Friday, May 2, 2014

ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ምድር የዘራው የብሄር ፈንጂና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን!

ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ምድር የዘራው የብሄር ፈንጂና የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን!

Abrha-Desta1-150x150
  • digg
  • 1496
    Share
በአዲሱ የአዲስ ማስተር ፕላን በአዲስ አበባ ዙርያ ያሉ የኦሮምያ ክልል ገጠር መሬቶች የአዲስ አበባ ከተማ አካል ያደርጋቸዋል። ይሄን ጉዳይ በኦሮሞ ህዝብ ባጠቃላይ በኦሮሞ ተማሪዎች ደግሞ በተለይ ዓመፅ አስነስቷል።
ማስተር ፕላኑ የገጠር ቦታዎች ማካተቱ በራሱ ችግር አይደለም። እንዳዉም ፕላኑ ኦሮምያ አልፎ መቐለም ቢያጠቃልል ደስ ባለኝ ነበር። ከተማ ቢያድግ መልካም ነው። ከተማ ሲያድግም በዙርያው ይሰፋል። ይህ ባህርያዊ ነው። ግን ችግር አለ። በኢህአዴግ ዘመን እየተስተዋለ ያለው የከተሞች ማስፋፋት ስትራተጂ አፈፃፀም ኗሪዎችን እጅግ ይጎዳል።

የገጠር መሬት ወደ ከተማ<span class=”text_exposed_show”> ሲገባ በዛ የሚኖሩ አርሶአደሮች ያለ ፍቃዳቸው ከቀያቸው ይፈናቀላሉ። በቂ ካሳ (ክፍያ) አይሰጣቸውም። በዚህ መሰረት አርሶአደሮቹ ተቃውሞ ያሰማሉ። ይህ ጉዳይ በኦሮምያ ብቻ አይደለም የተከሰተው። በመቐለ ከተማም ተመሳስይ ችግር አለ። በመቐለ ዙርያ የሚኖሩ የእንደርታ ኗሪዎች ሁሌ ያለ ፍቃዳቸው እንደተፈናቀሉ ነው። በመቐለ ዙርያ ሁሌ ተቃውሞ አለ። ዓመፅ አለ። በመቐለ ዙርያ በዓይናለም፣ እግሪሓሪባ፣ ሰራዋት ወዘተ ያለ ከፍተኛ የህዝብ ተቃውሞ አሁን በኦሮምያ እየተካሄደ ካለው ተመሳሳይ ነው። የመንግስት አካላት ተቃውሞ ለሚያሰሙ ሰዎች የኃይል እርምጃ እየወሰዱ ይደበድቧቸዋል፣ ይገድሏቸዋል፣ ያስሩዋቸዋል፣ ያሰቃያቸዋል።
ይሄ ነገር በኦሮምያም መከሰቱ አይቀርም። ምክንያቱም በትግራይ የሚከናወን የህወሓት ተግባር በኦሮምያም በኦህዴድ መተግበሩ አይቀርም። ምክንያቱም ህወሓትና ኦህዴድ ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉና ነው። ይህን ነገር ተቃውሞ መቀስቀሱ ታድያ አይገርምም። አርሶአደሮች ኮ ከቀያቸው ሊፈናቀሉ ነው። “ገበሬዎች መሬታቸው ሽጠው ከቀያቸው እንዳይፈናቀሉ መሬት የመንግስት አድርገዋለሁ” ብሎ የሚዘፍን ስርዓት አርሶአደሮቹን ያለፍቃዳቸው ያፈናቅላል።
ሌላው ምክንያት ደግሞ የብሄር ፖለቲካችን ነው። ኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካ እያራመደ እርስበርሳችን እንዳንተማመን በብሄር ለያይቶናል። ይሄ የናንተ መሬት ነው፣ ይህ ደግሞ የነሱ ነው ወዘተ እያለ በቡድን ከፋፍሎናል። በብሄሮች መግባባት እንዳይኖር እነእገሌ እንዲህ አደረጓቹ ታሪካችሁ እንዲህ ነው። መጀመርያ መምጣት ያለበት ብሄር ነው ወዘተ እያለ የብሄር ጥላቻ እንዲሰፍን ሐውልት ሰርቶልናል። ባጠቃላይ የዓመፁ ምክንያት የኢህአዴግ የጥላቻ ፖለቲካ ሰበካ ነው።
ኢህአዴግ ብሄር መሰረት ባደረገው ፌደራሊዝሙ “ይሄ መሬት የኦሮምያ ነው፣ ነፍጠኞች እንዳይወስዱባቹ ተጠንቀቁ!” እያለ ጥላቻ ሲሰብክ ከርሞ አሁን የኦሮሞ ተወላጆች “የኦሮምያ መሬት የኛ ነው። ለማንም አሳልፈን አንሰጥም!” ሲሉት ግዜ ለምን የኃይል እርምጃ መውሰድ መረጠ? ኢህአዴግ ራሱ የዘራውን ነው እያጨደ ያለው።
<span class=”text_exposed_show”>የኦሮምያ ጉዳይ አሳሳቢ ነው። መንግስት የኃይል እርምጃ ከመውሰድ ተቆጥቦ መፍትሔ ቢያፈላልግ መልካም ነው። ጉዳዩ መፍትሔ ካልተበጀለት የብሄር ፈንጂ በተቀበረበት ሀገር ፈንጁ ይፈነዳና ህዝቦችን ሊጎዳ፣ ሀገርን ሊበታትን ይችላል። ከዓመፅ የሚጠቀም የለም፤ በግድያ የቆመ ዓመፅም የለም። ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ምድር የዘራውን የብሄር ፈንጂ በጥንቃቄ ማምከን ካልቻልን ረግጠን፣ አፈንድተን ራሳችንን እንጨርሳለን። በሀገራችን ጉዳይ ሁላችንን ያገባናል። የኃይል እርምጃ ይቁም፤ ነፃነት ይስፈን።
ለማንኛውም አሁን ሁኔታው ማረጋጋት አለብን። ኢህአዴግም በጉዳዩ ራሱን መፈተሽ ይኖርበታል። የኢህአዴግ የብሄር ፖለቲካ ከባድ ፈተና ደቅኖብናል።

No comments:

Post a Comment