Tuesday, December 30, 2014

የኢንተርኔት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ


በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክን በመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። 


የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም የሕትመት ሚዲያውን የሚመለከት ነው።  በዚህ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንተርኔት ድረገጾች ፈቃድ ማውጣት የግድ መሆኑን ደንግጎአል።  


በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል የመረጃ መረብ አማካኝነት ለስርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ፕሮግራም በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል ፣በአገር ደህንነት፣ ክብርና ጥቅም ላይ ጉዳት የሚያደርስ ፣የአገር ሚስጢርን የሚገልጽ ፣ አመጽና ጦርነትን የሚቀሰቅስ፣ የሰው ልጆችን ስብዕና ፣ነጻነት ወይንም ስነምግባር የሚጻረር ፣የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ መሆን እንደሌለበት ደንግጎአል። 


በተጨማሪም ሥራዎቹ ማንኛውንም የህብረሰተብ ክፍል፣ብሔር፣ጎሳ፣ቀለም፣ጾታ፣ዘር፣ቋንቋ፣ሃይማኖት፣ማህበራዊ አመጣጥ፣ ወይንም ሌላ መሰል አቋምንና ክብርን የሚነካ ወይም የሚያዋርድ፣ በህዝቦችና በሃይማኖቶች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት የሚቀሰቅስ ወይንም ጥላቻ የሚያስፋፋ፣ የግለሰብን ስም የሚያጠፋ፣፣ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን አመለካከት ስሜት የሚጎዳና ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንዲያዘነብሉ የሚገፋፋ፣ የህብረሰተቡን ሞራል የሚጥስ ወይንም በሕግ የተከለከለ ማንኛውንም ድርጊት የሚፈጽም መሆን የለበትም ይላል። 

ኢሳት

No comments:

Post a Comment