ምንሊክ ሳልሳዊ
የጎንደር ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብሶታቸውን በከፍተኛ ቁጣ ገልጸዋል።
- ለወያኔ ባለስልጣናት የቀረበው ሪፖርት እንደሚያሳየው ስልጠናው ምንም የስኬት ፍንጭ አላሳየም።
- የሃምሳ አመት እቅድ ለምን አስፈለገ የስልጣን ጥመኝነትን ያሳያል።
- ለሶስተኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ እየተካሄደ ነው።
- በኢሕአዴግ ውስጥ ያሉ አመራሮችም ይሁኑ አባላቶቹ የአስተዳደር ብቃት የላቸውም።
- ኢትዮጵያውያን በህግ ፊት እኩል የሚሆኑት እና ፍትህ የሚነግሰው ቀን እንናፍቃለን።
- በቫት ስም መንግስት ዘረፋ ይዟል በህጉ ቫት አይከፈልበትም የተባለው የጤና ዘርፍ ሳይቀር ቫት እየቆረጠ ነው።
በየአከባቢው እየተካሂደ ያለው ልማታዊነትን ሽፋን አድርጎ የስልጣን ማስረዘሚያ ሰበካ (ስልጠና) እንደቀጠለ ቢሆንም በህዝቡ እና በአሰልጣኞች መካክል ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት ከመከሰቱም በላይ ህዝቡና ተማሪው በአገራችን ጉዳይ ከኢህአዴግ ጋር ልንግባባ አልቻልንም ስለዚህ አበል ይቅርብን እና ስልጠናውን አቋርጡልን በማለት እየጠይቀ መሆኑን ዘገባዎች አመልክተዋል። ሰልጣኞች እንደሚሉት እየተካሄደ ያለው ስልጠና ሳይሆን የፖለቲካ ሰበካ ነው ይህ ደሞ የተለያየ አስተሳሰብ ያላቸውን ህዝቦች ለማደናቆር ካልሆነ በስተቀር ተቀባይነት የለውም። ስለዚህ የያዛችሁን ስልት ቀይራችሁ ህዝብ መሃል ግቡና አናግሩን እንጂ በ አበል እና በቀበሌ ጥቅማጥቅም አታስገድዱን፡ አያዋጣችሁም ሲሉ ተናግረዋል።