Thursday, February 28, 2013

የፍርሃትና ስም ማጥፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ

2011፡ የሙስና አገዛዝ፤ ፍርሃትና ሰም ማጥፋት

Ethiopia The Politics of Fear in the police statesበዲሴምበር 2011 ‹‹ኢትዮጵያ የደም ሃገር ወይም የንቅዘት (ሙስና) ሃገር›› በሚል ርእስ የኢትዮጵያን ሁለት ገጽታ በማመዛዘን አንድ ጦማር አስነብቤ ነበር፡፡ በዚያን ወቅት ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል በተባለው ተቋም ተቀምጦ የነበረው ገጽታ ያሳየው ኢትዮጵያ ለም መሬቶች በተንኮል በተጠቀለለ ስውር ደባ እየተቸበቸቡ እንደነበር ነው፡፡በዘገባው ላይ ተቋሙ ለኢትዮጵያ ያሰፈረው ነጥብ (10 ከሙስና የፀዳ ማለት ሲሆን 0 ደግም በሙስና ንቅዘት ያጨማለቀው ማለት ነው) ኢትዮጵያ 2.7 ነበር ያገኘቸው፡፡ በሙሰና ከታወቁት የኣለም ሃገሮች ዋነኛዋ ኢትዮጵያ ናት ይል ነበር::  የግሎባል ፊናንሻል አንተግሪት ድርጅት ደግሞ ባለፉት ፲ ኣመታት ከኢትዮጵያ 11.7 ብልዖን  ያሜርካን ብር በሀገወጥ መንገድ ከኣገሪቷ ወጥቶአል ብሎ ዘገቦ ነበር::
ባልፈው ኣመት: አሁንም በስላጣን ላይ ያለው ገዢ ኣስተዳደር ኢትዮጵያን በሽብርተኞች ማነቆ ውስጥ ተወጥራ እንዳለች ሃገር አድርጎ ለማቅረብ ባወጣው የልመናና የገንዘብ መቧገቻ እቅዱ ባለሶስት ክፍል የፕሮፓጋንዳ የቅጥፈት ታሪክ ‹‹አኬልዳማ›› በማለት (ወይም የደም መሬት በማለት ከአክትስ 1፡19 በመዋስ፤ የአስቆሮቱ ይሁዳ ክርስቶስን ክዶ በመሸጥ ባገኘው ገንዘብ የተገዛ መሬት) ከልብ ወለድ የማይሪቅ ትርኢት ለሕዝብ ኣቅርቦ ነበር፡፡ ይህም ትርኢት በአትዮጵያና በኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሰዎች በሚታገዝና በሃገርም ውስጥ ባሉት የሚደገፍ የሽብር ተግባር አምባ አድርጎ ለማሳመን የተሰራ ነው፡፡ አኬልዳማ ሲጀምር በኢትዮጵያ ውስጥ ሊከሰት የሚችል በማለት የደም ጎርፍ መምጣት እንደሚችልና፤ ሸብር ዓለምን በማጥፋት ላይ ነው፡፡ ‹‹አኬልዳማ›› ሲተረት: “ሽብርተኝነት የቆምንበትን መሬት እያነቃነቀ፤ ዕለታዊ እንቅስቃሴያችንንም እየገታ መሆኑን በቅጥፈታዊ ፈጠራ ለማሳየት የቀረበ ትርኢት፡፡ አሁን እየተናገርኩ ያለሁት ስለዓለም አቀፉ ሥብርተኝነት አይደለም፡፡ እኔ እያልኩ ያለሁት በገዢው መንግስት ለኢትዮጵያ የተቀመጠውን የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳና በዚያም ውስጥ ስለተካተተው አኬልዳማ ተብሎ ስለተቀፈቀፈው፤ ሸብርተኝነት ለኢትዮጵያ አስጊና አሳሳቢ ችግር ነው…… ስለተባለው ነው፡፡”

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል

 “አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ

ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።

Wednesday, February 27, 2013

ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት



የዘረኛው የህውሃት ስርዓት በነፃ አውጪ ስም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም ከዛም በፊት የሚከተለው የተሳሳተ ሃገር መገነጣጠሉንና ቤሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ መስጠቱንtplf rotten apple መመልከት የተለመደና የቀን ከሌት ክንውናቸው መሆኑ በሃይል ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሚታይ እውነታ ነው፡፡
ከምስረታው ጀምሮ ይዞት የተነሳው የኢትዮጲያን ሉዋላዊነት የማፍረስና የመበተን አላማውን መተግበር የጀመረው የሻቢያ አሽከር በመሆን ለሃገር አንድነትና ክብር ዘብ የቆመውን የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት በመውጋት ሃገራችን ያለ ባህር በር እንድትቀርና በኢትዮጲያዊነት የታነፀውን ዘመናዊ የወታደር ሃይል በትኖ በምትኩ የአንድ ብሄር የበላይነት የሚታይበት፣ ቤሄራዊ ስሜት የሌለው፣ በአለቆቹ ከመታዘዝ ውጪ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት ያልዘለቀው ጀሌዎቻቸውን በህዝብ ላይ አንግሰው ያሻቸውን ሲገሉ፣ የሻቸውን ሲያስሩ እንሆ አሁን ያለንበት ደርሰናል፡፡
በመሰረቱ ይህ እኩይ ስርዓት(ቡድን) በኢትዮጲያዊነት ላይ ካለው የመረረ ጥላቻ የተነሳ አብረው የመሰረቱትን ግን በኢትዮጲያዊነት ላይ ፅኑ አቋም የነበራቸውን ባልንጀሮቻቸውን ሳይቀር እያስወገዱና እያባረሩ በምግባር የሚመቻቸውን በተለይ በህዝብና በሃገር ላይ የጠለቀ ጥላቻ ያላቸውን አስከትለው የጥፋት ዘመናቸውን ቀጥለውበታል፡፡
በተለይ የመንግስት ስልጣን ከያዙ በሗላ ከስልጣን በተጨማሪ በገቢ እራሳቸውን ለማጠናከር ከኢትዮጲያ ህዝብ በዘረፉት ሃብትና ንብረት በትግራይ ህዝብ ስም ባቋቋሙት ኢፈርት ሃገሪቱን ጫፍ እስከ ጫፍ በመቆጣጠር የንግዱን መስክ በበላይነት በመያዝ ገቢና ወጪው የማይታወቅ ትልቅ የሃብት ምንጭ በመፍጠር የአገሪቱን የትኛውም የንግድ እንቅስቃሴ በበላይነት ይዘው ነግሰውበታል፡፡

የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?


From Borkena blog/ ቦርከና
ሰሞኑን የዞን 9 አባላት የብሎጋቸውን በኢትዮጵያ መከልከል ተከትሎ ከክፈቱልን ያለፈ ፤ መሰረታዊ ሊባል የሚችል ዘመቻ በማህበራዊ ድህረ ገጾች ጀምረዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ምላሽ መስጠቱ እና መጠቀም የሚቻለውን መድረክ ተጠቅሞ የችግሩን ጥልቀት ለማመላከት መሞከር ጥሩ ነው። ነገር ግን የመጻፍ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እየተጠየቁ ያሉትን ቡድኖች(‘ፎርማሊ’ ካወራን መንግስት ናቸው -ያውም ፈላጭ ቆራጪ) ባህሪ  ግምት ውስጥ በማስገባት፤ ዘመቻው እነዚሁ ቡድኖች አምነትውበት በማናለብኝነት የወሰዱትን ርምጃ ከማስቀየር ይልቅ በስነ ልቦናቸው ለተቀረጸው የትምክህት እና የበላይነት አስተሳሰብ ሃሴት የሚሰጥ ሆኖ ስለተሰማኝ ለነሱ ትምክህት ሃሴት ላለማዋጣት ስል በዚህ በዘመቻ አልተሳተፉኩም።
እንኳንስ የመናገር ነጻነት አይደለም ለእምነት ነጻነት ጀርባቸውን ሰጥተው የክስርቲያኑን የእምነት ተቋማት በቁጥጥር ስር አድርገው ሙስሊሙንም እንዲሁ እምነቱን ለመንጠቅ ቤት ለቤት ጭምር አሰሳ የገቡ ሰዎች ናቸው፡፡ የመናገር እና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ጋር በእጂጉ የተቆራኘ  የጋዜጣ ህትመት ማስቆም ሳያንሳቸው ዜጎችን –ያውም ኩሩ ሀገር ወዳድ ዜጎችን በሽብረተኛነት በመክሰስ ፣ብዙ እንግልት በማድረስ እና ክብራቸውን ጭምር ለማዋረድ በመሞከር ሌሌች ዜጎች የዜግነት ክብር እና ነጻነት  ጥያቄ ቅብጠት እና በህይወት መቀለድ እንዲመስላቸው በማድረግ የባርነትን እስተሳሰብ በደህንነት ተቋማት ፣በህግ ተቋማት እንዲሁም የማህበራዊ ድንዝዝነት በሚያስፋፉ ሌሎች ልማዶች የሚስፋፉበትን መንገድ በስውርም በግልጽም በማበረታታት  የባርነትን መስረት ለማጽናት ሌት ከቀን የሚሰሩ ለመሆናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ያለ ብዙ ምርምር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም!



ትላንት የተናገሩትን ዛሬ፤ ዛሬ የተናገሩትን ነገ የማይደግሙ ከሀዲ አንባገነን እና ዘረኛ ቡድኖች የስልጣን ኮረቻ በሀይል ከተፈናጠቱበት እለት ጀምሮ የተለያዩ የማወናበጃ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ የበርካታ ንጹሀን ዜጎችን ህይወት ቀጥፈዋል አስቀጥፈዋል፡፡እንኳን እንደጠላት የሚቆጥሩትንና በመርሃ ግብራቸው ነድፈው መጥፋት አለበት ብለው የፈረጁትን ህዝብ ቀርቶ አርነት እናወጣሀለን እያሉ ክእናንተ በመፈጠራችን ኮራንባችሁ የሚሏቸውን የትግራይን ንጹሀን ዜጎች ሳይቀር  የራሳቸውን የስልጣን ዕድሜ ለማራዘም ውድ ህይወታቸውን እንዲገብሩ አድርገዋል፡፡ የሀውዚንን ጭፍጨፋ አቀናብረዋል፣በ1991ዓ.ም በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በተደረገው  ጦርነት ከ70000 በላይ የጠርነቱ ሰለባ ሁነዋል፡፡አልሻባብን ለመደምስስ በሚል በሶማሊያ በረሃ የረገፉትን ወታደሮች ቤት ይቁጠራቸው፡፡ስልጣን ለወያኔ ከምንም ነገር በላይ ነው፡፡ ስልጣን ከሉአላዊነት፣ከባህር በር ፣ከሀገርና ከህዝብ እንደሚበልጥባቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ የወሰዷቸው እርምጃዎች ማሳያ ናቸው፡፡የገንዛ ሀገሩን ቆርሶ ለሱዳን የሚሰጥ፣የባህርበር አያስፈልገኝም የአሰብን ወደብ ውሰዱት፣ኤርትራ እንድትገነጠል ፈቅጃለሁና እውቅና ስጡልኝ እባካችሁ እያለ የአለም መንግትታትን  የተማጸነ፣የገንዛ ዞጎቹን አፈናቅሎ ለውጭ ባለ ሀብቶች መሬታቸውን የሚሰጥ፤የሀገሪቱን ሀብት ለተደራጁ ወንበዴወች የሚያስዘርፍና የሚዘርፍ፤ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችን አጥፍቼ  ታላቋን ትግራይን እመሰርታለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ አንባገነን እንዴት ያለ ሀገራዊ ራዕይ ነው የሚኖረው፡፡
ዘረኛው መንግስት በተለያዩ ጊዜያት እንዱን ብሄር በሌላው ብሄር ላይ በማነሳሳት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለው ሀብትና ንብረታቸውን ተዘርፈው ለከፍተኛ ችግር ሲዳረጉ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ ለእልፈት ተዳርገዋል፡፡የፖለቲካ ፓርቲዎችና ጋዜጠኞችን  በሽብር ስም እያሰረ ንጹሀንን ሲያሸብር ቆይቷል፡፡በርካታ ፓርቲዎች በሰርጎ ገብ ሰላዮች የተነሳ ይዘውት የተነሱትን አላማ እና  የህዝብ አደራ እዳር ሳያደርሱ በጅምር ቀርተዋል፡፡በወያኔ መሰሪ ተንኮል በተቀነባበረ ሴራ ጦርነት ውስጥ ያልገባ ክልልና ብሄር ባይገኝም ውጤቱ እንደሚፈልጉት ስላልሆነላቸው እና የኢትዮጵያ ህዝቦችም ባላቸው አርቆ አስተዋይነትና ረጅም ጊዜ በሰላም አብሮ የመኖር ባህሉ በመታገዝ  የፕሮፖጋንዳቸው ሰለባ ባለመሆናቸው ለወያኔዎች ትልቅ ራስ ምታት ጥሮባቸዋል፡፡እስካሁን ሲጫወትበት የነበረውን ካርድም እንዲቀይርም ተገዷል፡፡ አዲሱ የመጫወቻ ካርድም ከብሄር ግጭት ወደ ሐይማኖታዊ ግጭት ለማሸጋገርም የሚያስችለውን “ጀሀዳዊ ሀረካት”የተሰኘ ዘጋቢ ፊልም በመስራት ከ1500 አመት በላይ አብረው የኖሩትን ሁለቱን ታላላቅ እምነቶች ማለቂያ ወደሌለው ጦረነት በመማገድ የስልጣን ጊዜውን ለማራዘም ቢምክርም እናንተ ከመጣችሁት ገና 21 ዓመታችሁ ነው እኛ ደግም ለረጅም ጊዜ  በፍቅር አብረን ኑረናል፤  የጋራ ጠላታችን ዘረኛው ወያኔ ነው፡፡እኛ ከእነሱ እንሻላለን አንለያይም እያሉ በየአደባባዮ አንገት ላንገት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቁጭታቸውን ሲገልጹ መመልከት የተለመደ ተግባር ነው፡፡ሰሞኑን ለኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም ሙኒክ ላይ የታየውም ህብረት የዚሁ አካል ነው፡፡
እንዴት እንደ  ኢትዮጵያ ያለች ታላቅ ሀገር እና እንደ ኢትዮጵያውያን ያሉ ቀደምት ህዝቦች እንደ ወያኔ ባሉ ትንሽ ሰዎች ይገዛሉ?እንዴት የአለም ማህበረሰብ በሀሰት የወያኔ ፕሮፖጋንዳ ሲታለል ይኖራል?እስከመቼ ብቻቸውን በምርጫ ተወዳድረው አሸነፍን እያሉ ሲያላግጡ ይኖራሉ? ወያኔዎችስ በቀጣይ ምን የማደናገሪያ ስልት ያመጡ ይሆን? እኔ በበኩሌ በቃ ብያለሁ፡፡ ወያኔ ራዕይ የለውም ኑሮትም አያውቅም፤ ወደፊትም አይኖረውም፡፡የወያኔ  ሀገር እና ህዝብ የማውደም ቅዠት እንጂ ሀገራዊ ራዕይ ብሎ ነገር አያውቅም፡፡በጋራ ጠላታችን ላይ በጋራ እንነሳ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

Monday, February 25, 2013

ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ (ክፍል ሁለት)



ድምፃችን ይሰማ
አቶ ሽመልስ ኡስታዝ አቡበከርን ‹‹አጥፍቶ ጠፊ›› ብለው መዝለፋቸውን ሰምተዋል?
‹‹መንግስት መፅሐፍ ቅዱስንና ቁርአንን ጠቅሶ ክርክር ውስጥ ሊገባ አይችልም፡፡››
የአመቱ ምርጥ ቀልድ
አቶ ሽመልስ ኢቲቪ ከዶኩመንታሪው በኋላ በስህተት ባስተላለፈው የቪዲዮ ፊልም ውስጥ የኮሚቴያችን ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በካቴና ተጠፍሮ መታየቱን አስመልክተው በሰጡት ምላሽ ደግሞ ክፋት የተመላበት ንግግር ተናግረዋል፡፡ ‹‹ራሴን አጥፍቼ እጠፋለሁ፣ ወደ ጥፋትና ወደ ሽብር ሥራ እገባለው ያለ ሰው ለጥንቃቄ ተግባር ሲባል በካቴና እጁን እንዲታሰር ማድረግ የየትኛውንም ህግ የሚጥስ አይደለም›› ብለዋል፡፡ ይሄ ወንጀል ነው! አንድን ነጽህና የሚልዮኖች ውክልና ያለው ዜጋ ‹‹አጥፍቶ ጠፊ›› ሲሉ መሳደብ ለአንድ ባለስልጣን አሳፋሪ ነው፡፡ ኡስታዛችን አንድም ቀን እንኳን እንዲህ ያለ ንግግር ተናግሮ አያውቅም፡፡ እጅግ ሰላማዊና ሰላምን ሲሰብክ የቆየ ሰው ነው፡፡ ሁልጊዜም ሚዛናዊ አስተሳሰብ ያለው አስተዋይ መሪያችን ነው፡፡ መንግስት መሪዎቻችንን ለማሰር ባሰበበት ወቅት እንኳ እኛ ብንታሰር ከስሜታዊነት ራቁ! ሲል ነው ህዝበ ሙስሊሙን ቃል ያስገባው፡፡ ይህን ለሚሊዮኖች ተምሳሌት የሆነ ሰው ‹‹አጥፍቶ ጠፊ›› ሲሉ መሳደብ ወንጀል ነው – ምን ያደርጋል! ይህን እንኳ የሚያርም የአስተዳደርም ሆነ የፍትህ ስርአት የለም እንጂ፡፡ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ (ክፍል ሁለት)
አቶ ሽመልስ በቃለ መጠይቃቸው ሌላ ቦታ ላይ የተናገሩት ንግግር ደግሞ መንግስት እስልምናን ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳ መሆኑን የሚያረጋግጥ ይመስላል፡፡ ‹‹በየሲዲው ፀብ ቆስቋሽ ፕሮፓጋንዳዎችን የሚያስፈፅሙት፣ በቲቪ አፍሪካ የተለያዩ ቻናሎችን በመጠቀም የሚያሰራጩት እነዚሁ አክራሪዎችና ሽብርተኞች ናቸው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡ በንግግራቸው ውስጥ እንደምናየው ሁሉንም ነገር በባዶ ከመወንጀል ያለፈ ያቀረቡት ማስረጃም የላቸውም፡፡ ሰላማዊ የእስልምና ትምህርት እየሰጠ የሚገኘው ቲቪ አፍሪካ ለምን ኢላማቸው ሆነ? ህገ መንግስታችን የሃይማኖቶችን ሰበካ የማድረግ መብት አስጠብቆ የለም እንዴ? ይህን መብት በመጠቀም ሁሉም ሀይማኖት ሰበካ እያደረገ አማኞቹን ያስተምራል፡፡ ቲቪ አፍሪካም ያደረገው ይህንኑ ሆኖ ሳለ ጸብ ቀስቃሽ እየተባለ ነው፡፡ ጣቢያው ምንድነው ጥፋቱ? ኢትዮጵያ ምድር ላይ እስልምናን መስበክ ክልክል የሚያደርግ አዲስ ህገ መንግስት ሳናውቀው ወጥቶ ይሆን?
ከአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ ውስጥ እስቲ የሚቀጥለውን ንግግር እንመልከት፡፡ ‹‹መንግስት መፅሐፍ ቅዱስንና ቁርአንን ጠቅሶ ክርክር ውስጥ ሊገባ አይችልም፡፡ ይሄ ምድራዊ መንግስት ነው፡፡ የትኛውንም ሃይማኖት አይደግፍም፡፡ የትኛውንም ሃይማኖት የማይቃወም መንግስት ነው፡፡ አለማዊና ምድራዊ መንግስት ነው፡፡››

ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ



ድምፃችን ይሰማ
በእርግጥ ግለሰቡ የባለስልጣን ግብር አላቸው?
ባሳለፍነው ሳምንት የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ዲኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ኢትዮ ቻናል ከተባለው ጋዜጣ ጋር አንድ ቃለመጠይቅ አድርገው ነበር፡፡ ጋዜጣው የመንግስት ፕሮፓጋንዳ መንዣ መሳሪያ ከሆኑ ‹‹የግል›› ጋዜጣዎች ውስጥ አንዱ እንደመሆኑ ምን አይነት ይዘት ያለው ነገር እንደሚያወጣ ለብዙዎች ድብቅ አይደለም፡፡ ያወጣውም ብዙዎች ከሱ የሚጠብቁትን ፕሮፓጋንዳ አይነት ጽሁፍ ነበር፡፡ ኢቲቪ የፍርድ ቤት ትእዛዝን ጥሶ ባስተላለፈው አሳፋሪ ‹‹ዶኩመንታሪ›› ፊልም የተነሳ የደረሰበትን ውግዘት እና የፕሮፓጋንዳውን መክሸፍ ሊያስተባብሉ ነበር አቶ ሽመልስ ከማል በኢትዮ ቻናሉ ቃለ መጠይቅ ብቅ ያሉት፡፡ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ
ቃለ መጠይቁ ከአንድ ትልቅ የመንግስት ባለስልጣን እንደመምጣቱ ጨዋነትን የተላበሰና ደረጃውን የጠበቀ መሆን በተገባው ነበር፡፡ ያ ግን አልሆነም፡፡ አስገራሚ በሚባል ደረጃ ከቃላት አጠቃቀሙ ጀምሮ በሁለመናው ዝቅ ያለ እና የወረደ ነበር፡፡ ቃላቶቹ ተራና ‹‹የመንደር›› ከመሆናቸውም ሌላ ግለሰቡ ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ የሻቸውን የሚናገሩ እንደሆኑ ያሳብቁ ነበር፡፡ አንድ የመንግስት ባለስልጣን የሚናገራቸውን ነገሮች የኋላ ውጤት ያለምንም ማገናዘብ እንዳመጣለት መናገሩ አገራችን ውስጥ በመንግስት እና በግለሰብ መካከል ያለው ለውጥ ከነጭራሹ እየጠፋ መምጣቱን እንድንገነዘብ ያደርገናል፡፡
ግለሰቡ በረዥሙ ቃለ መጠይቃቸው በርካታ ሀሳቦችን አንስተዋል፡፡ ሁሉንም እዚህ እያነሳን ልንነጋገርባቸው ባንችልም የተወሰኑትን ብቻ ጠቀስ ጠቀስ እያደረግን ምልከታችንን እንሰጥባቸዋለን፡፡