Monday, May 16, 2016

                             What if I Covet the Norwegian 17th of May?

Norway is a free independent democratic kingdom. The nation’s constitution was penned in 1814 in an effort to free the country from the foreign domination 202
years a go.
 Being inspired by a great zeal and love of their country; based on the then great interest and need of the nation; as much as the scope of their knowledge allowed them some 120 Norwegian nationalists came up with such an amazing work.
 Being the second largest in the world, this constitution officially called “Kongeriket Norges Grunnlov” was first adopted on May 16 and subsequently signed and dated on 17 May 1814 by the Norwegian constituent Assembly at Eidsvål. Since then, the day 17th May is being celebrated as a national day indicating that Norway is a sovereign state.
 The constitution was not formed and or created to serve the few parliament members or the ruling organ. Rather, it was to magnify the nations freedom and to keep it’s democratic right and uphold the peoples sovereignty. In addition to that, it was related it’s character, to the international democratic rules and laws as general.
 

Wednesday, February 25, 2015

እነ ማን ነበሩ? አሁንስ ማን ናቸው?


ገብረመድህን አርኣያ
ፐርዝ፤ አውስትራሊያ

ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሚሰጠው በትግል በረሃ በነበርንበት ወቅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት.) በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች ላይ ሲከተል የነበረውን አቋሙን ተቀብሮ ከነበረበት ጉድጓድ አውጥቼ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነማን ናቸው የሚለውን ታሪካቸውን እና የተፈጸመውን ጸረ-እምነት ግፍ በአጭሩ ለማሳወቅ ነው።

ህ.ወ.ሓ.ት. ገና ሲፈጠርና ተ.ሓ.ህ.ት. ተብሎ እንደተመሰረተ ሙልጭ ያለ ጸረ-ዲሞክራሲ ድርጅት ነው። በጸረ-ኢትዮጵያነትና በጸረ- ሕዝብነት የተሰማራ ቅጥረኛ ድርጅት መሆኑን ብዙ ጊዜ በጽሑፍና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተናግሬአለሁ። የአሁኑ ጽሑፌ ህ.ወ.ሓ.ት. በሃይማኖት ላይ ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲ ገና ከመጀመሪያ ትግሉ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የነበረውን ጸረ- ሃይማኖት ተግባራቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልጽ አውቆታል። እኔ ደግሞ የራሴን ልበል።

በ1969 መጀመሪያ ጀምሮ “ወይን” በሚለው የድርጅቱ ልሳን መጽሔት ላይ በተደጋጋሚ “የክርስትና ሃይማኖትና አማራው” በሚል ርእስ ተጽፎ የሚወጣው ጽሑፍ፣ “የክርስትና ሃይማኖት የአማራው ዋና መሳሪያና የግዛቱን ህልውና ማስጠበቂያ ነው፣ በመሆኑም የትግላችን ጠላት አማራውና መሳሪያው የተዋህዶ ክርስትና ስለሆኑ አብረው እንዲጠፉ  ማድረግ አለብን” እያለ ያትት ነበር። ይህንን መጽሔት በሰፊው ለታጋዩና ለአባላቱ በማሰራጨት ሰፊ ቅስቀሳ አካሂዶበታል። በነሐሴ 1969 “ወይን” መጽሔት አማርኛ ቋንቋም አብሮ መጥፋት እንዳለበት ሃተታ ይዞ ወጥቷል።

Tuesday, February 17, 2015

እየከፋ በመጣው የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ የጋራ አቋም መግለጫ ከፖለቲካ ፣ ሲቪክ ፣ የሃይማኖት ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች

«ለውጥ በማይቆም ተሽከርካሪ የሚጓዝ አይደለም፤ የተከታታይ ትግል ውጤት ነው። ነጻነት የምንፈልግ ሁሉ ጀርባችንን ቀና አድርገን መታገል አለብን። ራሳችን ካልፈቀድንለትና ካልተሸማቀቅን፤ ማንም ሰው እንደ ከብት ሊጋልበን ከቶ አይችልም” ነበር ያሉት ዶር ማርቲን ሉዘር ኪንግ ጁኔር ።

በማንኛውም አገር ቢሆን፣  ነጻ የሆነ የዜና አገልግሎት የማያገኝ፤ ተቆርቋሪ የፖለቲካ ወይንም የማህበረሰብ ወይንም የሲቪክ ድርጅት እና በነጻነት የሚንቀሳቀስ የመገናኛ ብዙሃን አገልግሎች የሌለው  ሕዝብ መብት የለውም። መብቱ በመንግሥት የተከለከለ ግለሰብ ሆነ ቡድን፤ ማህበረሰብ ሆነ ሕብረተሰብ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው እድገት አይጎናፀፍም።


ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለሃያ አራት ዓመታት በበላይነት ሲገዛት የቆየችዋ ኢትዮጵያችን  ፍትህ፤ ነጻነት፤ ሰብአዊ መብት፤ የሕግ የበላይነት  የማይታይባትና  አምባገነናዊ ስርዓት የሰፈነባት ሃገር ሆናለች። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ የመድበል ፓርቲ ስርዓት የምትከተል መሆኗ በሕግ መንግስቱ ቢደነገግም፣ በተግባር የታየው ግን ከገዝው ሕወሃት/ኢሕአዴግ ነጻ የሆኑ ድርጅቶችን ሁሉ የማጥፋት ሂደት ነው። የአገሪቷን ሕግ ሆነ የምርጫ ቦርድን አሰራር  በጣሰ መልኩ፣ በቅርቡ በአገሪቷ ጠንካራ የሚባለውን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)  አመራርን በማገድ ራሱ ያቋቋማቸዉን ተለጣፊ መሪወች መሾሙ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ  በምርጫ የማያምንና፣ ብቻውን ለሚቀጥሉት ሃያ፤ ሰላሳ አመታት በጉልበት ለመግዛት እንደወሰነ አመላካች ነው። የዜጎችን የመደራጅትና የመሰባሰብ ሰባአዊ መብትም የረገጠ ነው።

Monday, February 16, 2015

‹‹ሰላማዊ ትግሉ ሲጠናከር ስርዓቱ ወደ አውሬነት ይቀየራል›› ‹‹ቃል ኪዳናችንን ማጥበቅ አለብን!›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት


‹‹ሰላማዊ ትግሉ ሲጠናከር ስርዓቱ ወደ አውሬነት ይቀየራል››
‹‹ቃል ኪዳናችንን ማጥበቅ አለብን!››
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
(በዛሬው ዕለት ለቀድሞው የአንድነት አመራሮችና አባላት የተዘጋጀው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ላይ ከተናገሩት)
ፓርቲ ጣኦት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ቅንጅትንም አፍርሶታል፡፡ አንድነትንም አልፈረሰም ብለው እንዳይከሱኝ እንጅ አፍርሰውታል ማለት እችላለሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰማያዊ ላይም አንድ ነገር ማምጣታቸው የማይቀር ነው፡፡ ያ ማለት ግን ሰላማዊ ትግሉ ምን ያህል እንዳስፈራቸው ነው የሚያሳየው፡፡ አገዛዙ በፓርቲዎች ላይ የሚወስደው እርምጃ የሚያሳየው ሰላማዊ ትግሉ መጠናከሩን እንጅ ወደኋላ መመለሱን አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲህ አይነት ችግር ሲከሰት ሰላማዊ ትግሉ አበቃለት ይላሉ፡፡ ሆኖም አገዛዙ ሰላማዊ ትግል አስፈርቶት አውሬ ሲሆን የሚያረጋግጥልን ሰላማዊ ትግሉ መጠናከሩን ነው፡፡
Blue Party
በመሳሪያ ትግል ውስጥ አንድ ጀኔራል ሲሞት አሊያም አንድ የጦሩ አካል ችግር ሲደርስበት ‹‹የትጥቅ ትግል አበቃለት›› እንደማይባለው ሁሉ ሰላማዊ ትግል ላይ አንድ ጫና ወይንም የስርዓቱ ደባ ሲከሰት ትግሉ አይሰራም ማለት አይደለም፡፡
ሰላማዊ ትግል መስዋዕትነት አያስከፍልም ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ሰላማዊ ትግል ውጤት ማምጣት ሲጀምር፣ ዙሩም ሲካረር፣ የሚከፈለው ዋጋም ይበልጥ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የስርዓቱ አውሬነት በተገለጠ ቁጥር፣ እኛም በተሻለ አመራር ትግሉን ስንመራው መስዋዕትነቱ ይበልጡን እየበዛ እንደሚመጣ እንረዳለን፡፡

Sunday, February 15, 2015

የምርጫ ሂደቱ በኢህአዴግና በምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ችግር እየደረሰበት ነው! ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ሰማያዊ ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ተወዳድሮ በማሸነፍ የመንግስትን ስልጣን ለመያዝ የሚያበቃውን ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ነፃና ፍትሀዊነት ለማረጋገጥ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ነፃነት ለፍትሀዊ ምርጫ የሚል መርሀ ግብር በማዘጋጀት ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ነፃና ገለልተኛ እንዲሆኑ በተለያዩ መንገዶች ጥያቄዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ እስካሁን ከተደረጉት እንቅስቃሴዎችም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድና የመንግስት አስፈፃሚ ተቋማት በህገ መንግስቱ በተደነገገው መሰረት ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲሰሩና የፖለቲካ ምህዳሩም ለሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ፍትኃዊ እሰኪሆን ድረስ የነፃነት ለፍትሃዊ ምርጫ ዘመቻችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በሁሉም የሀገሪቷ ክፍሎች እጩ ተወዳዳሪዎችን ለማስመዝገብ ባደረጋቸው እንቅስቃሴዎች በተለያዩ የምርጫ አካባቢዎች በዕጩ ተወዳዳሪዎቻችን ላይ በገዢው ፓርቲ አባላትና በምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ከፍተኛ እንግልትና እንቅፋት የተፈጠሩባቸው ሲሆን ለአብነት ከብዙ በጥቂቱ ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡



1. በተለያዩ አካባቢዎች ላይ እጩ ተመዝጋቢዎች የተወለዱበት ዞን መሆኑ እየታወቀ ነገር ግን ምስክር አምጡ በማለት እንዳይመዘገቡ ተደርገዋል፡፡

2. በሰሜን ጎንደር ዞን ባሉ ወረዳዎች በሙሉ የምርጫ አስፈፃሚዎች ፅ/ቤቶችን ዘግተው በመጥፋታቸው ምክንያት መመዝገብ በተደጋጋሚ የሄዱ እጩ ተመዝጋቢዎች ሳይመዘገቡ ጊዜው እንዲያልፍባቸው ተደርገዋል፡፡

Tuesday, February 3, 2015

ወያኔ ‘ታላቋን ትግራይ’ ለመመስረት ‘crime against humanity’ ና ‘genocide’ በመፈጸም ላይ ነው

ይህ ፅሁፍ የሚያተኩርበት ዋና ጉዳይ ወያኔ ‚ታላቋን ትግራይ‛ ተብላ የምትጠራ አገር ለመመስረት ሲል በጎንደርና በወሎ ህዝብ ላይ የፈጸመውንና አሁንም እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት(genocide) እና ትግራይ ያልሆነ ህዝብን ማፈናቀሌ (ethnic cleansing) ወንጀልች ሊይ ነው። በመላ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የኢኮኖሚ ገፈፋና በየትኛውም የመንግስትና የግል የኑሮ ዘርፎች የትግራይ የበላይነት ለማረጋገጥ ሲባል ወያኔ በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ የሚያካሂደውን የሽብር ዘመቻ የዚሁ መሰሪ አላማ አካል ነው። ከዚያ ባሻገር ጎጠኛ አስተዲደር (ethnic federalism) እና የመገንጠል አንቀጽ (አንቀጽ 39) የተባለት አንኳር የወያኔ መርሆች አገልግሎታቸው ወያኔ እንደሚለፍፈው የብሔሮችን እኩልነት ለማረጋገጥ ሳይሆን ሌሎች ብሔሮችን በማፈናቀልና በማራቆት የትግራይ ክልልና የትግራይ ተወላጆች ሀብት እንዱያካብቱና ለሚመሰርቷት ታላቋ ትግራይም ስትራቴጂካዊና ውሀ ገብ ለም መሬቶችን ለመንጠቅ እንዲያመቸው ያስቀመጣቸው ለመሆናቸው ይህ ጽሁፍ አባሪ መረጃዎች ያቀርባል። ወያኔ በጎንደርና በወሎ ህዝብ ላይ የሚፈጽማቸው ወንጀሎች በግብታዊነት የተከሰቱ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ በተጠና እቅድ መሰረት ነው።

ወንጀሎቹ ከሞላ ጎደል የሚከተለው ቅደም ተከተል አላቸው።

1. ለምና ስትራቴጂካዊ (strategic) የሆኑ ቦታዎችን ትግራይ ካልሆኑ ህዝቦች በመንጠቅ በትግራይ ክልል ስር እንዲጠቃለሉ ማድረግ፤

2. በተነጠቁ ቦታዎች ላይ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎችን ማስፈር፤ ከትግራይ ክልልና ከማእከላዊ የወያኔ መንግስት በሚለገስ ገንዘብ አማካኝነት አዲስ የትግራይ ሰፋሪዎችን ሀ) ማስታጠቅ፣ ለ) በእርሻና በሌላ የልማት መስኮች ማደርጀት፤

3. በአዱስ ታጣቂ ሰፋሪዎች አማካኝነትም በነባሩ ህዝብ ሊይ የማፈናቀልና የማሳደድ ዘመቻ በመክፈት አካባቢውን የትግራዮች ብቸኛ ሀብት ማድረግ፤

4. መስፋፋቱንና በሃይል መፈናቀሉን በቆራጥነት የሚቃወሙትንና በነዋሪው ህዝብ ዘንድ ተሰሚነት አላቸው የሚሏቸውን ግለሰቦችን ማፈን፣ ማሰርና መግደል፤ የቀሩትን ሰዎች በማንገላታት ቢቻል ክልሉን ለቀው እንዲሰደዱ ማዴረግ ካልተቻለ ደግሞ ለምነት በሌላባቸው መሬቶች ተጨናንቀውና ተጣበው እንዲታሰሩ በማዴረግ ለከፍተኛ ችግርና ረሀብ እንዱጋለጡ ማድረግ፤

5. የኗሪውን ህዝብ የደረሱ ልጃገረዶች በትግራይ ጎረምሳ ኮርማዎች ማስደፈር፤ (rape ማስደረግ)፤ በዚህ ባህልን፣ ሃይማኖትንና ሰብአዊነትን ባዋረደ ተግባር የትግራይ ዘር ያላቸውን
ልጆች እንዲወልዱ ማድረግና ከዚያ በበለጠ ደግሞ ሌላ ትግራይ ያልሆኑ ወላጆችንና ወንድ ወጣቶችን ቅስም መስበር ነው።

Saturday, January 31, 2015

የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሮ አያውቅም

የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ ኖሮ አያውቅም

(ecadforum.com ኢዲቶሪያል)

ሰሞኑን ወያኔ/ኢህአዴግ በህግ ተመዝግበው በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶችን ለማጥፋትና በመጪው ምርጫ ላይ እንዳይሳተፉ ለማድረግ በርትቶ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።


እስካሁን መኢሕአድ እና አንድነት ፓርቲ የዚሁ የወያኔ/ኢሕአዴግ የቅድመ ምርጫ “ተቃዋሚዎችን የማዳከም እና የማጥፋት ዘመቻ” ሰለባ ሆነዋል።


በቅርቡ ራድዮ ፋና እና ኢቲቪ ከሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ጋር አድርገውት የነበረውን ቃለ-ምልልስ (በኋላ የቃለ-ምልልሱ ድምጽ ጠፋብን ማለታቸው ይታወሳል፣ ይሁንና ኢሳት ቴሌቪዥን ጠፋ የተባለው ቃለ-ምልልስ በእጁ ገብቶ ኖሮ እያሰራጨው ይገኛል) ቃለ-ምልልሱን ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ። ከቃለ-ምልልሱ መረዳት እንደሚቻለው ፖሊስ ቀመሱ የወያኔ/ኢሕአዴግ ጋዜጠኛ ምን ያህል ሰማያዊ ፓርቲን የሚያስወነጅሉ ነገሮች ፍለጋ ይባዝን እንደነበር ነው። ይህ የሚያመለክተው ሰማያዊ ፓርቲ ቀጣዩ የወያኔ/ኢህአዴግ “ተቃዋሚዎችን የማዳከም እና የማጥፋት ዘመቻ” ሰለባ እንደሚሆን ነው።

ወደ ተነሳንበት ርዕስ ስንመለስ፣ ከላይ የተጠቀሱትን ሁነቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ አንዳንድ በተቃውሞ ጎራ የተሰለፉ ፖለቲከኞች እና ለውጥ አራማጆች “ወያኔ/ኢሕአዴግ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን እያቀጨጨ ነው፣ ገዢው ፓርቲ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን እያጠፋ ነው፣ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓት አከተመለት…” ሲሉ ይደመጣሉ።

Friday, January 30, 2015

አንድነትን “እናኝከዋለን፤ እንገድለዋለን” – ምርጫ ቦርድ

ትዕግስቱ አወሉ እንደ አየለ ጫሚሶ

የዛሬ አስር ዓመት “የሕዝብ ሱናሚ” እያለ ሲምል ሲገዘት የነበረው ህወሃት ሱናሚው ወደ እርሱ እየጎረፈ ሲመጣ በረገገ፡፡ መፍትሔ በጠብመንጃ አፈሙዝና በብረት ብቻ እንደሆነ የሚያምነው ህወሃት በረሃ የለመደውን በትሩን አነሳ፤ ንጹሃንን ጨፈጨፈ፤ ደም አፈሰሰ፤ ኢትዮጵያን ወደ እስርቤትነት ቀየራት፡፡ ትዕዛዙን በቀጥታ የሰጡት “ባለራዕዩ” ለፍርድ ሳይቀርቡ “እንደጀመርን እንጨርሰዋለን” ያሉትን ሰፊውን ሕዝብ ሳይጨርሱት እንደ ክዳን ቆርኪ ተስፈነጠሩት፤ ላይመለሱ ሄዱ፡፡
የዛሬ አስር ዓመት የቅንጅት አካሄድ ያስፈራው ህወሃት ጉዳዩን ለራሱ ለፓርቲውና ለሕዝብ ከመስጠት ይልቅ ደም መቃባት ውስጥ ገባ፡፡ ፓርቲው የነበረበት የውስጥ ችግር እንዳለ ሆኖ የፈሪ በትር የዘረጋው ህወሃት የገደለውን ገድሎ ከጨረሰ እና የኢትዮጵያን መሬት በደምና በእናቶች እምባ እንደገና ካጨቀየ በኋላ ቅንጅትን የማፍረስ ተግባሩን በዕቅድ ይዞ በይፋ መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ግምባር ቀደም ተሰላፊው የተቋም ባንዳ “ምርጫ ቦርድን”፤ በግለሰብ ደረጃ ደግሞ በተለይ ሁለት ግለሰቦችን አሰለፈ፡፡ ዘመቻ “ቅንጅትን መግደል” ተጀመረ፡፡

በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ምንም በማያሻማ ሁኔታ በኢትዮጵያ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ዶናልድ ያማሞቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ስቴት ዲፓርትመንት) ለሚገኙት አለቆቻቸው “THE ETHIOPIAN GOVERNMENT CHEWS THE CUD” (የኢትዮጵያ መንግሥት ቅንጅትን አኘከው) በሚል ርዕስ የጻፉት እንዲህ ይነበባል፤

Thursday, January 29, 2015

መልእክት አለኝ ለአንድነት አመራሮች እና አባላት

ግርማ ካሳ


የሕወሃት የደህንነት ሃላፊዎች፣ አንድነት መወዳደር የለበትም የሚል ዉሳኔ ካሳለፉ ቆይተዋል። ከዚህ በፊት፣ ፓርቲ እንደ ኢንጂነር ግዛቸው ባሉ ደካማ አመራር ሥር ስለነበረ ፣ የትም ገፍቶ እንደማይሄድ ተረድተው ነበር። ኢንጂነሩ በአባላት ግፊት ከሃላፊነታቸው ተነሱ። አዲስ ፣ ለዉጥ ፈላጊ አመራር መጣ። ችግሩ የአመራር ችግር ስለነበረ፣ አዲሱ አመራር ሃላፊነቱን በያዘ በሶስት ወር ጊዜ ዉስጥ ብቻ፣ የአገሪቷን ፖለቲካ አነቃነቀ። ፓርቲው ተቀባይነቱ ከመቼዉም ጊዜ በላይ አደገ። ይህን ጊዜ አይን ባወጣ መልኩ፣ አይኖቻቸዉን በጨው አጥበው፣ አንድነት ፓርቲ አገዱት። እኔ የምሬ ለነርሱ አዘንኩላቸው !!!! አቤት፣ አቤት፣ አቤት ፣ ……



ነጥብ አንድ። የዛሬው የሕወሃት ዉሳኔ የአንድነቶች የሥራ ዉጤት መሆኑን መረሳት የለበትም። ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ አገዛዙ እንዲዋረድና መሳቂያ እንዲሆን አድርገዉታል። ሕወሃት ጭንቅላት ባላቸው ሰዎች ሳይሆን፣ ፉዞ በሆኑ ሰዎች እየተመራ እንደሆን አለም አውቆታል። የሚቀበሩበትን መቃብር ቆፍረዋል።

Saturday, January 24, 2015

የመኢአድ ም/ፕሬዝደንት ከፍተኛ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ፓርቲው ገለፀ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የፓርቲያቸው ምክትል ፕሬዝደንት እና የሰሜን ቀጠና ኃላፊ የሆኑት አቶ ዘመነ ምህረት እጅግ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸው ሲል ፓርቲው ጥር 15/2007 ዓ.ም በሰጠው መግለጫ አስታወቀ፡፡


አቶ ዘመነ የመኢአድን ጠቅላላ ጉባኤ አድርገው ወደ መኖሪያቸው ጎንደር ከተማ ከተመለሱ በኋላ ከፍተኛ የደህንነት ክትትልና ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ለፓርቲያቸው አሳውቀው ነበር ያለው ፓርቲው በ10/05/2007 ዓ.ም ጎንደር ከሚገኘው መኖሪያው ቤታቸው ከባቤታቸውና ከህጻን ልጃቸው ፊት የፖሊስ ልብስ በለበሱ አካላት ከፍተኛ ደብደባ ተፈጽሞባቸው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ግልጾአል፡፡ 

Monday, January 19, 2015

ወከባ እና እስር በህገመንግስቱ እውቅና ይሰጣቸው:: በወከባ እና በእስር ሽብርን በደሃ ህዝብ ላይ መፍጠር ከተጠያቂነት አያድንም::

Minilik Salsawi ምንሊክ ሳልሳዊ)

ይህ የተገፋ ህዝብ እንዳጎነበሰ አይኖርም ቀና ያለ እለት …!!! ወህኒ የጀግና እንጂ የወያኔ እብሪተኞች ቤት አይደለም!!
ባለስልጣናት የጸረ አሸባሪነት ህግን ለማስፈጸምም ይሁን ለመተግበር ሞራላቸው ምን ድረስ እንደሆነ ሊመልሱልን ይገባል:: ተቃዋሚ ፓርቲዎች ያልተመዘገቡ ሀገወጥ እና አሸባሪ ከሆኑ የተወነጀሉበት ተቀባይነት ያለው ክራይቴሪያ ይነገረን እና እናውግዘው:: አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝቦች ጥያቄያቸው ግልጽ እና ግልጽ ነው ካልሆነ የሚዋከቡበት ምክንያት የለም ካለ ይነገረን እና እናውግዝ ተደጋጋሚ ጸሎት አንፈልግም መንግስታዊ አሸባሪነትን እያወገዝን ወያኔን በትእግስት እየጠበቅናት ነው ይህ ያበጠ ነገር የፈነዳ እለት ወዮላቹ…የምትገቡበት አታገኙም:: እንደ ደርግ ባለስልጣናት ወህኒ አንወሽቃችሁም:: ወህኒ እኮ የጀግና እንጂ የወያኔ እብሪተኞች ቤት አይደለም::

Thursday, January 8, 2015

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ደህንነቱ አደጋ ላይ መሆኑ ተገለፀ

በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት የሶስት ዓመት እስር የተበየነበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ደህንነቱ አደጋ ላይ መሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቹ ገለፁ። 

ጋዜጠኛ ተመስገን፣ በዝዋይ ወህኒ ቤት ኮማንደር ቢኒያም ተብሎ በሚጠራው የወህኒ ቤቱ አስተዳዳሪ ጠዋትና ማታ
ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት እንደሚገኝና በተጨማሪነትም በቀን ለአምስት ጊዜ ያህል ሌሊትን ጨምሮ በሰበብ አስባቡ ከክፍሉ እየተጠራ እንደሚወሰድ የቅርብ ቤተሰቦቹ አስታውቀዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን፣ በኮማንደር ቢኒያም እየተጠራ “እንገልሃለን፣ ከዚህ አንተ ሳይሆን ሬሳህ ነው የሚወጣው” የሚል ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰበት እንደሚገኝ ተገልጿል።


ዛቻው እና ማስፈራሪያው እየደረሰበት የሚገኘው በቅርቡ ለንባብ ባበቃው “የኢትዮጵያ መንግስት ገመና” በሚለው መጣጥፉ እንደሆነ የቅርብ ቤተሰቦቹ አያይዘው ገልፀዋል።  

Thursday, January 1, 2015

ወያኔ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ የህዝቡን ሰላም ለማደፍረስ ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ›› መረጃ ስጡኝ በሚል ለህዝቡ ቅጽ እያደለ ነው

(ነገረ ኢትዮጵያ)

የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በሰላማዊ ሰልፍ ስም የህብረተሰቡን ሰላም ለማደፍረስ እያደረገ የሚገኘውን እንቅስቃሴ በተመለከተ›› መረጃ እንዲሰጡት ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቅጽ እያከፋፈለ መሆኑ ታወቀ።

Wednesday, December 31, 2014

የመሰናዶ ተማሪዎች የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሙ አሰሙ

• በሶስት ከተሞች ረብሻዎች ተነስተዋል

(ነገረ-ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁሉም ትምህርት ቤቶች የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቁመው እንዲወስዱ የተደረገውን የ‹‹አብዮታዊ ዴሞክራሲ›› ስልጠና ላይ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ምንጮን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

በስልጠናው ወቅት የህዝቡ አስተሳሰብ፣ የግል ሚዲያ፣ ተቃዋሚዎች ለኢትዮጵያ እድገት ጠንቅ ተደርገው የቀረቡ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አቀራረብ ተቃውመውታል።  በአንጻሩ ከወራት በፊት ስልጠናውን የወሰዱት መምህራንም ዳግመኛ ስልጠናውን እየወሰዱ ቢሆንም ዝምታን መምረጣቸው ተገልጾአል። 

Tuesday, December 30, 2014

የኢንተርኔት እና የተንቀሳቃሽ ስልክ መረጃዎች ላይ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር የሚያደርግ አዋጅ ተረቀቀ


በሥራ ላይ ያለውን የብሮድካስት አዋጅ የሚሽርና ለመጀመሪያ ጊዜ በኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክን በመጠቀም የሚቀርብ የብሮድካስት አገልግሎቶችን ላይ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። 


የኢትዮጵያ የብሮድካስት ባለስልጣን ያዘጋጀውና በዚህ ዓመት ለፓርላማው ቀርቦ ይጸድቃል ተብሎ የሚጠበቀው ይህው የሚዲያ ረቂቅ አዋጅ አሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን ማለትም ራዲዮ፣ቴሌቪዥን፣ የኢንተርኔት ድረገጾች እንዲሁም የሕትመት ሚዲያውን የሚመለከት ነው።  በዚህ አዋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንተርኔት ድረገጾች ፈቃድ ማውጣት የግድ መሆኑን ደንግጎአል።  


በኢንተርኔት ፣በተንቀሳቃሽ ስልክ ወይም በመሰል የመረጃ መረብ አማካኝነት ለስርጭት የሚቀርብ ማንኛውም ፕሮግራም በአገር አንድነትና ሉአላዊነት ላይ አደጋ የሚጥል ፣በአገር ደህንነት፣ ክብርና ጥቅም ላይ ጉዳት የሚያደርስ ፣የአገር ሚስጢርን የሚገልጽ ፣ አመጽና ጦርነትን የሚቀሰቅስ፣ የሰው ልጆችን ስብዕና ፣ነጻነት ወይንም ስነምግባር የሚጻረር ፣የሌሎችን እምነት የሚያንኳስስ መሆን እንደሌለበት ደንግጎአል። 

Wednesday, December 24, 2014

ኤም አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዘው የጠፉት አብራሪዎች ቤታቸው ተፈተሸ


ታኀሳስ ፲፭(አስራ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የአየር ሃይል ደህንነቶች ወደ ጠፉት አብራሪዎች ቤት በድንገት በመሄድ ፍተሻዎችን ያካሄዱ ሲሆን፣ በቤቶች ውስጥ የተገኙ ሰነዶችን፣ የበረራ ማኑዋሎችን፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን፣ ትጥቆችንና ሌሎችም ቁሳቁሶች ወስደዋል።

ከደህንነቶች ጋር ምንም አይነት ፖሊስ ያልነበረ ሲሆን፣ ደህንነቶች ፍተሻውን ለማካሄድም የፍርድ ቤት ማዘዣ አላሳዩም። የመከላከያ ሰራዊት ባወጣው መግለጫ ሁለቱ አብራሪዎች በዋናው አብራሪ ተገደው መጥፋታቸውን ቢገልጽም፣ ከዋና አብራሪው ውጭ ያሉት ረደት አብራሪውና ቴክኒሻኑ ቤታቸው እንዲፈተሽ መደረጉ፣ ሚኒስቴሩ የሰጠው መግለጫ የተሳሳተ መሆኑን እንደሚያመለክት ምንጮች ገልጸዋል።

Tuesday, December 23, 2014

የፀጋዬ በርሔ ቪላ ተሸጠ – ከኢየሩሳሌም አረአያ


የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንትና በኋላ የፌዴራል ደህንነት ዋና ባለስልጣን የሆኑት የሕወሐት ፖሊት ቢሮ ባል አቶ ፀጋዬ በርሄ በመቀሌ ልዩ ስሙ “አፕርታይድ መንደር” ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ያስገነቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ ቪላ መሸጣቸውን ታማኝ ምንጮች አረጋገጠዋል። 10 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደፈጀ የሚነገርለት የአቶ ፀጋዬ ቪላ ለአንድ ባለሃብት 25ሚሊዮን ብር እንደተሸጠ ቢነገረም በትክክል የተሸጠበትን ዋጋ ማወቅ እንዳልተቻለ ምንጮቹ አስታውቀዋል። ፀጋዬ በርሄ የቅዱሳን ነጋ ባለቤት ሲሆኑ ቅዱሳን የስብሃት ነጋ ታናሽ እህት ናቸው።የመቀሌ ነዋሪ “አፓርታይድ መንደር” የሚል ስያሜ በሰጠው በዚህ ቦታ ከአቶ ፀጋዬ በርሄ በተጨማሪ አቦይ ስብሃት ነጋ በራሳቸውና በመጀመሪያ ልጃቸው ስም ሁለት ቪላዎችን ሲያስገነቡ ቴዎድሮስ ሃጐስ፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጎበዛይ ወ/አረጋይ፣ ተክለወይኒ አሰፋ ዘመናዊ ቪላዎችን ካስገነቡ የሕወሐት ባለስልጣናት ሲጠቀሱ ኪሮስ ቢተው በሰባት ሚሊዮን ብር ወጪ በዚሁ ስፍራ ያስገነቡትን ቪላ ከ9 ወራት በፊት መሸጣቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል። በሌላም በኩል የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበሩት የሕወሐት አባል ጄ/ል አበበ ተ/ሃይማኖት (በቅፅል ስማቸው ጆቤ) በቦሌ ያስገነቡትን ቪላ በ24 ሚሊዮን ብር መሸጣቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

Monday, December 15, 2014

ሕወሐት /ፂዮንን // ለማድረግ አቅዷል  የአዜብና የደህንነቱ ሹም ያልታሳካ እቅድ

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)

የጠ/ሚ/ር ስልጣን ወደ ሕወሐት ለመመለስ የፓርቲው ቁልፍ አመራሮች በምስጢር ሲመክሩ መስንበታቸውን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በአቶ ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፣ አባይ ፀሐዬ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ፣ ፀጋይ በርሔ፣ አርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ የሚመራው የሕወሐት ከፍተኛ አመራሮች ከዚህ ቀደም ሲካሂዱት በነበረውና ህወሀት የጠ/ሚ/ ርነት ስልጣን መልሶ መያዝ ይኖርበታል፣ የሚለውን ምክክር ከዳር ለማድረስ አቋም መያዘያቸውን ያስታወቁት ምንጮቹ በተለይ በቅርቡ የተካሄደው የአራቱ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በብአዴንና ኦህዴድ በኩል ቅሬታና ተቃውሞ እየበረታ በመምጣቱ የሕወሐት አመራሮች ስልጣኑን በእጃቸው ለማስገባት ቆርጠው መነሳታቸውን አስረድተዋል። 

በብአዴን በኩል የአቶ በረከት ስሞን ከስልጣን መገፋት በደጋፊዎችቻቸውና አመራሩ በኩል ቅሬታ መፍጠሩን የጠቆሙት ምንጮቹ በረከት ስሞን የጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም አማካሪ ተብለው ቢሾሙም ነገር ግን በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት ቢሮ እንዳልተሰጣቸውና የተሰጣቸው ካዛንቺስ አካባቢ የሚገኘው የቀድሞ የደህንነት ቢሮ መሆኑን ምንጮቹ ገልፀው በዚህ ቢሮ ኩማ ደመቅሳ እንደሚገኙና በጠ/ሚ/ር ፅ/ቤት አዲስ ቢሮ ተገንብቶ ይሰጣችኋል የተባለው ተግባራዊ እንዳልሆነ አያይዘው አስረድተዋል።

Wednesday, December 3, 2014

ዘጠኙ ፓርቲዎች ለቀጣይና ለቀሩ ስራዎቻቸው ያወጡትን እቅድ በተመለከተ መግለጫ ሰጡ።እንዲሁም የህዳር 27 እና 28 የተቃውሞ ሰልፉን እንደሚያካሂዱ አስታወቁ።


ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሺን፣ ፓርቲዎቹ ይህን አስታወቁት ባወጡት መግለጫ ነው።

ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ደብዳቤ ለመቀበል አሻፈረን ሲል የነበረው መስተዳድሩ በፖስታ የተላከለትን ደብዳቤ ከተቀበለ በሁዋላ ከህገመንግስቱና ከአዋጁ ቁጥር 3/1983 ተቃራኒ የሆኑ ምክንያቶችን በመደርደር ለሠላማዊ ሠልፉ ዕውቅና አልሰጠሁም ሲል ህዳር 22 ቀን  ድብዳቤ መጻፉን አስታውቀዋል። 

“በመሠረቱ መስተዳድሩ ጊዜና ቦታ እንዲቀየር አስተያየት ከማቅረብ ያለፈ ዕውቅና የመንፈግ መብት የሌለው በመሆኑ ትብብሩ የደብዳቤውን መልዕክት ያልተቀበለ መሆኑንና ሠልፉም በታቀደው ጊዜና ቦታ እንደሚደረግ ወስኖ የመልስ ደብዳቤ ” ማስገባቱንም ገልጸዋል።

የፓርቲዎቹ መግለጫ አያይዞም “ትግላችን ነጻነታችንና ክብራችን የማስመለስ በመሆኑ መንገዱም ፍጹም ሠላማዊ፣ ህጋዊና  ህገ- መንግሥታዊ ስለሆነ የህዳር 27/28  ሠላማዊ ሰልፍ የማይቀርና የማይቀርበት መሆኑን ለመግለጽና ነጻነትና ክብርን ወዳድ ኢትዮጵዊያንና የፖለቲካ ኃይሎች በሙሉ ለዚህ ታሪካዊ ዕለትና ሠላማዊ ትግል ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ጥሪያችንን እናቀርባለን።” ብሎአል። 

ከ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የተሰጠ መግለጫ

ኑ- ለነጻነታችንና ክብራችን ድምጻችንን በጋራ እናሰማ!

ከባርነትና ውርደት ለመላቀቅ ነውና በፍጹም አይቀርም፣ አይቀርም!

የ9ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ ››በሚል መርህ የመጀመሪያ ዙር ዕቅዱን ለህዳር ወር አዘጋጅቶ ወደ እንቅስቃሴ ከገባ ሦስት ሣምንታትን አሳልፏል።  

Monday, December 1, 2014

ህጋዊ ተቃዋሚዎችን በአክራሪነት ሰበብ ለመምታት የሚያስችሉ ሃሳቦች ቀረቡ

ኀዳር ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ህገ መንግስት አንቀጽ 31 መሰረት በህጋዊ መልኩ ተመዝግበው ሰላማዊ የፖለቲካ እንቃስቃሴ የሚያደርጉ ተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በሽብርተኝነት እና ጽንፈኝነት በመፈረጅ የጥቃት ኢላማ ለማድረግ መታሰቡን ኢሳት የፌደራል መንግስት የጸጥታ ጉዳዮች ሰሞኑን ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር  ካካሄደው ውይይት ለመረዳት ተችሎአል።

የትግራይ፣ቤንሻንጉል ጉሙዝና አማራ ክልል ሃላፊዎች ሰማያዊ ፣አንድነትና መኢአድ ፓርቲዎች ጽንፈኞች በመሆናቸው በአክራሪነት ሲሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን በማሰባሰብ ለሽብር እያዘጋጁ ነው በማለት የገዢውን መንግስት ፖሊሲዎች በሰላማዊ መንገድ የሚቃዎሙትን ፓርቲዎችን በወንጀለኛነት ሲፈርጁ ተደምጠዋል። 

መልካም ተሞክሮ ነው በማለት በየክልሉ አስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ኃላፊዎች የቀረበው ሪፖርትና የወደፊት እንቅስቃሴ በመጭው ምርጫ 2007 የተፈረጁት ፓርቲዎች የህዝብ ድምጽ በማግኘት የገዢው መንግስት ስጋት እንዳይሆኑ ከማሰብ የተነሳ መሆኑን የውስጥ ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።