ሐራ ዘተዋሕዶ
- ‹‹ዕርቅ ለመፈጸም በማለት ሰዎችን ሲልኩ የነበሩ ቄሶች መሰቀል አለባቸው፡፡››
- ‹‹ታምራት ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ ሊጠይቅ አይችልም፡፡››
- ‹‹[ሲኖዶስ ማቋቋም] በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከግራኝ ከጉዲት የባሰ ትልቅ ወንጀል ነው፡፡››
- <‹ኣቦይ ስብሃት አረጋዊ ናቸው፤ ይሄ የመነጣጠል አባዜ ቢቀርባቸውና ወደ ቤተ ክርስቲያን ሄደው የተጣላ ቢያስታርቁይሻላቸዋል፡፡. . .አርባ ዓመት ሙሉ ቀውስ አታቀጣጥሉ በሉልኝ፡፡›› /አቶ ኣስገደ ገብረ ስላስ ለኢትዮ ምኅዳርጋዜጣ/
ላይፍ፡- አንድ ጉዳይ እናንሣ፡፡ በአሜሪካን አገር የሚገኘው የኦርቶዶክስ ሲኖዶስም ኾነ አራተኛው ፓትርያሪክ ወደ አገር መምጣት የለባቸውም በማለት ደጋግመው ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ይህ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት አይኾንም?
አቶ ስብሓት፡- የተናገርኹት እንደ አማኝ እና እንደ ዜጋ የግል አመለካከቴን ነው፡፡ መጀመሪያ ፓትርያሪኩን ከኢትዮጵያ የሚያወጣቸው ምክንያት አልነበረም፡፡ ፓትርያሪኩ ኢሕአዴግ ይነካኛል የሚል እምነት አልነበራቸውም፤ ምክንያቱም እንደማንነካቸው ያውቃሉ፡፡ ብንነካቸው እንኳን መሰየፍ ነበረባቸው ወይም ገዳም ገብተው መመነን ነበረባቸው ወይም ኢየሩሳሌም መሄድ ነበረባቸው፡፡
ይህንን ሁሉ ትተው በመጨረሻ ግን ወደ አሜሪካ ወሰዷቸው፡፡ ይህም ሳያንስ በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ ትልቅ ወንጀል በመፈጸም ሲኖዶስ አቋቋሙ፤ የእስልምና አክራሪ እንቅስቃሴን ደገፉ፡፡ እነዚህን ነገሮች ስሰማ ሐሳቤን ገለጽኹ፡፡