Monday, July 7, 2014

ሕወሓት ሪከርድ በመስበር ቄሱን በሽብር ወንጀል ከሰሰች

ሕወሓት ሪከርድ በመስበር ቄሱን በሽብር ወንጀል ከሰሰች

Abrha Desta

ቀሲስ ብርሃነ ቆባዕ (ከእግሪሓሪባ) በሽብር ተጠርጥረው                                     (ከነ አደይ አልጋነሽ ጋ) ዛሬ ሰኞ ሰኔ 30, 2006 ዓም በፖሊስ                             ታሰሩ። ቀሲስ ብርሃነ እያረሱ እያሉ ነው በአራት ፖሊሶችና                                 ስድስት ምልሻዎች ተከበው ከእርሻ ማሳ ታስረው ፖሊስ ጣብያ                             የገቡ። የነ ቀሺ ብርሃነ ጉዳይ ሽብር የሚል ነው።                                              
ህወሓት የኦርቶዶክስ ሀይማኖት አባት በሽብር በመክሰስ ሪከርድ ሰብራለች።                       ወይስ ቀስን በሽብር የከሰሰች ሌላ ሀገር አለች?
ጉድ ብዪ ሀገሬ ቄሱም፣ ሐጂውም፣ ኡስታዙም አሸባሪ ነው።                                                                                                                                        የሀይማኖት አባቶች አሸባሪ  ተሰኝተው የሚታሰሩበት ዘመን ደርሰናል።

ሚስስ አና ጎሜዝ፣ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ማረጋገጣቸውን ለእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊልያም ሔግ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡

ሚስስ አና ጎሜዝ፣ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ማረጋገጣቸውን ለእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊልያም ሔግ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡




የአውሮፓ ኅብረት ፓርላማ አባል የሆኑትና የኢትዮጵያን መንግሥት በመንቀፍ የሚታወቁት ሚስስ አና ጎሜዝ፣ አቶ አንዳርጋቸው ለኢትዮጵያ ተላልፈው መሰጠታቸውን ማረጋገጣቸውን ለእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊልያም ሔግ በጻፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡

Saturday, July 5, 2014

አንዳርጋቸው ጽጌ፣ የስደተኛው “ሲኦል ምድር ” የመን እና የእኛ ስጋት …

Andargachew Tsige
እግረ መንገድ…
   ሰሞነኛው የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን መታገትና ወደ ኢትዮጵያ የመተላለፍ ዜና ብዙዎችን እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ሆኗል። በአረብ ሃገር የሚገኙን ጨምሮ ኢትዮጵያውያንን በመላ አለም ከአድማስ አድማስ በተቃውሞና በድጋፍ እያነቃነቀም ይገኛል። 
   
   ምሽቱን በፊስ ቡክ በ Facebook ማህበራዊ ገጽ ከተንሸራሸሩት አስተያየቶችና ወቅታዊ መወያያ ርዕሶች መካከል የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታገት ሲሰማ የመን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፋ እንደምትሰጥ ምንጩን ሳይነግረን መረጃ ያቀበለን የአውራምባ ታይምስ አዘጋጅ ዳዊት ከበደ ያስተላለፈው የማወያያ መጠይቅ አስገርሞ አሳዝኖኛል። ዳዊት በዚህ መጠይቁ”…አቶ አንዳርጋቸው የኢትዮጵያ ፖስፖር ይዞ መቆየት የለበትም ትላላችሁ ? ” በማለት ዳዊት ራሱ ለመረጃ ቅርብ እንደሆነ ባለሙያ በአለማችን ነባራዊ ሁኔታ የነጻነት ታጋዮችን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ እያወቀ እንዳላወቀ ሆኖ በለቀቀው በሚመስለኝ መጠይቁ ሊያወያየን    ከጅሏል…

አዜብ መስፍን በጠና ታመዋል፤ የአባዱላ ገመዳ ልጅ አረፈ –


ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ ከፖለቲካው መድረክ እየተገለሉ የመጡት ወ/ሮ አዜብ መስፍን በጠና መታመማቸውን ቅርበት ያላቸው     ታማኝ ምንጮች አስታወቁ። በስኳር ህመምና በደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት አዜብ መስፍን የሰውነት ክብደታቸው እንደቀነሰና የመጎሳቆል ሁኔታ በገጽታቸው እንደሚታይ የጠቆሙት ምንጮቹ ለስኳር በሽታ በየእለቱ ከሚወስዱት መድሃኒት በተጨማሪ ለደም     ግፊትም እንክብሎችን እንደሚወስዱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። አዜብ በመኖሪያቸው አብዛኛውን ቀናት እንደሚያሳልፉ የጠቆሙት     ምንጮቹ በፖለቲካው የደረሰባቸው ኪሳራ ብስጭት ውስጥ እንደከተታቸውና ለበሽታ እንደዳረጋቸው አያይዘው ገለጸዋል።
ቦሌ ከሳይ ኬክ ቤት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ የሚገኘውና አቶ ስዩም መስፍን ለ19ዓመት የኖሩበት እንዲሁም አቶ ሙክታር ከድር     ለሁለት አመት የኖሩበት መኖሪያ ቪላ ውስጥ የሚኖሩት አዜብ መስፍን ከዚህ በተጨማሪ ቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ላይ የሚገኘውን   የቀድሞ የደህንነት ቢሮ ለአዜብ በቢሮ መልክ እንደተሰጣቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል።

Thursday, July 3, 2014

በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ… ኤርትራ እና የመን ተፋጠዋል

 

ኤርትራ የየመንን አየር መንገድ እንደምትዘጋ አሳወቀች (ምክንያቱ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር ነው)
(ኢ.ኤም.ኤፍ) አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰና፣ የመን ውስጥ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ታፍኖ መታሰሩ ብሎም አሁን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ አለመታወቁ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ትራንዚት እያደረገ በነበረበት ወቅት ነበር በየመን ታጣቂዎች ታፍኖ የተወሰደው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን በየቦታው ድምጻቸውን ለማሰማት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው። ከ’ነዚያ ሁሉ ድምጾች ግን ጎልቶ የወጣው በኤርትራ በኩል የተላለፈው መግለጫ ነው። ይህን የኤርትራን መግለጫ መሰረት በማድረግ፤ ሌሎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የራሳችንን ሃሳብ እንሰጣለን።

Tuesday, July 1, 2014

የኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ልጅ በእንግሊዝ መነጋገሪያ ሆኗል

ዴቪድ ካሜሮንን ጨምሮ 19 የእንግሊዝ ጠ/ ሚኒስትሮች የተማሩበት ታዋቂ ኮሌጅ ይገባል “ፖለቲከኛ ለመሆን የግድ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን የለብኝም!…” – ልጁ
“ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን አንጸባራቂ ኮከብ እንደሚሆን አምናለሁ!” – መምህሩ

Ishak Ayiris Eton Scholar

በአገረ እንግሊዝ ያጡ የነጡ ድሆች ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች አንዷ ናት – ኒውሃም፡፡
እዚህ ግባ የሚባል ገቢ የሌላቸውና ከመንግስት በሚያገኙት ድጎማ ከእጅ ወደአፍ ኑሮን የሚገፉ ድሃ ዜጎችና ስደተኞች የከተሙባት የምስራቅ ለንደኗ ኒውሃም፣ ከሰሞኑ የበርካታ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን የዜና ርዕስ ሆናለች፡፡
የድሆች መንደር ኒውሃም፣ በአንድ ልጇ ስሟ ተደጋግሞ ተጠራ። ነገ ከነገ ወዲያ የኒውሃምና የድሃ ነዋሪዎቿ ብቻ ሳይሆን፣ የመላ እንግሊዝ ተስፋ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት የተሰጠው ይህ ልጅ፣ ይስሃቅ አይሪስ ይባላል፡፡ ይስሃቅ አሁን፣ የመንግስት ተረጂ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወላጆቹ የአቶ አባተ እና የወ/ሮ በቀለች ብቻ ሳይሆን የኒውሃም ብሎም የእንግሊዝ ልጅ ነው፡፡ ከሰሞኑ ስለይስሃቅ የተሰማው ወሬ፣ ለወላጆቹ ብቻ አይደለም የምስራችነቱ – ለመላ ኒውሃም ነዋሪዎች ጭምር እንጂ፡፡