Monday, February 18, 2013

ወንጀለኛ ሊፈራና ሊሸማቀቅ እንጂ ሊያስፈራራ አይገባውም የውጭውን አለም ከወያኔ ሰላዮችን ማጽዳት ቁጥር 2



ከዚህ በፊት የወያኔ ሰላዮችን ከውጭ አለም ማጽዳት በሚል አጭር መልእክት አስተላልፌ ነበር አሁንም ያንኑ በተመለከተ ተጨማሪ ማብራሪያና እና መረጃ ለመስጠት ይችን አጠር ያለች ጽሁፍ ማቅረብ ፈለግሁ።
ከዚህ በፊት እንደጠቀስኩት የወያኔ ሰላዮችም ሆኑ እበላ ባዮች የኢትዮጵያ መንግስት አሰረኝ፤ ገረፈኝ፤ አሰቃየኝ ብለው የስደተኝነት ጥያቄያቸው ተቀባይነት በገኘ ማግስት ከወያኔEthiopian spy in London, UK ባለስልጣናትና ኢምባሲ ሰራተኞች ጋር ሲሞዳሞድ እና ሌሎች በትክክል ወያኔ አላኖር ብሏቸው የተሰደዱትን ሲተናኮሉ ይገኛሉ። ከዛም አልፈው እገልሀላሁ በሚል ዛቻ እያሰፈራሩ መሆኑን አይተናል፡ የስደተኛ ተቀባይ ሐገራት ህጎች በትክክል እንዳሰፈሩት ማንም ሰው ዋሽቶ ጥገኝነትን መጠየቁ ከተረጋገጠ ወዲያው ከሀገር እንዲወጣ ይደረጋል ይላል።
አንድ ግለሰብ የወያኔ መንግስት በፖለቲካ አመለካከቴ፤ በዘሬ፤ በሃይማኖቴ እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች አቅርቦ አላኖር አለኝ ብሎ የፖለቲካ ጥገኝነት ከጠየቀ ያ መንግስት እስካልተቀየረ ድረስ ችግሩ እንዳለ ነው ተብሎ ስለሚታመን ወያኔ በሚያዘጋጀው ስብሰባ ላይ መገኘት፡ በወያኔ ካድሬወችም ሆነ ደጋፊዎች በሚዘጋጁ የድጋፍ ሰልፎች ላይ መገኘት፡ የወያኔ ባለስልጣናት ባዘጋጁት ድግስና ስብሰባ ላይ መገኘት፡ በሁለት መልኩ ሊታይ ይችላል፡
  1. ያ ግለሰብ ምንም ብሎ ይመጣ የወያኔ ሰላይ ነው ወይም
  2.  ጥገኝነት ሲጠይቅ ያቀረባቸው ምክንያቶች ውሸት ናቸው፡
ከሁለት አንዱ ሆነው ከተገኙ ደግሞ የሀገራቱን ህግ ተላልፈዋል፡ አገራቸውም ቢገቡ ምንም ችግር እንደማይገጥማቸውና ፊትም ችግር እንዳልነበረባቸው ስለሚያመለክት ተመልሰው አገራቸው መግባት አለባቸው።

በነጻው አለም እንደዚህ አይነት ሰዎች በምንም መልኩ ጨቋኙን የወያኔ አገዛዝ ሊያጠናክሩብን አይገባም፡ እንደዚህ አይነት ሰዎችን ለሚመለከተው ከፍል ጥቆማ መስጠት የዜግነትና የህሊና ግዴታ ነው፡ ጥቆማ የምትሰጧቸው ክፍሎች ማንነታችሁን እንደማይገለጹና በሚስጥር እንደሚጠብቁት በድጋሜ ላረጋግጥላችሁ አፈልጋለሁ፡ ከዚህ ቀደም እንደገለጽኩት፡ በግል ኮምፒዩተራቸሁ መረጃ መስጠት ካልፈለጋችሁ ህዝብ መጻህፍት ቤት ወይም ኢንተርኔት ካፌ ተጠቅማችሁ መረጃውን ማስተላለፍ ትችላላችሁ፡ አሁንም ደግሜ አደራ የምለው ግን በግል ቂም ወይም በተወሰነ የህብረተ ሰብ ክፍል ያነጣጠረ እንዳይሆን አደራዬ የጠበቀ ነው።

ባለፈው ካሰፈርኳቸው አድራሻዎች በተጨማሪ በማጭበርበር የተፈቀደላቸውን ሰዎች በመረጃ በቀጥታ ለሚመለከተው ክፍል ለማስተላለፍ፡

1.  በአውስትራሊያ፡ Immigration Dob-in Service፡ http://www.immi.gov.au/contacts/dob-in/#a
3.  በዪናይትድ ስቴትስ፡ Immigration Fraud (Illegal Aliens http://howtoreportfraud.com/report-other-fraud/immigration-fraud
ከዚህ በተጨማሪ የማስፈራራት ወይም የወንጀል ድርጊት እንቅስቃሴ ሲያጋጥማችሁ ያለምንም ይሉኝታ በቀጥታ ለሚመለከተው ክፍል ጥቆማ ማድረግ ያስፈልጋል፡  ወንጀለኛ ተደብቆና ተሸማቆ መኖር ሲጠበቅበት በእብሪት ተወጥሮ ሃቀኛ ኢትዮጵያውያንን ለመግደል ማሴር፤ አገልሃለሁ እያሉ ማቅራራት ምን ይባላል፡ “ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ” ይላል ያገሬ ሰው።

በየሃገራቱ ሪፖርት ለማድረግ እነዚህን አድራሻዎች ተጠቀሙ።

United Kingdom፡ MI6: https://www.sis.gov.uk/contact-us.html please read contact us form before you    fill out the form for useful advice.
Australia: Australian Secret Intelligence Service e-mail asis@asis.gov.au
Germany: German Intelligence Agencies:  https://www.fas.org/irp/world/germany/index.html
Norway: (Norwegian National Security Agency/Authority)  https://www.nsm.stat.no
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
እስከ ነጻነት

No comments:

Post a Comment