Friday, May 10, 2013

ያበቃለት ስርአት








አንድ ስርአት ሕይውት አለው(alive) ይሠራል(working/Functional) ጥሩ ይንቀሳቀሳል(Vibrant) የሚባለው እንደ ስርአት፤እንደ መንግሥትና እንደ መልካም አስተዳደር ማድረግ የሚገባውን ሲያደርግ ነው። በየትኛውም ቦታና ጊዜ የአንድ መንግሥት አይነተኛ ተግባር፤ለእድገት ለብልጽግና ለሰላም ለደሕንነትና ለለመለመ ተስፋ አስፈላጊውን ሁኔታውች መፍጠር ነው። አንድ መንግሥት እንደ እድገት ደረጃዎቹ በተለያ ጊዜ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን መሥራት ቤገባውም፤እዝብን ተክቶ በጅምላ ተቆጣጥሮ እራሱ መሥራት አይገባውም ቢሠራም የሚያሰኬድ አይሆንም፤ከግል ጥቅም ባለፈ፤የተፈለገውንም እድገትና ብልጽግና ለማምጣት አይችልም። ሁሉም ቀና መልካምና ተገቢም የሚሆነው መንግሥት በሞኖፖል ሁሉን በመቆጣጠር ሳይሆን ነጻና ሕዝብን ያሳተፈ የህዝብ ቀዳሚ አለኝታነት ያለው መሰረተ ሰፌ የግንባታ ሥራ ሲሠራ ነው።
አንድ ስርአት ህይወት አለው ለማለት የሚያስችሉ መመዘናዎቹ ምን መሆን አለባቸው የሚለውን ስንመልስ ህያውለቱን ወይም ሙትነቱን ማስቀመጥ እንችላላለን። መኖር ከተባለ ቆሞ የሞተ፤ሕይወት እያለው በድን የሆነ ስርአትም አለ። በቀላሉ መኮፈሱ ሕይወት አለው ለማለት ዋስትና አይሆነውም ለማለት ነው።አንድ ስርአት የሚሠራና ህይወት አለው የሚባለው፦

Thursday, May 9, 2013

ወያኔ ሕወሃት ያልከበደው ኢትዮጵያዊ ማነው?






ሌቱ መሽቶ ይነጋል፤ ሳምንታት ወራት ዓመታት በፍጥነት መንጎዳቸውን አላቋረጡም፤ ክረምትና በጋ ይፈራረቃሉ፤ ወቅቶችም ማንም ሳይረብሻቸው ጊዜያቸውን ጠብቀው እያለፉ ነው፤ አፍጣጭ ገላማጭ ያለባቸውም ማዘዣ ጣቢያቸው ከእኛ አይደለምና። የክረምቱን ዝናብ ቀድሞ ለማምጣት፤ ፀሐይዋን ትንሽ ቀደም ወይም ዘግየት ብላ እንድትወጣና እንድትገባ ለማድረግ፤ የምንተነፍሰው አየር ባንድ አካባቢ ብቻ እንዲነፍስ ለማዘዝ፤ ብርሃን ብቻ እንዲሆን ወይም ጨልሞ እንዲቀር ማድረግ የሰው ልጅ የሚችል ቢሆን በተለይ እኛ ኢትጵያዊያን ምን ይውጠን ነበር? ለሀገርም ለሕዝብም ለታሪክም ለባህልም እንዴው ለምንም የማይጨነቅ ገዥ ሕወሃት ለተጫነብን።
“ሲለምኑ ማፈር ድሮ ቀረ” አሉ አድስ አበቤዎች። እንዴው ግን ሰራተኛው፣ ገንዘብ አስገቢና መላሹ፣ የሙስና ዘዋሪውና አስዘዋሪው፣ ቀጣሪውና አባራሪው፣ ባለስልጣኑና ባለፋብሪካው፣ ኢንቨስተሩና ነጋዴው፣ አምራቹ አከፋፋዩና ቸርቻሪው፣ መሬት ሰጭና ነሽው፣ አራሹና አሳራሹ ባጠቃላይ ሁሉም በሕወሃትና የአገዛዙ አባላት ቁጥጥር ስር በሆነበት ሀገራችን “ሲለምኑ ማፈር ቀረ” ቢባል የሚያስደንቅ አይሆንም። ህግን አክብሮ በራስ መንገድ መስራትና እራስን መደጎም አይቻልማ፣ ከህሊናው ጋር ሆኖ ከወያኔ ጋር መስራት የመጨረሻ እጣው ከስራ መባረርና ልመና ነዋ። ድሮ እኮ መስራት የማይወድ ነው የሚለምነው፣ ያኔ እኮ ቀን ከሌት ደክሜ በላቤ በደሜ ሀገሬን ሕዝቤን እራሴንም ላሻሻል የሚለው ሳይሆን መድከምን እየጠላ መጎሳቆልን እየሸሸ በምላሱ ስንቱን አውለብልቦ እራሱም ተውለብልቦ በመሽሞነሞን ለመኖር የሚፈልገው ነበር የሚለምነው። ስለዚህም በዚያ ዘመን መለመን ያሳፍር ነበር። አሁን ግን ቀረ።

Monday, May 6, 2013

የኢህአዴግ ባለስልጣናትን ዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት የማቅረቡ ጉዳይ ከመለስ ሞት ጋር የሚሞት አይሆንም። እኛ ስንስተካከል ዓለምና የፍርድ ሚዛንዋ ወደ እኛ ያዘማሉ።



አቶ ኦባንግ ሜቶ የአኢጋን ዋና ስራ አስፈፃሚ
ከጥላ መጽሄት የተወሰደ
አቶ ኦባንግ ሜቶ ይባላሉ። የስቃይ ሰለባ የሆኑና እሳቸው የሚመሩትን ድርጅት ድጋፍ ያገኙ ኢትዮጵያውያን “አባታችን“ ይሏቸዋል። እሳቸው ብዙ ሃላፊነት ያለባቸው ሰው በመሆናቸውObang Metho's interview with Tela Magazine  ዛሬ አፍሪካ ነገ አውሮፓ ከነገወዲያ አሜሪካ ከዛም ኤሺያ የማይዞሩበት ዓለም የለም።ግን የትም ይሂዱ ሁል ጊዜም በራቸው ለሁሉም ዜጋ ክፍት ነው።የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ወይም አክቲቪስት ናቸው።አሁን አሁን በየትኛውም ዓለም ኢትዮጵያን አስመልክቶ በሚዘጋጁ መድረኮች ላይ ግንባር ቀደም ተጋባዥ በመሆን የሚያምኑበትንና ለአገሪቱ ይጠቅማል የሚሉትን ሃሳብ ግራና ቀኝ ሳያዩ በቅንነትና በግልፅ ያቀርባሉ።በዚህ አቋማቸውም የበርካቶችን ቀልብ ለመግዛት ችለዋል አንደበተ-ርቱዕ ናቸውም ይሏቸዋል በቅርብ የሚያውቋቸው ሰዎች- አቶ ኦባንግን።
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኦባንግ ስም ካላቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች በማይተናነስ እንዲያውም በሚልቅ ሁኔታ ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያላቸው ሰው በመሆናቸው የኢትዮጵያውያንን ብሶትና ቅሬታ በማንኛውም መድረክ ላይ ፊት ለፊት በማቅረብ ለመፍትሄ የሚሰሩ ናቸው። ምንም እንኳን እንዲህ ይሰራል መባላቸውን ውዳሴ ከንቱ አታድርጉብኝ ቢሉም እውነታውን ግን ከመግለፅ ወደ ሁዋላ ለማለት ያስቸግራል።

ኦባንግ የኢህአዴግ ደጋፊ ስደተኞችን አስጠነቀቁ “በአስመሳይ ስደተኞች ላይ በቂ መረጃ አለ”





“ክፉን በክፉ መመከት ባያስደስትም ወቅቱ ያስገድደናል” ሲሉ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል ተናገሩ። አገዛዙን ሸሽተው በተለያዩ አገራት ከለላ አግኝተው በስደት የሚኖሩም ሆኑ ጉዳያቸው እየታየ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ አስጠንቅቀዋል።Solidarity movement leader Obang Metho
የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህግ አውጪዎች፣ የጀርመን የኢሚግሬሽን ሃላፊዎችና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎች፣ ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ጉዳይ ሃላፊዎችና ተዛማጅ ሃላፊነት ካላቸው የህግ ክፍሎች፣ በካናዳ በተለያዩ ደረጃ ካሉ ባለስልጣናትና ወትዋቾች (አክቲቪስቶች)፣ በስዊድን አንዲሁም በእንግሊዝ በተመሳሳይ ግንኙነት ፈጥረው እየሰሩ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አገራቱ የስደት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ለስደት ዳረገን ከሚሉት መንግሥት ጋር በቅርብ እየሰሩ ስላሉ አስመሳይ ስደተኞች አስገራሚ መረጃዎች መሰብሰባቸውን አውቃለሁ” ብለዋል።
አቶ መለስ በሞቱ በወር ጊዜ ውስጥ ብቻ በካናዳ ቫንኮቨር 27 አንድ አይነት ቋንቋ ብቻ የሚናገሩ ወጣቶች ጥገኛነት መጠየቃቸውን ጉዳዩን በጥብቅ እየመረመሩት ካሉ ክፍሎች ማረጋገጣቸውንና የምርመራውን ውጤት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ “ወጣቶቹ ካናዳ የገቡት ለእያንዳንዳቸው 75 ሺህ ዶላር በማውጣት ነው። ይህን ገንዘብ ማን ሰጣቸው? እንዴት አገኙት? እንዴት ከአንድ አካባቢ (ክልል) ብቻ ሊሆኑ ቻሉ? የሚሉት ጉዳዮች ምርመራውን በያዙት ወገኖች ላይ ግራሞት የፈጠረ ትልቅ ጉዳይ ነው” በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከገንዘብ ማሸሽ ጋር በማያያዝ አመላክተዋል። ለምሳሌ አንድ ጉዳይ አነሱ እንጂ በመላው ካናዳ በተመሳሳይ የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ተናግረዋል።

Friday, May 3, 2013

የህማማት ማሰታወሻ ‹‹ህዝቤን ልቀቅ!›› እስክንድር ነጋን ልቀቅ!…




ይህ ሳምንት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ‹‹ሰሞነ ህማማት›› ተብሎ በፀሎትና በስግደት ይከበራል፡፡ ይህ የሆነው ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ በሀሰት ተወንጅሎ ለስቅላት ተላልፎ የተሰጠበት፣ በሰው ልጅ ከሚደርስ ስቃይ፣ መከራና ግርፋት ሁሉ የከፋውን የተቀበለበት ሳምንት በመሆኑ ነው፡፡
…የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖት ጥብቅ አማኝ ነው፤ የሀይማኖቱን ትእዛዛቶች በጥብቅ ያከብራል፤ ሁሉንም አፅዋማትም ይፆማል፡፡ ዛሬ በግፍ ታስሮ በሚገኝበት የቃሊቲ ወህኒም ሆኖ እንኳ የኩዳዴን ፆም ከመፆም አልሰነፈም (በነገራችን ላይ እስክንድር የሚገኝበት ‹‹ዞን ሶስት›› ፈርሶ እንደገና ሊሰራ ስለሆነ እስረኞቹ ወደሌላ ቦታ ሊዘዋወሩ እንደሆነ ተነግሯቸዋል)
እስክንድር የተወለደው ጥቅምት 27 ነው፡፡ ይህ ዕለት ደግሞ ለእምነቱ ተከታዮች የ‹‹መድሐኒያለም ዕለት›› እየተባለ የሚከበረበት ቀን ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ምንጊዜም ጠዋት ወይም ማታ ከስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ ከፍ ብሎ በሚገኘው ‹‹ምስኪያዙና መድሐኒያለም ቤተ-ክርስቲያ››ን የፈለገ አያጣውም፡፡የህማማት ማሰታወሻ  ‹‹ህዝቤን ልቀቅ!››  እስክንድር ነጋን ልቀቅ!...
…የፊታችን ሀሙስ (ሚያዚያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም) የእስክንድር ነጋ ይግባኝ ‹‹ለመጨረሻ ጊዜ›› ተብሎ ተቀጥሯል፡፡ ዕለቱ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ‹‹ፀሎተ ሀሙስ›› ታስቦ የሚውልበት ቀን ነው (አይሁዳውያን ኢየሱስ ክርስቶስን አሳልፈው ሰጥተው ሲያበቁ ስለሁከት፣ ስለመግደል በወሀኒ ታስሮ የነበረውን በርባንን ‹‹ፍታልን!›› ያሉበትን እና የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በትህትና ያጠበበትን ለማስታወስ ነው ቀኑ ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ተብሎ የተሰየመው)
…በድህረ ምርጫ 97 ለእስር ከተዳረጉ ጋዜጠኞች መካከል እስክንድር ነጋ አንዱ ነበር፡፡ የተፈታውም በ‹‹ይቅርታ›› ሳይሆን ፍርድ ቤቱ ‹‹ነፃ ነህ!›› ብሎ አሰናብቶት ነው፡፡ ቀኑም የ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ዕለት ነበር፡፡ …የከነገ በስቲያ ሚያዚያ 24 ግጥምጥሞሽስ ምን ያሰማን ይሆን?

የዘመኑ ትውልድ ሥነ-ምግባር ወዴት?





አንድ ትውልድ ትውልዳዊ ፍሰቱን ጠብቆ ዘመናትን በስኬት መጓዝ ይችል ዘንድ ከቁሳዊ ሥልጣኔ  ባሻገር በመንፈስ የሰለጠነ፤ በሥነግባር የታነፀና ባለራዕይ ሊሆን ይገባል። ከዚህ አኳያ በወያኔ ዘመን በሥነምግባር የታነፀ፤ ባለተስፋና በትክክል ማለም የሚችል ስነ አዕምሮና  ጠንካራ ስነልቦና ያለው ትውልድ ከመፍጠር አኳያ ምን ላይ ነው ያለነው? የትውልዱ ሥነ-ምግባር በምን ልክ እየተቀረፀ ነው? ትውልዱ በጥሩ ሥነ-ምግባር ይታነጽ ዘንድ ከፍተኛው ድርሻ የሚጠበቅባቸው ተቋማት ድርሻቸውን እየተወጡ ነውን? ካልሆነ ምን ዓይነት ነገ ይጠብቀናል? መፍትሔውስ ምንድነው?
በእኔ እምነት የአንድ ትውልድ ሥነምግባር በቅጡ ይታነጽ ዘንድ የሚከተሉት ተቋማት ኃላፊነት አለባቸው። ይህን ኃላፊነታቸውን ከመወጣት አኳያ ምን ሳንካ እየገጠማቸው ነው የሚለውን አያይዤ ለመጥቀስ እሞክራለሁ።
1.     ቤተሰብ
ቤተሰብ የአንድን ማኅብረሰብ እጣ ፈንታ ለመወሰን የሚችል የሚታይና የሚዳሰስ ተቋም ነው።ጥሩ ቤተሰብ የጥሩ ማኅበረሰብ መሠረትነው። ጥሩ ማኅበረሰብ የጥሩ ሃገር መሠረትነው። ስለዚህ በአንድ ቤተሰብ ውስጥ የሚኖር ግብረገባዊ መስተጋብር፡ እናት ወይም አባት (የቤሰብ ሃላፊዎች)  ልጆቻቸውን በሥነ ምግባር ለመቅረጽ የሚኖራቸው ኃላፊነት እና አደራ እጅግ ከባድ ነው። ልጆች ትምህራቸውን በደንብ እንዲከታተሉ፤ ሰው ማክበርና ሰው  መውደድን፣ ሰብዓዊነትን፣ ቅንነትን፣ “ይቻላል” ባይነትን፣ ምክንያታዊነትን፣ የሌሎችን ሃሳብ ማዳመጥንና ከሌሎች መማርን፣ መረዳዳትን፣ መተጋገዝን፣ የሃገር ፍቅርን … ወዘተ ባህሪያቸውና የሕልውናቸው አካል እንዲያደርጉ፤ በአንፃሩ ተንኮልን፣ ክፋትን፣ ግትርነትን፣ ቂመኛነትን፣ መጠላለፍን፣ ሰው መናቅን፣ እና የመሳለሉ የመንፈስ እድፎችን እንዲጠሉና እንዲያስወግዱ በማድረግ ልጆቻቸውን የእውነት “ሰው” አድርጎ  የመቅረጽ ኃላፊነት አለባቸው። የሕፃንነት ዘመናቸው የነገ ማንነታቸው ፈጣሪና መሠረት ነውና።