Monday, December 17, 2012

ኢትዮጵያ ዘመናዊ የህፃናት የውጭ ንግድ





የጉዲፈቻ ታሪክ በኢትዮጵያ በባህላዊ መንገድ ሲደረግ የቆየ ነው መቼ 
እንደተጀመረ በእርግጠኝነት ለማወቅ ባይቻልም በ18 ክፍለ ዘመን በኦሮሞ 
ብሔረሰብ እንደተጀመረ ይታሰባል። ጉዲፈቻ የሚለው ቃል የመጣው ከኦሮሚኛ 
ቋንቋ ሲሆን ትርጓሜውም ተፈጥሮዓዊ የወላጅነትና የልጅነት የሥጋ ዝምድና 
ሳይኖር ከሌላ ሰው አብራክ የተወለደን ልጅ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ጥቅሙን 
ጠብቆ እንደ አብራክ ክፋይ ልጅ ማሳደግ ማለት ነው። በኢትዮጵያ የጉዲፈቻ 
ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1952 ዓ.ም በወጣው የፍትሐብሔር ሕግ ማዕቀፍ 
ተሰጥቶታል ይህም ሕግ የሕፃኑን መብት የሚያስጠብቅ ሆኖ የተዘጋጀ ነው።

Monday, November 26, 2012

የሰማዕቱ የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ለባቡር ሀዲድ ግንባታ ሲባል ይፈርሳል መባሉ ከፍተኛ ህዝባዊ ቁጣ ቀሰቀስ


ኢሳት ዜና:-መንግስት በበኩሉ  ሐውልቱ ለደህንነቱ ሲል ከተነሳ በሁዋላ ወደነበረበት ስፍራ ይመለሳል እያለ ነው።
በአዲስ አበባ ውስጥ ሊሠራ በታቀደ የ ከተማ ውስጥ የባቡር  ሀዲድ ሥራ ምክንያት  የዓፄ ምኒልክና የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ሊፈርሱ የመቻላቸው ወሬ  አስቀድሞ የሾለከው ፤ለምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ቅርበት ካላቸው  ምንጮች  ነው።
እነዚህ የዘርፉ ሙያተኞች በ አምስት ዓመቱ የልማትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መሰረት በ አዲስ አበባ ውስጥ ሊዘረጋ የታሰበው የባቡር ሀዲድ ፕላን  የዳጋማዊ አፄ ምኒልክንና የ አቡነ ጴጥሮስን ሐውልት እንደሚነካ በመጥቀስ፤ በተለይ የጣሊያንን ወረራ አልባርክም በማለታቸው ሳቢያ በመትረየስ ተደብድበው የተገደሉት የ አቡነ-ጴጥሮስ  ሐውልት ሙሉ በሙሉ እንደሚፈርስ ተናግረዋል። ዜናውን የሰሙ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያንም በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ተቃውሟቸውን ማሰማት ጀምረዋል።

የአሻንጉሊቱ “ፍርድ ቤት” ራሱን እንደገና አዋረደ!



የወያኔ አገዛዝ ከፍርድ ቤትት ወደ ተራ የፖለቲካ ማጥቂያ መሳሪያነት የለወጣቸዉ የኢትዮጵያ ፍርደ ቤቶች የዕለት ከዕለት ዉርደት አሁንም እነደቀጠለ ነዉ። ሃያ አመት ሙሉ አገዛዙ የወነጀላቸዉነ እየኮነነና አገዛዙ አሸባሪ ያላቸዉን በሽብርተኝነት ፈርጆ አስራትና የሞት ፍርድ ሲፈርድ የከረመዉ የወያኔዉ ፍርድ ቤት ከሰሞኑ ሙሉ ኃይሉን ወደ ኦሮሞ ህዝብ በማዞር የኦርሞ ፌዴራሊስት ዲሞክራቲክ ንቅናቄ (ኦፈሰዴን)ና  የኦሮሞ ህዝብ ኮንግሬስ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አካል አባል  የሆኑትን አቶ በቀለ ገርባንና አቶ ኦብላና ሌሊሳን ኦነግን ትረዳላችሁ የሚል ሰንካላ ምክንያት ፈጥሮ ወነጀለኛ አድርጓቸዋ ል። 

የትግራይ ህዝብን ማታለል ይብቃ! በቃ!



በትግራዩ ህዝባችን ስም የሚደረገው ንግድ አሁንም ከ21 የግፍና የከፋፍለህ ግዛ አመታት በኋላ ተባብሶ እንደቀጠለ ነው።ዘረኛውየወያኔ ቡድን ህወአት “እውነት እውነት እላችኋለሁ መለስ ከመሞቱ በፊት ለትግራይ ህዝብ ያስቀመጠው ጣፋጭ ከረሚላ እና ዝም በሉ” ሲሉ ይደመጣሉ::
የትግራይ ህዝብ እንደ ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ የስርአቱ የስቃይ፣ የሰቆቃ፣ የስደት፣ የግድያና የእስራት ገፈት ቀማሽ ነው። ከጥቂት የሕወአት ጎጅሌዎች በስተቀር! ታዲያ ይህንን እውነት በጠራራ ጸሃይ ላይ በህወአት/ወያኔ የጨለማ ዘመን የሚኖረውን ምስኪኑን የትግራይ ህዝብ ለመካድ እና እንደ ህጻን ልጅ የሚጣፍጥ ከረሚላ አዘጋጅተንልሃል እና ስለዲሞክራሲ ስለነጻነት አትናገር አትጠይቅ ዝም በል አታልቅስ በሚል የማታለል ስራቸውን አሁንም በማደስና ተግባራዊ ለማድረግ በአምባገነኑ የሟቹ ባለቤት አዜብ መስፍን አማካኝነት የትግራይ ህዝብን ለመስበክ ያስባሉ።

Sunday, November 11, 2012

34 ፓርቲዎች በ2ዐዐ5 ዓም በሚካሄደው ምርጫ ለምርጫ ቦርድ ያቀረቡት ጥያቄ


                                                                                                                ጥቅምት 29 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- ጥቅምት 15 ቀን 2ዐዐ5 ዓም በአዳማ ከተማ ቦርዱ ‹‹በ2ዐዐ5 ዓም በሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ አፈፃፀም
የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ›› ላይ ከፖለቲካ ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባአደረገው ምክክር ፕሮግራም ተገኝተው
ፔቲሽን ከፈረሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረበ ጥያቄ ስለማቅረብ፣

Ethiopia woman tells of sex slavery in Saudi Arabia



 | 11 November 2012 |
ADDIS ABABA: An Ethiopia woman revealed that she was the victim of sex slavery after she attempted to find work as a domestic worker in Saudi Arabia.
(Picture: Ethiopian women face massive hardships, including sexual violence in Saudi Arabia.)
For H, who asked that her identity remain anonymous, her ordeal began after she took a boat to

‹‹ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ›› እስክንድር ነጋ


(በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ) ከነገ በስቲያ (ማክሰኞ ህዳር አራት) በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት የእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ይሰየማል፡፡
በትላንትናው ዕለት የክስ ቻርጅና መንግስት እወርሳቸዋለሁ ያላቸውን የእስክንድር ሁለት ቤቶች ካርታ የተያያዙበት መጥሪያ ደርሶታል፡፡ (በነገራችን ላይ መንግስት ሊወስዳቸው ከተዘጋጁት ቤቶች አንዱ በእናቱ ስም ያለ ሲሆን የዛሬ ዓመት አካባቢ ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል የቤቱን ስም ለማዞር ፈልጋ ‹‹ካርታው የለም›› በሚል አንዴ ቀበሌ፣ ሌላ ጊዜ ክፍለ ከተማ፣ ቀጥሎ አዲስ አበባ መስተዳደር ስትመላለስ ከርማ ሊገኝ ስላልቻለ ሰልችቷት ትታው ነበር፡፡ ትላንት ግን ዓቃቢ ህግ ከክስ ቻርጁ ጋር አያይዞ አቅርቦታል፤ እናም ምንአልባት ያን ግዜ ‹‹ካርታው የለም›› የተባለው ሆነ ተብሎ ተደብቆ ሊሆን ይችላል)