የማፈኛ መዋቅሩን መሰረት በማድረግ በርካቶች ጀግኖች ኢትዮጵያዊያን እጅግ በከፋና በሚዘገንን ሁኔታ በማጥፋት እኩይ ተግባሩ የሚታወቀው አረመኔው የወያኔ ስርዓት በአገራችን የተንሰራፋውን መጠነ-ሰፊ ተግዳሮት ከመሰረቱ ለመንቀል በሚደረገው ትግል ብርቱ ጥረትና እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከየመን መንግስት ጋር በማበር የአንድን ሰው ከአገር አገር የመንቀሳቀስ መብት በመጣስ የየመን መንግስት ለወያኔው ማስረከቡ አጥብቀን የምናወግዘውና የምንቃወመው ሲሆን ድርጅታችን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ በደረሰው አፈና መሰረት በማድረግ ማንኛውንም አይነት እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን አበክረን እናስታውቅለን።
ለአገርና ለወገን ዕድገት ብልጽግና ሲሉ በመታገላቸው ሳቢያ የየመን መንግስት እሳቸውን አፍኖ በማስረከቡ ምክንያት አገር ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ትግል ለአንድም ደቂቃ ቢሆን የሚገታው አለመሆኑን እብሪተኛው ቡድን ሊረዳው ይገባል።
በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በደረሰው የተቀነባበረ አፈና ዛሬ ላይ መግለጫ የማውጣታችን ምክንያት ጉዳዩ እስኪረጋገጥ በሚል እንጂ ቀደም ባሉት ቀናቶች መግለጫ ማውጣት ይጠበቅብን እንደነበረ እናምናለን ስለሆነም መላው የአገራችን ለውጥ ናፋቂ ወገናችን ሁሉ ይሄንኑ ሃሳባችንን በቅጡ እንዲረዳልን እናስገነዝባለን። እንደ አንድ ታጋይና አታጋይ እሳቸውን በተቃውሞ ትግል ማጣታችን ቃላት ሊገልጸው ከሚችለው በላይ በውስጣችን ቁጣን ፈጥሯል።
አገዛዙ አቶ አንዳርጋቸውን ከየመን መንግስት መረከቡ ለውጥ ናፋቂው ሕዝብ በፍርሃት ተሸብቦ ለትግል እንዳይነሳሳና ማንኛውም ተቃዋሚ የትም ሄደ የትም ከገባበት ገብተን በእጃችን ለማስገባት የሚያስችለን የዲፕሎማሲ ግንኙነት አለን በሚል ስጋት ለመፍጠር የተሰራ ቀመር ስለመሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም።
ትምክህተኛውና ዘራፊው ቡድን ያልተረዳው ነገር ቢኖር ሕዝቡ ለሚያነሳቸው መሰረታዊ ጥያቄዎች ትኩረት ሰጥቶ በማዳመጥ አግባባዊ በሆነ መልኩና ሕዝቡን ተጠቃሚ ሊያደርግ በሚችል መልኩ ምላሽ እስካልሰጠ ድረስ በማፈን፣ በማሳደድ፣ በማዋከብና በመግደል የሚመጣ መፍትሄ አለመኖሩን ብቻም ሳይሆን በሕዝብ ላይ የሚወሰዱ ጭፍን ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች በጨመሩ ቁጥር ስርዓቱ ራሱን ወደ መቃብር ጉድጓድ እያስጠጋ እንዳለ ሊረዳው ይገባል።
አንድነትሃይልነው!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር /ኢሕአግ/
|
No comments:
Post a Comment