Wednesday, June 25, 2014

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትን የደፈጠጡ አገር አልባ ናቸው!

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ወንጀል ፍፃሜ መሪ ተዋንያን ሆነው ከቆዩ በኋላበመሰደድ በአሜሪካ እራሳቸውን ደብቀው በተቀመጡ የሰብአዊ መብትደፍጣጮች ላይ የዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የፍትህ መምሪያ ጥቆማእንዲቀርብለት ኢትዮጵያውያንን/ትን በማበረታታት ላይ ይገኛል፡፡
እነዚህ በሰው ልጆች ላይ ወንጀልን የፈጸሙ ጨካኞች በሰው አገር ሄደው ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ ወንጀለኞች በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ በበማታለል  ገብተው ለ30 ዓመታት ተደብቀዋል፡፡ እነዚህ በሰው ደም የተዘፈቁ ወንጀለኞች በቀላሉ ሊያዙ በሚችሉበት አገር በመሄድ ለድፍን ሶስት ዓመታት የተደበቁም አሉ ፡፡
እነዚህ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ ወንጀለኞች ከኒዮርክ እስከ ሎስአንጀለስ ባሉ ታላላቅ ከተሞች እራሳቸውን ደብቀው ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የፉኝት ዘሮች ማንም አይነካንም በሚል የእብሪት ስሜት ህዝብ በሚሰበሰብባቸው የአደባባይ ቦታዎች እና በእምነት ተቋማት ሳይቀር ደረታቸውን ገልብጠው ይንፈላሰሳሉ፡፡ በየቡና ቤቶች እና ምግብ ቤቶች ሲወጡ ሲገቡ ይውላሉ፡፡ በጎዳናና በመንደር መንገድ ላይ ይንፏቀቃሉ፡፡ የተማሩም አሉባቸው ያልተማሩም አሉባቸው፡፡ በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ጊዚያት የዘረፏቸውን ገንዘቦች በውጭ ባንኮች አጭቀዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የንግድ ተቋማትን በማንቀሳቀስ ንብረት አፍርተዋል፡፡ ሌሎቹም  ኑሯቸውን ለመምራት እና ዓላማዎቻቸውን ለማሳካት የአገልግሎት ሰራተኞች ሆነው ህይወትን በችግር መግፋት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከንጹሀን የግፍ ሰለባዎች ጋር የሞት ዋስትና ተፈራርመዋል፡፡ ንጹሀን ዜጎችን ጨፍጭፈዋል፣ አስጨፍጭፈዋል፣ ረሽነዋል፣ አስረሽነዋል፣ ገድለዋል፣ አስገድለዋል፣ ፈጅተዋል፣ አስፈጅተዋል፡፡

Tuesday, June 24, 2014

ከሕገ-መንግሥቱ በፊት


ትናንት ሰኔ 14 ቀን 2006 ዓ.ም ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ያገባኛል ባይነት እና ጋዜጠኝነት በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ›› በሚል ርዕስ እኔን ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ እና ዳዊት ሰለሞንን የውይይት መነሻ እንድናቀርብ በጋበዘን መሰረት በእኔ በኩል ለውይይት መነሻ ሀሰብ ይሆናሉ ብዬ ያቀረብኋቸውን ሶስት ነጥቦች እንዲህ አቅርቤያዋለሁ፡፡

በመጀመሪያ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ጉዳይ ‹‹ያገባኛል ባይነት እና ጋዜጠኝነት በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ›› በሚል ርዕሥ የውይይት መነሻ ሀሳብ ከሙያ አጋሮ ቼ ጋር እንዳቀርብ ስለጋበዘኝ በቅድሚያ ማመስገን እፈልጋለሁ፡፡




የሕገ­መንግሥቱ አንቀጽ 29

ነሐሴ 15 ቀን 1987 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ­መንግሥት ሲጸድቅ የፈረሙበት የወቅቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ነበሩ፡፡ ይህ ሕገ­መንግሥት በአንቀጽ 29 (1) እና (2) ላይ ሃሳብን በነጻነት የመገለጽ መብትን በተመለከተ እንዲህ ይላል፡­
‹‹ማናኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት መያዝ ይችላል፡፡ ፣ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፡፡ ይህ ነጻነት በአገር ውስጥም ሆነ ውጪ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ­ጥበብ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ በማንኛውም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል፡፡››
ባለፈው ዓመት መጨረሻ ላይ ከጓደኛዬ አቤል ዓለማየሁ ጋር ‹‹ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?›› በሚል ርዕስ ለንባብ ባበቃነው መጽሐፍ ውስጥ ይህን ሕገ­ መንግሥት አስመልክቶ ዶ/ር ነጋሶን ቃለ መጠይቅ በማድረግ አነጋግረናቸው ነበር፡፡ ከላይ በመግቢያዬ የጠቀስኩት አንቀጽ 29 መከበር አለመከበሩ ከጥያቄዎቼ መካከል አንዱ ነበር፡፡ ዶ/ር ነጋሶም እሳቸው በምላሻቸው እንዲህ አሉ፡­

Sunday, June 22, 2014

አንድነት ፓርቲ በአዋሳ ሊያደርገው የነበረው ሰልፍ አመራሮችንና አባላትን በማሰር ከተማዋን በፀጥታ ኃይሎች በመውረር ተደናቀፈ

በዛሬው ዕለት በአዋሳ ከተማ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) በሀዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የፓርቲው አባላት ከሐሙስ ዕለት ጀምሮ እስከ ትላንት ድረስ ከ30 በላይ በፖሊስ የታሰሩ ሲሆን የሲአን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለገሰ ላንቃሞ ለምን ይታሰራሉ ብለው በመጠየቃቸው እሳቸውንም አስረው ከምሽቱ 3፡30 ለቀዋቸዋል፡፡ በቅስቀሳው ወቅት ወረቀቶች የተበተኑ በመሆኑ ህዝብ በነቂስ ሊወጣ እንደሚችል ስጋት ያደረባቸው የደህዴን ካድሬዎች ትላንት ማታ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ተጨማሪ 7 የአንድነት የሀዋሳ አመራሮችና አባሎች በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡ የደቡብ ክልል የደህዴን ካድሬዎች ከተለቀቁ ነገ ሰልፉን ከማድረግ ወደኋላ አይሉም በሚል ለሁለት ተከፍለው ሲሟገቱ ማምሸታቸውንና አቶ መንድሙ ወታንጎ የተባሉት የደህንነት ኃላፊ መፈታት የለባቸውም መፍታት እንኳን ካለብን የሰልፉ ሰዓት ካለፈ በኋላ ነው በማለታቸው በእስር ቤት እንዲያድሩ መወሰኑና በዛሬውም ዕለት የሀዋሳ ከተማ በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጥበቃ ሥር መሆኗን የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገልፀዋል፡፡
ሳም ቮድ ሶን's photo.
ሳም ቮድ ሶን's photo.

በሺህ የሚቆጠሩ አማሮች አማራ በመሆናቸው ብቻ ተመርጠው ከምዕራብ ወለጋ ከጊምቢ እና ቄሌም (እንፍሌ ወረዳ አሽ ቀበሌ) ተፈናቀሉ


ጉዳያችን

 14/2006 ዓም (ጁን 22/2014)

በብዙ ሺህ የሚቆጠር የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያውያን ከምዕራብ ወለጋ ጊምቢ እና ቄሌም በኃይል አካባቢውን እንዲለቁ ከመደረጉ በላይ ድብደባ እና ግድያ እንደተፈፀመባቸው ቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ሰኔ 12/2006 ዓም ምሽት ባስተላለፈው ዘገባ ገለፀ።
ዘገባው የተፈናቃዮችን ምስክርነት እንዳስደመጠው ድብደባው እና ግድያው በከተማው ሕዝብ እና ፖሊስ የታገዘ መሆኑን እና ህይወታቸውን ያተረፉት በኮርኒስ እና ጫካ በመደበቅ መሆኑን ሲገልጡ፣አንድ ምስክርነታቸውን ለቪኦኤ የሰጡ ተፈናቃይ አክለው እንደገለፁት ከጊምቢ ከተማ ብቻ ከሶስት ሺህ በላይ የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያውያን መፈናቀላቸውን ተናግረዋል።ሌላው ምስክርነት ሰጪ ደግሞ ቁጥሩን ከስምንት ሺህ ሕዝብ በላይ አድርሶታል።

አምስት ልጆች የነበራቸው መሆናቸውን የተናገሩት ሌላ ተፈናቃይ የነበራቸው መደብር መዘረፉን እና ካለምንም ሀብት መቅረታቸውን፣ጉዳዩን አቤት ለማለት ወደ ባለስልጣናት ቢሄዱም ሰሚ ማጣታቸውን አስታውቀዋል።
የቪኦኤ ጋዜጠኛ ጉዳዩን አስመልክቶ ቀደም ብሎ የአካባቢው የፀጥታ ጉዳይ ኃላፊ የተባሉ እሳቸው ግን የኦሕዴድ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ነኝ ያሉ አቶ አወቀ የተባሉ የክልሉ ባለሥልጣን ስለጉዳዩ ሲናገሩ ”ያባረረ የለም’ ሲሉ ተደምጠዋል።

የኦሮምያ ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳይ ኃላፊ ወ/ሮ ራቢያ ኢሳ ”ሰዎቹ የሄዱት ፈርተው ነው” ካሉ በኃላ ”ቁጥራቸው ”መቶ አይሞሉም ማለታቸው ግርምትን ፈጥሯል።የቪኦኤ ጋዜጠኛ አቶ ሰለሞን በመቀጠል ቁጥሩ አይደለም ወሳኙ አንድም ሰው ቢሆን ለምን ተፈናቀለ? ደግሞስ ምን ያስፈራቸዋል? ያብራሩልኝ ብሎ ለጠየቃቸው ወ/ሮ ራቢያ አጥጋቢ መልስ ለመስጠት ሳይችሉ ቀርተዋል።
የኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሕዝቡን በአካል መለብለብ ከጀመረ ሰነበተ።ሺዎች የእዚህኛው ሌሎች የእዚያኛው ብሄር ተወላጅ ናችሁ እየተባሉ ተፈናቅለዋል።በተለይ ከአማራው ህዝብ ተወላጅ የሆኑ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከጉርዳፈርዳ፣ከበንሻጉል፣ከኢልባቦር እና ከወለጋ አሰቃቂ ግድያ እና ድብደባ እየተፈፀመባቸው ለዘመናት ያፈሩትን ንብረት እየተነጠቁ መባረራቸውን ያመለከቱ ዘገባዎች ሲወጡ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

Saturday, June 21, 2014

ድርብ አኃዝ ዕድገት ወይስ ድርብ ድህነት?


poor1


በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የዓለምአቀፍ ልማት ትምህርት ክፍል ሥር የኢኮኖሚ ጥናት የሚያካሂደው የኦክስፎርድ የድህነትና የሰብዕ ልማት ማዕከል (The Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHI)) ሰሞኑን ባወጣው የ2014 የጥናት መረጃ ደሃ ከሚባሉት አገራት ዝርዝር ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ሁለተኛ መሆኗን ገለጸ፡፡ የጥናቱ ዘገባ ኢህአዴግ በየጊዜው ከሚያቀርበው የዕድገት ስሌት ጋር በግልጽ የሚጋጭ መሆኑ ተነገረ፡፡
በዓለማችን በሚገኙ 108 በማደግ ላይ ባሉ አገራት በየጊዜው ጥናት የሚያካሂደው ማዕከል ጥናቱን በሚያካሂድበት ጊዜ 10 መለኪያዎችን እንደ ግብዓት እንደሚጠቀም ይናገራል፡፡ እነዚህም በሦስት ዘርፎች የተጠቃለሉ ናቸው – ትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ፡፡ በተለይ በኑሮ ሁኔታ ሥር ኤሌክትሪክ፣ ጽዳት፣ የሚጠጣ ውሃ፣ የንብረት ባለቤትነት፣ ወዘተ በግብዓትነት ተወስደዋል፡፡
በዚህ ዓይነት እኤአ ከ2002 እስከ 2011 ድረስ ያለውን መረጃ በማጠናቀር በወጣው ዘገባ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ ከ100 ሰዎች መካከል 87ቱ ድሃ ተብለው የሚጠሩ ሲሆን 58ቱ ሰዎች ግን መናጢ ደሃ ተብለው የሚጠሩ መሆናቸውን ይናገራል፡፡ ድህነቱ በገጠር እጅግ የከፋ እንደሆነ በመጠቆም ከ100 ሰዎች ውስጥ 96ቱ ደሃዎች እንደሆኑ፤ በከተሞች አካባቢ ግን ከ100 ሰዎች መካከል 46ቱ ደሃ ተብለው የሚጠሩ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በአጠቃላይ የአገሪቷ ክፍሎች ከ100 ሰዎች መካከል 31ዱ በቀን ከ20ብር በታች በሚገኝ ገቢ እንደሚኖሩ ጠቁሟል፡፡
ድህነቱ የከፋባቸው “ክልሎች” ብዙም ልዩነት እንደሌላቸው የሚያሳየው የጥናቱ ዘገባ ከሁሉም ግን ሶማሊ በደሃነት ቀዳሚ ነው፡፡ በጥቂት ነጥብ ልዩነት ኦሮሚያ፣ አፋር፣ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል፡፡ በእነዚህ አምስት ክልሎች ከ100 ሰዎች ውስጥ 90 እና ከዚያ በላይ የሚሆኑት ደሆች መሆናቸው በጥናቱ ተዘርዝሯል፡፡
የ108 በማደግ ላይ ያሉ አገራት የድህነት መለኪያ ዝርዝር የያዘው ዘገባ በግልጽ እንደሚያሳየው የመጨረሻዋ ደሃ አገር ኒጀር ስትሆን ከዚያ ቀጥላ ኢትዮጵያ ነች፡፡ እስከ 10 ባሉት የመጨረሻ አገራት ውስጥ ማሊ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ላይቤሪያ፣ ጊኒ፣ ሶማሊያ፣ ቡሩንዲ፣ መካከለኛው አፍሪካ እና ጊኒ ቢሳው ከ3 – 10 ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡
በየጊዜው የኢትዮጵያ ዕድገት “ድርብ አኻዝ” እንደሆነ ለሚናገረው ኢህአዴግ ይህ ዓይነቱ ዓለምአቀፋዊ ዘገባ የከፋ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በአስተያየት ሰጪዎች ዘንድ ይነገራል፡፡ በተለይ “ምርጫ” እየቀረበ ባለበት ወቅት ይህ ዓይነቱ በታዋቂ ዩኒቨርሲቲ የሚመራ ማዕከል የወጣ የጥናት ዘገባ የሚያመጣው ተጽዕኖ ከፍባለ ሁኔታ ለመጠቀም ተቃዋሚ ፓርቲዎች በቂውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባቸው እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ፡፡ ኢህአዴግ የማይስማማውን ማንኛውንም ዓይነት ዘገባ “የልማት ጸሮች” ያወጡት፣ “የአሸባሪዎች እጅ ያለበት”፣ “የኒዎ ሊበራል አቀንቃኞች ዘገባ”፣ “የኪራይ ሰብሳቢዎች ምኞት”፣ ወዘተ እያለ እንደሚያጥላላውና እንደሁኔታው የተለመደውን “ማጣፊያ” በኢቲቪ ወይም ሌሎች ድቃይ “የሚዲያ” ክፍሎች ላይ እንደሚያቀርብ ጎልጉል አስተያየት የጠየቃቸው በኢትዮጵያ የከፍተኛ ተቋም ምሁር ገልጸዋል፡፡
ይህ የኦክስፎርድ ማዕከል ይህንን ጨምሮ በየጊዜው የሚያቀርባቸው የጥናትና ምርምር ውጤቶች በበርካታ ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች፣ በፖሊሲ አውጪዎች እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማት ጥቅም ላይ እንደሚያውሉት በድረገጹ ላይ አስታውቋል፡፡
የጥናቱን ዘገባ በPDF ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ በቀጥታ ከማዕከሉ ድረገጽ ላይ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

Saturday, June 7, 2014

የኢህአዲግ/ህወሃት ቁልፍ ተግባር:- አራት ኪሎን መጠበቅ


የኢህአዲግ/ህወሃት ቁልፍ ተግባር:- አራት ኪሎን መጠበቅ

ልብ ብላችሁ ተመልከቱ:: ኢህአዲግ/ህወሃት ስልጣን ከያዘበት “ግንበት” 1983 ጀምሮ የሚፈጽማቸው ነገሮች ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያልሙት ቤተ መንግስን ለመጠበቅ ያለሙ ናቸው።  ላፍታ ወደ ኋላ ልመላሳችሁ።  ብዙ ሀገሮች ዋና ከተማቸውን የሚመሰርቱበት ቦታ ለሀገራቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ውጭያዊ እና ሌሎች ስትራቴጅ ጠቀሜታዎች የሚያበረክተውን አንድምታ መሰረት በማድረግ ነው። በተለይ የባህር በር ያላቸውን ሀገሮች ስንመለከት ብዙዎቹ ዋና ከተማቸው የባህር በርን የተንተራሰ ነው።  ኢትዮጵያ ረጅም የባህር በር የነበራት ሀገር ነበረች። ከሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ምስራቅ (ከአማሴን ሰሜን ጫፍ እስከ ጅቡቲ ደቡባዊ ክፍል) ድረስ በቀጭን መስመር የባህር አዋሳኝነቷን ማጣቷ የኢትዮጵያን ካርታ የሚመለከት ባዕድ እንኳን የሚያጤነው ጉዳይ ነው። ይሄ ለምን ሆነ? የቀደሙ መንግስታት እራሳቸውን ከውጭ ወራሪ በህዝብ ለመከለል ይረዳናል ሲሉ ባላቸው ግንዛቤ እንደሆነ አንድ የታሪክ መምህሬ ክፍል ውስጥ ሲናገር አስታውሳለሁ:: ለእኔም ትርጉም ሰጥቶኛል። እናም ቤተ_መንግስትን ለማስከበር በማሰብ ዘላለማዊ የሀገር ማንነት እና ጥቅምን ወደ ጎን በመተው ዋና ከተማን መሃል ሀገር እና ቤተ ክርስቲያንን ከፍተኛ ቦታ (ኮረብታ) ላይ መመስረት የተለመደ ሆኖ የዘለቀ እውነታ ነው።