ፅናት
ከምናሴ መስፍን
ከኖርዌ ኦስሎ
ይህን ዕርዕስ
ስመርጥ ስለ ፅናት ትንታኔ ለመስጠት ሣይሆን ወይም ለፅናት ያለኝን አመለካከት ለመግለፅና ትምህርታዊ ዘገባ ለማቅረብ አይደለም ።
ይልቁንም
ፅናት ምን እንደሆነ ከፅናት ባለቤቶች ዘወትር ፅናት የሚሰብኩ ኢትዮጵያዊነታቸው አይሎ ሕዝባዊ ወገንተኝነታቸው ጉልቶ እድሜያቸው
ሙሉ በውስጣቸው የፍም እሣት የሆነው ሃገራዊ ፍቅር በማንኛውም
አይነት የግል ጥቅም ሳይሸነገሉና ሳይደለሉ ክብር ሕይወታቸው ለህዝብ ቤዛ ያደረጉ በለስ የቀና በጦርነት
አውድማ ላይ ከፀረ ሕዝብና ፀረ ዲምክራሲ ከህዝብ ጠላቶች ጋር ሳንጃ ለሳንጃ ተሞሽላልቆ አኩሪ መሠዋትነት ሲከፍል አንዳንዱ ደግሞ
ከጦርነት ሜዳ ውጭ ሠላም ባለበት አገርና መንግስት ባለበት የበአድ አገር
ላይ በጠላት
እጅ ይወድቅና ፅናት ምን እንደሆነ በአይበገሬነት የጠላት ዱላ ግልምጫና ወከባ ሣይበግረው ወይ ፍንክች ሣይል ዛሬም ለህዝብ መቆሙን
በጠላት ሚዲያ ሳይፈራ በጠንካራ መንፈስና አንደበት ለአመነበት አላማ ለፍትህና ለኩልነት ለሠላምና ለብልፅግና ፀንቶ ሰሞኑን ስላየሁት ስለ አንዳርጋቸውን ፅጌ ትንሸ ለማለት ብዬ ነው ።
አንዲ ፅኑ
ነው። ዛሬ በአለማችን ያሉ አንባገነን መንግስቶች ንፅሀን የአገራቸው ዜጎች ሲገርፍ፥
ሲገሉ፥
ሲያስሩና ሲያዋክብ የግል ጥቅማቸውን ለማሳካት ያገርና የህዝብን ሃብት እየዘረፉና ኪሳቸውን እያደለቡ በህዝብ ሰቆቃና ስቃይ ላይ
ጮቤ ሲረግጡ ይስተዋላል።
ከነዚህም ውስጥ በአለማችን ላይ ተወዳዳሪ የማይገኝለት አንባገነን ስርዓት የሚያራምደውና የአባገነኞች አንባገነን
TPLF
ሰው በላ ስርዓት ዛሬ የዛችን ትልቅ ሃገር ህዝብ ፍላጎትና ጥቅም በመርገጥ ህዝብን እያሰቃዮና እያሠረ፥እየገደለ፥እያፈነ ደብዛቸውን
እያጠፋ በማን አለብኝነት በዘረጋው የጭቆና መረብ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት አረመኔ ስርዓት መሆኑን ከታወቀ ውሎ አድሮአል ።
ታዲያ ይህን
ስርዓት በምንም መልኩ መታገስ የማይቻለው አስተዋይና አርቆ አሳቢ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በአመነበት መስመር የዘርና የሃይማኖት ልዩነት
ሣይበግረው የፓለቲካ
ልዩነት
ሣያፍረከረከው ይህን ሠው በላይ የወያኔ ስርዓት ዘላለማዊ መቃብር እየማሰለት ይገኛል።
ፈረንጆችም
enough is enough ይላሉ ያገሬ ህዝብ በአንድ ድምፅ ወቶ
በቃ ሊለው ይገባል። ነገር ግን የወያኔን ስርዓት በቃ በማለት ብቻ ፥በመፎከርና በቀረርቶ ስርዓቱን ልናሶግደው
የምንችለው ባለመሆኑ
ሁላችንም
በሕብረትና በጋራ ትከሻ ለትከሻ ተደጋግፈን እኛም አንድአርጋቸውን ሆነን በፅናት አብረን ስንቆም ብቻ ነው ።
እንግዲህ
ልብ ያለው ልብ ይበል አንዳርጋቸውን የበላ አውሬ ያንተንም ቤት ማንኳኳቱ አይቀርምና ተነሳ !!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!
No comments:
Post a Comment