ይህ ፅሁፍ የሚያተኩርበት ዋና ጉዳይ ወያኔ ‚ታላቋን ትግራይ‛ ተብላ የምትጠራ አገር ለመመስረት ሲል በጎንደርና በወሎ ህዝብ ላይ የፈጸመውንና አሁንም እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋት(genocide) እና ትግራይ ያልሆነ ህዝብን ማፈናቀሌ (ethnic cleansing) ወንጀልች ሊይ ነው። በመላ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የኢኮኖሚ ገፈፋና በየትኛውም የመንግስትና የግል የኑሮ ዘርፎች የትግራይ የበላይነት ለማረጋገጥ ሲባል ወያኔ በሌላው ኢትዮጵያዊ ላይ የሚያካሂደውን የሽብር ዘመቻ የዚሁ መሰሪ አላማ አካል ነው። ከዚያ ባሻገር ጎጠኛ አስተዲደር (ethnic federalism) እና የመገንጠል አንቀጽ (አንቀጽ 39) የተባለት አንኳር የወያኔ መርሆች አገልግሎታቸው ወያኔ እንደሚለፍፈው የብሔሮችን እኩልነት ለማረጋገጥ ሳይሆን ሌሎች ብሔሮችን በማፈናቀልና በማራቆት የትግራይ ክልልና የትግራይ ተወላጆች ሀብት እንዱያካብቱና ለሚመሰርቷት ታላቋ ትግራይም ስትራቴጂካዊና ውሀ ገብ ለም መሬቶችን ለመንጠቅ እንዲያመቸው ያስቀመጣቸው ለመሆናቸው ይህ ጽሁፍ አባሪ መረጃዎች ያቀርባል። ወያኔ በጎንደርና በወሎ ህዝብ ላይ የሚፈጽማቸው ወንጀሎች በግብታዊነት የተከሰቱ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ በተጠና እቅድ መሰረት ነው።
ወንጀሎቹ ከሞላ ጎደል የሚከተለው ቅደም ተከተል አላቸው።
1. ለምና ስትራቴጂካዊ (strategic) የሆኑ ቦታዎችን ትግራይ ካልሆኑ ህዝቦች በመንጠቅ በትግራይ ክልል ስር እንዲጠቃለሉ ማድረግ፤
2. በተነጠቁ ቦታዎች ላይ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የትግራይ ሰዎችን ማስፈር፤ ከትግራይ ክልልና ከማእከላዊ የወያኔ መንግስት በሚለገስ ገንዘብ አማካኝነት አዲስ የትግራይ ሰፋሪዎችን ሀ) ማስታጠቅ፣ ለ) በእርሻና በሌላ የልማት መስኮች ማደርጀት፤
3. በአዱስ ታጣቂ ሰፋሪዎች አማካኝነትም በነባሩ ህዝብ ሊይ የማፈናቀልና የማሳደድ ዘመቻ በመክፈት አካባቢውን የትግራዮች ብቸኛ ሀብት ማድረግ፤
4. መስፋፋቱንና በሃይል መፈናቀሉን በቆራጥነት የሚቃወሙትንና በነዋሪው ህዝብ ዘንድ ተሰሚነት አላቸው የሚሏቸውን ግለሰቦችን ማፈን፣ ማሰርና መግደል፤ የቀሩትን ሰዎች በማንገላታት ቢቻል ክልሉን ለቀው እንዲሰደዱ ማዴረግ ካልተቻለ ደግሞ ለምነት በሌላባቸው መሬቶች ተጨናንቀውና ተጣበው እንዲታሰሩ በማዴረግ ለከፍተኛ ችግርና ረሀብ እንዱጋለጡ ማድረግ፤
5. የኗሪውን ህዝብ የደረሱ ልጃገረዶች በትግራይ ጎረምሳ ኮርማዎች ማስደፈር፤ (rape ማስደረግ)፤ በዚህ ባህልን፣ ሃይማኖትንና ሰብአዊነትን ባዋረደ ተግባር የትግራይ ዘር ያላቸውን
ልጆች እንዲወልዱ ማድረግና ከዚያ በበለጠ ደግሞ ሌላ ትግራይ ያልሆኑ ወላጆችንና ወንድ ወጣቶችን ቅስም መስበር ነው።
ከላይ በዝርዝር የቀረቡት የወንጀል ዝርዝሮች ስፋት ባለውና በጣም በከረረ መልኩ የሚካሄደት ወልቃይት ጠገዴ አርማጭሆና ብራ ዋስያ በተባለ የጎንደር ክፍሎች ስለሆነ በዛሬው ጽሁፋችን ወያኔ በጎንደር ህዝብ ላይ የሚያደርገው ዘረኛ ዘመቻ ላይ እናተኩራለን። ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንም በደንብ እንዲረዱት ለማዴረግ ሲባልም ከወያኔ ጓዳ ያገኘናቸውን 5 ካርታዎች በአባሪነት እናቀርባን።
ሀ) ከ1991 እ.አ.አ በፊት የነበረው ትግራይና የአሁኑ የትግራይ ክልል (ካርታ1 ይመልከቱ)
1. በወይን ጠጅ (pink) የተቀመጠው ከ1991(እ.አ.አ.) በፊት የነበረው የትግራይ ግዛት ነው።
2. በአረንጓዴ የተመለከቱት
ሀ) 1991 (እ.አ.አ.) ከወሎ ተነጥቆ ትግራይ የተጨመረውን የአሸንጌ ባህርን፣ የወራ ውሃንና ኮረምና አላማጣን የሚያካትተው ለም መሬት
ለ) በ1991 (እ.አ.አ) ከጎንደር ተነጥቀው የተወሰዱትን የሁመራ፣ የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የዋልድባ ክልል፣ ብራ ዋስያንና ጠለምት መሬቶች፤
3. የዛሬ 11 ዓመት (2002) በአማራው ክልል ከነበረው ከጠገዴ ክፍል ግጨው የተባለው የእርሻ ቦታና አብደራፊ ከተማን የሚያካትተው የታች አርማጭሆ የእርሻ መሬት ነው።
ለ) የተነጠቁት ቦታዎች በዝርዝር ሲታይ፤
1. ሁመራና አካባቢው
በአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመን ሁመራ ራሱን የቻለ ወረዳ ነበር። ዋና ከተማውም ሁመራ ይባልል። ሁመራ በአብዛኛው ጥቁር አፈር (ዋሌካ) የሆነ ሰፊ ቦታ ሲሆን ተከዜን ተከትሎ ኤርትራን በሰሜን፤ ሱዳንን በምእራብ ያዋስናል። በምስራቅ የዳንሻን ከተማንና አካባቢውን ጨምሮ የወልቃይት ጠገዴ ወይና ደጋዎችን ተጓድኖ ወደ ደቡብ በመዘርጋት ከጎንደር ደጋማ ክፍል ተነስቶ ወደ ሱዳን ከሚፈሰው ከአንገረብ ወንዝ ይደርሳል። ከአንገረብ ወንዝ በስተደቡብ እስከ መተማ ድረስ ያለው የሁመራ መሰል መሬት የአብደራፊ ከተማ ጨምሮ የሚያካትተውን የግማሽ ጠገዴን፣ የአርማጭሆና የጫቆ ቆላ መሬት ነው።
ሁመራ ወያኔ በጉልበት እስከነጠቀው ጊዜ ድረስ ምንጊዜም በጎንደር የበላይ አስተዳደር ስር ሆኖ በወልቃይትና ጠገዴ ህዝብ ባለቤትነት ሲተዳደር የቆየ የእርሻና የከብት እርቢ ቦታ ነበር። በአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት ደግሞ ዘመናዊ ሰፋፊ የግል እርሻ ከተስፋፋባቸው የኢትዮጵያ ክፍሎች አንዱ ነበር። በዚያን ዘመን ምንም እንኳ መንግስታዊ መዋቅሩ በወልቃይትና ጠገዴ ሰዎች ስር የነበረ ቢሆንም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ (ከኤርትራና ከትግራይ ጭምር) ያልተከለከለበት እንዲያውም ወደ አካባቢው በመጉረፍ የግልና የጋራ ሰፋፊ እርሻዎች ባለቤት ለመሆን የበቃበትና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን ወደ የተሻለ ነዋሪነት የተሸጋገሩበት ነበር። ከዚህ ሌላ ከሁመራ እስከ መተማ የተንጣለለው መሬት ላይ በሚመረተው ሰሊጥ፣ ጥጥና ማሽላ ለኢትዮጵያ የእህል ጎተራና የውጭ ገንዘብ ምንዛሬ ዋና ምንጭ ሆኖ ነበር። ልማቱ ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት ዘመንም በሁመራ ብቻ እንኳ ብዛቱ ከ700,000 በላይ የቀንና የኮንትራት ባሙያ ሰራተኛ የተሰማራበት ነበር።
3.ሰራተኛውና አሰሪው ከባሌና ሲዳሞ እስከ ኤርትራ ጫፍ ድረስ የሚመጣ ስለነበር የጎሳና የዘር ጥያቄ የሚታሰብ አልነበረም። ዛሬስ? ከ1991 (እ.አ.አ) ጀምሮ ሁመራና የዳንሻ አካባቢ በይፋ በትግራይ ክልል ተጠቃሏል።ከዛም እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ ከ25,000 ያላነሱ የወያኔ ተዋጊ የነበሩ የትግራይ ተወላጆች በዳንሻ ከተማ ዙሪያ እንዲሰፍሩ ተደረገ።ቀጠለና በትግራይ ክልል አስተዳደር አቀናባሪነት ተጨማሪ የትግራይ ተወላጆች ወደ ሁመራ እንዲነጉዱ በማድረግ በመላው የሁመራ መሬት ላይ የትግራይ ተወላጆች ብቻ ያካተቱ መንደሮች ተቆረቆሩ። አዲስ ታጣቂ ቡድኖችም በየመንደሩ ተደራጁ። በአዲስ ታጣቂ ሰፋሪዎች አማካይነትም የወልቃይትና የጠገዴ ገበሬዎችና ቤተሰቦቻቸው ከሁመራና ከዲንሻ ከተሞችና ከገጠሩ የርሻ ቦታዎች እየታደኑ መጀመሪያ የጦር መሳሪያቸው ተነጠቀ፣ ከዚያም ያልተቋረጠ አፈናና እስራት ተፈጸመባቸው። ከእስራትና ከግዴያ የተረፉትም አባቶቻቸው ከቱርክ፣ ከግብጽና ከጣልያን ወራሪዎች በአጥንታቸውና በደማቸው አጥረው ከአቆዩአቸው መሬት ተፈናቅለው በአራት አቅጣጫ ተሰደዱደ።የመጀመሪያው ክፍል ወደ ሱዳን በመሄድ በስደት መኖር ጀመሩ። ሁለተኛው ክፍል ወደ ጎንደር ከተማ ተሰደደ። ሶስተኛው ክፍል ወደ ወልቃይት ጠገዴ ወይና ደጋዎች በመሄድ ከሌሎች ወገኑ ጋር ተጣቦ መኖሩን ወሰነ። አራተኛውና በቁጥርም በዛ ያለው ክፍል ከአርማጭሆ፣ ከቋራና ከጭልጋ ህዝብ ጋር በመጠጋት አብደራፊንና መተማን ከሚያካትቱ መሬቶችና ሽንፋ በረሃ በሚባለው የቋራ ቆላ መሬት በማረስ አዲስ ኑሮ ጀመረ። (ጥቂት ወረድ ብለን ወያኔ አራተኛውን ክፍል በተሰደደበት ቦታ ተከትሎ እንዳፈናቀላቸውም እናያለን።)
ዛሬ በሁመራ ወረዳና በዳንሻ ከተማ አካባቢ ከ475,000 በላይ የትግራይ ተወላጆች ሰፍረዋል። የሁመራ ከተማ ብቻ ከ150,000 ያላነሰ የህዝብ ብዛት ሲገኝባት ከሶስት ወልቃይቴዎች በስተቀር የቀሩት የትግራይ ተወላጅ ናቸው። እነዚህ ሶስት ወልቃይቴዎች እንዴት የዘሩን ወንፊት አምልጠው ሊቀመጡ እንደቻሉ በብዙ ወልቃይቴዎች እንደ ትአምር ነገር ይወራል።
ላለፉት 20 አመታት የሁመራ ወረዳና የዳንሻ አካባቢ ለአዲሶቹ የትግራይ ሰፋሪዎች ማርና ቅቤ የሚፈሰባቸው የከንዓን መሬቶች ሁነዋል። ከትግራይ ክልል እና ከማእከላዊ መንግስት በገፍ በሚለገስ በዘመናዊ የእርሻ መሳሪያና የገንዘብ ድጋፍ ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላ፣ እጣንና የከብት ርቢ ከምን ጊዜውም በላይ በመመረት ላይ ይገኛል። አብዛኛው ምርት በሱዳን በኩል ለአለም ገበያ በመቅረብ ለትግራይ መንግስት ዋና የውጭ ምንዛሬ ምንጭ ሆኗል። ባንጻሩ ዘመን ከተቆጠረ ጀምሮ ባለይዞታ የነበሩት የውልቃይትና የጠገዴ ህዝቦች ለሁሉ ኢትዮጵያዊ በተሰወረ ጭካኔና ዘረኝነት አባቶቻቸው ባጥንታቸው አጥረው ካቆዩአቸው መሬቶች ተፈናቅለው በስደት ይገኛሉ።
2. የወሌቃይት መዘጋ (ካርታ 1 ይመልከቱ)፤
ከሁመራ ወረዳ ወደ ምስራቅ የሚዘረጋው በቆላነትም ይሁን በአፈር አይነት ሁመራን የሚመስለው መሬት የወልቃይት መዘጋ ይባላል። የወልቃይት መዘጋ በሰሜን በተከዜ ወንዝ አከፋፋይነት ኤርትራንና የሽሬ አውራጃ (ትግራይ) አዋስኖ በደቡብ በኩል መላውን የወልቃይት ወይና ደጋውን ታኮ በሁለት ወንዞች መካከል ከሚገኘው የዋልድባን ገዳም ድንግል መሬት ይቀላቀላል። መዘጋው ለዘመናት ሁመራ መሄድና ማረስ ለማይፈልግ ወይንም ለማይችል የወልቃይት ህዝብ የእርሻ ቦታና የከብቱ መሳደጃ ነበር። ባለፉት ሁለት መቶ አመታት ደግሞ ከወይና ደጋው ወደ ቆላው ወርደውና መንደሮችን ቆርቁረው ሙሉ ኑሯቸውን ያደረጉ ወልቃይቴዎች እየበረከቱ በመሄዱ አዲጎሹ፣ መጉእ፣ ቃሌማ፣ እጣኖ ማይ ሃርገጽ የመሳሰሉትን ከተሞች ቆርቁረው አስፋፉ።
4.ዛሬስ? ወያኔ በመዘጋ የሚኖሩትን ወልቃይቴዎች ማፈናቀል የጀመረው ገና በዱር አሸባሪ በነበረበት ወቅት ጀምሮ ነው።በስልጣን ከተረጋጋ በኋላ ደግሞ አፈናውና ግድያው ተጠናክሮ ብዙ ቤተሰቦች ለወሬ ነጋሪ እንኳን ሰው ሳይተርፋቸው ተገድለዋል። ለምሳሌ አቶ ማሞ ዘውዱ የተባሉ የአዳጎሹ ነዋሪ ወልቃይቴ ዘጠኝ ቤተሰቦቻቸው ጋር ነበር የተረሸኑት። ዛሬ መዘጋው አንድም ወልቃይቴ ብቅ እንዳይልበት ተከልክሎ 100% የትግራይ ተወላጆች ሃብት ሆኗል።
ወያኔ እስካሁን ድረስ በመዘጋው ያሰፈረው የትግራይ ተወላጅ ከ 180,000 በላይ እንደሆነም ይነገራል። እነዚህ አብዛኛዎችም የታጠቁ ሲሆኑ ዋናው ስራቸውም ሰሊጥ፣ ጥጥ፣ ማሽላና እጣን ማምረት፤ ከብት ማርባት እና ወልቃይቴው ከወይና ደጋ አፋፍ እንዲይወርዱ መጠበቅ ነው።
በአጠቃላይ በሁመራ፣ በዳንሻ አካባቢና በወልቃይት መዘጋ የተደረገው ዘር ማጥፋት (genocide) በዩጎዝሊቪያው ከሆነው የማይተናነስ ነው። ልዩነቱ ወያኔ የሚፈጽመው ወንጀል ከአለም የዜና አውታሮችና ከአዱስ መገናኛ ዘዳዎች (ፌስ ቡክ፣ ትዊተር…) የተሸሸገ መሆኑ ብቻ ነው።
3.የዋልድባ፣ የጠለምት፣ የአላማጣና የኮረም አካባቢዎች
በ1991(እ.አ.አ) ወያኔ አዱስ አበባ በገባ ማግስት አንድ ደረቱን የነፋ የወያኔ ካድሬ የአዳርቃይን ከተማ ህዝብ ሰብስቦ ‚እንደምታውቁት የትግራይ ግዛት ጠለምትንና አዳርቃይን አጠቃሎ የሰሜን ተራራዎችን ማለት ራስ ደጀንና ጃንአሞራን ይጨምራል…‛ ብሎ ንግግሩን ሲከፍት በትዝብት ከሚሰሙት ህዝብ መካከል ፊታውራሪ ያይኔ የተባሉ አዛውንት ተነስተው ‚ይህን ታሪክ ማነው የነገራቹህ? የነገራቹህ ሰው ፍጹም አሳስቷቹኋል። ትግራይ የሚባለው ግዛት ከተከዜ ወንዝ ማዶ ነው ከተከዜ ወዲህ ያለው መሬት ትግራይ ሆኖ አያውቅም። አሁንም ለወደፊት እንዳትሞክሩት..‛ ብለው መለሱለት። የሚያስደንቀው ነገር የሰቆጣ (ወሎ) ህዝብ ለወያኔ የሰጠው ምላሽ የአዳርቃይ ህዝብ ከሰጠው ምላሽ ፍጹም ተመሳሳይ ነው። በ1991(እ.አ.አ) የሰቆጣን አካባቢ ወደ ትግራይ ለማድረግ ወያኔ ሲከጅል የሰቆጣ ህዝብ የሰጠው መልስ ‚እኛ የዛጔዌ ዘር ነን ከማእከላችን ከላሊበላና ከመላው ከወሎ ህዝብ ወጥተን መኖር አንችልም።በታሪካችን የትግራይም ሆነን አናውቅም።‛ የሚል ነበር። በጊዜው የወያኔ መንግስት ያልተረጋጋ ስለነበር ከወሎ የወይራ ውሃን፣የአላማጣንና የኮረምን ለም አካባቢ ከጎንደር ደግሞ ከወልቃይት ጠገዴ በተጨማሪ ማይጸምሪ የተባለችውን ከተማ ማእከል በማድረግ የዋድልድባ፣ የብራዋስያንና የጠለምት አካባቢ ብቻ በትግራይ ክልል አጠቃለለ። ጠለምት የሚባለው በሰሜን ተከዜን ተከትሎ ተንቤንን፣ በምስራቅም ተክዜ ተከትሎ የዋግን አውራጃና በደቡብ የስሜን ተራራዎች የሚያዋስን ስትራተጂካዊ ደጋ፣ ወይና ደጋንና ቆላን የሚያካትት ቦታ ነው።
በ1991 (እ.አ.አ) በተደረገው ቅርጫ የቆቦ፣የአዲርቃይንና የስሜን ተራራን በይደር በአማራ ክልል እንዱቆይ ቢወሰንም በአሁኑ ጊዜ ወያኔ ስለተደላደለ የአዲርቃይን፣ የስሜን ተራራዎችንና የቆቦን አካባቢዎች ወደ ትግራይ ክልል ለማጠቃለል እየቋመጠ ይገኛል።
የ2010 (እ.አ.አ) አዱስ የትግራይ መስፋፋት ዘመቻ፤
አዱሱ የትግራይ መስፋፋት ዘመቻ በአብደራፊ፣ በአማራው ክልል ጠገዴ፣ በስሜን ተራራዎችና በመተማ በኩል በጉልህ እየታየ ነው።
ሀ) የአብደራፊ ከተማና አካባቢው፤
እስከ አለፈው አመት ድረስ በአማራው ክልል የነበረችው የአብደራፊ ከተማ አሁን በትግራይ ክልል ተጠቃልላለች። በዚህ አቅጣጫ ያገረሸው የትግራይ ተስፋፊነት የአብደራፊን ከተማ ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ከአንገረብ ወንዝ ወደ መተማ በኩል የዘረጋውንና ሱዳንን ከሚያዋስነው ጓንግ ተብሎ የሚጠራውን ታላቅ ወንዝ ተከትሎ ያለውን መሬትንም ያጠቃልላል። ይህ ሰፊ መሬት በማነኛውም የታሪክ ወቅት የቆላውና የወይና ደጋው የአርማጭሆ ህዝብ የእርሻና የከብት መሳደጃ ቦታ ነው። የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ ደጋግሞ ባወጣው መግለጫ እንደተገለጸው ከአብደራፊ ጀምሮ እስከ ጋምቤላ አክባቢ ድረስ ክ30 እስክ 60 ኪል ሜትር ስፋት ያለው መሬት ለሱዳን እንደተሰጠና በዚያም ሳቢያ ወያኔ የአርማጭሆን ህዝብ ከአብደራፊና ከአካባቢው ከ2006 አ.ም ጀምሮ እያፈናቀለው መሆኑን የሚታወስ ነው። አሁን ደግሞ ከሱዳን በተረፈው መሬት ላይ ምናልባትም አሁን ሱዳን በደቡብ በኩል የገጠማትን ውጥረት በመጠቀም ለሱዳን ተብል በተለቀቀው መሬት የ‛ታላቋ ትግራይ‛ ህዝብ እየተደላደለበት ነው። ከ2002 አ.ም ግንቦት ወር ጀምሮ ከ20,000 ያላነሱ የትግራይ ተወላጆች በአብደራፊና በአካባቢዋ ሰፍረው በእርሻና በልዩ ልዩ መንግስታዊ መዋቅሮች ተሰማርተዋል።ለዘመናት በባለቤትነት የኖሩት የአርማጭሆ ገበሬዎችና ቤተሰቦቻቸውም ግን ከከተማ ቤታቸውና ከገጠር የእርሻ ቦታቸው ታድነው እየተፈናቀሉ ወደ ምእራብ ካለው ከተጣበበውና ከተበላው የአርማጭሆ ወይና ደጋ መሬት በግድ እየተገፉ ይገኛሉ። በአሁኑ የወያኔ ዘረኛ የማፈናቀል ዘመቻ ከወልቃይትና ጠገዴ ተፈናቅለው በአርማጭሆ ህዝብ አጋዥነት በአብደራፊና አካባቢዋ አዱስ ህይወት ጀምረው የነበሩትን የወልቃይት ጠገዴ ስደተኛ ገበሬዎችና ቤተሰቦቻቸው ይገኙበታል። ሁለተኛ የማናቀል ዘመቻ ወንጀል ተፈጸመባቸው ማለት ነው። ወገኖቻችን ትግሬዎች ባለመሆናቸው እየደረሰባቸው ያለው የማጥፋት ዘመቻ አቻ አይገኝለትም።
ለ) ግጨው የተባለ የጠገዴ ቆላ መሬት፤
ባለፈው ስድስት ወራት የትግራይ ክልል አስተዳደር ለአማራው ክልል አስተዳደር ከአርማጭሆ ሰሜን ምእራብ የአንገረብ ወንዝን ተከትል ያለው ‚ግጨው‛ የተባለው የጠገዴ እርሻ መሬት ወደ ትግራይ ክልል መጠቃለሉን ይገልጻል። አንዲንድቹ የአማራ ክልል አስተዳደር ተብለው የተቀመጡ የወያኔ ሎሌዎች እንኳን በግልጽ በዚህ ‚አንስማማም‛ የሚል ተቃውሞ እንዳቀረቡ ቢነገርም እንኳ አሁን ግጨው የሚተዳደረው በትግራይ ክልል ስር ነው።
በዚሁብ አዲስ ባቀናው የግጨው አካባቢም የትግራይ ሰፋሪ መንደሮች እየተቆረቆሩ እንደሆነ የጠገዴ ገበሬዎች ይናገራሉ።
ለ) የመተማ ከተማና አካባቢው፤
ባለፈው ወር የኢትዮጵያ የዴንበር ኮሚቴ እና የኢሕአፓ ዴርጅት በመተማ ከተማ ያሊቸውን የየግሌ የዜና ምንጫቸውን ጠቅሰው ወያኔ በመተማ ከተማና በአካባቢው ያለትን ገበሬዎችና የከተማው ነዋሪ ህዝብ ሰብስቦ ‚…አካባቢው ለጦር ክምችትና ለጦር ማእከሊዊነት እንዲሆን ስለተወሰነ ወደ ምስራቅ ባለው የወይና ደጋው ጥግ ለመስፈር ዝግጅት እንድታደርጉ…‛ የሚል ዘመቻ መጀመሩን መዝግበዋል። በ2009 (እ.አ.አ) ነብስ ገቢያ በሚባለው የቋራ ቆላ ክፍሌ የሱዲን ወታደር አርሻ አቃጥሎ፣ ንብረት ዘርፎና ወገኖቻችንን ማርኮ ወደ ሱዳን ሲወስድ መተማ የተከማቸው የወያኔ ወታደር አንዲት ጥይት እንኳን አለመተኮሱን የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ በማያወላዳ ማስረጃ መመዝገቡ የሚታወስ ነው። ሰለዚህም መተማ የተከማቸው የወያኔ ወታደር ዋና ተግባሩ የኢትዮጵያኖችን ደህንነት ለማስጠበቅ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ወታደሩ እስካሁን ድረስ ያሳየው ታሪክ ቢኖርም የአማራውን ገበሬ ማፈናቀል፤ ማሰር፣ መግደልና ሃብት ማቃጠል ነው።ወደ ፊትም ከዚህ የተለየ አይጠበቅበትም። ይልቅስ በመተማ አቅጣጫ ያገረሸው የወያኔ መልቲ ዘመቻ ግልጽ ያደረገው ነገር፤
1. የትግራይ መስፋፋት በአብደራፊና በአካባቢው እንደማይቆም፤
2. የትግራይን ግዛት ከጣና ባህርና ከተቻለም ባሁኑ ወቅት አባይን እገድባለሁ እያለ ከበሮ ከሚደልቅበት ቦታ ለማድረስ ለሚደረገው የመጨረሻው ዘመቻ የመጀመሪያው መስተንግዶ (appetizer) መሆኑ ነው።
መ) የስሜን ተራራዎችና አካባቢው፤
የስሜን ተራራዎች የውጭ ወራሪዎችን በማስፈራራት ይሁን በማጥቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ብዙ የታሪክ ጠበብት የተረኩት ነው። በ1991(እ.አ.አ) ወያኔ የስሜን ተራራዎችን ወደ ትግራይ ለማጠቃለል አዱአርቃይ ከተማ ላይ ሙከራ አድርጎ አደገኛ ስለመሰለው ወደኋላ ማለቱን ከላይ ጠቅሰናል። ዛሬ ‚ከእኔ በላይ አዋቂ ላሳር ነው‛ ያለው ወያኔ የስሜን ተራራዎች የትግራይ ለመሆናቸው ወጣት ልጆችና የውጭ መንግስታት እንደ እውነት እንዲቀበሉት ከማድረግ አኳያ በስድስተኛ ክፍል የእንግልዝኛ መማሪያ መጽሀፍ ገጽ 148 ላይ (ሲተረጎም) እንዲህ ይላል፤ ‚ራስ ደጀን በስሜን ተራራዎች የሚገኝ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተራራ ነው። የሰሜን ተራራዎች በክሌሌ አንድ (ትግራይ) ውስጥ ይገኛል።…..‛ ይላል። ይህ የወያኔ ስትራቴጂክ የስሜን ተራራዎችን ወደ ትግራይ ለማስገባት ለሚያደርገው ዝግጅት ሌላው የመጀመሪያው መስተንግዶ (appetizer) መሆኑ ነው።
የምእራብ ጎንደር ወይና ደጋው ክፍል በር የሌላቸው የወያኔ እስርቤቶች ስለመሆናቸው፤
ከመካከለኛው ምስራቅ የሚነሱ ጠላቶች ሁሌጊዜም ኢትዮጵያን ሲአጠቁ መረማመጃ ያደረጉት ዋና ከከሰላ እስከ ኦሜድላሊ (ጎጃም) ያለው አካባቢ ነበር። የነዚህ ተጋፊ የኢትዮጵያ ጠላቶችን የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ የምእራብ ጎንደር ህዝብ ነበር። ለአጼ ተዌዴሮስ መነሳት ለአጼ ዮሃንስም መሰዋእትነት ምክንያት የሆኑት በዚሁ አካባቢ የኢትዮጵያን ልእልና ለመድፈር የተደረጉ ሙከራዎችና ጦርነቶች ናቸው። የምእራብ ጎንደር ህዝብም ድንበሩን ለመከላከል ሲል ያልተቋረጠ መስዋእትነትን ከፍሎበታል።
በ15ኛው ምዕተ አመት (ከግራኝ መሃመዴ ወረራ) ጀምሮ የአርማጭሆ፣ የወልቃይት፣ የጠዴ፣ የጫቆና የቋራ ህዝብ ‘ድንበር ጠባቂ’ ተብሎ ስያሜ ተሰጥቶት በማህል ኢትዮጵያ በሚነሳ ጦርነት እንዳይሳተፍ በአዋጅ የተከለከለ ነበር።በዚህም ምክንያት የወልቃይት፣ ጠገዴ፣ የአርማጭሆ፣ የጭሌጋና የቋራ ህዝብ ቤተሰቡን ያሰፈረው ከጠላት ለመመከት የተሻለ ከሆነው ከወይና ደጋው ነው። የምእራብ ጎንደር ወይና ደጋዎች፤ አዳረመጥ የተባለውን የወልቃይት ከተማና አካባቢውን፣ ቀራቅር የተባለውን የጠገዴ ከተማና አካባቢውን፣ የአርማጭሆ የጭልጋና የቋራ ወይና ደጋ መሬቶችን ያጠቃልላል። ይሁንና የወይና ደጋው አፈር በውሀ የተሸረሸረ፣ መሬቱም በህዝብ ሰፈራ የተሰላቸና የተጣበበ በመሆኑ በቆሎና ድንች ከመሰለ አነስተኛ ምርቶች በስተቀር የወይና ደጋው ህዝብ የሚተዳደረው በቆላው መሬት በሚያመርተው ምርትና ከብት እርባታ ነው። ለአለፉት ሁለት መቶ አመታት ደግሞ የወይና ደጋው ህዝብ እርሻውንና ከብት ርቢውን በመከተል በቆላዎች ሰፈራዎችን አስፋፍቶ፤ በወልቃይት መዘጋ (አዳጎሹ፣መጉእ፣ቃላማ፣እጣኖ፣ማይሃርገጽ..)፣ የሁመራ፣ የዳንሻ፣ የአብደራፊ፣ የመተማና በቋራ እንደ ዮሀንስ የመሳሰለትን ከተሞችን ቆረቆረ። ይህ ደግሞ የድንበር ጥበቃውን በይበልጥ አጠናከረው።በዚህም ምክንያት ነበር ጣልያን በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በአርማጭሆና በመተማ አካባቢ ከፍተኛ ሽንፈት የደረሰበትና አካባቢውም ከየትም ለመጣ የኢትዮጵያ አርበኛ ቡድን ከፍተኛ ምሽግ ሆኖ የቆየው።የወያኔ መሪዎች ግን ገና ሀ ብለው እንቅስቃሴ ሲጀምሩ ዋና ተልእኮ አድርገው የያዙት የዚህን ዳር ድንበር ጠባቂ ህዝብ የጀርባ አጥንት መስበር ነው።ይህንንም ህዝብ ነው ትግሬ ባለመሆኑና በተለይም አማራ በመሆኑ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት በወያኔ እቅድ የወጣለት።
ዛሬ የወልቃይት፣ የጠገዴ፣ የአርማጭሆ፣ ጫቆና ቋራ ህዝብ አማራ በመሆኑ ብቻ ለዘመናት ከሞተለት መሬት ተፈናቅሎ በተጨናነቁ በምእራብ ጎንደር ወይና ደጋዎች ታጉሯል። የተጣበበው ህዝብ እንደ አባቶቹ ወደ ቆላ መሬቶቹ ወርዶ ከብት አርብቶና አርሶ እንዳይበላ የትግራይ ክልል አስተዳደር እስክ አፍንጫቸው ባስታጠቋቸው የትግራይ ሰዎች ይጠበቃለ፤ ይህ አሌበቃ ብል ዯግሞ በወይና ዯጋዎቹ ሊይ በማንአለብኝነት የተደራጁት የወያኔ አስተዳዳሪዎች በሰበብ አስባቡ (መሳሪያ አሽገሀል….ወዘተ..) በማለት ሁለንም ቤተሰብ ያንገላቱታል፣ያስሩታል። በተለይ ወጣት ወንዶች ከፍተኛ ያፈና በደልም ይፈጸምባቸዋል።
በዘላቂ መንገድም የወይና ደጋው ህዝብ የሽንፈትና የወኔ መፍሰስ ስሜት እንዲያድርበት ወያኔ ከህዝቡ አብራክ የወጡትን ልጃገረዶችን በትግራይ ጎረምሳ ኮርማዎች ግብረ ስጋዊ አመጽ ያስፈጽምባቸዋል። ይህ በተለይ በወልቃይትና ጠገዴ ወይና ደጋዎች በሰፊው የሚካሄድ ወንጀል ነው።
በአጠቃሊይ ዛሬ የምእራብ ጎንደር ወይና ደጋዎች በር የማያስፈልጋቸው የወያኔ እስር ቤቶች ሆነዋል።
ወያኔ በ1991 (እ.አ.አ) ለሽግግር መንግስት ያቀረበው ካርታ 2 እና 3
ካርታ2 እና3 በ1991 (እ.አ.አ) ወያኔ ሽግግር መንግስት ለሚባለው ያቀረባቸው የአማርኛና የእንግልዝኛ ካርታዎቹ እንደሚታየው ቤን ሻንጉል የተባለው ክልል (ክሌሌ6) ተለጥጦ አንገረብ ወንዝ ላይ ከትግራይ ክልል ጋር ይገጥማል።የዚያ አላማ አማራውን ከለም መሬቶች ለማፈናቀልና ከውጭ አገር ጋር ግንኙነት እንዳይኖረው ለማዴረግ ነበር። ይሁንና በጊዜው ሊፈጠር የሚችለውን ከፍተኛ አመጽ በመፍራት ወያኔ ካርታውን ለመቀየር ተገዶል። ዛሬ ቀስ በቀስ ግን ባልተቋረጠ መልኩ አማራውን ለማፈናቀል ድሮ የተሸረበው ሴራ በሰፊው እየተካሄደ ነው። በተሻሻለው የወያኔ የመስፋፋት ዘመቻ በቤንሻንጉል ፈንታ ታላቋ ትግራይ እንደ እስስት ምላስ ተለጥጣ አካባቢውን እንድትውጥ እየተደረገ ነው።
የ‘ታላቋ ትግራይ’ የመጀመሪያ ካርታ (ካርታ 4)
ካርታ 4 የሚያሳየው ወያኔ ለንደን ኮንፈረንስ ከመግባቱ በፊት ያዘጋጀውን ነው።
በዚህም ካርታ ‚ታላቋ ትግራይ‛ ከጅቡቲ እስከ ሱዳን ከዚያም የሰሜን ተራራዎችን አካቶ ወደ ጎንደር ከተማ ከሚያንደረድረው የዳባት ከተማን ሲያጠቃልል በወሎ በኩል ደግሞ ከሰቆጣ እስከ ላሊበላ ድረስ ነበር። የወያኔ የውስጥ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት አዲሱ የ ‛ታላቋ ትግራይ‛ ግዛት በምስራቅ በኩል እስከ ጅቡቲ ያለው እንዳለ ሆኖ ከሰቆጣ እስከ ላሊበላ ድረስ ያለውን ወደ ጎን በማድረግ በዚያ ፋንታ ከሁመራ ጀምሮ ጣናና ቤንሻንጉልን ጨምሮ እስከ አባይ ወንዝ ድረስ መሄድ ነው። አሁን በምእራብ ኢትዮጵያ የሚደረገው ተስፋፊነትም እነዚህን የውስጥ ምንጭ መረጃዎች በበለጠ ያጠናክራል።በቅርቡ ደግሞ የትግራይ ክልል አስተዳደር ከሁመራ እስከ ፖርት ሱዳን ከዚያም
ከመቀሌ እስከ ጅቡቲ ድረስ የባቡር ሃዲድ ለመዘርጋት ይፋ ያደረገው እቅድ ሌላ ተጨማሪ መረጃ ነው።
ውዴ ኢትዮጵያዊያን ሆይ!
ወያኔ ለሚያደርጋቸው ማንኛውም ተግባር መሰረታዊ አንቀሳቃሽ ሀሳብ የ‛ታላቋ ትግራይ‛ አገርን ለመመስረት ያለው ቁርጥ ውሳኔ ነው። በርግጥ ይህ ‚ታላቅ‛ እየተበለ የሚለለቀው መዝሙር ምንም አይነት የትልቅነት ባህሪይ የለውም።እንዲያውም በጣም ትንሽ፣ለዘመናት የተሳሰረውን ህዝብ የሚለያይ ወራዳና የሚያሳፍር መርህ ነው።ብልህነትና ሰፊ አመለካከት ባህል በሚገዛቸው የኤስያ መሪዎች (ኮሪያ፣ ቬትናም ቻይና) ለዘመናት በትግል የተዋደቁትና አሁንም የሚታገሉት በድንበርና በግዛት የተነጣጠለውን ህዝባቸውን ሰፊ በሆነ አንድ አገር ውስጥ ለማኖር ነው። እንደዚህ ዓይነት ታላቅ ሀሳብ በወያኔ ዱ.ኤን.ኤ (DNA) በፍጹም የለም።የወያኔ መሪዎችና አጫፋሪዎቻቸው የትልቅ ሀሳብ ፍጹም ድሀዎች ናቸው። የሀሳብ ድሀዎች ባይሆኑ ኖሮ አብዛኛውን የኢትዮጵያ ህዝብ በማደኽየት የትግራይን ብልጽግና እናመጣለን ብለው ባላሰቡ ነበር።የወያኔ መሪዎችና አጫፋሪዎች አርቀው የሚያስቡ ቢሆኑ ኖሮ አሁን ኢትዮጵያን ለማስተዳደር ያገኙትን እድል ተጠቅመው ሁለንም ኢትዮጵያዊ በማሳደግና በማቀራረብ የትግራይን ህዝብ ተወዳጅነት ባተረፉለት ነበር። በዚህ ፋንታ የወያኔ ስርአት ዋና መለያ የሆነው አሸባሪነቱ ብቻ ሳይሆን በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኘውን የኢትዮጵያ ህዝብ መተዳደሪያና የኑሮ አውታሮች ነጥቆና ጋፎ ለትግራይ ተወላጆች ብቸኛ ሀብት ማድረግ ነው። በአገር ደረጃ ጠቅላይ ምኒስትርነቱን፣ በቤተክርስቲያን ፓትሪያርክነቱንና በወታደራዊ መዋቅሩ የበላይ የጦር አበጋዝነቱ የትግራይ ብቻ እንዱሆን የተደነገገ ይመስላል። ለይስሙላ ከተቀመጡት አሻንጉሉቶች በስተቀር በሁለም የቢሮክራሲ እርከኖች ቁልፍ ቦታዎች የተያዙት በትግራይ ተወላጆች ነው። የከተማውን አጠቃላይ የኑሮ እንቅስቃሴ ስንመለከት ደግሞ የጫቱ፣ የሽሻውና የቢራው አከፋፋይነትና ባለቤትነት፤ የጅምላው የችርቸራው የአስመጭና ላኪ ንግዱና ባለቤትነት፣ የመንገዶችና የቤት ስራ ተኮናታሪነት፣ የቦሌ መንደሮችና የአራት ኪሎ አፓርትመንቶች ባለቤትነት፣ የመጻህፍትና የሙዚቃ ህትመትና የሬሳ ሳጥን ተቋራጭነት ውዘተ.. በሙሉ በትግራይ ተወላጆች ብቻ እንዲሆን በአዋጅ የወጣ ይመስላል።በመንግስት ቢሮክራሲ፣ በንግዴና በሌላ የግል ስራዎች ይተዳደሩ የነበሩት የከተማ ወገኖቻችን የስራ መስካቸው ተነጥቆ በርሃብና በእርዛት እስከነ ቤተሰቦቻቸው ይታሻሉ።
በገጠሩ አካባቢ ይህ ‚ለትግራዎች‛ ብቻ የሆነው ያልጠግብ ባይ አዋጅ ሁለት ዘርፎች ይዞ ይገኛል፤
ሀ) የትግራይ ክልል ሊለጠጥ በሚችሉ ቦታዎች ኢትዮጵያዊ ገበሬዎችን ከቀዬ መሬታቸው አፈናቅል (ገድሎ፣ አስሮ..) በምትካቸው የትግራይ ሰዎችን ማስፈርና ማበሌጸግ፤
ለ) የትግራይ ክልል ዘሎ ማዳረስ ባልቻለባቸው ቦታዎች ደግሞ ኢትዮጵያዊያኖችን አፈናቅሎ (ብዙ ግድያም ፈጽሞ ለምሳሌ የአኙዋክ ወገኖቻችንን) ለሙን መሬት ለህንዴ፣ ለቻይና፣ ለማላዥያና ለሳኡዳ አረቢያ ለመሳሰሉ መንግስታትና ከበርቴዎች መቸብቸብ (ካርታ 5 ይመልከቱ)፤ በዚያ ገንዘብ አማካኝነትም የወያኔ ባለስልጣናትንና የአጫፋሪዎቻቸውን የውጭ ባንክ ሂሳብ (አካውንት) ማድለብና፣ ውጭ ሀገር በሚገኙ ዘመድቻቸው አማካይነት በውጭ ሀገር መሬትና ቤት መግዛትና ልዩልዩ የንግድ አውታሮች ማስፋፋት። ከዚህ በተረፈ በአዱስ አበባና በሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶችና ከተሞች የተሰገሰጉት የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የወያኔ ካድሬዎች የሚያሳዩት ደረት መንፋትና ማንአለብኝነት የሚያሳፍር ነው። ለምሳሌ ጨለም ሲል በአዲስ አበባ ሸራተን ሆቴል፣ በሂልተን ሆቴል ጎጆዎችና በርዋንዳ ኤምባሲ አካባቢ ለነርሱ ብቻ በተሰሩ መጠጥ ቤቶች ውስኪ እያርከፈከፉ በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚያደርሱትን በደል እንደ ጀብዱ እያወሩ የሚያቧርቁት ሳቅና የሚያሳዩት የማናለብኝነት ስሜት
በጣም የሚያሳፍር የነርሱ ወገን ሆኖ መፈጠርንም የሚያስጠላ ነው። ከጥንት ጀምሮ የትግራይ ህዝብ አንደ የሚታወቅበት ባህሪው ፈርሀ እግዚያአብሄርነቱ፣ ትህትናውና ቸርነቱ ነው። ወያኔ ምን ቢግታቸው ነው እንደነዚህ አይነት ፍጥረታት ከዚያ ህዝብ አብራክ መውጣት የቻሉት? እንዴት ከርግብ እንቁላል እባብ ይፈለፈላል?
የወያኔ ዘረኛ አመለካከት፣ ይሉኝታ ያጣ ስግብግብነትና አሸባሪነት እንደ ክፉ የነቀርሳ በሽታ (metastasized cancer) መልካሙን የትግራይን ህዝብ ባህል እየወረረው ነው። ለዚህ ጉልህ ማስረጃ ከተፈለገ በሀገር ውስጥ የተንሰራፋው አሸባሪነት፣ ስግብግብነትና ማንአለብኝነት ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገር በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ በስፋት የሚታየው ጭፍንነት ነው። ድሮ በአጼ ኃይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት በውጭ ሀገር በትምህርትም ሆነ በሌላ የኑሮ ዘርፍ ይኖሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ያዩት በነበረው የፖለቲካ ነጻነትና የኢኮኖሚ እድገት የመንፈስ ቅናት አድሮባቸው ኢትዮጵያን ከነበረችበት የጭቆና ቀንበር ለማውጣት በነበረው ትግል የመጀመሪያዎቹ ተሳታፊዎች ነበሩ። ከነርሱ መካከል ከነበሩት አብዛኛዎቹ የመኳንንት ልጆችም የወላጆቻቸው ድሎትና እነርሱም ከሚጠብቃቸው የስኬት ኑሮ በማመጽ በትግሉ ቆራጥ ተሳትፎ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። በ1960(እ.አ.አ) በተሞከረው መገልብጠ መንግስት (የጀነራል መንግስቱ-ገርማሜ ነዋይ) ሆነ ከዚያ በኋላ ለተቀጣጠሉት እንቅስቃሴዎች በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈው ለሀገራቸው መስዋእት መሆናቸውን ታሪክ የመዘገበው ነው። ከነርሱም(ከመኳንንቱ ልጆች) ብዙዎቹም ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ የ‛መሬት ላራሹን‛ መፈክር አንግበው ወላጆቻቸውንና ዘመዶቻቸውን አቅፎና ደግፎ ከነበረው ስርአት ጋር በመፋለም ህይወታቸውን መስዋእት አድርገዋል።
የዘመናችን አሳዛኝ ገጽታ ግን በውጭ ሀገር የሚገኙ አብዛኛዎቹ የትግራይ ተወላጆች (የዘመኑ መኳንንት) በወያኔ ድርጊት በማፈር ፈንታ ሲፎክሩበትና ደረታቸውን ሲመቱበት መታየታቸው ነው። በተለይ የፖለቲካ ስብሰባ በሚካሄዴዱበት ጊዜና የወያኔ ወንጀል በሚዘረዘርበት ስአት ምንም ትርጉም የማይሰጥ ጥያቄ ጠይቀው መልሱን ሳይሰሙ በአጃቢነት ካስከተሏቸው ሆዳም አማራዎች‛ ጋር ስብሰባውን ረግጠው ይወጣሉ። እነዚህ በውጭ አገር የሚገኙ የትግራይ-ተወላጅ-የወያኔ ካድሬዎች የአሜሪካና የአውሮፓውያን ህግ ባይገዛቸው ኖሮ እነ መለስ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ወንጀል ዉጭ በሚኖረው ኢትዮጵያዊ ላይ ከመድገም የሚመለሱ አልነበሩም።
በውጭ ሃገር ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መካከል የወያኔን አሸባሪና ፀረ ኢትዮጵያ ባህርይን የሚያወግዙ በጣት ብቻ የሚቆጠሩ ናቸው። በደቡብ አፍሪካ አፓርታይዴ ዘመን ከማንዳላ ድርጅት (ANC) ጎን የቆሙ የደቡብ አፍሪካ ነጮች ቁጥር እንኳ ይህን ያህል አያንስም ነበር።
ውድ ወገኖቻችን ሆይ!
አገር ቤት ያለ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን፣ ሽማግላዎችና ባልቴቶች፣ ወጣት ሴቶችም ሆኑ ወንዶች ሕፃናትም ጭምር ‚የፍርድ ያለህ‛ እያለ እየጮህብን ነው። የወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በአፍሪካ ተንሰራፍቶ ከነበረው ከአውሮፓ ቅኝ ግዛትና በቅርቡ በብዙ መስዋእትነት ከተገረሰሰው የአፓርታይድ ስርአት በጣም የከፋ ነው። በዚህ አኳያ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ግልጽ መሆን ያለበት ጉዲይ አለ። በአጼ ኃይለስሊሴ ዘመነ መንግስት ወረዳ አስተዳዳሪ ቢበድል ወደ አውራጃ አስተዳዳሪ ቀርቦ አቤት ማለት ይቻል ነበር። ያ ደግሞ ፍርድ ካጓተተ ሥርአቱን ተከትሎ እስከ ዙፋን ችሎት ድረስ ይግባኝ ማለት ይቻል ነበር። ምንም እንኳ ሁሌጊዜም ሀቀኛና ፈጣን ፍርድ ይሰጥ ነበር ለማለት ባይቻልም የዳኝነት እርከኖች ግን የታወቁ ነበሩ። በወያኔ ዘመን ግን የትግራይ ክልል ቢፈልጥ ወንም ቢቆርጥ የት መሄድ ይቻልል? ከመለስ ዜናዊ፣ ከስብሃት ነጋ ወይንስ ከበረከት ስምኦን? ወይንስ ከአሻንጉሊቱ ከተገኘ
ጌታነህ (የአሁኑ ዋና ዳኛ)? በወያኔ ስርዓት በየትኛውም የስልጣን እርከን ተሸጋግሮ በትግራይ ተወላጅ ወንም በትግራይ ክልል ፍርድ ተጓደለብኝ ብሎ ይግባኝ መጠየቅ ማለት ፍየል ‚ተኩላ ሊበላኝ ያራሩጠኛል‛ ብላ ለጅብ አቤቱታ እንደማቅረብ ይቆጠራል።
ውድ ወገኖቻችን ሆይ፤
እኛ በበኩላችን የጀርመንና የአሜሪካ ድምጽ ሬዴዮ ጣቢያ የአማርኛ ፕሮግራም ክፍሎች ወደ ወሎና ምእራብ ጎንደር ጋዜጤኞቻቸውን እንዲልኩና ያለውን የህዝብ መፈናቀልና እልቂት እንዲያጣሩ ደጋግመን ጠይቀናል። ‚ባለፉት 20 አመታት ለኢትዮጵያ መንግስት ወደ ምእራብ ጎንደርም ሆነ ባጠቃላይም በአማራው ክልል ሂደን ጋዜጣዊ ሪፖርት እንድናጠናክር ደጋግመን ጠይቀን ፍቃድ ተከልክለናል‛ ብለው ነግረውናል። ስለዚህም የህዝብ መፈናቅልና ግድያ (genocide)፣ አካባቢውን ትግራይ ካልሆኑ ሰዎች ማጥራት (ethnic cleansing) እና ህዝብን በወይና ደጋዎች አጣቦ ለርሀብ ማጋለጥ (mass starvation) የመሳሰለትን ከባድ ወንጀሎች የሚካሄደት ከአለም ህዝብ በስተጀርባ በመሆኑ እውቅነት ያላቸው የሰው መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ወንጀል በሚሰራባቸው የኢትዮጵያ ቦታዎች ሰዎቻቸውን በመላክ ጭብጥ መረጃዎች እንዲሰበስቡ የመማጸኑ ጉዳይ የሁለም ኢትዮጵያዊ ጉዳይና ግዴታ መሆን አለበት እንሊሇን።
በዚህም አኳያ
ሁለንም የኢትዮጵያ ልጆች
የኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዴርጅቶች
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች
የኢትዮጵያዊያን የሙያና የማህበርስብ አገልግሎት ማህበራት
ግለሰብ ምሁራን፤ ዋይታቸውን ለአለም ህብረተሰብ ለማሰማት የሚከተሉትን አለም አቀፋዊ መርሀ ግብሮች መሰረት እንዱያደርጉ እንጠይቃለን።
በጎንደር፣ በወሎ፣ በጋምቤላና በሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች ወያኔ የሚፈጽማቸው የዘር ማጥፋትና (genocide) ሌሎችም በዘረኝነት ፖሊሲ ላይ የተመሰረቱ ወንጀሎች (ለምሳሌ ethnic cleansing) በተለያዩ ዓለም አቀፍ ህጎችና ስምምነቶች በጥብቅ የተወገዙ ናቸው። ለምሳሌ በ1949 (እ.አ.አ) በጸደቁት የዥኔቫ ስምምነቶችና በ1992 (እ.አ.አ) የተባበሩት መንግስታት
የጸጥታው ምክር ቤት ያስተሊለፈው ውሳኔ እንዴሚደነግጉት፤
ሀ) በማንኛውም ሰላማዊ ህዝብ ላይ የዘር ግንድን መሰረት በማድረግ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈጸም፣ ህዝብን ከመኖሪያ ቦታ የማፈናቀል፣ የማሳደዴ፣ ግዴያና ግብረ ስጋዊ አመጽ መፈጸም፣ የመሳሰሉ ተግባሮች ወንጀልነታቸው ‚crime against humanity‛ በመባል ይታወቃል።
ለ) እንዱሁም አንዱን ህዝብ ሆን ብሎ ከስፍራው ማፈናቀልና የሌላ ጎሳ ተውላጆችን በምትኩ ማስፈር በዘር ማጥፋት (genocide) ደረጃ የሚፈረጅ ወንጀል መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ በ1992 (እ.አ.አ) ባስተላለፈው ውሳኔ በግልጽ አስቀምጦታል።
ስለሆነም ይህን ጉዳይ ቀዳሚነት ሰጥተንና ከላይ በሀ) እና በለ) የተጠቀሱትን አለምአቀፋዊ ውሎች መሰረት በማድረግ የሚከተሉትን ድርጅቶች በሚቻለው መንገድ ሁሉ እየተገናኘን በህዝባችን እየተፈጸመ ያለን ግፍና በደል በማሳወቅ ረገድ ያልተቋረጠ ዘመቻ እንዲካሂድ እንጠይቃለን።
No comments:
Post a Comment