Monday, September 22, 2014

ሕዝቡና ተማሪው በአገር ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር መግባባት አልቻልንም በማለት ስልጠናው እንዲቋረጥ ጠየቀ


ምንሊክ ሳልሳዊ

የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብሶታቸውን በከፍተኛ ቁጣ ገልጸዋል።

- ለወያኔ ባለስልጣናት የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም።

- የሃምሳ አመት እቅድ ለምን አስፈለገ የስልጣን ጥመኝነትን ያሳያል።

- ለሶስተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ እየተካሄደ ነው።

- በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይሁኑ አባላቶቹ የአስተዳደር ብቃት የላቸውም።

- ኢትዮጵያውያን በህግ ፊት እኩል የሚሆኑት እና ፍትህ የሚነግሰው ቀን እንናፍቃለን።

- በቫት ስም መንግስት ዘረፋ ይዟል በህጉ ቫት አይከፈልበትም የተባለው የጤና ዘርፍ ሳይቀር ቫት እየቆረጠ ነው።


በየአከባቢው እየተካሂደ ያለው ልማታዊነትን ሽፋን አድርጎ የስልጣን ማስረዘሚያ ሰበካ (ስልጠና) እንደቀጠለ ቢሆንም በህዝቡ እና በአሰልጣኞች መካክል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ከመከሰቱም በላይ ህዝቡና ተማሪው በአገራችን ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር ልንግባባ አልቻልንም ስለዚህ አበል ይቅርብን እና ስልጠናውን አቋርጡልን በማለት እየጠይቀ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። ሰልጣኞች እንደሚሉት እየተካሄደ ያለው ስልጠና ሳይሆን የፖለቲካ ሰበካ ነው ይህ ደሞ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸውን ህዝቦች ለማደናቆር ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ የያዛችሁን ስልት ቀይራችሁ ህዝብ መሃል ግቡና አናግሩን እንጂ በ አበል እና በቀበሌ ጥቅማጥቅም አታስገድዱን፡ አያዋጣችሁም ሲሉ ተናግረዋል።

Sunday, September 21, 2014

በጸረ ሽብር ህጉ የሚፈጸመው በደል እንዲቆም ተጠየቀ

በየተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት አማካሪ ባለሙያዎች የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር ህጉን ሰብአዊ መብትን ለመደፍጠጥ ከማዋል እንዲቆጠብ አሳሰበ፡፡ ይህ ማሳሰቢያ የመጣው የተለያዩ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሰብአዊ መብት ጥሰትና አፈና እንዳሳሰባቸው መግለጻቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተግልጾአል፡፡ ማሳሰቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና በጸረ ሽብር ስም የሚወሰደውን እርምጃም ለመከላከል ያግዛል ተብሏል፡፡

‹‹ችግሩ እየተከሰተ እንደሆነ ከገለጽንበት ከሁለት አመት በኋላም ጸረ ሽብር ህጉ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎችንና ተቃዋሚዎችን ሰለባ እያደረገ እንደሚገኝ ሪፖርት እየደረሰን ነው›› ያሉት ባለሙያዎቹ በተለይ በእስር ቤቶች ማሰቃየት፣ ኢሰብአዊ የሆኑ እርምጃዎች እየተፈጸሙ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
ባለሙያዎቹ አክለውም ‹‹ሽብር መዋጋት ጠቃሚ ነው፡፡ ነገር ግን ውጤታማ ለመሆን ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብትን በማክበር መከናወን አለበት›› ብለዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የጸረ ሽብር ህጎች በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ ውስጥ በግልጸ መቀመጥና መጠቀሚያ መሆን እንደሌለበት መክረዋል፡፡

Tuesday, September 2, 2014

የወገኔ ዓማራ ነገር!

ከ ቦጋለ ካሳዬ


በወልቃይትም ሆነ በተቀረው ኢትዮጵያ ወያኔ ካለማቁዋረጥ ላለፉት 23 ዓመታት የሚያካሄደው አማራን የማጽዳት ዘመቻ
በኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ በሌላ አገር የሚወዳደረው እንዳለ አላውቅም። ህዝብን ማጽዳት ግን እጅግ የቆየ፤ ምናልባት በአሳርያን
የተጀመረ ድርጊት እንደሆነ ጻሕፍት ያስረዳሉ።

ኢትዮጵያውያን ደጎችም ቂሎችም ስለሆንን፤ ወያኔ የሚያደርገውን ጭካኔ ስንሰማ፤ ኸረ ይኼ እንዴት ተድርጎ! ብለን የሆነውንና እየሆነ ያለውን ነገር ለመቀበል እንቸገራለን። ውይ! ውይ! እምጽ! የሰይጣን ጆሮ አይስማ ብለንም በደሉን እንደ ቀላል ነገር የምናረግብ አድርባይ የህሊና ዱልዱሞችና የውሸት ቤተክርስቲያን ተሳላሚዎችም ብዙዎች ነን።

የወገናቸውን በደል እውነት መሆኑን አጣርተው፤ ግፉ ነገ በራሳቸው ላይ ሊደርሰም እንደሚችል አስበው፤ ለችግሩ የማያዳግም መፍትሄ ለመስጠት ጥቂቶች ቁርጠኝነት ማሳየት ቢጀምሩም ለእስር፣ስደትና ግድያ እየተዳረጉ ነው። ብዙሃኑ በተለይ መረጃ በቀላሉ የሚያገኘው ከተሜ፤ መቼ የራሱም ሆነ የወገኑ በደል አንገፍግፎት ይኼን ዘረኛ የወያኔ አገዛዝ በሕብረት ከትከሻው ላይ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል አምላክ ብቻ ነው የሚያውቀው ማለት ሳይሻል ይቀራል?

ኽረ ለመሆኑ የሕዝብ ጽዳት ምንድን ነው? ነገሩ በእቅድ ተይዞ፤ ሆን ብሎ በጎሳ/ነገድ/ ብሄር፣በሃይማኖት፣በዘር፣በመደብ፣ ወይም በጾታ የሚለይና የማይፈለግ ሕዝብን ከአንድ አካባቢ ማስወገድ ነው። አተገባበሩም፤ ሰፋ

Thursday, August 21, 2014

አብርሃ ደስታ ሃብታሙ አያሌዉና እና ኤርትራ

 ( ግርማ ካሳ)


ራሱን ግንቦት 7 ብሎ ከሚጠራ ድርጅት ጋር እና ከድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በመገናኘት ፤ እንዲሁም ከባንክ በትዕዛዝ ብር በመቀበል የግንቦት 7 ተልዕኮና አላማ ለመፈፀም፤ ቁጥራቸው ከ60 በላይ የሆኑ ግለሰቦችን ለዚህ ጥፋት እንዲሰማሩ በማድረግ» የሚል ክስ ነው በወዲ ሃዉዜን/ትግራይ በሆነው አንጋፋ ፖለቲከኛ እና ብሎገር ላይ ክስ የቀረበው። ሌላው አንጋፋና አንደበተ ርትኡ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ፣ ሃብታሙ አያሌውም፣ «የግንቦት ሰባት ተባባሪ ነው» በሚል ነው ለመክሰስ ነው ዝግጅት እየተደረገ ያለው።


አብርሃ ደስታ እና ሃብታሙ አያሌው ፣ «ግንቦት ሰባትን ይደግፋሉ» የሚል ክስ ከቀረበባቸው፣ በተዘዋዋሪ መንገድ «ከሻእቢያ ጋር ወዳጆች ናቸው» ማለት ነው። ታዲያ የሻእቢያ ወዳጅ የሆነ ሰው፣ የኤርትራን መገንጠል ተቃዉሞ፣ ወይንም የኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤት መከበር እንዳለበት በማስመር ይናገራል ወይ ? እስቲ የጸረ-ሽብርና የአገር ደህንነት ተብዬው ምላሽ ይስጠን !!!
ሁላችንም እንደምናውቀው፣ በኤርትራ በኩል ትግል እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች፣ ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት ሊናገሩ አይችሉም። በሻእቢያ ሥር እስካሉ ድረስ ቀይ መስመር ተሰምሮላቸዋል። እነ ግንቦት ሰባቶች፣ ኦነጎች ...፣ እርዳታ የሚያገኙጥ ከሻእቢያ ማእከላቼ ደግሞ አስመራ እስከሆነ ድረስ፣ «ኢትዮጵያ የባህር በር ያስፈልጋታል» ብለው የመናገራቸው ነገር ጭራሽ የማይታሰብ ነው።

የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት የዞን9 ጦማርያኑን እና የጋዜጠኞቹን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አደረገ (ዞን 9)

ስድስቱን የዞን ዘጠኝ አባላት ማለትም በፍቃዱ ኃይሉ፣ አቤል ዋበላ፣ ማኅሌት ፋታሁን፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ዘላለም ክብረት እና አጥናፍ ብርሃነ እንዲሁም በሌለችበት ክሷ እየታየ ያለው በሶልያና ሽመልስ እንዲሁም በጋዜጠኞቹ ኤዶም ካሳዬ፣ ተስፋለም ወልደየስ እና አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ በልደታ 19ኛው የወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት የተሰየመ ሲሆን ከሙስሊም ኮሚቴ አመራሮች ጋር በአንድ ችሎት እንዲታደሙ በመደረጉ የታሳሪዎችን ቤተሰቦችም ሆነ ወዳጆችን ለማስተናገድ ቦታ የለም በሚል ለጋዜጠኞች ብቻ የፍርድ ሂደቱ እንዲታይ በፖሊስ ተፈቅዶ ነበር፡፡

በሌለችበት የተከሰሰችው ሶልያና ሽመልስ መጥሪያ በጋዜጣ መውጣቱን ፍርድ ቤቱ ያረጋገጠ ሲሆን የዋስትና
መብትን በተመለከተ በዛሬው ዕለት ተሰይሞ የነበረው ችሎት በጸረ ሽብር አዋጁ መሰረት በአንቀጽ 3 የሽብር
ተግባራት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ አንድም ወይም ሁለትም ከዚያም በላይ ወንጀል የፈጸመ መሆኑ
ወይም ለመፈጸም ያቀደ ለመሆኑ ተገልጾ ክስ ሲቀርብ ነው በተመሰረተባቸው ክስ ዋስትናን ሊያሳጣቸው
የሚችለው ብለው ጠበቆቻቸው የተከራከሩ ሲሆን ደንበኞቻቸው በአዋጁ መሰረት የሰሩት የሽብር ተግባር ክስ
አልቀረበባቸውም ስለዚህ በአዋጁ ተጠቀሰ ማለት በአዋጁ መሰረት ክስ ቀርቧል ማለት ስለማይቻል
የዋስትናው ጥያቄ በመደበኛ ስርዓት እንጂ በጸረ­ሽብር ሕጉ መሰረት ሊታይ አይገባም፤ በተጨማሪም አዋጁ

ዋስትና ይከለክላል ተብሎ ቢተረጎምም ከሕገ­መንግስቱ ጋር ስለሚጋጭ ዋስትና ሊፈቀድላቸው ይገባል
ቢሉም፤ ፍርድ ቤቱ አንቀጽ ተጠቅሶ መከሰሳቸውን እንጂ በዚህ መከሰስ ነበረባቸው ወይም አልነበረባቸውም ብሎ ለማየት ፍርድ ቤቱ አይገደድም እንዲሁም የጸረ­ሽብር አዋጁ ከሕገ­መንግስቱ ጋር አይጋጭም ብለዋል በዚሁም መሰረት የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ ተደርጎ ለጥቅምት 5 ቀን 2007ዓ.ም ቀጠሮ በመስጠት የዛሬው ችሎት የተጠናቀቀ ሲሆን ጠበቆቻቸውም የዋስትና ጉዳይ በተመለከተ ለጠቅላይ ፍረድ ቤት ይግባኝ እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡

የወያኔ ጁንታ በግዳጅ እየሰጠ ባለው ስልጠና ከባድ ተቃውሞ ከሰልጣኞች እየገጠመው ነው ።

ምንሊክ ሳልሳዊ


የመንግስት ሰራተኛው እና የዩንቨርስቲው ተማሪዎች የከተቱት ስልጣና ላይ ወያኔ በጥያቄዎች ተወጥሯል፡፤

በሚቀርቡ የስልጠና ርእሶች ላይ ከፍተኛ አለመግባባት እና ጩኽት እየተከሰተ ነው፡፡


ከኑሮ ውድነቱ በባሰ ያቆሰሉን የሕወሓት አባላት ናቸው ።" የመንግስት ሰራተኛው


መልካም የልማት አስተዳደር በሚል ሽፋን ለመንግስት ሰራተኞች እና ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች በተከታታይ ለ15 ቀን እየተሰጠ ያለው ስልጠና የወያኔን አመራሮች እና ከፍተኛ ካድሬዎች አጣብቂኝ ውስጥ የከተታቸው መሆኑን እና ተቀባይነት ማግኘት እንዳልቻሉ ከሰልጣኞች የሚመጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።

ሰራተኞቹ እና ተማሪዎቹ በየፊናቸው ያነሱት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ወቅታዊ ጥያቄዎች ወያኔዎች ፊታቸው ላይ ከፍተኛ ድንጋጤ ከመነበቡም በላይ ለመመለስ ሲደናበሩ እና እፍረት ሲሰማቸው የታየ መሆኑን እና መጭውን እንደማይችሉት ስሜታቸው ላይ ሲነበብ እንደነበረ የጠቆመው መረጃ ከወያኔ ካድሪዎች አከባቢ የተገኘ መረጃ እንደጠቆመው ይህን ያህል አስጨናቂ ነገር ይነሳል የሚል ግምት ስላልነበረ ለአሰልጣኝ ካድሪዎች ቀድሞ የተሰጠው ስልጠና ምንም ውጤት ላይ ባለማሳየቱ አዳራሾች በተማሪዎቹ በፉጨት እና በከፍተኛ ተቃውሞ እንደተሞሉ መሆኑ ታውቋል።

Tuesday, August 19, 2014

የፀጥታ ሃይሎች በጭፍን ታዛዥነት የሚጥሷቸው መሰረታዊ መርሆች

ድምፃችን ይሰማ!

በሃገራችን ኢትዮጵያ ህገ መንግስት መግቢያ ላይ በግልፅ እንደሰፈረው ሃገራችንን እንዲመራ የሚመሰረተው መንግስት በኢትዮጵያ ህዝቦች ነፃ ፍላጎት፣ በህግ የበላይነት እና በህዝቦች ፈቃድ የህዝቡን የጋራ ጥቅም፣ መብት እና ነፃነት እንዲያስከብር የሚመሰረት የፖለቲካ ተቋም ነው፡፡ ይህ የፖለቲካ ተቋምም ህዝባችንን በትጋት እና በህግ በታቀፈ አካሄድ እንዲያገለግል ተደርጎ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባው ህገ መንግስቱ በጥብቅ ያሳስባል፡፡ በመቀጠልም ህገ መንግስቱ በአንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ህዝቦች የሃገራችን ኢትዮጵያ ሉአላዊ ስልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ረጋግጣል፡፡ ከዚያም በመቀጠል በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 1 ከህገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን ማንኛውም የውስጥ ደንብም ይሁን መመሪያ ውድቅ መሆን ያለበት መሆኑን በማስገንዘብ ያሰፈረ ሲሆን በአንቀፅ 9 ንዑስ አንቀፅ 2 ደግሞ ማንኛውም የመንግስት አካልም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት ለህገ መንግስቱ ተገዢ መሆን እንዳለበት በጥብቅ ያስገነዝባል፡፡