Tuesday, April 30, 2013

“የተዘነጉት እስረኞች” እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ





ላለፉት አራት ዓመታት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቅዳሜ እና እሁድ የሄደ ሰው ወጣቷን ናርዶስን ሳያገኝ አይመለስም፡፡ ናርዶስ ገና የ20 ዓመት ወጣትእና በኪያሜድ የመጀመሪያ ዓመት የነርሲንግ ተማሪ ናት፡፡ ናርዶስ ዘሪሁን በየሳምንቱ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትመላለሰው በ‹‹አሸባሪነት›› ‹በእነብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ› ከተከሰሱት 36 ሰዎች መካከል ዕድሜ ልክ የተፈረደባትን እናቷን ልትጎበኝ ነው፡፡ እነዚህ እስረኞች ሚያዝያ 16/2001 አመሻሹ 12 ሰዓት አካባቢ ነበር ሁሉም በያሉበት በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡ እኛም 4ኛ ዓመታቸውን ለማሰብ ተሰባስበን ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተለይ እማዋይሽ ዓለሙን ለመጠየቅ ሄደን ነበር፡፡ እንደተለመደው ናርዶስንም አገኘናት እና ብዙ ነገሮችን አጫወተችን፡፡“የተዘነጉት እስረኞች” እና የተዘነጋው የቤተሰቦቻቸው ስቃይ
ናርዶስ ትረካዋን የጀመረችው እናቷን እና ሌሎችም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሰው የተፈረደባቸውን ሰዎች አያያዝ ነበር፡፡ ‹‹ሳስበው የተረሱ ያህል እየተሰማኝ ነው፤ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ሚዲያዎች ስለነሱ አይደለም እያነሱ ያሉት፡፡በእናቴ ክስ የታሰሩት ከ30 ሰዎች በላይ ናቸው፡፡ አንድ ሰሞን ከይቅርታ ጋር በተያያዘ ስማቸው እየተነሳ ነበር አሁን ግን ሁሉነገር የተረሳ ይመስለኛል›› በማለት የእስሩ ሕመም ለታሳሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ግን የሚረሳ ዓይነት አለመሆኑን ነገረችን፡፡
‹‹ሚያዝያ 16፣ አርብ ቀን ነበር ሁሉም የተያዙት›› በማለት ሲታሰሩ የነበረውን ጠቅላላ ሁኔታ በማስታወስ ትጀምራለች፡፡ ‹‹ለአንድ ሰው የመጡ የማይመስሉ ብዙ ሲቪል የለበሱ እና የፌዴራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች መሳሪያቸውን አቀባብለው ነበር ወደቤት የገቡት፡፡ ስልካችሁን አጥፉ ወደማንም እንዳትደውሉ አሉን፡፡ የብርበራ ማዘዣ ይዘው ነበር፤ ‹ቤት ልንፈትሽ ነው የመጣነው እማዋይሽ ዓለሙ በቁጥጥር ስር ውለሻል› አሏት ቤት ፍተሻው እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ድረስ ቀጥሏል፡፡ ቀኑ አርብ ነበር፤ እናቴ ደግሞ እስከ 12 ሰዓት ትጾም ስለነበር ከሥራ ወደቤት እንደገባች ‹ምግብ ስጡኝ› እያለች እያለ ነበር ፖሊሶች የገቡት ስለዚህ ምግብ ሳትበላ ውላ ነው ወደ እስርቤት የወሰዷት፡፡ ከዚያ በኋላ አራት ወራት ያክል ዓይኗን አላየነውም ነበር፤ ትሙት ትኑር የምናውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ደግነቱ በሌላ ጉዳይ ታስራ በተፈታች ሴት አማካይነት መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ‹አንቺ ደህና ከሆንሽ ሽሮ እና ጎመን ሰርተሸ አስገቢልኝ፤ እኔ ደግሞ ደኅንነቴነን የባናና ማስቲካ ወረቀት እልክልሻለሁ፡፡ ደኅና ካልሆንኩኝ ግን ያ ነገር ይቀራል› ብላ ላከችብኝ፡፡ ከዚያ እኔም ሽሮ እና ጎመን ሠርቼ በመላክ፣ እሷም የባናና ወረቀት በመላክ ደኅንነታችንን የሚገልፅ መልዕክት እንለዋወጥ ነበር፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ባለበት ሰዓት እኛ በሌለንበት ጉዳያቸው ፍርድ ቤት ይታይ ነበር፡፡›› በማለት ጉዳያቸው በኢ ፍትሐዊ መንገድ በመንግሥት እንደተያዘ አጫውታናለች፡፡

Monday, April 29, 2013

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ… (ክፍል ፩) – ከተመስገን ደሳለኝ | Zehabesha Amharic

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ… (ክፍል ፩) – ከተመስገን ደሳለኝ | Zehabesha Amharic

የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) የደቀነብን አደጋዎች! – ክፍል 1

የመለስ መታሰቢያ ተቋም (Foundation) የደቀነብን አደጋዎች! – ክፍል 1

ግጭቱን ማን ለኮሰው?




ቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ… አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈAddis Ababa, Ethiopia 2005 protest ቁልቁል ወርዶ ..ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ።…በዚህ ቅፅበት አንዲት ነጭ ቶዮታ ፒካፕ (ታርጋ የሌላት ወይም ያለጠፈች) ከሱማሌ ተራ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየከነፈች ከመጣች በኋላ < በላይ ተክሉ ኬክ> ቤትን አለፍ ብላ ቆመች። ከሹፌሩ ጎን ሲቪል የለበሰና ኮፍያ ያጠለቀ ሰው የተቀመጠ ሲሆን ከመኪናው ጋር ከተገጠመው ሬዲዮ መገናኛ በተጨማሪ ሁለት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ይዟል።… 25 ወጠምሻዎች፣ ሁሉም ረዘም- ወፈር ያሉ ዱላዎችን፣ ገሚሶቹ ደግሞ ገጀራ እንደጨበጡ እንዲሁም ከመካከላቸው ሁለቱ አነስተኛ ጀሪካን እንደያዙ…ከመኪናዋ ዘለው ወረዱ። ሁሉም የተቀዳደ ተመሳሳይ ድሪቶ አጥልቀዋል፤ « አደገኛ ቦዘኔ» መሆናቸው ነው። ነገር ግን « ሆን ተብሎ » የተዘጋጀ ድሪቶ እንደሆነ የሚያሳብቀው ….በግልፅ የሚታየው የሁሉም ፈርጣማ ጡንቻ ከጥሩ እንክብካቤ ጋር በስፖርት የዳበረና ወታደራዊ አቋም እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ መሆኑ ነበር።

Friday, April 26, 2013

ኣይጋ – ለአውራምባ አቀበለው – አውራምባ ደግሞ- ለትግራይ ኦንላይን!





ዑደቱ እንዲህ ይዞራል፡፡ ተረቱም እንዲህ ተለውጧል! «ትንሽ አሻሮ ይዘህ ከቆሎ ተጠጋ»፡፡ ወያኔን  ትንሽ እምት! እምት!  ትንሽ ቦጨቅ፥ ቦጨቅ፡፡ ከዚያም ተቃዋሚ መባል፡፡ ከተቃውሞው አምባ አድብቶ ገብቶ ደግሞ ቀበሮ  መሆን፡፡ ከዚያም እይጋ እየቆነጸለ የሚያወጣውን ትንሽ ለወጥ አድርጎ በአውራምባ ታይምስ ላይ ማውጣት፡፡ ገረብ ገረብ ትግራይ! መቃብረ አምሃራይን በተዘዋዋሪ አጠይሞ ማጮኽ፡፡
ከባለቤቴ ጋር ሆነን የአውራምባውን ዳዊት ከበደን የአከረባበት ስልት አንስተን ስንጨዋዋት ! እኔ ዳዊትን የገመገምኩባቸውን ነጥቦች ባለቤቴ በከፊል ተቀብሎ፣ ላይሆኑ ይችላሉ ያላቸውንም ነጥቦች አነሳሳልኝ፡፡ ዳዊት ወያኔ ሊሆን አይችልም አለኝ መሬት በደንብ ቆንጥጦ፡፡ ለምን አይሆንም አልኩት? ከቅንጅት መሪዎች ጋር አብሮ ሁለት አመት ታስሮ አለኝ፡፡ ብዙ ጊዜ ዞምቢዎች ያሞኙሃል አልኩት፡፡ የባለቤቴን የዋህነቱን ስለማቅ!
የዶክተር አረጋዊ በርሄን መጽሃፍ አንብበህ የለ? ወያኔ እኮ የጦርነት ልብሳቸውን አስወልቆ፣ ኮበሌዎቹን የመነኩሴ ልብስ አስለብሶ ዋልድባ የከተተ መንግሥት ነው፡፡ ለዓላማቸው ቋርፍ እየበሉ፣ ቀኑ ሲደርስ ዋልድባን ያሳረሱት እኮ የወያኔ መነኩሴዎች ናቸው፡፡ ይህ እንዴት ተዘነጋህ ? ለዚያውም ገዳም ውስጥ ሃያ አንድ አመት ችሎ መክረም የሚችሉ ናቸው እንኳን ቃሊቲ ሁለት ዓመት አልኩት፡፡ ለዓላማህ ስትል ቃሊቲ ሁለት ዓመት ብትታሰር ምንድነው? ለዚያውም ጥሩ ጥሩ «ኡፋ» እየጠለፍክ አልኩት፡፡

Wednesday, April 24, 2013

የህወሀት ደህንነቶችን ጤና የነሳው የፌስቡክ ጦማር



በህወሀት/ኢህአዴግ ውስጥ መግባባት ጠፍቷል፣ የወያኔ ቁንጮዎች ወዴት እንደሚሄዱ አያውቁም። እንደው በደፈናው “የመለስ ዜናዊ ራዕይ” ይበሉ እንጂ ራዕዩን እነርሱም አያውቁትም። ካድሬውም ሹማምንቱም እርስ በርስ ተናንቋል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ሁኔታቸውን ህዝብ እንዳያውቅባቸው እያደረጉ ያሉት ጥረት እምብዛም የሰራ አይመስልም። የሙስሊሞች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው፣ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ ህዝቡን ከዳር እስከዳር አስተባብሯል/ቀስቅሷል፣ ምርጫውን ምርጫ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አለማቀፉ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጫና ፈጥረዋል። ለዚህም ይመስላል የወያኔ የደህንነት ሹሞች የሀሰት ዜናዎችን በፌስቡክ እያሰራጩ ፋታ ለማግኘት የሚጣጣሩት። ከዚህ በታች አብረሃ ደስታ ከመቀሌ በፌስቡክ የለቀቀውን ጦማር፣ የህወሃት/ኢህአዴግን ወቅታዊ አቋቋም እንደወረደ አቅርበነዋል።

በህወሓት የጉባኤ ኣጀንዳ ዙርያ ስብሰባ ሊጠራ ነው

አብረሃ ደስታ፣ ከመቀሌ
ከኢህኣዴግ ጉባኤ በኋላ መሪዎቻችን (ከበፊቱ ብሶባቸው) መግባባት ኣቅቷቸዋል። በፌደራል ደረጃ የሚደረጉ ስብሰባዎች ያለ ዉጤት ይጠናቀቃሉ። ለምን ኣይግባቡም? (‘ቀሽምEthiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekele ጥያቄ’)። የሚያግባባ ነጥብ የላቸውማ። ድሮ (ከ‘ባለራእዩ መሪ’ ዕረፍት በፊት) ሁሉም ነገር እሳቸው ይሰሩት ስለነበር) በመሪያቸው ነበር ‘የሚግባቡት’ (አብረው የሚጓዙ)። በሰው ‘ይግባባሉ’ (ሌላ ሊያግባባቸው የሚችል ሓሳብ ወይ መርህ አልነበራቸውም፣ የላቸውም)። አሁን ታድያ እንዴት ይግባቡ?
‘ባለራእዩ’ ሰውዬ መመርያ ይሰጣል፣ ‘ፖሊሲ ነው ተግብሩት’ ይላቸዋል፣ እነሱም እሱ የተናገረውን ‘ቃል’ እየደገሙ (ከላይ እስከ ታች) ይዘምራሉ። ስሕተት መሆኑ (ሊተገበር የማይችል መሆኑ) ሲረዱ ‘ስሕተቱ ያለው አፈፃፀም ላይ ነው’ ብለው ራሳቸው ያፅናናሉ። ህዝቡ በማይፈፀሙ ፖሊሲዎች ተስፋ እንዳይቆርጥ መሪዎቻችን ሁሌ ስለ አዲስ ፖሊሲ ወይ አሰራር ይሰብካሉ። ሁሌ ስለ ‘አዲስ ኣሰራር’ ወይ ዕቅድ ሲወራልን ለውጥ የመጣ ያህል እንዲሰማን ለማድረግ ያህል ነው።

Sunday, April 21, 2013

ኢህአዲግ (ወያኔ) የአባይን ግድብ የቦንድ ሽያጭ በባህር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መተንኮሻ አድርጎታል




ዛሬ እነሆ በኖርዌይ እንዲህ ሆነ
Ethiopians in Norway protest, April 2013

ከኖርዌይ ከተሞች ውስጥ በደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ስታቫንገር ከተማ ዛሬ ሚያዝያ 12/2005 ዓም በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ መብራት በተገኙበት ለአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ የተዘጋጀው ዝግጅት ከኦስሎ ከ ስምንት ሰዓታት በላይ በአውቶቡስ ተጉዘው በስብሰባው በተገኙ ኢትዮጵያውያን በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱ ተሰርዞ አምባሳደሯ በፖሊስ ቦታውን ለቀው  እንዲሄዱ ተመክረው አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል።