በህዝብ ላይ የሚደርሰው ጭቆናና እርዛት እስከመቼ?
ከኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ የተሠጠ መግለጫ
የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ዘወትር ስልጣናቸውን ለማራዘም ካላቸው ነቢራዊ ፍላጎት የተነሳ በህዝብ ላይ ግድያ እና እስር ከመፈፀም አልፈው ሐገራችን ኢትዮጵያን ከማትወጣበት ማጥ ውስጥ ለመክተት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ በቅርቡ እንኳን በአሶሳ ከተማ ንፁሀን የትግራይ ወጣቶች ማንነታቸው እስካሁን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል ይኸውም መንግስትእየተከተለው ብልሹ የዘውግ አስተዳደር ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ እየታየ ነው በሌላ በኩል ይህ ግድያ መንግስት እራሱ የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሠለፍ በማሠብ እንደገደላቸው ግምታቸውን አስቀምጠዋል እንደምክንያት የጠቀሱት ምርጫ 97ን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ መንግስት ተቃውሞውን ለማባባስ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከቀድሞዋ የትምህርት ሚኒስቴር ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ግቢ ወደውጭ ቦንብ በመወርወር 6 ፖሊሶችን በመግደል ፖሊሶችን ለማነሳሳት እና ህዝቡን ለማሳሳት ቢሞክርም በመጨረሻ ጉዳዩን የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋ ሲያወጣው የመንግስት ሴራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአሶሳው፣ የአምቦው፣ የጎንደሩ እና የወለጋው ግድያም ከዚህ የተለየ አይሆንም፡፡