የዘረኛው የህውሃት ስርዓት በነፃ አውጪ ስም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም ከዛም በፊት የሚከተለው የተሳሳተ ሃገር መገነጣጠሉንና ቤሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ መስጠቱን መመልከት የተለመደና የቀን ከሌት ክንውናቸው መሆኑ በሃይል ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሚታይ እውነታ ነው፡፡
ከምስረታው ጀምሮ ይዞት የተነሳው የኢትዮጲያን ሉዋላዊነት የማፍረስና የመበተን አላማውን መተግበር የጀመረው የሻቢያ አሽከር በመሆን ለሃገር አንድነትና ክብር ዘብ የቆመውን የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት በመውጋት ሃገራችን ያለ ባህር በር እንድትቀርና በኢትዮጲያዊነት የታነፀውን ዘመናዊ የወታደር ሃይል በትኖ በምትኩ የአንድ ብሄር የበላይነት የሚታይበት፣ ቤሄራዊ ስሜት የሌለው፣ በአለቆቹ ከመታዘዝ ውጪ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት ያልዘለቀው ጀሌዎቻቸውን በህዝብ ላይ አንግሰው ያሻቸውን ሲገሉ፣ የሻቸውን ሲያስሩ እንሆ አሁን ያለንበት ደርሰናል፡፡
በመሰረቱ ይህ እኩይ ስርዓት(ቡድን) በኢትዮጲያዊነት ላይ ካለው የመረረ ጥላቻ የተነሳ አብረው የመሰረቱትን ግን በኢትዮጲያዊነት ላይ ፅኑ አቋም የነበራቸውን ባልንጀሮቻቸውን ሳይቀር እያስወገዱና እያባረሩ በምግባር የሚመቻቸውን በተለይ በህዝብና በሃገር ላይ የጠለቀ ጥላቻ ያላቸውን አስከትለው የጥፋት ዘመናቸውን ቀጥለውበታል፡፡
በተለይ የመንግስት ስልጣን ከያዙ በሗላ ከስልጣን በተጨማሪ በገቢ እራሳቸውን ለማጠናከር ከኢትዮጲያ ህዝብ በዘረፉት ሃብትና ንብረት በትግራይ ህዝብ ስም ባቋቋሙት ኢፈርት ሃገሪቱን ጫፍ እስከ ጫፍ በመቆጣጠር የንግዱን መስክ በበላይነት በመያዝ ገቢና ወጪው የማይታወቅ ትልቅ የሃብት ምንጭ በመፍጠር የአገሪቱን የትኛውም የንግድ እንቅስቃሴ በበላይነት ይዘው ነግሰውበታል፡፡
በተለያየ መስክ ከሚፈፀመው የሰብዓዊ መብት እረገጣ በተጨማሪ የሃገርን ቤሄራዊ ጥቅም አሳልፈው በመስጠት ወይም ገንዘብ የሚይስገኝላቸውን ሁሉ በመዝረፍና በማሸሽ፣ ምስኪኑ ህዝብ በዜግነቱ ሊያገኝ የሚገባውን ብቻ ሳይሆን በስሙ ተለምኖ የመጣውን ሁሉ በመንጠቅ ብዙሃን በርሃብ በሚሰቃይበት ሃገር ለአራት ለአምስት ትውልድ የሚበቃ ሃብት አሽሽተዋል፡፡
ከምርጫ 1997 ዓ.ም በፊት በተወሰነ መጠን እራሳቸው ላወጡት ህገ-መንግስት ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ቢያስቸግራቸውም ህጋዊ መስሎ ለመታየት የሚሞክሩበት ሁኔታዎች ይስተዋሉ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ፍርድ ቤት መመላለስ የእለት ከእለት ስራቸው ቢሆንም ከአሁን በተሻለ የህትመት ውጤቶች በቁጥርም በይዘትም የተሻሉ ነበሩ፡፡ በሌላም በኩል ይህው እኩይ ስርዓት ህግን ከመሻሩ በፊት የፓርላማ ጀሌዎቹንን ሰብስቦ ሊሽር ባስበው ህግ ላይ ሌላ ህግ ሲያወጣ ታይቷል ለምሳሌ የቀድሞ የህውሃት አባል የነበሩት አቶ ስዬ አብረሃ በተከሰሱበት ወንጀል ህጉ የሚፈቅድላቸውን የዋስትና መብት ለመከልከል ከፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት አዲስ ዋስትና የማያሰጥ የፀረ-ሙስና ህግ ማፅደቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ህውሃት በአመለካከትም ይሁን በግል ጥላቻ የራሱን ሰወች ሲበላ ከቻለ አንዱን በአንዱ ላይ አስነስቶ በማጫረስ አልያም በአደባባይ በደላቸውን እንዲናዘዙ በማስገደድ ከተጠያቂነት እራሱን ሲከላከል መቆየቱ አንድም እራሱን ላለማጋለጥ አልያም በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚፈፅማቸው በደሌች ሰርዞም ደልዞም ህግዊ ለመምሰል የጥር ነበር፡፡
ከምርጫ 1997ዓ.ም በሗላ ያለው በፊት ከነበረው ጋር ማነፃፀር ይከብዳል እጅግ ብዙ እርቀት ወደ ሗላ የመመለስ ያህል ነው ምክንያቱም በዛን ወቅት በተፈጠረው በጣም ጠባብ አጋጣሚ ህዝቡ ለስርዓቱ ይለውን ጥላቻና ለውጥ ፈላጊነቱን እንዲሁም እነሱ በተግባር የማያውቁትን ዴሞክራሲ ህዝቡ ሲዘምርላቸው፣ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከነሱ እንደሚሻል ሲያሳያቸው፣ ይበጁኛል የሃገሬንና የእኔን ህልውና ይጠብቁልኛል፣ ብሩህ የነፃነት ጊዜ ያመጡልኛል ይሆኑኛል ብሎ የሚላቸውን እንደራሴዎቹን ሲመርጥ ለአፍታ ይስተዋልባቸው የነበረው ሰዋዊ ባህሪየቸው ጠፍቶ ጫካ ተወልዶ ጫካ ያደገው አውሬነታቸው ሲመለስ የሚችሉትን ገለው ገሚሱን ወደ ማጎሪያቸው አግዘው ጭልጭል ትል የነበረች ተስፋችንን አደበዘዟት፡፡
ከዚህ በሗላ ያለችው ኢትዮጲያ የግል የህትመት ውጤቶች ሙሉ በሙሉ በማፈን በሃገራችው በሞያቸው ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ጋዜጠኞችን በማሰርና በማሳደድ፣ ለሃገራችን ክብርና ለህዝቧ ነፃነት የሚሟገቱ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት ወይም በሃገራቸው በነፃነት የመኖር መብት አጥተው የሚሰደዱባት አልያም የነሱ የሆነው በሌሎች ተቀምተው የመከራ ቀንበር ከብዶ በግዞት የሚኖርባት ስትሆን ለኢምንት ባለ ጊዜዎች ግን የምድር ገነት ሆና ያሻቸውን የሚሆኑባት የግል እርስት አድርገዋታል፡፡
ይህ ከላይ ያነሳሁትና ተነግሮ የማያልቀው በህዝብ በሃገር ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ በወያኔ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን የኛም ግፍና በደልን የመሸከም አቅም ወይም እንደ ሰው መብታችንን የማስጠበቅ፣ ህልውናችንን ያለማስደፈር ወይም በውርደት መኖር በቃኝ ብለን ሃላፊነታችንን ሳንወጣ እንዲሁ ከድርጅት ድርጅት ስንላተም፣ ከፓርቲ ፓርቲ ስንከለስ በተዘዋዋሪ የወያኔ መሳሪያ ሆነን በህዝባችንና በሃገራችን ላይ የሚደርሰውን በደልና እንግልት ዘመን እናሻግራለን፡፡
ይህ ከላይ ያነሳሁትና ተነግሮ የማያልቀው በህዝብ በሃገር ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ በወያኔ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን የኛም ግፍና በደልን የመሸከም አቅም ወይም እንደ ሰው መብታችንን የማስጠበቅ፣ ህልውናችንን ያለማስደፈር ወይም በውርደት መኖር በቃኝ ብለን ሃላፊነታችንን ሳንወጣ እንዲሁ ከድርጅት ድርጅት ስንላተም፣ ከፓርቲ ፓርቲ ስንከለስ በተዘዋዋሪ የወያኔ መሳሪያ ሆነን በህዝባችንና በሃገራችን ላይ የሚደርሰውን በደልና እንግልት ዘመን እናሻግራለን፡፡
ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ገዢዎቻችን ከተፈጥሮ ባህሪያቸው አንፃር የፈለጉትን ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብ ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ ህዝብ እንደ ህዝብ በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብሎ ለለውጥ እንዲነሳ በህብረት ከመስራት ይልቅ የነሱን መበታተንና መሰነጣጠቅ አውርተን በድክመታቸው ሳንጠቀም መልሰው ተደራጅተው መብትና ክብራችንን ሲገፉንና ሲፃረሩን እናያለን፡፡ ሃገርና ህዝብን ከዚህ እኩይ ስርዓት መታደግን ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ትተን በሰሞነኛ የወያኔ የጭካኔ ገድል ላይ ቡና እየጠጣን ስናነሳና ስንጥል ከወሬ የዘለለ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ሳንገባና የታደሉት ለሃገራቸውና ለህዝባቸው የሚከፍሉትን መስዋህትነት የሚሰሩትን ታላቅ ስራ ስናፈርስና ስንክብ የዜግነት ግዴታችንን በአግባቡ ሳንወጣ ለገዢዎቻችን መሳሪያ ሆነን በዛ ደሃ ህዝብና ሃገራችን ላይ ቁማር እንጫወታለን፡፡
ነፃነት በወሬና በዲስኩር አይመጣም የመስዋህቱ አይነት የለያይ እንጂ አነሰም በዛም የነፃነት ትግል ወይ ሃብትን ወይም የህይወት መስዋህትነት ይፈልጋል፡፡ ዶክተር መርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር እንዳለው “ለውጥ በመንኮራኩር ተጭኖ የሚቀርብ ነገር አይደለም ሊገኝ አይችልም፣ በማያቋርጥ ትግል እንጂ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን ለነፃነታችን መጣር አለብን ወገብህ ለመጥ ካላለ ጠላትህ ሊጋልብህ አይችልም. . . . . ከልምድ እንዳየነው ጨቋኝ ገዢ ነፃነትን በፈቃደኝነት አይሰጥም በተጨቋኞች መገደድ እንጂ” ይህ ነው እውነቱ ይህንን ሁሉ በህዝብና በሃገር ላይ የሚደርሰውን ለከት ያጣ ጭቆና የምናይና የምንሰማ በተለይ በሰለጠነው አለም የምንኖር ወገኖች እኛ በሰው ሃገር የምናገኘውን ነፃነት ወገናችን በገዛ ሃገሩ ሲያጣ፣ ይህ ነው የማይባል ችግር ሲወርድበት ከወሬ ያለፈ በተግባር የተፈተን ስራ መስራት ስለምን ተሳነን፣ ስለምን የህይወት መሰዋትነት ለሚከፈልበት የነፃነት ትግል በገንዘብ ለማገዝ ሰነፍን፣ስለምን ከወያኔ ለምናገኝው ቁራሽ መሬት ብለን የወገኖቻችንን የመከራ ጊዜ እናራዝማለን፣ ቁጥር ስፍር የሌለው ህዝብ በውጪው አለም እየኖረ ስለምን የህዝባችን የመረጃ ምንጭ የሆነው ኢሳት መስራት ያለበትን ያህል እንዲሰራና ህዝባችን እየተራበ መጥገቡን፣ እየከሰረ ማትረፉን፣ እየተቸገረ መበልፀጉን ከሚነግረው የወያኔ ዲስኩር አውጥተን አማራጭና እውነተኛ መረጃ የሚያገኝበትን፣ ወያኔ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው እያደረገ ያለውን ዘርን ከዘር ሃይማኖት ከሃይማኖት የማጋጨትና የመሳሰሉትን የወያኔን ሴራ ህዝቡ እንዲያቅና በአንድነት ለመብቱና ለነፃነቱ እንዲነሳ ኢሳትን በመረዳት የዜግነት ግዴታችንን አንወጣም?
በነፃነት በመኖር የምንቀድማቸው ሃገራት ሰልጥነው በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አሰተዳደር የህዝቦቻቸውን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ዘመን የሗሊት የሚጓዘው ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት ከብዙ ዘመናት በፊት በነበረው አስተሳሰብና የሃይል አገዛዝ ተሸብቦ ያልደረሰበት ጫፍ፣ ያላስነባው ህዝብ፣ ያልጣሰው ህግና ስርዓት፣ ያላፈረሰው አንድነት፣ያላዋረደው የህዝብ ስብእና፣ ያልገባበት የእምነት ተቋም፣ ያልበተነው የሞያ ማህበራት ከከተማ ነዋሪ እስከ ገበሬው አልፎም እስከ አርብቶ አደሩ ያልገደለው፣ ያላሰረውና ያላስለቀሰው የህብረተሰብ ክፍል የለም፡፡
በአሁኑ ወቅት አዛዥና ታዛዥ የሌለበት የወያኔ ስርዓት ዘመኑ እያከተመ መሆኑን ከሚሰራቸው ስራዎች መገንዘብ አይከብድም ህግ ማሰከበር ያለበት መንግስት ላወጣው ህግ መገዛት የማይችልበት ደረጃ ከደረሰ ህልውናው አደጋ ውስጥ ለመሆኑ ማሳያ ነው ለዚህም መብቱን በወያኔ የተነጠቀው ህዝብ የህገ-መንግስቱን አንቀፅ እያሳየ የህግ ያለህ ሲል መደመጡ፡ በግምት የሚመራን ስርዓት የመጨረሻው ጠርዝ ላይ መቆሙን አመላካች ነው፡፡
ስለሆነም ኢትዮጲያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማረግ ለነፃነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ከወሬ በዘለለ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!
No comments:
Post a Comment