ዲሞክራሲ !!!
በዜማ እንጉርጉሮ በግጥም ደርድሮ
ያልዘከረሽ ማነው አንቺን ስንኝ ቛጥሮ
ወረቀት ከብእር ያገጣጥምና
ያወዳድስሻል ቀለም ያፈስና ፥
እጫኛሽ ብዛቱ ቀለበት አሳሪው
በፍቅርሽ ታማሚው
ለሶስት አራት ቀን ጫጉላ ቤት አዳሪው
ዳሩ መች ይቆያል ፍቅርሽ
እንደደራ ደጅሽ እንደሞቀ ቤትሽ
በሩቅ ምስራቅ አገር ስምሽን አስጠርተሽ
አውሮፓንም ዳሰሽ አሜሪካ ብትገቢ
የሕዝብ እልቂት ገዶሽ አፍሪካ ብትገቢ
ውሎ ገባ ሆነ አልሆንሽም ከራሚ
ንጉስ ስትሾሚ ንጉስ ስታወረጂ
አንዱን ስታነጂ አንዱን ስታበርጂ
ሕዝብን ስታድኚ ሕዝብን ስታስፈጂ
እድሜ ዘልዛላ ነው መቼም አታረጂ ፥
ሞተሽ እንዳንል አልሞትሽም ይሉናል
ስምሽን ሲያነሱ ሲጠርሽ ሰምተናል
የለሽም እንዳንል አናይሽም ባካል
ታመሻል እንዳንል የለሽም ሆስፒታል
አንችን በመፈለግ እግራችን ቀጠነ
ተስፉችን ባከነ እንደጉም በነነ
ወዴት ነው መንኛሽ መኖሪያ ሰፈርሽ
መጠሪያቸው ማነው የእናትና አባትሽ ፥
ምለሻል ይሉናል አፍሪካን ላትረግጪ
የተገፉውን ህዝብ ነፃ ላታወጪ
ምን ይበጃል ታዲያ ፍጠሪ እስቲ መላ
እስክትመጪ ድረስ ይፍጁን ወይ በጅምላ ?
No comments:
Post a Comment