Saturday, May 10, 2014

በግንቦት ወር የተከሰቱ 11 ታሪካዊ ሁነቶች


በግንቦት ወር የተከሰቱ 11 ታሪካዊ ሁነቶች


1. ግንቦት 1, 1947 ዓ.ም ሀገራቸውን ከድተው ለጣሊያን በባንዳነት ሲያገለግሉ የነበሩት የአስረስ ተሰማ የልጅ ልጅ የነበረው የቀድሞው አምባ­ገነኑ፣ ከፋፋዩና ጎጠኛው መሪ ለገሰ/ መለስ/ ዜናዊ የተወለደበት ቀን።

2. ግንቦት 8, 1981 ዓ.ም የሀገሪቱ ጄኔራሎች በመንግስቱ ሀይለማሪያም ላይ የመፍንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉበት ቀን።

3. ግንቦት 8, 1982 ዓ.ም በመንግስቱ ኃይለማሪያም ላይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉት ጄኔራሎች የተረሽኑበት ቀን።

4. ግንቦት 13, 1983 ዓ.ም አምባ­ገነኑ፣ ሰው በላውና ጨፍጫፊው መንግስቱ ኃይለማሪያም ሀገሪቱን ጥሎ ወደ ዚምባቡዌ የፈረጠጠበት ቀን።


5. ግንቦት 16, 1983 ዓ.ም ሻዕቢያ የኢትዮዽያ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የነበረችውን አሥመራን የተቆጣጠረበት ቀን።

6. ግንቦት 20, 1983 ዓ.ም አምባ­ገነኑ ኢህአዴግ የቀድሞውን አምባ­ገነን ደርግን የተካበት ቀን።

7. ግንቦት 4, 1990 ዓ.ም ሻዕቢያ ኢትዮጵያን የወረረበት ቀን።

8. ግንቦት 7, 1997 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በነቂስ ወጥቶ በምርጫ የራሱን መሪዎች
የመረጠበት ቀን። /በኋላ ኢህአዴግ ቢያጭበርብረንም/

9. ግንቦት 7, 1997 ዓ.ም ማታ ላይ መለስ የራሱን ሕገ­መንግስት ጥሶ ከግንቦት 8, 1997 ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት ከቤት ውጪ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ መከልከሉን ያወጀበት ቀን። ከ8 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከመለስ ሞት በኋላ በመለስ የታወጀው ሕገ­ወጥ ክልከላ እንዲሻር ማድረጉ ይታወቃል።

10. ግንቦት 8, 1997 ዓ.ም በሀገሪቱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የምርጫ ቆጠራው ሳይጠናቀቅና ምርጫ ቦርድም ምንም አይነት መግለጫ ከመስጠቱ በፊት ኢህአዴግ ከአዲስ አበባ በቀር በሁሉም የሀገሪቱ ክልል ምርጫውን ማሸነፉን በጉልበት ያወጀበት ቀን።

11. ግንቦት 10, 2004 ዓ.ም አበበ ገላው በአሜሪካ የመለስን ቀልብ የገፈፈበትና መለስም በአደባባይ ሲደነግጥ የታየበት ቀን። ከድንጋጤው ሳያገግም ከዚያ በፊት የነበረበት ህመም ተባብሶበት ከ2 ወር በኋላ በዚያው ሞተ። 

No comments:

Post a Comment