Saturday, November 15, 2014

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ታሰሩ


በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ለእሁዱ የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የታሰቱትን የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ለመጠየቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄዱት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታሰሩ። 
በቅስቀሳ ወቅት የነበሩት የሰማያዊ አባላትና አመራሮች መያዛቸውን ተከትሎ የእሁዱን የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ለስበስባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ያሳወቁበትን ህጋዊ ደብዳቤ በመያዝ የአባላቱና አመራሩ እስራት ህገ ወጥ መሆኑን ለማስረዳትና አባላቱን ለመጠየቅ ወደ አራዳ መምሪያ ፖሊስ ጣቢያ ያቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ የፋይንስ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወሮታው ዋሴ እና የአደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል። 

በቅስቀሳ ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች እየታሰሩ ነው የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር እሁድ ህዳር
7/2007 ዓ.ም ለሚያደርገው የአደባባይ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና አመራሮች ታሰሩ።

Tuesday, November 11, 2014

ግልጽ ደብዳቤ ”ለጠቅላይ ሚኒስትር” ኃይለማርያም ደሳለኝ : ከታሳሪ ዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች


ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሕገ መንግስታችንን ያክብሩ!

ሠላም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር!? እንዴት ነዎት? ያስታውሱ ከሆነ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢከፊሉ የዚህ ማስታወሻ ፀሃፊዎች  ‘ግልፅ ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ’


“ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እባክዎትን የተለያዩ የመንግስት አካላት የሕገ መንግስታችንን ድንጋጌዎች እየጣሱ ነውና እርስዎም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 74/13/ መሠረት ሕገ መንስቱን የማስከበርና የማክበር ግዴታ ስላለብዎት ሕገ መንግስቱን ያክብሩ” በማለት አንዲት አጭር ደብዳቤ ፅፈንልዎት ነበር፡፡


ድንገት በተለያዩ ምክንያቶች የጻፍንልዎትን ደብዳቤ ካላነበቡት ወይም ማስታወስ ካልቻሉ ዛሬ ይሄን ማስታወሻ ስለምንፅፍልዎት ግለሰቦች አንድ ሌላ ማስታወሻ እንስጥዎ፡ ከ6ወራት በፊት /በሚያዚያ 2006 ዓ.ም/ ሶስት ጋዜጠኞችንና ስድስት ጦማሪያንን ‘ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ በመሞከር ወንጀል ጠርጥሬያችኋለሁ’ በማለት መንግስትዎ ልማታዊ ርምጃ (አብዮታዊ ርምጃ እንደሚባለው) ወስዶ ነበር፡፡

Friday, November 7, 2014

እሥሩ ተጧጡፏል፣ አንድነት ምርጫ እንዳይወዳደር አገዛዙ ይፈልጋል


ግርማ ካሳ

ዜጎች መታሰራቸው እየቀጠለ ነው። በተለይም የአንድነት ፓርቲ አባላት (በጎንደር፣ በትግራይ፣ በመቱ፣ በአዲስ አበባ ፣ በወላይታ ….) ። ብዙዎች ከፍተኛ ደብደባ እየደረሰባቸው ነው። ሕወሃት ፣ በሕዝብ እንደተጠላ ስላወቀ የአንድነት ፓርቲ እንዲዳከም ወይም ከምርጫው ዉጭ እንዲወጣ እየሰራ ነው። አንድነት ሊያሸንፈው እንደሚችል ስላወቀ።

የድርጅቶች መተባበር አስፈላጊ በመሆኑ፣ አንድነት ከመኢአድ ጋር ተስማምቶ የቅድመ ዉህደት ስምምነት ፈርሞ ነበር። ሁሉም ነገር አልቆ ነበር። ሆኖም ምርጫ ቦርድ ወይንም አገዝዙ፣ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ ዉህደቱን አስቁሞታል። ይኸው እስከአሁን ድረስ በአቶ አበባው ለሚመራው መኢአድ እውቅና አልሰጠም ብሎ መኢአዶችን ምርጫ ቦርድ እያጉላላቸው ነው።

የአንድነት ፓርቲ በቅርቡ በድርጅቱ ሕገ ደንብ መሰረት፣ አዲስ አመራር መርጦ መንቀሳቀስ መጀመሩም ይታወቃል። ሆኖ ምርጫ ቦርድ/ ሕወሃት ፣ በንድነት ዉስጥ አስርጎ አስገብቷቸው ከነበሩን በአንድነት እንዲራገፉ ከተደረጉት 2፣ 3 ግለሰቦች ጋር በመመካከር፣ እንደገና ለአዲሱ የአንድነት አመራር እውቅና አልሰጠም እያለ ነው። (የዛሬዉን ሰንደቅ ያንብቡ) ምናልባትም መኢአድ እና አንድነት ከምርጫዉ ሊያግዳቸው፣ አሊያም የነርሱን ሰርተፊኬት፣ ቅንጅትን ለአየለ ጫሚሶ እንደሰጠው፣ ለነ ማሙሸትና እና ለነ ዘለቀ ረዲ ሊሰጣቸውም ይችልም ይሆናል።

Thursday, November 6, 2014

መልዕክት ከቃሊቲና ከቂሊንጦ


ነገረ ኢትዮጵያ

የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ የዝግጅት ክፍል አባላት ወደ ቂሊንጦና ቃሊቲ እስር ቤቶች በማቅናት እስረኞችን ጠይቀዋል፡፡ እስረኞቹ ያስተላለፉትን መልዕክት ነገረ ኢትዮጵያ እንደሚከተለው ጠቅለል አድርጋ አቅርባዋለች፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አይቀርም›› እስክንድር ነጋ

በማህበራዊ ድረ-ገጽም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች መልካም ልደት ለተመኛችሁልኝ ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ፡፡ የቡርኪናፋሶው አምባገነን መውደቁን በመስማቴ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ይህ ለእኔ ውድ የልደት ቀን ስጦታየ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፡፡ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ለውጥ የሚቀር አይደለም፡፡ የእኛ ችግር ከማንም የባሰ ነው፡፡ ቱኒዚያ ላይ የተጀመረው አብዮት ሰሜን አፍሪካ አንቀጥቅጧል፡፡ ኢትዮጵያ ከሰሜን አፍሪካ አገራት ይልቅ ለእነ ቦትስዋና ትቀርባለች፡፡ የቦትስዋና ጉዳይ ሌሎቹንም ማነቃነቁ የማይቀር ነው፡፡ ይህ ለውጡ ቅርብ እንደሆነ የሚያሳይ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ አይቀርም፡፡
‹‹ቂሊንጦም ገደብ አለብኝ›› አብርሃ ደስታ

Monday, November 3, 2014

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር “የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ እራስህን ከወያኔ አሽከርነት(መጠቀሚያነት) ልታርቅ ይገባል” አለ


በህዝብ ላይ የሚደርሰው ጭቆናና እርዛት እስከመቼ?

ከኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ የተሠጠ መግለጫ

የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት ዘወትር ስልጣናቸውን ለማራዘም ካላቸው ነቢራዊ ፍላጎት የተነሳ በህዝብ ላይ ግድያ እና እስር ከመፈፀም አልፈው ሐገራችን ኢትዮጵያን ከማትወጣበት ማጥ ውስጥ ለመክተት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡ በቅርቡ እንኳን በአሶሳ ከተማ ንፁሀን የትግራይ ወጣቶች ማንነታቸው እስካሁን ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል ይኸውም መንግስትእየተከተለው ብልሹ የዘውግ አስተዳደር ዋጋ እያስከፈለ መሆኑ እየታየ ነው በሌላ በኩል ይህ ግድያ መንግስት እራሱ የትግራይ ህዝብን ከጎኑ ለማሠለፍ በማሠብ እንደገደላቸው ግምታቸውን አስቀምጠዋል እንደምክንያት የጠቀሱት ምርጫ 97ን ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ መንግስት ተቃውሞውን ለማባባስ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ከቀድሞዋ የትምህርት ሚኒስቴር ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ግቢ ወደውጭ ቦንብ በመወርወር 6 ፖሊሶችን በመግደል ፖሊሶችን ለማነሳሳት እና ህዝቡን ለማሳሳት ቢሞክርም በመጨረሻ ጉዳዩን የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋ ሲያወጣው የመንግስት ሴራ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የአሶሳው፣ የአምቦው፣ የጎንደሩ እና የወለጋው ግድያም ከዚህ የተለየ አይሆንም፡፡