አባይ ሚዲያ፡ እንደተለመደው ሁሉ ወያኔዎች የኢትዮጵያ ህዝብ እንደማያምናቸው በተረዱ ጊዜ በርካታ ዘዴዎችን እየፈጠሩ ማሀበረሰቡን እያዋረዱ ረግጠው ለመግዛት ያላቸውን ሃይል ሁሉ ተጠቅመው ለማሳመን ጥረት ማድረጋቸውን እያየን ነው። ይህም አንዳርጋቸው እኔ ደህና ነኝ በል ተብሎ ያለው እና “እንደምታዩት ነው” ያለው ትልቅ መልእክት አለው።

የህግን ስርአት ገድሎ የቀበረው ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን ሲቀርጽ የታፈኑ የሲቃይ እና የድረሱልኝ ጩኸቶች ይሰሙ ነበር። ምናልባትም አቶ አንዳርጋቸው ከዛ ድብደባ በኋላ እንደወጣ ይገመታል።
ይህን በማስመልከት ወደ አዲስአበባ ዘጋቢያችን በመደወል የህዝቡን ስሜት እንዲገልጽልን ጠይቀነው ነበር።
የአዲስ አበባ እና የተቀረው ማህበረሰብ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ቲቪ ምንም አይጠብቅም አንዳንዶቹ አቶ አንዳርጋቸውን በል የሚሉትን ቀድመው መናገር እንደሚችሉ ለምሳሌ ግንቦት 7 በሀገር ውስጥ ያሉ እነ እከሌ፣ ቦንብ ያስገባነው ብዛት ያቀድናቸው ታርጌቶች እኔ ይቅርታ እጠይቃለሁ ወዘተ የሚሉ ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመውኑ ይናገራሉ በማለት አብራርቶል። በርካታ ኢትዮጵያኖች አንዳርጋቸው ያለበትን ሁኔታ ስለሚረዱ አንዴ በጠላት እጂ ከወደቀ በሆላ የሚናገራቸውን እንደምንም እንደማይቆጥሩት ምክንያቱም ዜጎችን ለማዋረድ ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በርካታ ልምዶች ያሉት እና የሰራ በመሆኑ እንደማይደንቃቸው በርግጠኝነት ተናግረዋል።
ስለዚህም ላስተዋለው ቪዲዮውን ሁለት የተለያየ ልብስ እንደለበሰ እና የተቆራረጡት ምስሎች ይህን እንደሚያስረዱ ያሳያሉ። በመሆኑም አዲስ ነገር መጠበቅ እንደሌለብን አሳስቦል።
No comments:
Post a Comment