ሰሞኑን የአለምንና የኢትጵያውያንን ሀሳብና አስተየት ለመለዎጥ ወይም ለማሳሳት ወያኔ በወኪሎቹ አማካይነት የተለመደዉን ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ ከርሞአል። ዓባይ እንደሚጠቅመን ሆኖ ቢገደብልን እጂግ ደስ ይለን ነበር። የወያኔ ትግሬዎች ሰለአባይ ከባለቤቱ ከኢትጵይያ ህዝብ በላይ የሚያቀነቅኑበት የሚጮሁበትና ሚያስመስሉበት ምክንያቱ ሌላ ነው። እነሱ ሃገር ወዳድ ሌሎች ኢትዮጵዉያን ሀገራቸዉ ብታድግና ብትጠቀም የሚጠሉ ሆነው አይደለም።
የኢትዮጵያም ህዝብ ይህንን በደንብ ያዉቀዋል። ከእባብ እንቁላል እርግብ ኣልጠብቅም ብሎአቸዋ። ታዲያ ይኸ ሁሉ የአዞ እንባ ማፍሰስና የኢትዮጵያን ሀዝብ ጩኸት ለመቀማት የመሞከር ሚስጥሩ ምንድነው??? ወያኔ ኢትዮጵያን ለመጉዳትና ለረጂም ጊዜ እችግር ዉስጥ ለማስገባት ካስጠናቸዉ ትልልቅ ጉዳዮች (ፕሮጀችቶች) ኣንደኛዉና ዋናው የአባይ ግድብ ነው። ለዚህም ማስረጃ የሚከተሉትን ነጥቦች ተመልከቱ:
ሀ) ግድቡ የሚሰራው በጥንቃቄ የመሀል ሀግሩን ህዝብ በተለይም አማራዉንና ኦሮሞዉን እንዳይጠቅም በጣም እርቆ በጠረፍ ላይ ነዉ። ይህም በተለይ አማራዉና ሌሎች በአካባቢው የሚኖሩ ህዝቦች በምንም አይነት ለእርሻ (ለመስኖ) ለመጠጥ ለኢንዱስትሪና ለኤሌክትሪክ ኣገልግሎት እንዳይጠቀሙ ታስቦ የተሰራ ነው።
ለ) ሁለተኛዉ የተንኮል አካል ይኽ ጥቅም የማይሰጥ ነገር ግን ሆን ተብሎ በኣካባቢዉ ግጭት እንዲነሳና በዚያ ጥቅም በሌለዉ ግድብ ክዚህ በፊት በሺራሮና በባድመ ላይ እንደተደረገዉ ሁሉ የኢትዮጵያዉያንን ደም በማፍሰስና እነሱ እየዘረፉ ለመኖር የዘረጉት ወጥመድ ነው። ግድቡ ከፍ ብሎ ከተሰራ ወደ ሌሎች ኣካባቢዎች ወደ ምስራቅና ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ተዘርግቶ ሌሎች የሀገሪቱ ኣካሎች ይጠቀሙ ነበር ። ነገር ግን ያ ባለመፈለጉ የግድቡ ስራ ኤሌክትሪክ ለሱዳንና ለግብጽ ማመንጨትና መሽጥ ብቻ ሲሆን የተመረጠዉም ቦታ እድንበር ኣካባቢ ነው:: ይህም በመሆኑ ድንገት ግጭት ቢከሰት እድንበር ላይ በመሆኑ በግብጽም ሆነ በሱዳን በቀላሉ የሚመታና የሚመክን ነዉ። ልክ ወደ ትግሬ የባቡር ሃዲዱ ሲዘረጋ አማራዉንና ኦሮሞዉን አግልሎ ወይም ሳይነካ ከአዋሽ ተነስቶ ዳር ዳሩን እየዞረ በአፋር በረሀ እንደ ደጋን ጎብጦ ከተጉአዘ በሁዋላ ወደ ቀኝ በመታጠፍ የትግሬ ከተሞችን አዳርሶ እንደቆመው የባቡር መንገድ አይነት መሆኑ ነው።
ሐ) ሶስተኛዉ ትልቁ የሴራው አካል በአባይ ግድብ ስም እጂግ ግዙፍ የሆነ የኢትዮጵያ ሀዝብ ገንዘብ በህጋዊ መልክ መዝርፍና ማደህየት ነው። በዚህ ግዙፍ የዝርፊያ ስልት በኑሮ ውድነት ላይ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች አርሶ ኣደሮች ነጋዴዎችና ሌሎች የህበረተሰብ ክፍሎች ካፋቸዉ እየተነጠቁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ለማይጠቅምና በራሳቸዉ ላይ ችግር ለሚፈጥር ሰራ እየተበዘበዙ (እየገበሩ) ነው። በሌላ በኩል በጣም የሚያሳዝነዉ ወያኔዎች የዘርፉትና በግልጽ አለም ካወቀዉ ገንዘብ ዉስጥ 3 .00 ቢሊዮን በመለስ ሰም የተቀመጠ ሲሆን 11.70 ቢሊዮኑ ደግሞ ከኢትዮጵያ ውስጥ በህገወጥ መንገድ ተዘርፎ የሽሸ ነው። ይህ ማለት ወያኔወች የዘርፉት ገንዘብ ብዛት አራት የአባይ ግድቦችን ሊያሰራ የሚችል በመሆኑ ኢትዮጵያ በመድማት ላይ መሆኑዋን የዉጭ ሚዲያዎ በግልጽ ጽፈዋል።
መ) ሌላዉ ኣስገራሚ ሚስጥር አልጃዚራ ላይ ከግብጽ ከኢትዮጵያና ከእንግሊዝ አገር ተጋብዘው በተደርገው ዉይይት ላይ ግብጻዊቱዋ እዲህ ብላለች ” ግድቡ ሀገራዊ (ናሽናል) ሳይሆን ክፍለ አሁጉራዊ (ሪጂናል) መሆኑን ሙዋቹ መለስ ዜናዊ ተስማምቶበታል” በማለት የዎያኔዉ መሪ ክህደት መፈጸሙን አጋልጣለች (ይህንን ታሪካዊቪዲዮ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማየት ኣለበት)። ይህም ማለት የግደቡ ባለቤቶች ሱዳን ግብጽና ሌሎች በአካባቢዉ የሚገኙ ሀገሮች ጭምር ናቸዉ ማለት ነው::
ከዚህም አልፎ ተርፎ ዜጎች መሰዋእትን ከፍለዉ ባቆዩዋት ሀገር ዉስጥ መብታቸዉን በመጠየቃቸዉ ብቻ በጸራራ ጸሃይና በድብቅ ሲገደሉ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ወገኖቻችንን ከሚኖሩበርት ቦታ በግፍ እያፈናቀሉ የነጻነት ታጋዮችን እያሳደዱ እየደበደቡ እያሰሩና እያሰቃዩ ለህዝቡ ጠላት ከመግዛት በስተቀር ለእድገት ለማይጠቅም ግድብና በአባይ ስም ለኢትዮጵያ አሳቢ መስሎ ለመታየት እየሞከሩ ነው። ፕሮጀክቱ ሲነደፍ በጥላቻና ግዙፍ ገንዘብ ለመዝረፊያ በመሆኑ በአጠቃላይ ኢትዮጵያዉያንንና በአባይ ተፋሰስ አካባቢ ኑዋሪ የሆነውን ሰፊ ሕዝብ አላማከሩም። ህዝቡም ሃሳቡን ተጠይቆ አልተሳተፈበትም።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! ወያኔ ለአንተ በታሪክ ዉሰጥ ጥሩ አስቦም ሆነ ሰርቶ ስለማያዉቅ በምትወደዉ ወንዝሕ በአባይ ሽፋን የተጋረጠብህን ተንኮል በጣጥሰህ ወያኔን በማስወገድ በሚጠቅምህ መልኩ አባይንና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችህን ወደፊት ለመገንባት ስለምትችል አሁን ወያኔ በሚነዛው የዉሸትና ፕሮፓጋንዳ እንዳትረታ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
No comments:
Post a Comment