ያ ትውልድ እና እኛ
እኔ ማለት የዘመን ክስተት ነኝ የሚገርመኝ
ልጅነቴን ሳላውቀው እንደሸኘሁት
ሁሉ ወጣትነቴም ለጎልማሣነት አሣልፍ
ሊሰጠኝ ከጫፍ ያደረሰኝ ሰው ነኝ
ሁሌም የሚገርመኝ እና የሚደንቀኝ ነገር
ስለምን ያ ትውልድ አልፉታን አለ
በራሱ የሚተማመን የራሱን አብዬት ሊያስነሳ
የሚችል የሀገር ፍቅር ስሜት
ከውስጡ የሚፍለቀለቅ ትውልድ ስለምን
መሆን አቃተን እንዴትስ በሁሉም አቅጣጫ
ያ ትውልድ ስለምን ተቆጣጠረን የሚለው
የዘወትር ጥያቄዬ ነው
ልብ በሉ ለሃገር አንድነት አቀንቃኝ ከሆኑት ለብሄር ታጋዮች ከሆኑት እና ሃገርን
ለጥቅም የሚሸጡትን ጨምሮ ሁሉንም ስመለከት የዚህ የኔ ዘመን ትውልድ የለበትም ለማለት እደፍራለሁ እንደውም እጅግ አግራሞት
የሚፈጥርብኝ እንዴት በሁሉም አቅጣጫ የዛ የአስራ ዘጠኝ
ስልሳዎቹ አብዮት የፈጠራቸው የዘመን ክስተቶች የእነሱ አሸብሻቢ ለመሆን ስለምን
ተገደድን ልብ በሉ ግንባር ቀደም ከሆኑት
የብሄር
ታጋዩች እንደነ “ኢጭአት” የአሁኑ ኦነግ እናም ህዋሃትን የመሰሉ እንዲሁም
በሌላው ጉራ ኢሀፓ መኤሶን ደርግን የመሳሰሉ የዛ ዘመን ፍብርኮች ናችው
ከብዙ በጥቂቱ የኔ ንግግር የግድ አዲስ የፓለቲካ ፓርቲ እንመስርት የሚል አይደለም
አጀንዳዬ ስለምን ከገዢ ፓርቲ እስከ ተቃዋሚው ፓርቲ ድረስ የዛ ዘመን አስተሳሰብ
ስለምን ተቆጣጠረን የሚለው ነው ይህንን የአለምክንያት አላልኩትም አዳዲስ ፓርቲ
ከሚባሉት እንደነ ግንቦት ሰባት እና አርበኞች ግንባር እንዲሁም ”አረና”እና “ደምሂት”
እያንዳንዱን ድርጅት በማስተዋል ብትመረምሩዋቸው የዛን ዘመን አብዬት ቀስቃሽ የነበሩና ዋና ተዋናይ
እንደሆኑ ይታወቃ
ከኢሀፓ ወይም ከኢጫት አልያም መኤሶን ወይም የደርግ አባላት የነበሩ ናቸው
እንደ እኔ እምነት ይሄ ትውልድ የሰለጠነ ነው ብዬ አምናለሁ ምክንያቱም በንግግር
በመወያየት ያምናል ስለዚህ መነጋገር የቻለ ትውልድ ደግሞ የሚገራርሙ አስተሳሰቦችን
ማንሸራሸር ይችላል ይህን ማድረግ የማይሳነው ከሆነ ደግም በአስተሳሰቡ ለሁላችን
የምትመች የማትጎረብጥ የማታዳላ የማትከፉፈለዋን የምናልማትን ኢትዬጵያ መፍጠር
ይችላል እመኑኝ በአስተሳሰባችን የምናልማትን
ኢትዬጵያን እንፈጥራታለን ባይነኝ
ታዲያ ስለምን እኛ የዚህ ዘመን ትውልዶች የራሳችንን አሻራ ማሳረፍ ስለም አቃተን አሁን
የሚያስፈልገን ችግራችንን መተረክ ሳይሆን መፍትሄ ማፍለቅ ነው አዲሱን
ወይን በአሮጌ አቁማዳ ማስቀመጥ ለወይኑም ለአቁማዳው ይበጃል ትላላችሁ እስቲ
እንነጋገር
ምናሴ መስፍን
No comments:
Post a Comment