Saturday, July 12, 2014

‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር ነው? ጽዮን ግርማ

ኢትዮጵያ በፓርቲ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባህል ውስጥ የገባችው የ1960ዎቹን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ርዮተ ዓለሞች ተፋጭተው ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ይመሰረትባታል በሚል ተስፋ ቢጣልም የድርጅቶቹ የኋላ ታሪክ እንደሚያስረዳው ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ለውጥ ከማምጣት ይልቅ እርስ በእርስ የመጨራረስ ባህል እንደነበራቸው ነው፡፡ ከበርካታ ንፁሃን ዜጎች ደም መፍሰስና እልቂት በኋላ ህወሓት ኢሕአዴግን መሥርቶ ወደ ሥልጣን ሲመጣም ከሻዕቢያ በስተቀር ሌሎቹ ድርጅቶች እስከ አመራሮቻቸው ደብዛቸው ጠፍቶ ነበር።ኢህአዲግ የሥልጣን ወንበሩን ከጨበጠ በኋላ በሽግግር መንግሥት ምስረታ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ይፋዊ ጥሪ በማስተላለፍ በፓርላማ መቀመጫ እንዲያገኙ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የተመሰረተ ለማስመሰል ጥረት ቢያደርግም በተለያየ ምክንያት አባሮ መልሶ ለመበታተን ጊዜ አልወሰደበትም ነበር ፡፡

No comments:

Post a Comment