Sunday, December 8, 2013

ልማት ወይስ ስጋት ?

         
             ልማት ወይስ ስጋት ?


ወያኔ-ኢሕአዴግ ያገሪቱን የኢኮኖሚ አውታር በሰፊው በመቆጣጠር፣ በዙሪያው ለተሰባሰቡ የጥቅም አጋሮቹ
የማየርነጥፍ የሃብትና የንዋይ ጎተራ ሆኖላቸዋል፡፡ ሰፊው ሕዝብ የእለት ጉርስ አሮበት፣ መታከሚያ ቸግሮት፣ ፍትህና ርትእ ርቆት በችግር በሚጉላላበት ሰአት፣ ወያኔና አሽከሮቹ በድሎት እየተንደላቀቁ ሕዝብ ላይ ማግሳት ከጀመሩ ከ21 አመታት በላይ ሆኗል፡፡ በዚህም አገሪቱ በጥት ጠመንጃ ነካሽ ያገር ጠላቶች እጅ ወድቃ በመማቀቅ ላይ ትገኛለች፡፡

አገራችን በእንዲሀ አይነቶቹ የቀን ጅቦች መዳፍ ስር ወድቃ ወዴትም ልትራመድ የማትችል በመሆንዋ ቀጣ እጣ ፈንታዋ ሁሌም አሳሳቢ ሁኖ ይቀጥላል፡፡  የሀገሪቱን ቀጣይ ሂደት ወቅታዊውን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የማህበራዊ እድገት የሚያቀጭጭ ብቻ ሳይሆን፤ በሀገሪቱ ታሪካዊና ብሄራዊ ኩራቶች ላይ ሁሉ ትልቅ ስጋት የሚደቅን ነው፡፡ ይህ በጠመንጃ ላይ የተመሰረተ የግፍ አገዛዝ፣ ከአለማቀፉዊ የመረጃ ፍሰትና የንቃተ ህሊና
እድገት ጋር በፍፀም ሊጣጣም የማይችል ነው፡፡ የሰውን ልጅ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በዘመናዊ ባርነት ቀንበር ስር ለመግዛት የሚያደርገው ጥረት ባጭሩ መቀጨት ያለበት ነው፡፡

ዛሬ አገሪቱን የፍጢኝ አስረው በሕዝብ ላይ የሚቀልዱት እነዚህ አምባገነኖች ለየት ባለ መልኩም ሊያታልሉን ይሞክራሉ፡፡ የሄውም  ልማት የሚሉትን  ሽፉን መጠቀም ነው፡፡  ዜጎች መሰረታዊ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ፤ ማዋከብ፣ ማሰር ግፋም ሲል መገደል ነው፡፡  ስለ ነፃነት የሚታገሉ ሀይሎችንም ፀረ ልማትና ቴረሪስት ብሎ መፈረጅና ማሰቃየት ነው፡፡

በ2003 ዓ/ም ወያኔ ( ኢሕአዴግ ) የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱን በአስተዋወቀበት ወቅት ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ የኢኮኖሚ ልማት አጋር ከሚባሉ ወገኖች ትልቅ ትችትና አሉታዊ አስተያየቶችን አትርፎበታል ። የልማት ማስፈፀሚያ ገንዘብና የማስፈፀም አቅምን ሳይገነባ እቅድን ብቻ ለህዝብ ይዞ መቅረብ የስልጣን ቆይታን እድሜ ለማራዘም የሚደረግ ጥረት ብቻ መሆኑ ተጋልጧል፡፡ በእርግጥ ሳይታለም የተፈታ ህልም ቢሆንም ያለው ብቸኛ አማራጭና ሊሞክሩት የሚችሉት ብቸኛ ስልት ስለሆነ፤ ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም፡፡

ለምሳሌም ያህል የአባይ ገድብ ግንባታ ጉዳይም እንደዚህ አይነቱን ስልጣን  የማራዘሚያ ስልትን ያገናዘበ እንጂ ካቅምና ከነባራዊ ሁናቴ ጋር የተገናዘበ አይደለም፡፡ በመሆኑም ባሁኑ ጊዜ ከፕሮጀክቱ ከ25  በላይ ማካሄድ አልተቻለም፡፡ በቢሊዮን ዶላርን አምጡ እያለ ነው፡፡ ቦንድ ካልገዛችሁ እየተባለ አግረ የሚታመሰውም፣ ሳይኖራት አበድራ ሳትቀበል ሞተችን ተረት እንዳያስከትልበት ሕዝቡ ስጋቱን እየገለጸ ነው፡፡ ግብጽን ከመሳሰሉ የላይኛው ተፋሰስ አገሮች ጋር አስቀድሞ አለመምከርና አለመተግበር ያስነሳውን ሃይለኛ አቧራ ዛሬ ማቆም አልተቻለም፡፡

ስለዚህ ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታልና፣ የኔ ቆም ብሎ ሊያስባቸው የሚገቡ አገራዊ አጀንዳዎች ከፊቱ ተደርድረዋል፡፡ ባገሪቱ ውስጥ የነገሰው ፍርሃትና ንቅዘት ወይኔን የዛፍ ላይ እንቅልፍ እንዲተኛ እያደረገው ነው፡፡ ሕዝቡ በጠመንጃ ያጣውን መብቱን በሰላምም ይሁን በተመሳሳይ መንገድ ከማስመለስ በስተቀር ሌላ አማራጭ እንደሌለው እያረጋገጠ በመሄድ ላይ ይገኛል፡፡
                                                  ምናሴ መስፍን 
                                         almazmina@yahoo.com 

No comments:

Post a Comment