የኢህአዲግ/ህወሃት ቁልፍ ተግባር:- አራት ኪሎን መጠበቅ
ልብ ብላችሁ ተመልከቱ:: ኢህአዲግ/ህወሃት ስልጣን ከያዘበት “ግንበት” 1983 ጀምሮ የሚፈጽማቸው ነገሮች ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያልሙት ቤተ መንግስን ለመጠበቅ ያለሙ ናቸው። ላፍታ ወደ ኋላ ልመላሳችሁ። ብዙ ሀገሮች ዋና ከተማቸውን የሚመሰርቱበት ቦታ ለሀገራቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ውጭያዊ እና ሌሎች ስትራቴጅ ጠቀሜታዎች የሚያበረክተውን አንድምታ መሰረት በማድረግ ነው። በተለይ የባህር በር ያላቸውን ሀገሮች ስንመለከት ብዙዎቹ ዋና ከተማቸው የባህር በርን የተንተራሰ ነው። ኢትዮጵያ ረጅም የባህር በር የነበራት ሀገር ነበረች። ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ምስራቅ (ከአማሴን ሰሜን ጫፍ እስከ ጅቡቲ ደቡባዊ ክፍል) ድረስ በቀጭን መስመር የባህር አዋሳኝነቷን ማጣቷ የኢትዮጵያን ካርታ የሚመለከት ባዕድ እንኳን የሚያጤነው ጉዳይ ነው። ይሄ ለምን ሆነ? የቀደሙ መንግስታት እራሳቸውን ከውጭ ወራሪ በህዝብ ለመከለል ይረዳናል ሲሉ ባላቸው ግንዛቤ እንደሆነ አንድ የታሪክ መምህሬ ክፍል ውስጥ ሲናገር አስታውሳለሁ:: ለእኔም ትርጉም ሰጥቶኛል። እናም ቤተ_መንግስትን ለማስከበር በማሰብ ዘላለማዊ የሀገር ማንነት እና ጥቅምን ወደ ጎን በመተው ዋና ከተማን መሃል ሀገር እና ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ቦታ (ኮረብታ) ላይ መመስረት የተለመደ ሆኖ የዘለቀ እውነታ ነው።