Thursday, January 17, 2013

ኢትዮቴሌኮም የወያኔ ዘረኝነት ፖሊሰ መንጸባረቂያ መሆኑን የግንቦት ሰባት የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ አጋለጠ


የመረጃ ቴክኖሎጂ መሠረት የሆነዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ አፍሪካ፤ ላቲን አሜሪካና ኢሲያ ዉስጥ የሚገኙ በእደገት ወደ ኋላ የቀሩ አገሮችን ለዘመናት ከተዘፈቁበት የኋለ ቀርነት ማጥ

GINBOT 7 Movement ዉስጥ ጎትቶ አዉጥቶ ወደ ፈጣን የእድገት ጎዳና ይወስዳቸዋል ተበሎ የታመነበትና በአንዳንድ አገሮች ዉስጥ ይህ ለእድገት አመቺነቱ በተግባር የተመሰከረለት ዘርፍ ነዉ። ይህ ዘርፍ ገበሬዉ፤ ሰራተኛዉ፤ ተማሪዉ፤ ወታደሩና ለሌላም በማንኛዉም የስራ ዘርፍ ለተሰማራ የህብረተሰብ ክፍል የእዉቀት ምንጭ በመሆን የስራ ምርታማነቱን እንዲያሳድግ የሚረደና በህብረተሰብ መካከል ፈጣን የሆነ የመረጃ ልዉዉጥ አንዲኖር የሚያደርግ ዘርፍ ነዉ። በእድገት ወደ ኋላ ለቀረችዉ አገራችን ኢትዮጵያም ይሀ ዘርፍ እጅግ በጣም አስፈላጊ የሆነ ዘርፍ ነዉ። ነገር ግን በአፍሪካ ዉስጥ አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ በጣም ወደኋላ ከቀርችባቸዉና ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ዘረኛና አምባገነን አገዛዝ ሆን ብሎ እድገታቸዉ እንዲገታ ካደረጋቸዉ ኋላ ቀር ዘርፎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛዉ ይሄዉ የቴሌኮሚኒኬሺን ዘርፍ ነዉ።
እራሱን “ልማታዊ መንግስት” ብሎ የሚጠራዉ የወያኔ አገዛዝ ስልጣን ከያዘባቸዉ የመጀመሪያዎቹ አመታት ጀምሮ አስከ ቅርብ ግዜ ድረስ እንደ ቤት ዉስጥ ዕቃዉ ከተቆጣጠራቸዉና የኢትዮጵያን ህዝብ በሚጠቅም መልኩ እንዳያድጉ ካደረጋቸዉ ቁልፍ መስሪያ ቤቶች ዉስጥ አንዱ ኢትዮቴሌኮም ነዉ። ወያኔ ኢትዮቴሌኮምን ያላደረገዉ ነገር የለም። ዘረኝነትን በሚጠቅም መልኩ አደራጅቶታል፤ የራሱን ሰዎች ጠቅጥቆበታል፤ ቻይናዎችን አምጥቶ የስለላ ተቋም አድርጎታል፤ የሚገርመዉ ዛሬ ኢትዮቴሌኮም የተራቀቀዉ በስልክ፤ በኢንተርኔትና በሌሎችም የመገናና አገልግሎቶች ሳይሆን ዜጎችን በመሰለልና የመረጃ ጨለማ በመፍጠር ርካሽና ጎታች ስራዎች ነዉ። ይህንን ርካሽ ስራ ደግሞ በቅርቡ የአገዛዙ የኢንፎርሜሺን ደህንነት ኤጀንሲ ሹም ብ/ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ “የኢትዮጽያ ቴሌኮምኒኬሽን” የኀብረተሰቡን ሰላም የሚያጠፉ ዌብሳይቶችን የመቆጣጠርና የኢንተርኔት ድረገጾችና ብሎጎችን የማገድ አቅም ሊኖረው ይገባል፡፡መርሁም ይህ ነዉ በማለት በአዳባባይ አረጋግጧል።

የግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የአገር ዉስጥ ኢንተሊጀንስ ዘርፍ በላፉት አስራ ሁለት ወራት ይህንኑ ኢትዮቴሌኮም በሚል መጠሪያ የሚተወቀዉንና በስለላ ስራ ላይ የተሰማራዉን የሲቪል መስሪያ ቤት አደረጃጀት፤ አወቃቀርና የሰዉ ኃይል አመዳደብ በቅርብ ተከታትሎ ከዚህ ቀትሎ የሚታየዉን መረጃ አጠናቅሯል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሚገባ እንደሚያዉቀዉ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ የኢትዮጵያን ቴሌኮሚኒኬሺን ተቋም ከኋላ ቅርነት ለማላቀቅ በሚል ሰበብ የኮርፖሬሺኑን የማኔጅመንት ዘርፍ ለፈረንሳይ ኩባኒያ መስጠቱ የሚታወስ ነዉ። ወያኔ እንደሚለዉ የኢትዮቴሌኮም ማነጅመንት ለፈረንሳዩ ኩባኒያ የተሰጠዉ የኮርፖሬ ኑን አቅም ለማሳደግ ቢሆን ኖሮ መልካም ነበር፤ ነገር ግን ወያኔ የሚናገረዉና የሚሰራዉ ስራ የተለያየ በመሆኑ ዛሬ ወያኔ ኢትዮቴሌኮም በየዘርፉ የረጂም ግዜ ልምድ ያላቸዉን ባለሙያዎች አባርሮ ታማኝ የህወሀት ታጋዮችን በመተካት ኮርፖሬሺኑን የለየለት የስለላ ተቋም አድርጎታል። ስለሆነም ዛሬ ብዙ የአፍርካ አገሮች ትልቅ ግስጋሴ ያደረጉበትና የዜጎቻቸዉን ህይወት የለወጡበት ዘርፍ ኢትዮጵያ ዉስጥ ዜጎችን እየሰለለ አገረን የመረጃ ጨለማ ዉስጥ የከተተ ተቋም ሆኗል።
ባላፉት ሁለት አመታት የኢትዮቴሌኮም ማነጅመንት ኤን አንድና ኤን ሁለት በሚባሉ ሁለት ከፍተኛ የአስተዳደር እርከኖች ተከፍሎ በሁለቱም ከፍተኛ የአመራር እርከኖች ዉስጥ የሰዉ ኃይል ተመድቧል። ይህ በከፍተኛ ማነጅመንት ደረጃ የተመደበዉ የሰዉ ኃይል ኢትዮጵያዉያንንና የፈረንሳይ ዜጎችን የሚያጠቃልል ነዉ። በኤን አንድና በኤን ሁለት የማነጅመንት ደረጃ የስራ ድርሻ የተሰጣቸዉ ኢትዮኦጵያዉያን በቁጥር 54 ሲሆኑ ከዚህ ዉስጥ 46.3 በመቶ ወይም ሃያ አምስቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። በዚህ ከፍተኛ የማነጅመንት እርከን ዉስጥ የኦሮሞ፤ የአማራና የተቀሩት ስድሰት ክልሎች ድርሻ በቅደም ተከተል 18. 5 በመቶ፤ 29.6 በመቶና 5.6 በመቶ ብቻ ነዉ። ከሁለቱ የማነጅመንት እርከኖች ዉስጥ ኤን አንድ የሚባለዉ ከፍተኛዉ ሲሆን በዚህ እርክን ዉስጥ ሰምንት የትግራይ ተወላጆች ሲኖሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች እያንዳንዳቸዉ ሁለት ቦታ የያዙ ሲሆን በዚህ ከፍተኛ የአመራር እርከን ዉስጥ ከተቀሩት ስድስት ክልሎች የተመደበ አንድም ሰዉ የለም።
ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 194 ሺ የትግራይ ተወላጅ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል። ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያለቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም። ሌላም መራራ ሀቅ አለ። 66 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያቅፉት ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር አርከን ዉስጥ በአመራር ቦታ የተቀመጡ ዜጎች ብዛት አራት ብቻ ነዉ (ሁለት ከኦሮሚያ ሁለት ከአማራ)። ከጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 5.4 በመቶዉ ብቻ ከሚኖርበት ከትግራይ ክልል ግን ስምንት ሰዎች ኤን አንድ በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ተቀምጠዋል።
በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ከተቀሩት ስድስት የአገሪቱ ክልሎች የመጡትን ሰዎቸ ስንመለከት የሚታየዉ ስዕል እጅግ በጣም የሚያሳዝንና ወያኔ የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት እያለ ከሚሰብከዉ ስብከት ጋረ የሚጋጭ ነዉ። በ2012 ከኦሮሚያ፤ ከአማራና ከትግራይ ክልል ዉጭ በተቀሩት ስድስት ክልሎች ዉስጥ የሚኖረዉ ህዝብ 25,627,349 እንደሚሆን ይገመታል። ከዚህ ህዝብ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የመቀመጥ እድል ያገኙት 0.000012 በመቶ ብቻ ወይም ከእያንዳንዱ 8.5 ሚሊዮን ህዝብ አንዱ ብቻ ነዉ። እንግዲህ ይህንን ነዉ ወያኔ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነታቸዉን ተጎናጽፈዋል እያለ የሚናገረዉ።
የግንቦት ሰባት የፍትህ፤ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ከዚህ ቀደም ወያኔ “የኢትዮጵያ መከላከያ” ጦር እያለ የሚጠራዉን ሠራዊት ምን ያክል የኔ በሚላቸዉ የህወሀት ሰዎች ብቻ እንደሚቀጣጠር የሚያሳይ መግለጫ በመረጃ አስደግፎ ለህዝብ ማቅረቡ የሚታወስ ነዉ። አሁንም ወያኔ ኢትዮቴሌኮምን ምን ያክል የራሱ የቤት ዉስጥ እቃዉ እንዳደረገዉ የሚያሳየዉን በጽሁፍና በአኀዝ የተፈገፈ መረጃ በዛሬዉ እለት ለህዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን እየገለጸ ከአሁን በኋላም የወያኔን ዘረኝነትና ህግወጥነት የሚያጋልጡ ስራዎችን በተከታታይ እየሰራ ለህዝብ የሚያቀርብ መሆኑን ይገልጻል።

የጥናቱ እጠቃላይ ውጤት

ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication1
ማስታወሻ: ከላይ በስዕሉ የሚታየው እንደተጠበቀ ሆኖ በኢትዮ-ቴሌኮም ቁልፍ የሃላፊነት ቦታወች ውስጥ ቢያንስ ቢያንስ ወደ 50% የሚሆነው ቦታ የተያዘው በትግራይ ተወላጆች ነው።
ይንንም ለማብራራት ያህል በአሁኑ ሰአት ካለው ጠቅላላ የሃፊነት ቀልፍ ቦታወች 14ቱ በፈረንሳውያን የተያዙ ቢሆንም ከ14 የፈረንሳይ ባለሙያወች ከያዟቸው ቀልፍ ቦታወች ውስጥ 7ቱ በትግራ ተወላጆች እንደሚያዙ ይጠበቃል። ይህም ማለት በትግራይ ተወላጆች የተያዙትን እና የሚያዙትን ቁልፍ የኢትዮ-ቴሌኮም ቦታወች ከተጠቅላለው 64ቱ የሃላፊነት ቦታቸው ውስጥ 32ቱ በትግራይ ተወላጆች የተያዙ ይሆናሉ። ይህም ማለት ከጠቅላላወ የኢትዮ-ቴሌኮም ቁልፍ የሃልፊነት ቦታቸው ውስጥ ግማሹ ማለትም 47% የሚሆኑትን በትግራይ ተወላጆች የተያዙ መሆናቸው ያሳያል።

የጥናቱ ዝርዘር ማብራያ

በዚህ ሰነድ ላይ የተጠቃለሉት ስሞች በኢትዮ ቴሌኮም ዋና መስሪያ ቤት ዉስጥ በሁለት ከፍተኛ (N1 & N2) የአመራር እርከኖች ዉሰጥ የተመደቡ ሰዎች ስምና የመጡበት ብሔር ስብጥር ነዉ። ባጠቃላይ በሁለቱ የአመራር እርከኖች ዉስጥ 68 ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ አስራ ሰባቱ (N1 ዉስጥ 8 N2 ዉስጥ 9) የፈረንሳይ ተወላጆች ነበሩ። ሆኖም ቀስ በቀስ በተደረገዉ መሸጋሸግ የፈረንሳይ ዜጎች የለቀቁት ቦታ እየተመረጠ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ በመሰጠቱ አሁን በN1 ዉስጥ 5 N2 ዉስጥ 9 ባጠቃላይ 14 የፈረንሳይ ዜጎች አሉ ፤ በቅርቡ አንድ ሌላ የፈረንሳይ ዜጋ በኢትዮጵያዊ የተተካ ቢሆንም ይህ ሠኢድ አራጋዉ የተባለ ግልሰብ አማራ ይሁን ትግሬ ለግዜዉ በዉል ለይቶ ማወቅ አልተቻለም። በእርከን አንድ ዉስጥ ስምንት የትግራይ፤ ሁለት የአማራና ሁለት የኦሮሞ ተወላጆች ሲኖሩበት ከሌሎቹ ሰባት ክልሎች የመጣ አንድም ሰዉ በዚህ N1 በሚባለዉ የአመራር አርከን ላይ አልተመደበም። በአጠቃላይ በ N1 የአመራር አርከን ዉስጥ 17 ሰዎች ሲኖሩ አስራ ሁለቱ ኢትዮጵያዉያን አምስቱ ደግሞ የፈረንሳይ ተወላጆች ናቸዉ። ከአስራ ሁለቱ ኢትዮጵያዉያን ዉስጥ ሰባቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። N2 በሚባለዉ የአመራር አርከን ዉስጥ ደግሞ 51 ግለሰባኦች በአመራር ቦታ ላይ የተመደቡ ሲሆን 42 ኢትዮጵያዉያን 9ኙ ፈረንሳዉያን ናቸዉ። ከአርባ ሁለቱ ኢትዮጵያዉያን ዉስጥ አስራ ሰባቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ።
ይህ በከዚህ ቀጠሎ የተቀመጠዉ ግራፍ እና ሰነተረዥ የሚያሳየዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የተቀመጡትን ሰዎች የብሔር ስብጥር ነዉ። ግራፉ የሚያሳየዉ ሦስቱን ማለትም ከኦሮሚያ፤ ከአማራና ከትግራይ ክልል የተመረጡ ሰዎችን ለየብቻቸዉ ሲሆን ከተቀሩት ሰባቱ ክልሎች የመጡት ሰዎች ግን ተጨፍለቀዉ አንድ ላይ ነዉ የቀረቡት።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication2ማስታወሻ: ከላይ በሰንጠረዡ የጠቀሰው የህዝብ ብዛት እኤአ በ2007 CSO ያወጣዉን የህዝብ ብዛት መግለጫ ተንተርስሶ በ2012 የኢትዪጵያ ህዝብ ብዛት 90,076, 661 ይሆናል በሚል ግምት የተቀመረ ነዉ።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication3
በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ የተቀመጡት ሰዎች የብሔር ስብጥር
ከላይ በተቀመጠዉ የህዝብ ብዛት መሠረት በ N-1 እና በ N-2 የአመራር እርከን ኢትዮ ቴኦኮም ከተመደቡ ሰራተኞች ዉስጥ የሚከተለዉን ገሀድ እዉነት መመልከት ይቻላል።
ከእያንዳንዱ 3.3 ሚሊዮን የኦሮሞ ተወላጅ ዉስጥ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ የተሰጠዉ አንድ የኦሮሞ ተወላጅ ብቻ ሲሆን ትግራይን ስንመለከት ግን ከእያንዳንዱ 193.9 ሺ የትግራይ ተወላጅ ዉስጥ ቢያንስ አንድ ሰዉ በኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ተቀምጧል። ይህ የስራ አመዳደብ የትምህርት ችሎታንና ልምድን ተከትሎ የተሰራ ነዉ ቢባል እንኳን የላቀ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ያለቸዉ የኦሮሞ ተወላጆች ቁጥር ተመሳሳይ የትምህርት ደረጃና የስራ ልምድ ካላቸዉ የትግራይ ተወላጆች ቁጥር በአስር እጥፍ መብለጡ ምንም ጥርጥር የለዉም። ሌላም መራራ ሀቅ አለ። 66.2 በመቶ የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚያቅፉት ከኦሮሚያና ከአማራ ክልል N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር አርከን ዉስጥ በአመራር ቦታ የተቀመጡ ዜጎች ብዛት 4 ብቻ ነዉ (2 ከኦሮሚያ 2 ከአማራ)። ከጠቅላላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ዉስጥ 5.4 በመቶዉ ብቻ ከሚኖርበት ከትግራይ ክልል ግን 7 ሰዎች N1 በሚባለዉ ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ ተቀምጠዋል።
ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ የሚያሳየዉ ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-1 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር ነዉ፤ በዚህ ስብጥር ዉስጥ የፈረንሳይ ዜጎችም አሉበት። በ N-1 አመራር እርከን ዉስጥ ከትግራይ፤ ከኦሮሚያና ከአማራ ብሔረሰቦች ዉጭ ከሌሎቹ የተካተተ ማንም የለም።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication4
ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-1 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር
ከላይ ካለው ሰንጠረዥ ላይ እንደምንመለከተዉ በ N-1 የአመራር እርከን ደረጃ ላይ የተቀመጡ ኢትዮጵያዉያን ብዛት አስራ አንድ ሲሆን ሰባቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸዉ። የእነዚህን 7 ሰዎች የስልጣን ቦታ ስንመለከት ደግሞ ሁሉም የያዙት ቦታ ቁልፍ ቁልፋዩን ቦታ ነዉ። ለምሳሌ የፕሮግራም ማነጀር፤ ፕሮግራም ዳይረክተርና የቺፍ ፋይናንሻል ኦፊሰርነቱን ቦታ የያዙት የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ የኦሮሞዉና የአማራዉ ተወላጆች በቅደም ተከተል የህግ አማካሪነቱንና የኢዲተርነቱን ቦታ ነዉ የያዙት።
ከዚህ በታች ያለው ሠንጠረዥ የሚያሳየዉ ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-2 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር ነዉ። በ N-2 ከፍተኛ የአመራር እርክን ዉስጥ ዘጠኝ የፈረንሳይ ዜጎች የሚገኙ ቢሆንም በሰንጠረዡ ዉስጥ የፈረንሳይ ዜጎች ቁጥር አልተካተተም (N-2 ከ N-1 ያነሰ ደረጃ ነዉ)።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication5
ኢትዮ-ቴሌኮም ዉስጥ N-2 በመባል በሚታወቀዉ ከፍተኛ የአመራር እርከን ላይ የተቀመጡትን ባለሙያዎች የብሔር ስብጥር
ኢትዮጵያ ዉስጥ በህዝብ ብዛትም ሆነ በተማረ ሰዉ ሀይል ብዛት ከፍተኛዉን ቦታ የያዘዉ የኦሮሚያ ክልል ነዉ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ከፍተኛዉን የመቀመጫ ቁጥር የያዙት የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ናቸዉ። ሆኖም በሰንጠረዡ ላይ እንደምንመለከተዉ ኢትዮቴሌኮም ዉስጥ በN-1ም ሆነ በN-2 ደረጃ በአመራር ላይ ከተቀመጡት መሪዎች ዉስጥ የኦሮሚያ ድርሻ ከክልሉ ትልቅነት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነዉ ወይም ከትንሿ ትግራይ ጋር ሲወዳደር ቁጥሩ እጅግ በጣም አነስተኛ ነዉ።
በፖለቲካ ሀይል መስክም ቢሆን እንደዚሁ ነዉ። ህወሀት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዉስጥ ያለዉ መቀመጫ ብዛት 8 ብቻ ነዉ። ሆኖም የፖለቲካዉ ጡንቻዉ 178 መቀመጫ ካለዉ ኦህዴድ ጋር ሲወዳደር ሰማይና ምድር ነዉ። ህወሀት የአገሪቱን ጦር ሀይል፤ ፖሊሰ ሰራዊት፤ የደህንነት ተቋምና የኤኮኖሚ መዋቅሮች ይቆጣጠራል። ኦህዴድ ግን ከሰሞኑ እንደማስተዛዘኛ ከተወረወረለት የይስሙላ ምክትል ጠ/ሚኒስትርነት ዉጭ ይህ ነዉ የሚባል የፖለቲካ ጡንቻ የለዉም።
ከሦስቱ ክልሎች ማለትም ከአማራ፤ ከኦረሚያና ከትግራይ ክልሎች ዉጭ በሌሎቹ ስድስት ክልሎች ዉስጥ 25,627,349 ያክል ህዝብ እንደሚኖር ይታመናል። ኢትዮቴሌኮም ዉስጥ በ N- 1 ከፍተኛ የአመራር ቦታ ላይ የእነዚህ ሰባት ክልሎች ድርሻ ሦስት ብቻ ነዉ። እንግዲህ ዜጎች በሞያቸዉ በሚሰሩት ስራ፤ በፖለቲካ ህይል አሰላለፍና በኤኮኖሚዉ ዘርፍ ዉስጥ በሚጫወቱት ሚና እንዲዚህ አይነት አይን ያወጣ አድሎ የሚደረግባቸዉ ከሆነ ወያኔ ኢትዮጵያ ዉስጥ ፈጠርኩት የሚለዉ እኩልነት ምኑ ላይ ነዉ? የባህል ዘፈን መዝፈን ከሆነ እንደዛሬዉ በቴሉቪዥን አይታይም እንጂ ድሮም እንዘፍናለን።
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication6
ethio telecom, ethiopian telephone and mobile communication8

No comments:

Post a Comment