Monday, January 19, 2015

ወከባ እና እስር በህገመንግስቱ እውቅና ይሰጣቸው:: በወከባ እና በእስር ሽብርን በደሃ ህዝብ ላይ መፍጠር ከተጠያቂነት አያድንም::

Minilik Salsawi ምንሊክ ሳልሳዊ)

ይህ የተገፋ ህዝብ እንዳጎነበሰ አይኖርም ቀና ያለ እለት …!!! ወህኒ የጀግና እንጂ የወያኔ እብሪተኞች ቤት አይደለም!!
ባለስልጣናት የጸረ አሸባሪነት ህግን ለማስፈጸምም ይሁን ለመተግበር ሞራላቸው ምን ድረስ እንደሆነ ሊመልሱልን ይገባል:: ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያልተመዘገቡ ሀገወጥ እና አሸባሪ ከሆኑ የተወነጀሉበት ተቀባይነት ያለው ክራይቴሪያ ይነገረን እና እናውግዘው:: አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄያቸው ግልጽ እና ግልጽ ነው ካልሆነ የሚዋከቡበት ምክንያት የለም ካለ ይነገረን እና እናውግዝ ተደጋጋሚ ጸሎት አንፈልግም መንግስታዊ አሸባሪነትን እያወገዝን ወያኔን በትእግስት እየጠበቅናት ነው ይህ ያበጠ ነገር የፈነዳ እለት ወዮላቹ…የምትገቡበት አታገኙም:: እንደ ደርግ ባለስልጣናት ወህኒ አንወሽቃችሁም:: ወህኒ እኮ የጀግና እንጂ የወያኔ እብሪተኞች ቤት አይደለም::


መፈክር እና ባንድራ ይዞ የወጣን የህዝብ ጥያቄ ያነገቡ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትን እና ደጋፊዎችን ማዋከብ እንዲሁም ባዶ እጁን ሙስላያ ይዞ ወደ መስኪድ የሚተመስን ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ማዋከብ እና ማሰር ማፈስ ከሽብር ተለይቶ አይታይም:: ይህ የሕወሓት ደባ የያዘችውን ወታደር እና መሳሪያ ተማምና መንግስታዊ ሽብር በዜጎች ላይ ፈጥራለች:: ይህንን መንግስታዊ ሽብር እያንዳንዳችን ልናወግዘው ይገባል::

ለይስሙላ በወረቀት የታተመው የሃገሪቱ የበላይ ህግ ተብየው ህገ መንግስት በየት ቦታ በየትኛው አገር በየትኛው ቀን እና ሰአት በእነማ እየተተረጎመ እንደሆን ግልጽ ሊሆንልን አልቻለም እንደዜጋ የሃገራችን ጉዳይ ያገባናል ብለን እስከተነሳን ድረስ አቤቱታችን ሊታይ ይገባዋል:: አሸባሪ የሆኑ ባለስልጣናት የጸረ አሸባሪነት ህግን ለማስፈጸምም ይሁን ለመተግበር ሞራላቸው ምን ድረስ እንደሆነ ሊመልሱልን ይገባል::

ህገመንግስታዊ መብቶችን የተጠቀሙ ግለሰቦች ካለምንም የፍርድ ቤት ትእዛዝ ወደ እስር ቤት መወርወር የት ነን ያለነው ወዴትስ እያመራን ነው የሚል ጥያቄዎች ደጋግመን እንድናነሳ አስገድዶናል:: ችግር ካለ ይነገረን እና አስፈላጊውን እርምጃ መንግስት ቢወስድ እንስማማለን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ወረቀት ይዘው ነው ለነጻነት የዘመቱት ይህም የሚያሳድድ የሚያዋክብ ከሆነ በህገመንግስቱ ውስጥ ይካተት እና የነጻነት ጥያቄው ይቆማል:: ወገናችን ቀላል እና ሊመለስ የሚችል ጥያቄዎችን ይዞ ነው የተነሳው ይህም የሚያስገድል የሚያዋክብ የሚያሳስር ከሆነ የዜጎች መብት በህግ አግባብ ይገደብ እና ነጻነት ፈላጊው ህዝብ ዜግነት አልባ ሆኖ ይሰደድ:: ወከባ እና እስር በህገመንግስቱ እውቅና ይሰጣቸው ይህ ካልሆነ ወያኔ ህጎችን ይሰርዝልን::

የህዝቦች ጥያቄ ማለት ለወያኔ ምን እንደሆነ እንዴት እንደሚተረጎም አልተረዳንም ስልጣንን ለማራዘም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና የባለስልጣናት እርስ በእርስ አለመነባበብ የሚያስከትሉት ግድፈቶች በሃገር እና በህዝብ ላይ ከፍተጫ ጥፋት ያስከትላሉ:: በወከባ እና በእስር ሽብርን በደሃ ህዝብ ላይ መፍጠር ከተጠያቂነት አያድንም:: የማይነጋ መስሏት…….እንዳይሆን ነገን ለሃገር እና ለህዝብ እናስብ…ድንጋይ እየቆለሉ ይኸው ፎቅ ሰራንልህ.. በብድር እየተከናነቡ መንገድ አሰራንልህ …. ወዘተ ቢባል ይህ ህዝብ ቅድሚያ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ነጻነት ይፈልጋል እና በጥሞና እና በአትኩሮት ሊታይለት ይገባል::

No comments:

Post a Comment