደርግ አምላክ ለፍጻሜው ይርዳን። ከምንም ይልቅ በውጭ ያለን ኢትዮጵያውያን ተቃዋሚዎች ለአገር ውስጥ ተገንና ደጀን ከመሆን ፉንታ፣ ላለንበት ፓርቲ ብቻ መጮህ የሚቀናን የትግል አቅጣጫ እንዳልሆነ ቆም ብለን ማሰብ ይኖርብናል። የትግላች መሰረት ሀገርን ከወያኔ ነፃ ለማውጣት ከሆነ  ሀገራችንንና ህዝባችንን በቅንነት ለመርዳት በህብረት ቆመን እንታገል ።


                         ኢትዩጵያ አገራችን ለዘላለም ትኑር !!!    ምናሴ መስፍን 
                                                           almazmina@yahoo.com 

No comments:

Post a Comment