ሰሞኑን ወያኔ የተለመደ የውሸት ድራማ ሰርቶ፤ ሲሞን በረከት በሚባል፤ የማያምር፤ የማያፍር የኤርትራ ሰው፤ ጭራሹን አማራ ነኝ ብሎ እንዲያታልል ወያኔ የቀጠረው ባእድ የፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር፤ የሀሰት ፊልም ደራሲና የበላይ አዘጋጅ የሆነ ሰው፤ ሰርቶ ጨርሶ ያሳለፈውን “ጂሀዳዊ ሀረካት” በሚል ርእስ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ከሚያደርገው ነገር የተለየ ባይሆንም፤ ቀጣይ የማናደድ ስራቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ አቅርበው ነበር። እንደድሮው አረፍተነገርና የስእል እንቅስቃሴ እየበጣጠሱ፤ ቆርጠው እየቀጣጠሉ፡ እየገጣጠሙ፤ ውሸት እየደራረቱ፤ ለራሳቸው ያሳምናል ብለው እንደመሰላቸው ለኢትዮጵያ ህዝብም ይመስለዋል ብለው በታመመ አእምሮ ስለሚያስቡ ለቀውታል።
ከኢትዮጵያዊው ሙስሊም የመብት ጥያቄ ጋር እንዲሁም ባህሪ ጋር ከቶም ከቶ የማይገናኝ፤ የንጹሀን ሙስሊም ወንድሞቻችንን ስም ለማጥፋት፤ መልካሙን የኢትዮጵያ ሙስሊም ሀይማኖትና ወደር የለሽ መልካም ስነምግባር ጥላሸት ለመቀባት፡ ይህንን ውብ መልኩን ለማጠልሸት፤ ብሎም ከኢትዮጵያዊ ክርስቲያን ወንድሙ ጋር ለማጋጨት ደም ለማቃባት፤(የማይቻል መሆኑን ቢያውቁትም) የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ነዝተዋል።
ኢትዮጵያዊው ሙስሊምና ኢትዮጵያዊው ክርስቲያን ተቃቅፎ፤ ተደጋግፎ፤ በሞት በልደት ተጠያይቆ፤ ተቀባብሮ፤ ተዛዝኖ፤ የሚኖር፤ ክርስቲያኑ የሙስሊሙን አውድአመት አክብሮ፤ ኢድ አልፈጥር፤ ኢድሙባረክ ተባብሎ፤ ሙስሊሙ የክርስቲያኑን አውዳመት አክብሮ እንኳን ለገና እንኳን ለመስቀል አደረሳችሁ ብሎ፡አብሮ በልቶ፤ ጠጥቶ፤ ተደስቶ፤ ሰምና ወርቅ ሆኖ ለዘመናት የኖረ፤ እየኖረ ያለ፤ ወደፊትም የሚኖር ህዝብ ነው።
ወያኔዎች፤ የጣሊያን ጻእረመንስ ርኩሳን፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ዘርን ከዘር በማጋጨት አልሆን ሲላቸው፤ በሀይማኖቱም ሞክረው ባይሳካላቸውም፤ አሁን ያደረጉት ነገር የሚያሳየው ተስፋ አለመቁረጣቸውን ነው። “አንድቀን እናያይዛቸዋለን” የሚል ህልም እስካሁን እንዳላቸው ይህ ፊልም ያረጋግጣል።
እንደዚያ መሰሪ አለቃቸው ከርሰመቃብር ካልወረዱ ጥረታቸው እስከመጨረሻው ይቀጥላል። ግን..ግን..ሁለት ሁለቱን እያጣመረ እግዜር እየወሰደ እሰከሚጨርሳቸው እኛም የምንጠብቅ ከሆነ ጅሎችና ፈሪዎች ነን። እግዚአብሄር ጀምሮ አሳይቶናል። የስርአቱን እስትንፋስ መጨረስ የኛ ፈንታ ነው።
በፈጠራው ፊልም ለማሳየት የተሞከረው የመላውን አለም ቀልብ የሳበውን፤ የብዙ ሀገር መንግስታት ያስቀናውን፤ በየትም ያልታየውን፤ ፍጹም ሰላማዊ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ንቅናቄ፤ ናይጄሪያ ውስጥ እንዳሉት እብዶች፤ ማሊ፤ ሶማሊያ፤ አፍጋኒስታን አሁን አለማችን ካለችበት የስልጣኔ ደረጃ እጅግ በራቀ ሁኔታ ወደሗላ ተመልሰን እንተዳደር፤ የሚሉ፤ ቅዱስ ቁርአንንም ጠንቅቀው ያልተረዱ፤ ነብያችን ሙሀመድ ያሉትንም ጠንቅቀው የማያውቁ አሸባሪዎች፤ናቸው ተብሎ የሚነገርላቸው ጂሀዲስቶች፤የሚያደርጉትን ነገር፤ ኢትዮጵያዊው ሙስሊም የመረጣቸው መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፤ መሪዎች ሊያደርጉ የተዘጋጁ ወይም የሚያደርጉ ናቸው የሚል ነው።
ኢትዮጵያዊው ሙስሊምማ አሸባሪ አልቃይዳ ቢሆን ኖሮ እየተገደለ ሰላምን ለማምጣት ባልጣረ ነበር። ኢትዮጵያዊው ሙስሊምማ አልቃይዳ ቢሆን ኖር ገና የመጀመሪያዋ ጥይት ከወያኔ ስትተኮስበት አፈርድቤ ባስጋጣቸው ነበር። ችግሩ ትንንሽ ሰዎች ታላላቅ ሰዎቸን የሚያስተዳድሩ ሆነ። ይህንን ፊልም ለኢትዮዮጵያ ህዝብ ከሚያሳዩት ይልቅ፤ለምእራባውያን ጌቶቻቸው፤ ወይንም ለቻይና የንግድና የሌብነት ሸሪኮቻቸው ቢያሳዩት ስለሚታመኑ እንደልማዳቸው የገንዘብ እርዳታ በማጭበርበር ማግኝት ያስችላቸው ነበር። ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳየታቸው ከንቱ ድካም ነው። ተስፋ ያለመቁረጠቸው አስገራሚ ሊሆን ይችላል።
ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቻም አይደለም ለመላው ዓለም በየትም ባልታየ መልኩ ታላቅ ትምህርት እያስተማረ ይገኛል። እየተገደለ፤ እየተገረፈ፤ እየታሰረ፤ መብቱን ለማስከበር “በዲናችን እንጽና “ ብሎ በጽናት መታገል ይዟል።ሚሊዮኖች ህዝብ፤ አንድ ሀይማኖት፤ አንድ ህዝብ፤ አንድ አቋም! “ ሕገመንግስታዊ መብታችን ይከበር! ድምጻችን ይሰማ!” ሌላ ነገር የለም።
ለኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች፤ ሙስሊም ወንድሞቻችን እህቶቻችን የሚጠይቁት የሀይማኖት ነጻነት የሚመለከተን አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። ፈሪሀ እግዚአብሄር የሌላቸው፤ ሀይማኖት የሌላቸው፤ ኢትዮጵያዊ ሰብእናናሞራል የሌላቸው፤ በጦር ሀይል መደራጀት የቻሉ ሌቦች፤ ዝቃጭ የህብረተሰብ ክፍሎች፤ኢትዮጵያን የምታህል ትልቅ ሀገር መቆጣጠር የቻሉ ፍጹም እድለኛ ወንጀለኞች ይዘውናል። እስላምንም እኛ የምንፈጥረውን ካልሆነ፤ ክርስትናውንም እኛ የምንፈጥረውን ካልሆነ ምንም መሆን አትችሉም ብለው ዘጠና ሚሊዮን ህዝብ ወጥረዋል። እኛ ነን እነሱ ናቸው ብዙና ሀይለኛ?
የኢትዮጵያ ሙስሊም እንኳን ጂሀድ ሊያውጅ፤ እየተገደለ፤ እየታሰረ፤ እየተገረፈ፤ ባሳለፈው አንድ አመት ጠጠር አንስቶ የወረወረ ሕዝብ አይደለም። ሕዝቡ ታላቅ የሰላም ሀዋርያ ነው። ወደ አላህ ከማልቀስ በቀር ያደረገው ነገር የለም። የኢትዮጵያን ህዝብ ታላቅነት ያመለከተ ታላቅ ተግባር ነው። ትግስት። ይህ ስልጣን ላይ ላሉት ባለጌ የባንዳ ልጆች ትርጉም የሚሰጣቸው ነገር አይደለም።
ጂሀድ!..አዎ.. ትክክለኛ ወያኔያዊ ጂሀድ! በኢትዮጵያ ከሰፈነ ሀያ ሁለት አመት አስቆጥሯል። በሰይፍ ዘረኝነትን ማስፋፋት፤ በሰይፍ ህዝብን መከፋፈል፤ በሰይፍ የግለሰብን የሀገርን ሀብት መዝረፍ፤ በሰይፍ የኔ ዘር እንጂ የማንም ዘር ጦር መሆን አይችልም ብሎ የአንድዘር ሚሊሺያ ተቀበሉ ማለት፤ በሰይፍ ዜጎችን እየገደሉ መሬታቸውን ለባእዳን መሸጥ፤ በሰይፍ ተቃዋሚን ሁሉ ማጥፋት፤ በሰይፍ እኔ ያመጣሁልህን ሀይማኖት ተቀበል ማለት፤ ሀያ ሁለት አመት! የኢትዮጵያ ህዝብ ሊዋጋው የሚገባ ጂሀድ ይህ ነው።
ለብዙ ሺህ ዘመናት ተፋቅሮ በየትኛውም አለም በሌለ መልኩ ተከባብሮ የሚኖርን ህዝብ ለማባላት “እስላም ጂሀድ ሊያውጅብህ ነው” ብሎ ክርስቲያኑን ቢያስፈራራ፤ ህይወትም ዩኒቨርስቲ ነውና ሀያ ሁለት አመት ሙሉ የመከራ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ያሳለፈ ህዝብ ለእያንዳንዱ ሰው ከእድሜው ቁጥር በላይ እየዋሹ ላያቸው ህዝብ ቢነግሩት ሊገባው የሚችል ነገር አይደለም።
ሙስሊም ወንድሞቻን ትርፍ ነገር አይደለም የጠየቁት። ወያኔ አስተዳድርበታሉ የሚለውን ሕገመንግስት እንዲያከብር ነው። ሕገመንግስቱን ካከበረ፤ ለህገመንግሰቱ ከተገዛ በኢትዮጵያ ምድር ሰላም ወረደ። ይህ የጋጠወጦች ቡድን ሕዝቡን ሰላም እየነሳ ያለው ራሱ ሕግን እየጣሰ፤ የፈለገውን ነገር እያደረገ መኖርን ስራ ስላደረገው ነው። ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አሁንም እየጠየቁ ያሉት “ሕገመንግስቱ ይከበር፤ ድምጻችን ይሰማ” ነው። “መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባ” ነው። “መሪዎቻችንን እኛው እንምረጥ፤ መንግስት አይደለም እነ እገሌ ናቸው የሚመሯችሁ የሚለን” ነው።
አዎ!.. ዘጠና ጊዜ ቢደጋገም ትርጉም የለውም። ሕገመንግስቱ “መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ አይገባም” ይላል። እርግጥ ነው አንደመንግስት ጣልቃ የሚገባበት ጊዜ አለ። ያ የሚሆነው በሀይማኖት ስም በሀገርና በህዝብ ደህንነት ላይ ወንጀል የሚፈጽም ሀይል መኖሩ ሲረጋገጥ ነው። ይህን አይነት ወንጀል ስልጣን ላይ ካሉት ሰዎች የበለጠ በኢትዮጵያ ውስጥ ያደረገ ህይማኖትም ዘርም; የለም፤.. የለም።
የኢትዮጵያን ህዝብ የምጠይቀው አንድ ነገር አለኝ። እነዚህ ሰዎች ከመጡ ጊዜ በሗላ እንዳየነው እስላምና ክርስቲያን ተጋጭቶ ቤት ተቃጠለ፤ ሰው ሞተ የሚባል ዜና ሰምታችሁ ታውቁ ነበር? ባለፈ አመትና ሁለት አመት በጅማ አካባቢና ወደደቡብ የተደረገ ነገር የኢትዮጵያዊ ሙስሊምና ክርስቲያን ተግባር የነበረ ድርጊት ነው ትላላችሁ? የወያኔ ስራና ፈጠራ አይደለም ብላችሁ የምታምኑ አላችሁ?.. አስረዱኝ።
አዎ!.. ህዝቡ ነጻነት ያስፈልገዋል። የሚፈልገውን የመምረጥ፤ የመሾም፤ የመሻር፤ ከየቤተ እምነቱ እስከላይ መንግስቱ፤ ዲሞክራሲ ያስፈልገናል። እኔ አውቅልሀለሁ የመባል የሩቅ አሮጌ ዘመን ያስተዳደር ስልት ይበቃናል። በኢትዮጵያ ምድር የመጨረሻዎቹን ድኩማን የትግራይ ፍልፈሎች ስናስወግድ ነገሩ የሚያልቅ ይመስለኛል።
እንደ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በቄስና በጳጳስ ልብስ፤ የትግሬና የአድርባይ ሆዳም መንጋ መልምሎ፤ ቤተክርስቲያኒቱንና፤ ሕዝበ ክርስቲያኑን እያመሰ፤ እንዳሽመደመደ፤ ሙስሊሙንም አሽመድምዶ ሊያስቀር፤የማያቋርጥ ጥረቱን አለማቆሙ የኢትዮጵያን ህዝብ መዳከም የሚያሳይ ትልቅ ምልክት ነው።
ይህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ ነው። ሙስሊም ወንድሞቻችን ወደ አላህ አለቀሱ እንጂ ጂሀድ አላወጁም። እየተገደሉ አልገደሉም። ለመግደልም አልተዘጋጁም።የኢትዮጵያ ህዝብ ሲገደል የመጀመሪያው አይደለም። ሸፈተ? ለመግደል ተነሳ? ሀያ ሁለት አመት። ለመላው አለም ታላቅ ትምህርት ነው። ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወንድሞቼ እንደወያኔና እንደ እኔ አይነት ደካማ አስተሳሰብ ያላቸው ዜጎች ቢሆኑ ኖሮ በወያኔ ላይ ጂሀዲ ከታወጀ ቆይቷል። ወያኔን መግደል ከተጀመረ ቆይቷል። ወያኔ መንግስት ነኝ ካለ በሗላ የኢትዮጵያን ህዝብ መግደል ሲጀምር እኛም ወያኔን መግደል ጀምረን ነበር።…ግና የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ እኔ አይነትም አይደል፤ እንደ እነሱ አይነትም አይደል፤ እየተገደለ ሰላምን ለማምጣት የሚጥር በአለም ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ህዝብ ነው።
እርግጥ አንባገነን መንግስታት ሁለመናቸው ውሸትነው። መዋሸትን የሚፈሩበት ምክንያት የላቸውም። ምክንያቱም ለሚያስተዳድሩት ህዝብ ስለዋሹ እናጣዋለን የሚሉት ጥቅም የለም። እናጣዋለን የሚሉት ስልጣን የለም። ሁሉም ነገር በጃቸው ነው። ዲሞክራሲ ባለበት ሀገር ከፍ ያለ ስልጣን ላይ ያለ ሰው (ፖለቲከኛ)፤ ውሸት ቢናገር ለብዙዎች ከፍተኛ ስልጣን ላይ ላሉ ከስራ መባረር ምክንያት ይሆናል። ለፓርቲውም የወደፊት ምርጫ እድል መበላሸት ምክንያት ይሆናል። ለራሱም ይከሰሳል። ጦሱ ብዙ ነው።
እንደ ወያኔ አይነት የሽፍታ ቡድን አገር የመግዛት እድል ባገኘበት ምድር ይህ የአደባባይ ውሸት የሚገርም ነገር አይደለም። ኮሎምቢያ ውስጥ ከባድ የወንጀለኞች ቡድን ህገወጥ ድርጅት አለ ። ጣሊያን ውስጥ ከባድ የወንጀለኞች ቡድን ማፊያ እስካሁን መንግስት መሆን አልቻለም። ኢትዮጵያ ውስጥ የወንጀለኞች ቡድን መንግስት መሆን ቻለ። ወያኔ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ስንቱን በደል ነው ተሸክሞ የሚኖረው?..ሳያጠፉ መታሰር፤..በፈጠራ ክስ ፍርድ ቤት መቅረብ፤..ሰውን እያሰቃዩ ያላደረገውን ያላለውን አደረኩ አልኩ ማስባል፤… ሌላ ቦታ ስለሌላ ጉዳይ የተናገረውን ቆርጠው ቀጣጥለው ለጣጥፈው ለክሳቸው የሚስማማ አረፍተነገር በመስራት ለህዝብ ማሰማት..የሀሰት ምስክሮችን መልምሎ አሰልጥኖ ማስመስከር፤ ሕሊናቸውን የሸጡ ዳኞችን በየፍርድቤቱ ኮልኩሎ ከላይ በሪሞት ኮንትሮል እንደ አሻንጉሊት እየተቆጣጠሩ የሚፈልጉትን ነገር ማስፈረድ፤መንግስት ነኝ የሚለውን የዘራፊዎች ቡድን ይቃወማል የተባለውን ዜጋ ሁሉ ረጅም እስራት፤ እድሜ ልክ፤ ሞት ማስፈረድ….እስከመቼ?..እስከመቼ?…እስከመቼ?..
ከቶውንም ወንድሞቻችን ሙስሊሙ ማሀበረሰብ የመረጣቸው መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ሲታሰሩም ያለምንም ምክንያት የውንብድና ስራ ሰለባ በመሆናቸው ብቻ ነበር።
ሀያ ሁለት አመት የኢትዮጵያን ህዝብ እየገደለ፤ እየዘረፈ፤ የሽብር ፐሮፓጋንዳ እየነዛ፤ ፈንጅ እያፈነዳ፤ እያሸበረ፤ የሚኖር የወሮበሎች ቡድን ኢትዮጵያዊውን ሙስሊም አሸባሪ ቢለው የኢትዮጵያ ህዝብ አይደለም በሌላውም ዓለም ያለ ህዝብ እንደሚሳለቅበት ምንም ጥርጥር የለውም። ምክንያቱም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ አሸባሪ ወያኔ ብቻ መሆኑን ዓለም ስለሚያውቅ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ ከሙስሊም ወንድሞቹ ጎን መቆም ይጠበቅበታል።እስላምና ክርስቲያኑ አብሮ ከቆመ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ማለት ይኸው ነው። ወያኔንም የሚያስፈራው የሙስሊሙና የክርስቲያኑ መደጋገፍና አንድ መሆን፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ መሆን ሰለሆነ የሁለቱ ታላላቅ ሀይማኖቶች አንድ መሆን ማለት ወያኔ ዘርን ከዘር እያባላ የመኖር ፊልሙ ተቃጠለ ማለት ነው። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ሁሉ ወይ ክርስቲያን ወይ እስላም ናቸው። ከሁለቱ ውጭ ያሉ እመነቶች በጣም ጥቂት ናቸው። ስለዚህ ክርስቲያን እስላም አንድሁን! ተባበር!
በመሰረቱ ሙስሊም ወንድሞቻን የጠየቁት የሀይማኖት ነጻነት መሰረታዊ መብት ነው። ትርፍ ነገር አይደለም። ሕገመንግስቱ ያሰፈረው ነገር ነው ( ህገ መንግስት በሀገሪቱ ገዢዎች ዘንድ ትርጉም አለው ባንልም) እኛ እንደ ህዝብ ትርጉም አንዲኖረው የጋጠወጦቹን ቡድን ማስተማር ይጠበቅብናል። እና ሙስሊም ወንድሞቻችን ያሉት “ህገመንግስቱ ይከበር! ድምጻችን ይሰማ” ነው። ወያኔ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያኒቱን እያመሰ ያለው ይህንኑ መሰረታዊ መብት በመንፈግ ነው።
አሁን ደሞ ይባስ ብሎ “እስላም ሊፈጅህ ነው;። ጂሀድ ሊያውጅብህ ነው። የእስላም መንግስት ሊያቆምብህ ነው።” እያለ የውሸት ሽብር በህብ ላይ ይነዛል። በራሱ በህዝቡ ግብር በሚተዳደር ራዲዮና ቴሌቪዥን። ይህን የሚያደርገው መንግስት ጋዜጠኞችን “ዋሻችሁ ህዝብና መንግስትን የሚያጣላ አንዲት አረፍተ ነገር ጻፋችሁ” ብሎ አመት ሁለት አመት የሚያር መንግስት ነው።
በስደት ያለው ሲኖዶች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አባቶች የኢትዮጵያን ሙስሊም ክርስቲያን ህዝብ ያስደሰተ፤ መግለጫና መልክት አስተላልፎ ነበር። በሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ ወያኔ እያደረሰ ያለውን በደል እንዲያቆም የሚያወግዝ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ ወንድማማችነት ታላቅ ግብአት ነው። ለወያኔ ታላቅ ፍርሀትና ጭንቅ ነው።ለዚህም ነው ይህ የሌቦች ቡድን ያለ የሌለ ውሸት እየፈጠረና እየደራረተ ሙስሊሙንና ክርስቲኑን ለማበጣበጥ ያለመታከት እየሰራ ያለው።
ኢትዮጵያዊው ክርስቲያን ሆይ! እስቲ ያንተም ጥያቁ መንግስት በሀይማኖታችን ጣልቃ አይግባ ይሁን! የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ባስቸኳያ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ በል፡ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ በል፡ የታሰሩ ጋዜጠኞች ይፈቱ በል። የኢትዮጵያን ህዝብ ወያኔ ካሰናዳለት ጥፋት የሚያድነው አንድ መሆን ብቻ ነው።መደጋገፍ ብቻ ነው።
በሰላማዊ ትግል ለውጥ ይመጣል ብለህ የምታምን ሙስሊም ወንድሞቻችንን ተከተል። ወያኔ አፍ የፈታበትንንና እስከ አሁን የሚናገረውን የጡንቻ ቋንቋ የተረዳህ ካለህ፤ በሚገባው ቋንቋ ሊያናግሩት የቆረጡ ጀግኖቻችንን ተቀላቀል። ሀያሁለት አመት ለተስፋና ለትግስት ከበቂ በላይ ነው። ከንግዲህ በሗላ ያለው ዝምታ የፍርሀት ነው። ለወያኔ ደግሞ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሰንሰለቱን የበለጠ የሚያጠብቅበትና መሬቱን ሸጠው ሲጨርሱ እንደባሪያ ህዝቡን በሰንሰለት አስረው መሸጥ የሚጀምሩበት ጊዜ ነው። በጉዲፈቻና በግርድና ስም ልጆቻችንንና እህቶቻችንን መሸጡ በቂ አልሆነም።
ሙስሊሙ አርብ ቤተ መስጊድ ተሰብስቦ ከጁምአ መልስ የሚያደርገውን “አላሁአክበር፤” ለእግዚአብሄር አቤቱታ፤ ክርስቲያኑም እሁድ እሁድ በየቤተክርስቲያኑ ከጸሎት መልስ ላምላኩ “እግዚኦ” በማለት ተመሳሳይ ተማጽኖ ማድረግ አለበት። የሙስሊም ወንድሞቻችን እንባ ወያኔን እሳት ሆኖ ይፈጀዋል። የክርስቲያኑም ይጨመርበት ይብሱን በቁም ይቀቅለዋል። ወጣቶች ይህን ሚና መጫወት ህብረተቡን እየቀደሙ መምራት ይጠበቅባቸዋል።
ዛሬ በኢትዮጵየያ ያለው የተማረ ወጣት ትውልድ ከሀምሳ እጅ በላይ ስራ አጥ ነው። በከንቱ የሚንገዋለል ነው። ከፊቱ ድቅድቅ ጨለማ ተጋርዷል። የሚያየው የሚጨብጠው ተስፋ የለውም። በአረቄ፤ በጫትና በሀሺሽ እየደነዘዘ ሲቃዥ ከሚኖር ለምን አንድ ሆኖ አይነሳሳምና ሕዝቡን ለለውጥ አያነሳሳም? ሀገሪቱ ከአንድጎሳ በተውጣጡ ጥቂት ጋጠወጦች መዳፍ ውስጥ ወድቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሰንሰለቱን እያጠበቁ ወያኔ ወጣቶቻችንን ባሪያ አድርጎ ሊሸጣቸው ሊለውጣቸው ሲዘጋጅ አፍጦ የሚያስተውለው ወጣት የተሻለ ቀን እንደመና ከሰማይ ይወርዳል ብሎ እየጠበቀ ይሆን?
ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!
አላሁአክባር!!
No comments:
Post a Comment