Thursday, July 31, 2014

41 አለማቀፍ ድርጅቶች የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ጠየቁ

የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ ይሻሻል ብለዋል

ከዚህ በፊት በሽብርተኝነት የተፈረደባቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል
41 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የፕሬስ ነጻነት አቀንቃኞች፣ አለማቀፍና ክልላዊ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማትና የሙያ ማህበራት መንግስት በቅርቡ የሽብርተኝነት ክስ የመሰረተባቸውን ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከትናንት በስቲያ በላኩት ደብዳቤ መጠየቃቸውን ብሉምበርግ ኒውስ ዘገበ፡፡

ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ አርቲክል 19 ምስራቅ አፍሪካ፣ ሲቪል ራይትስ ዲፌንደርስ፣ ወርልድ አሊያንስ ፎር ሲቲዝን ፓርቲሲፔሽን፣ ፔን አሜሪካና የመሳሰሉት አለማቀፍ ድርጅቶች በጋራ በጻፉት ደብዳቤ፣ መንግስት ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን በሽብርተኝነት እየከሰሰ ለእስር መዳረጉን መቀጠሉ ያሳስበናል፣ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተገቢነት የሌለው በመሆኑ መገታት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

ሶስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማርያን ሶስት ወራት ለሚሆን ጊዜ ይህ ነው የሚባል ክስ ሳይመሰረትባቸው ያለአግባብ በእስር ላይ መቆየታቸውንና አንዳንዶቹም በምርመራ ወቅት እንግልት እንደደረሰባቸው መናገራቸውን የጠቀሰው ደብዳቤው፣ ይህም አግባብ አለመሆኑን ገልጿል፡፡

Wednesday, July 30, 2014

የግል ሚዲያው “በፀረ ሽብር ህግ” ሊበላ ይሆን?

 [ኣቶ ግርማ ሠይፉ ማሩ]

የመንግሰትን ቀጣይ እርምጃ የሚያሳዩ ተከታታይነት ያላቸው በግል ሚዲያዎች ላይ የሚደረጉ ዘመቻው ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መልክቶች እየታዩ ነው፡፡ በቀጣይ ለሚቀርበው ዶክመንተሪ ተጋባዥ አንግዳ ሆኜ ለቆርጦ ቀጥሉ ኢቲቪ ቃለ ምልልስ እንደሰጣቸው ጥያቄዎቹ ደረስውኝ ተመልክቸዋለሁ፡፡ 

የጥያቄዎቹን ዝርዝር እንተወው እና ዓላማው ግን ባለፈው ከቀረበው ዘጋቢ ፊልም የተለየ ነገር የለውም፡፡ በነገራችን ላይ ባለፈው የቀረበውም ዘጋቢ ፊልም ላይ እንድሳተፍ ተጠይቄ እንደማይሆን ገልጨላቸው ነበር፡፡ ውሳኔዬ ትክክል መሆኑን ዘጋቢ ፊልሙን ካየሁ በኋላ ገብቶኛል፡፡ የዘጋቢ ፊልሞቹ ዋና ግብ “የኢህአዴግን አብዮታዊ ዲሞክራሲን መንገድ አምነው ያልገበሩ የግል የሚዲያ ተቋማትን ለማጥፋት ጥርጊያ መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡”
የግል ሚዲያውን ማጥፊያ መንገዶች ሁሉን አቀፍ ናቸው፡፡ በዋነኝነት ኤኮኖሚያዊ የሚባለው ሲሆን ይህም በምንም ሁኔታ ከመንግስት ወይም “ከልማታዊ ባለሀብቶች” ገንዘብ እንዳያገኙ ማድረግ ሲሆን ከአንባቢ የሚሰበሰቡትንም ገንዝብ ለእዕትመቱ ቀጣይነት እንዳይመች የሚቻለውን ቀዳዳ ሁሉ መዝጋት፤ ይህ የማይሳካ ቢሆን በአሰተዳደራዊ ዘርፍ እንዲወሰድ የተቀመጠው ፍርድ ቤትን በመጠቀም ጋዜጠኞችን ማስር ነው፡፡

የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ (አስቂኙ ክስና አስቂኙ ማስረጃ)

አገራችን ኢትዮጵያ በጥሩ ልትጠራባቸው የምትችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው በድህነት በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በሙስና እና ሃሳብን ነጻነት በመግለጽ መብት የተለመዱ የምናፍርባቸው ጉዳዩች ሆነውመቀጠላቸው እሙን ነው፡፡ ሃሰብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ ሶስት ወራትን ከፈጀ ምርመራ በኋላ በብዙ የፓሊስ ድብብቆሽሂደት የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ባለፈው አርብ ክስ መመስረቱም አብሮ ይታወሳል:

ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባትየምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰትእድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁንግን ክሱ አንድ የዞን 9 ጦማሪን ጨምሮ በይፋ በመመስቱ እነዲሁም በክሱ ላይ ተጠቀሱት ክሶች አንዳቸውም እውነት ባለመሆናቸውክሱን አስመልክቶ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ መስጠት እነዳለብን ተሰምቶናል፡፡

Tuesday, July 29, 2014

ስበር ዜና ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ህክምና ላይ የሚገኙት የአቶ በረከት ስሞኦን የጤነት ሁኔታ እያነጋገር ነው።


እሁድ ከአዲስ አበባ አንድ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ዶ/ር አስከትለው በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን እኩለለሊት ጅዳ ስውዲ አረቢያ ለህክምና በሚስጠር እደገቡ የሚነገርላቸው አቶ በረከት ስሞኦን በተለምዶ ብግሻን እይተባለ የሚጠራ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልቡ ደም ቧንቧ ለማስፋት የተደረገላቸው መሆኑን ከሳውዲ አየር መንገድ ምንጮቻችን ለማረጋገጥ ተችሏል ። የመንግስት ባለስልጣኑ ጤንነት በአሁኑ ሰዓት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሚገልጹት እንዚህ ምንጮች ዛሬ ጠዋት ከመካ የዒድ አል ፈጠር የፀሎት ስረአት ባሃላ ሼክ አላሙዲን በስልክ እንዳነጋገሯቸው ይናገራሉ። አቶ በረከት ስመኦን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ በድብቅ መምጣታቸውን የሚናገሩ እንዚህ የሳውዲ የአየር መገድ ምሲጥራዊ መረጃዎች ባለስልጣኑ በአሁኑ ሰዓት ጅዳ ሆስፒታል መተኛታቸው በተለያዩ የዜና ማስራጫዎች በመዛመቱ ህክምናቸውን በተረጋጋ ሁኔታ ሳይጨርሱ ወደ ሃገር ሊመለሱ እንድሚቸል ገልጸዋል።

Monday, July 28, 2014

በስቃይ ላይ ተመርኩዘው የሚወጡ ቃላቶች የአንዳርጋቸው እንዳልሆኑ መናገር ይቻላል።

አባይ ሚዲያ፡ እንደተለመደው ሁሉ ወያኔዎች የኢትዮጵያ ህዝብ እንደማያምናቸው በተረዱ ጊዜ በርካታ ዘዴዎችን እየፈጠሩ ማሀበረሰቡን እያዋረዱ ረግጠው ለመግዛት ያላቸውን ሃይል ሁሉ ተጠቅመው ለማሳመን ጥረት ማድረጋቸውን እያየን ነው። ይህም አንዳርጋቸው እኔ ደህና ነኝ በል ተብሎ ያለው እና “እንደምታዩት ነው” ያለው ትልቅ መልእክት አለው።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለሁለተኛ ጊዜ አወራ ያሉት ነገር ግን በየ 50 ሴኮንድና አንድ ደቂቃ ልዩነት በሆነ እየተቆራረጠ ኢዲት ተድርጎ መጀመሪያ አካበቢ የተቀረጸውን ምስል እንዲሁም የህዝቡን ቁጣ ለማብረድ የተጨመረበት መጨረሻው ደቂቃ ላይ ሌላ ልብስ ለብሶ የታየበት ምስል የወያኔን ጭንቀት የሚያጎላ እንጂ ከቶ የአቶ አንዳርጋቸው አንደበቶች  ሳይሆኑ መትረጌስና ሽጉጥ እንዲሁም ገዳይ ጅቦች ተደርድረው በማሰቃያ ቤት የተቀዳ ድምጽ እንጂ እንደሚሉት በፌድራል ምርመራ ጣቢያ አይደለም።

ሕወሓት አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ ራሷን በራሷ ያጋለጠችባቸው 4 ቅጥፈቶች

ስንታየሁ ከሚኒሶታ

እንደተጠበቀው በሕወሓት መንግስት በሚመራው የኢትዮጵያ ፖሊስ ፕሮግራም ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲቀርቡ ተደርጓል። የአቶ አንዳርጋቸው በቲቪ መቅረብ ከዚህ ቀደም በአንዷለም አራጌ፣ በብርቱካን ሚደቅሳ፣ በደበበ እሸቱ፣ በአቡበከር አህመድ ላይ የተለመደ በመሆኑ ብዙም አስገራሚ አልሆነም። ሆኖም ግን ቪድዮውን ልብ ብሎ ለተመለከተው ወያኔ እንዳሰበው ትርፍ ሳይሆን የበለጠ ኪሳራ እንዳገኘበት ለመረዳት ችያለሁ። ለዚህም ነው ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ የረሳቻቸው 4 ቅጥፈቶች ስል ለዚህ አስተያየቴ ር ዕስ የሰጠሁት።

ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በቲቪ ስታቀርብ ራሷን በራሷ ያጋለጠችባቸው 4 ቅጥፈቶች

1ኛ. ቪድዮው በጣም ኤዲት እንደተደረገ ያስታውቃል

ሕወሓት ያዘጋጀው የቪድዮ ካሜራ ማንና አቀናባሪው ደንጋጣ እንደሆነ ቪድዮው ያስታውቅበታል። በጣም ተቆራርጦ መቀጣጠሉ ከማስታወቁም በላይ ቢያንስ ከዚህ የተሻለ ኤዲቲንግ ሥራ መሥራት ይችል የነበረ ቢሆንም ይህን ባለማድረጉ ለፕሮፓጋንዳ ሥራ የተዘጋጀውን ቪድዮ ኪሳራ ላይ ጥሎታል። ቪድዮ አቀናባሪው ሆን ብሎ ሕዝብ መቆራረጡን እንዲያውቅ ያደረገ ከሆነ ልናደንቀው የሚገባ ሲሆን፤ ሆኖም ግን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ከሆነ ይህ ቪድዮ ቅንብሩ አይመጥንም።

ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ

 (ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም) 

ለእኔ ፖሊቲካና የግለሰብ ጠባይ እንደውሃና ዘይት የማይደባለቁ ነገሮች ይመስሉኛል፤ አጼ ምኒልክ ‹‹አመልህን በጉያህ›› ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፤ ዘይትና ውሀ በባሕርያቸው የሚለዩትን ያህል ፖሊቲካና ግለሰብም የባሕርይ ልዩነት አላቸው ማለት ነው፤ የወያኔ መሪዎች ምንም ነገር የማይሰምርላቸው፣ ከመጀመሪያውኑ እነዚህን ሁለት የማይደባለቁ ባሕርዮች አደባልቀው በመንሣታቸው ነው፤ ፖሊቲካ ለማኅበረሰቡ መቆርቆር ነው፤ ለሕዝቡ መቆርቆር ነው፤ ለአገር መቆርቆር ነው፤ የፖሊቲካ መነሻም ይኸው መሆን አለበት፤ ዓላማውም የማኅበረሰቡ፣ የሕዝቡ ልማት እንጂ ጥፋት አይደለም፤ የነበረውንና ያለውን ማጥፋት የፖሊቲካ ዓላማ ሊሆን አይችልም።

የደርግ መንደር ምሥረታ የሕዝብ ዓላማ ነበረው፤ የዓላማው መሣሪያ ግን የሕዝብ ሳይሆን ወታደራዊ ጉልበት ነበር፤ በዚህም ምክንያት የሕዝብ ዓላማ ያለው ሥራ የሕዝብን ህልውና በሚፈታተን የጉልበት መንገድ መከተሉ ዓላማው እንዳይሳካ፣ ሕዝብና አገዛዙ ባላንጣዎች ሆኑ፤ ጥሩው ዓላማ በከሸፈ ጉልበተኛነት ሳይሳካ ቀረ፤ በመንደር ምሥረታው ዓላማ ደርግ ክፋት ወይም ቂም ቋጥሮ አልተነሣም፤ ስሕተቱ ከውትድርና ባሕርይ የመጣ ይመስለኛል፤

ማጥፋት ዓላማ ሲሆንና ጉልበት የማጥፋት መሣሪያ ሲሆን ፍጹም የተለየ ነው፤ማጥፋት የሚመጣው ከግል ጠብና
ከግል ቂም ነው፤ የራሱን ወይም የአባቱን፣ ወይም የእናቱን ቂም በልቡ ቋጥሮ ፖሊቲካ ውስጥ የሚገባ ሰው
ለጥፋት የተዘጋጀ ነው፤ ለጥፋት የተዘጋጀ ሰው ፖሊቲካ ውስጥ ሲገባ እሳት አደጋ መኪና ላይ ቆሞ ቤት
እንደሚያቃጥል ሰው ነው፤ አታላይ ነው፤ ዓላማውንም የዓላማውንም መሣሪያ አያውቅም፤ የሚንቀሳቀሰው
በጥላቻና በቂም ነው፤ ወይ የሕጻን ልጅ ወይም የተስፋ­ቢስ ደደብ ጠባይ ነው፤ እንዲህ ያለ ሰው ፖሊቲካ ውስጥ
የሚገባውም በዚሁ በደደብነቱ ምክንያት ነው፤ የደደቡ ፖሊቲከኛ ሥራ የማያስወቅሰው ፖሊቲከኛውን ብቻ
አይደለም፤ በዚያ ፖሊቲከኛ የሚመራው ሰው ሁሉ አብሮ የሚወቀስ ነው፤ እንዲያውም በፖሊቲከኛው እውቀትና
ችሎታ ማጣት የተነሣ የሚደርሰው ስቃዩና መከራው፣ ችግሩና አበሳው በዚህ ዓይነቱ ፖሊቲከኛ ላይ አይደርስም፤
ሰቃዩንና መከራውን፣ ችጋሩንና አበሳውን የሚጋፈጠው በዚህ ዓይነቱ ፖሊቲከኛ የሚመራው ሕዝብ ነው፤ ሕዝብ መሪውን በትክክል መምረጥ ያለበትም ለዚህ ነው፤ ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ የሚባለው ይደርሳል።