Friday, December 27, 2013

ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊ እንሁን

      ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊ እንሁን

ይች ሃገር ያለመሪ ነው የምትመራው ብል ማጋነን አይሆንብኝም ምክንያቱም ህዝቦች ባላችው መቻቻል እና አብሮ የመኖር ፍቅር ሁሉን አቻችለው እንዲኖሩ አድርጝቸዋል ከሁሉ የሚገርመው መንግስት አንዱን ብሄር ከሌላው ሊያጋጭ የተቻለውን ሁሉ ሲያደርግ በየብሄሩ
ያሉ ምራቃቸውን ዋጥ ያደረጉ የሃገር ሽማግሌዎች ገና ከጥንስሱ ነገሩን ያመክኑታል ልጆቻቸውን እየገሩ ሃገር ማለት ምን ማለት  እንደሆነ እየመከሩ እያስተማሩ ያችን ሃገር  ሀገር ሆና እንድትቀጥል ላደርጉ ለነዛ የሃገር ባለውለታዎች ክብር እና ምስጋና ይሁን እንደ ወያኔዎች ሃሳብማ ገና ወንበር ከመያዛቸው ሃገሪቱ እንደ ሃገር አትቀጥልም ብለው ነበር ለዚህ ነው ሁሌ ሲያስፈራሩን ልትበጣጠስ አንድ ሳምንት የቀራትን ሃገር ከመከፋፈል አዳናት እያሉ ሊዘባነኑብን የሚፈልጉት።
       በመሰረቱ ያቺ ሃገር እንደ ሃገር ልትቀጥል የቻለችው ህዝቦች ባላቸው የዘመናት የመቻቻል ባህል ነው እንጂማ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት የተሰሩብን ደባዎች እንኩዋን ለኛ አለምን ያስገረመ ነው በዓለም ታሪክ የራሱን ህዝብ በተቀናጀ ሁኔታ ያሸበረ የመጀመሪያው መንግስት ወያኔ ።  

ከላይ ያነሳሁት ሃሣባቸው አልሳካ ሲል ሰሞኑን ደግሞ ሌላ መርዶ ሊያሰሙን ደፋ ቀና እያሉ ነው 1200 ኪ ሜትር እርዝመት ያለውን ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት እና የራሳቸውን የአየር ድንበር ለማበጀት መሪ ብለው ባስቀመጡት አሻንጉሊት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ
ህዝብ ሣያውቅ እንደ ወንበዴ ውስጥ ለውስጥ ስምምነት ላይ ለመድረስ ከጫፍ ደርሰዋል 


ጎበዝ ኢትዮጵያ ማለት እኮ ከሁሉ የአፍሪካ ሃገራት የመጀመሪያዋ የካርታ ባለቤት ነች በቅኝ ግዛት ስላልተያዘች League of Nations” ተመስርቶ ሁሉም ሃገራት የራሳቸውን የድንበር ወሰን ሲያቀርቡ ከአፍሪካ ብቸኛዋ ሃገር ኢትዬጵያ ነበረች በተለይ በምስራቅ አፍሪካ ያሉ ሃገራት በሙሉ የእንግሊዝ እጅ ስራዎች ናቸው


እስቲ አስቡት እንዴት ሆኖ ነው ሱዳን እኛ ላይ ቀሪ መሬት ኖሩዋት እንተሳሰብ የሚል ሃሳብ ልታቀርብ  የሞራል ብቃቱ የሚኖራት በየትኛውስ ስሌት ነው ሁሉም ሃገራት የየራሳቸውን የቦታ ይዞታ ሲያቀርቡ ሱዳን ማቅረብ እንኩዋን አልቻለችም ነበር ምክንያቱ ደግሞ ሌላ አይደለም ሰሪዎቹዋ  የቤት ስራቸውን አልጨረሱም እና ነው  

በርግጥ ጉዳዩ አሁን የተጀመረ ባይሆንም ቅሉ የዚን እልባት ለመስጠት ግን ወያኔ ኢሃዴግ አይችልም ሲጀመር ከህዝብ ተደብቆ እንደ ድርዬ ጟሮ ለጟሮ የሚደረግ ስምምነት የትም አይደርስም እያንዳንዳችን ልንቃወመው ይገባል
በርግጥ ኢትዬጵያዊ የሆነ መሪ በትግላችን እስክንመሰርት የነሱ አኩኩሉ ጨዋታ ሳይደርስ እንደርስበታለን

አሁን “ወያኔ” እንደሚያስበው አይደለም ነገሮች ሁሉ አቅጣጫቸውን ለውጠዋል ሁሉም መብቱን ለማስከበር በየጎራው መንቀሳቀሱን ተያይዞታል አንድ የሚያደርገን የሁላችንም ጉዳይ አለ በሃገር ውስጥም ይሁን በውጪ በወያኔ ስራአት ተዋረድን እንጂ ያተረፍነው ነገር የለም

በሳውዲ አረቢያ ወገኖቻችን ያንን ሁሉ ስቃይ አልፈው ለሃገራቸው የበቁት በስርአት አልበኞች የወያኔ ጉጅሌ በሆኑ ወታደሮች ዝርፊያ መንገላታት እንደደረሰባቸው የጉዳቱ ተጠቂ የሆኑ እየገለፁ ነው

አሁን ችግሮቻችን ውርደታችን ስቃዬቻችን በዝተዋል እውነት ነው ሃገራችን ኢትዬጵያ ናት ከሰማይ የሚወርድ ተአምር የለም አሁን ላይ  በፍትህ እና በዲሞክራሲ በጣም የሚያስቀኑ ሃገራት የተፈጠሩት በትግል ነው ስለዚህ እያንዳንዳችን በየራሳችን በምናምንበት መንገድ ሁሉ የትግሉ ተካፉይ እንሁን እኔ ብቻዬን ምን እፈጥራለሁ የሚባል ነገር አይሰራም አንድ ሳይባ                                                                                                                                   ሚሊዮን ላይ አይደረስም መጪው አመት መልካም ነገር የምንሰማበት ተመልካች ሳይሆን  ልተሳታፊ የምንሆንበት ይሁን ባይ ነኝ አበቃሁ     

                                      ምናሴ መስፍን

                                  almazmina@yahoo.com

No comments:

Post a Comment