የወያኔ አገዛዝ ከፍርድ ቤትት ወደ ተራ የፖለቲካ ማጥቂያ መሳሪያነት የለወጣቸዉ የኢትዮጵያ ፍርደ ቤቶች የዕለት ከዕለት ዉርደት አሁንም እነደቀጠለ ነዉ። ሃያ አመት ሙሉ አገዛዙ የወነጀላቸዉነ እየኮነነና አገዛዙ አሸባሪ ያላቸዉን በሽብርተኝነት ፈርጆ አስራትና የሞት ፍርድ ሲፈርድ የከረመዉ የወያኔዉ ፍርድ ቤት ከሰሞኑ ሙሉ ኃይሉን ወደ ኦሮሞ ህዝብ በማዞር የኦርሞ ፌዴራሊስት ዲሞክራቲክ ንቅናቄ (ኦፈሰዴን)ና የኦሮሞ ህዝብ ኮንግሬስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አካል አባል የሆኑትን አቶ በቀለ ገርባንና አቶ ኦብላና ሌሊሳን ኦነግን ትረዳላችሁ የሚል ሰንካላ ምክንያት ፈጥሮ ወነጀለኛ አድርጓቸዋ ል።
ወያኔ ሥልጣን ይዞ በቆየባቸዉ ባለፉት ሃያ አንድ አመታት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሳቸዉንና አሁንም በማድረስ ላይ ያለዉን ግፍና መከራ የተቃወሙ የኦሮሞ ልጆችን ህፃን፤ ሽማግሌ፤ ወንድና ሴት ሳይለይ እያሰረ አገሪቱን እስር ቤቶች በኦሮሞ ልጆች መሙላቱን ቀድሞ አባላቱ ሳይቀሩ የመሰከሩት ሐቅ ነዉ። አሁን ደግሞ ይህ አልበቃ ብሎት የህዝብን የነፃነት ፍላጎት ለማፈን ሆን ብሎ ያወጣቸዉን ህጎች መበጠቀም እሱ እራሱ ህጋዊ ብሎ በፈቀደዉ መንገድ የሚነቀሳቀሱ ፓርቲ መሪዎችን ሽብርተኛ በሚል የአሉባልታ ክስ ወንጀለኛ አድርጓቸዋል።
ባለፈዉ አመት በእነ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ ላይ አሁን ደግሞ በአቶ በቀለ ገርባና በአቶ ኦብላና ሌሊሳ ላይ የወያኔ ፍርድ ቤት ያስተላላፈዉ “ሽብርተኛ” ናችሁ የሚል የፍርድ ዉሳኔ የሚያመለክተዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለመብት፤ለነፃነትና ለእኩልነት መታገል በሽብርተኝነት የሚያስከስስ መሆኑን ነዉ፤ ወይም ከወያኔ አባላትና ከትቂት ለሆዳቸዉ ካደሩ ባንዳዎች ዉጭ ያለዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ቀን እየጠበቀ ሽብርተኛ ተብሎ መወንጀሉ የማይቀር መሆኑን ነዉ።
የኦሮሞ ህዝብ በሚኖርበት ቦታ የቆዳ ስፋትም ሆነ በህዝብ ብዛት በኢትዮጵያ ዉስጥ ትልቁን ቦታ የያዘ ህዝብ ነዉ። ይህ ታላቅ ህዝብ ዛሬም እንደትናንቱ ቁጥሩንና ብዛቱን በሚመጥን ልክ በአገሪቱ የፖለቲካ፤የኤኮኖሚና የማህበራዊ መስኮች ተሳትፎ በማድረግ ባለመቻሉ በገዛ አገሩ እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮ የበይ ተመልካች ሆኗል። ይህንን አስከፊ ሁኔታ ለመለወጥ የሚታገሉትን የኦሮሞ ልጆች ደግሞ ወያኔ በድህንነት ሀይሎቹ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱን ፍርድ ቤቶች ጭምር በመጠቀም ሽብርተኛ የሚል ታርጋ በመለጠፍ እያሰራቸዉ ነዉ። ለምሳሌ ባለፈዉ ሳምንት በሽብርተኝነት የተወነጀሉት አቶ በቀለ ገርባና አቶ አብላና ሌሊሳ የተወነጀሉት የኦነግ ተባባሪዎች ናችሁ በሚልና ለሂውማን ራይት ተቋማት መረጃ ሰጥታችኋል በሚል የፈጠራ ክስ ነዉ።
በሌላ በኩል ደግሞ ከመለስ ዜናዊ ህልፈት በኃላ በተደረገዉ የስልጣን ዝዉዉርና ሽግሽግ የኦህዴድ አባላትን ከዋና ዋና የስልጣን ቦታዎች በማራቅ ወያኔ አሁንም በኦሮሞ ህዝብ ላይ የጀመረዉን የንቀት ዘመቻ እንደቀጠለበት ነዉ። በተለይ በቅርቡ የ በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ በአቶ ጁነዲን ሳዶ ባለቤት ወ/ሮ ሀቢባ መሐመድ ላይ የተመሰረተዉ የሽብርተኝነት ክስ የሚያሳየው በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል ብቻ ሳይሆን ወያኔ ተጠግተዉት በከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ያስቀመጣቸዉን ሰዎችም ቢሆን አንገታቸዉን ደፍተዉ እስካልተገዙለት ድረስ ከመርካቶ እንደሚገዘ አላቂ ዕቃ ከተጠቀመባቸዉ በኃላ እንደሚወረዉራቸዉ ነዉ።

የህሊና እስረኞቹ ፍርደ ገምድል ውሳኔ ሲሰጣቸው ከቶ ሳይደናገጡ ጀግነነት በተሞላበት ለወያኔ ዳኞች የተናገሩት ምላሽ “እናንተ ለምትሰሩት የበደልና ፍርድቤቱን የማዋረድ ስራ ታሪክና ትውልድ ይጠይቃችኋል” በሚል ነው ስለዚህ ሁላችንም ከነዚህ የህሊና እስረኞች ብርታትና ጥንካሬ ብዙ ልንማር እንችላለን። ጀግኖችን በርቱ ማለትም የእኛ ፈንታ ነው።
በጥቅሉ በኦሮሞ ወገኖቻችን የሚደርሰው ማለቂያ የሌለውን በድል አብረን ልንታገለው ይገባል። የመብት ረገጣን በሚቃወሙ፣ የመልካም አስተዳደርን መመስረት በጠየቁ፣ ስለዲሞክራሲያዊ ስርአት መመስረትን ባነበነቡ የኦሮሞ ተወላጆች በእነ አቶ በቀለ ገርባ የተወሰነው የጥፋተኝነት ውሳኔ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ ነው።
አሻንጉሊቱም ፍርድ ቤት ተብየው ራሱን ከወያኔ መጠቀሚያነት ሊያጸዳ ይገባል፤ ለዚህም ምስክር እነ አቶ በቀለ ከይስሙላው የአእምሮ ድሃ ዳኛው ለተሰጣቸው የፍርድ ማቅለያ እድል እንዲናገሩ ሲሰጣቸው “ላልሰራነው ወንጀል እና እናንተ ላቀነባበራችሁት ፈጠራ መልስ እንደማይሰጡ ነገር ግን ታሪክ የማይረሳው ስራ መስራታቸውን ገልጸው እናንተ ለምትሰሩት የበደልና ፍርድቤቱን የማዋረድ ስራ ታሪክና ትውልድ ይጠይቃችኋል የሚል መደምደሚያ ሰጥተዋል። በመጨረሻም ሁላችንም በአንድ ድምጽ ወያኔ በኦሮሞው ወገናችን የሚያደርሰውን አዋርዶ የመግዛት እና የአሻንጉሊቱን ፈርደ-ገምድል ውሳኔ ልንቃወመውና ልንታገለው በቃህ ልንለው ይገባል!!

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
No comments:
Post a Comment