አዎ ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠንቀቁ! ትልቁ ስጋት እሱ ነው
መነሻ
ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ሰንደቅ ጋዜጣ በሚያዝያ 1/2006 ዓ.ም እትሙ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያወጣው ቃለ መጠይቅና ሀተታ ነው :: ሶስቱም አስተያየት ሰጭዎች “ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ነው:: ስለዚህም መንግስት ሊያፈርሰው ነው ” የሚለው ወቅታዊ ዜና ምንጩ ከየት እንደሆነ ግልጽ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል :: በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ ወርቁ ጉዳዩን “በሬ ወለደ ነው” ብለው ሲያጣጥሉት ፣ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ደግሞ ” የዚህ ወሬ ምንጩ ከየት እንደሆነ አናውቅም” ሲሉ ተመሳሳይ ነገር ተናግረዋል።
ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዴ?
በ 1955 እ. ኤ. አ የተመሰረተውና መቀመጫውን በኔዘርላድና በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው Open Doors : Serving Persecuted Christians Worldwide የተሰኘው ግዙፍ ድርጅት 2013 እ. ኤ. ኣ ባወጣው World Watch List ላይ ክርስትያኖችን በማሰቃየት በ63 ነጥብ ኢትዮጵያ 15ተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝና ፣ ለዚህም ስቃይ ዋና ተዋናይ ከሆኑት አካላት አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ጽፎ ፣ ሊስቱንም በመላው ዓለም በትኗል ። ይሄው በመላው ዓለም በድረ ገጽና በተለያዩ ኤለክትሮኒክ ሚድያዎች (hard and soft copy) የተበተነው ሪፖርት ከመስክ የመረጃ ሰራተኞቼ ፣ ከምሁራንና ከሰላዮቼ አገኘሁ ባለው መረጃ መሰረት አቶ መለስ ዜናዊን ሞት ቀደማቸው እንዲ ማኅበረ ቅዱሳንን እንክትክቱን ሊያወጡት አቅደው እንደነበረ ፣ ቀጣዩም ግዜ ማኅበረ ቅዱሳን የሚገንበት ግዜ እንደሚሆንና ይሄም ለተሐድሶዎች አስቸጋሪ ግዜ ስለሚሆን ከማኅበረ ቅዱሳንን እንዲጠበቁ እንዲህ በማለት ያትታል
“The death of Prime Minister Meles Zenawi, who sought to crush Mahibere Kidusan, the fanatical group inside EOC, is considered a big blow for the renewal movements. Zenawi was not a supporter of those movements, but his actions against Mahibere Kidusan for political survival were considered by the EOC renewal movements as helpful for less squeeze. His replacement, Haile Mariam Desalegn, does not possess the political and religious background required to confront the fanatical group. Mahibere Kidusan is currently riding high and…. In addition to this, the death of the EOC leader is a big shock for the renewal movements as he was reluctant to take action against them. “
ይሄው ዓለማቀፋዊ “የክርስትያኖች እንባ ጠባቂ” ነኝ የሚለው ድርጅት ማኅበረ ቅዱሳን በመንግስት የደህንነት መዋቅር ውስጥ ዘልቆ እንደገባና የመንግስትን ስልጣን በመቆጣጠር በተለይ “የተሐድሶን ቡድን ” ለማጥፋት መነሳቱን በዚህ መልኩ ሪፖርቱ ላይ ገልጾታል
(MK) normally monitor the churches. The fanatic group inside the EOC (Mahibere Kidusan) has to be mentioned here. Particularly Open Door Field experts report that the group is now a growing threat for non-traditional protestant churches and renewal movements with in the EOC. The group ( MK) allegedly has an ambition to influence and control the government policies to restrict the activities of other religions. There are reports that Mahibere Kidusan has managed to infiltrate the government security and administrative apparatus. In the absence of a powerful leader and the death of a relatively moderate patriarch (late leader of EOC) the next move of the group is nervously watched.
እስካሁም “ያዋጣናል ፤ ማኅበሩን ለመምታት ጥሩ መላ ነው” ብለው ያሴሩት “ማኅበሩ አስራት ይወስዳል፣ ግብር አይከፍልም ፣ ሕንጻ ገንብቷል ወዘተ” የሚል ነበር። ማኅበሩ አስራት እንደማይወስድ ፣ ሂሳቡንም በተመሰከረላቸው የሂሳብ ባለሙያዎች ኦዲት በማስደረጉና ከግብርና መሰል ክፍተቶች የጸዳ መሆኑን በማረጋገጡና የውንጀላ ክፍተት በመጥፋቱ ሌላ ዜማ ጀምረዋል። አሁን ደሞ ክሱ “ማኅበሩ መንግስት ደህንነት መዋቅር ውስጥ ገብቶ ሊያፈርሰን ነው” የሚል ሆኗል።ይሄም እንደማያዋጣ ያወቁት እኩያን አሁን ደሞ የመጨረሻ ጥይታቸው ተቀይሯል። ማኅበሩ ፖላቲካ ውስጥ ገብቷል እና መንግስት ወዮልህ አይነት ዝባዝንኬ።
እናም ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠንቀቁ !
ይሄው ሪፖርት ኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተ ክርስትያን ውስጥ ገብተው፣ ቤተ ክርስትያንን እየገዘገዙ ላሉ ራሳቸውን ተሐድሶ ብለው ለሰየሙ ውስጠ ተኩላ ወገኖቹ ያስተላለፈው ጥሪ አንድ ነው :: “አክራሪው ማኅበረ ቅዱሳንን እየበረታና እየጠነከረ ስለሄደ የሚቀጥሉት አመታት ለተሐድሶዎች እጅግ አስቸጋሪ ነውና … ማኅበረ ቅዱሳንን ነቅታችሁ ጠብቁ:: ከዚህም ስጋት የመነጨ ይመስላል ግብረ አበሮቻቸው ማኅበረ ቅዱሳንን ለማወክ ያለ የሌለ ሃይላቸውን አስተባብረው መንጫጫት ከጀመሩ ሰነባተዋል
Now, in his absence and with the government’s reduced leverage, this fanatic group (Mahibere Kidusan) appears to be taking charge. The coming months may bring difficult times for the renewal movements inside the EOC…the next move of the group is nervously watched.
ይሄ ድርጅት መንደርተኞች የፈጠሩት የሰፈር እቁብ አይደለም:: በመላው ዓለም ኔት ወርክ ያለው መሰረተ ሰፊ ድርጅት ነው:: የሚያወጣቸውንም ሪፖርቶች ሚሊዮኖች ያነቡታል:: የኢትዮጵያ “ክርስትያኖችን ዋይታ” በተመለከተ ያወጣው ጽሁፍ ግን ይገርማል:: ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ክርትስትያኖች ተገድለዋል:: ተሳደዋል:: አብያተ ክርስትያናትም ተቃጥለዋል:: ገዳማትም ተደፍረዋል:: ክርስትና ለሚገደው አካል እነዚህ ብዙ የሚያስጽፉ ነበሩ:: ይሄ ሪፖርት ግን ያተኮረው ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ነው:: የማኅበሩም ወንጀሎች ብሎ ሊነገረን የሚፈልገው አንድ ነገር ” ማኅበረ ቅዱሳንን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን ትምህርትና ዶግማ አፍርሰው ወደ ሌላ እምነት ድርጅት ለመቀየር የተነሱ ተሐድሶዎችን አላስቀምጥ አለ:: ለተሐድሶ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆነብን “ የሚል ነው:: እንግዲህ የማኅበሩ ወንጀል ይሄ ነው:: ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር የተናገሩትንም አስተያየት ጠምዝዞ ” ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሞት ቀደማቸው እንጂ ሊያፈራርሱት ነበር” በማለት እውነቱን ሳይሆን ምኞቱን ተርኮልናል:: የሚገርመው ” ማኅበረ ቅዱሳንን በማፍረስ ሂደት ጉልህ ሚና አልተጫወቱምና ተተኪው ጠቅላይ ሚኒትር አቶ ኃይለማርያምን “አቅም ያነሳቸው” እስከማለት ደፍሯል:: ፓትርያርክ ጳውሎስንም ” ተሐድሶ ላይ እጃቸውን ማንሳት የማይፈልጉ ለዘብተኛ” ሲል አሞግሷቸዋል:: እንደዚህ ድርጅት ዘገባ ቤተ ክርስትያንን ለመሰርሰር ሰርገው የገቡ መናፍቃን ሰማዕታት ሲሆኑ፣ የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም በሚል ለቤተክርስትያን ትውፊትና እምነት መጠበቅ የሚደክመውን ማኅበረ ቅዱሳንን ደግሞ አሸባሪ ፣አክራሪ የሚል የስም ጥላሸት እንዲቀባ ተደርጓል:: እንግዲህ የማህበረ ቅዱሳን ወንጀሉ ይሄ ነው::
ማኅበረ ቅዱሳን ወሳኝ ሃይል ሆኗል
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ማኅበረ ቅዱሳንን በአክራሪነትና በነውጠኛነት የመፈረጁ አባዜ በአካዳሚክ ጽሁፎች ላይም እየታየ ነው :: ለምሳሌ የዶክተር ጥበበ እሸቴን የዶክትሬት ማሟያ ጽሁፍ ማንሳት ይቻላል:: ዶክተር ጥበበ በ 1960ዎቹ ውስጥ በነበረው የተማሪዎች እንቅስቃሴ ተሳትፎ የበራቸው እና በኋላ ደግሞ የፕሮቴስታንቱን ዓለም በመቀላቀል በዛው ድርጅት ውስጥ የአስተዳደር ቦታ እስከመያዝ የደረሱ ሰው ናቸው:: እኚህ ሰው 2009 ላይ The Evangelical Movement in Ethiopia : Resistance and Resilience በሚል ርዕስ የጻፉትን የዶክትሬት ሟሟያ ጽሁፋቸውን አሳትመዋል:: በዚህ አወዛጋቢ መጽሐፍ ዶክተር ጥበበ ማህበረ ቅዱሳንን militant, aggressive, anti evangelical በማለት ጥላሸት በመቀባት አንባቢን የሚያደናግር አንቀጽ አስፍረዋል:: ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ ነው ነገሩ::
The emergence of a highly aggressive and more militant movement that arose with in the Orthodox Church under the name of Mahibere Kidusan in recent years should be seen in multidiscrusive context… (Mahibere Kidusan) as a nationalistic and strongly anti-evangelical movement enjoying the backing of some orthodox conservative intellectuals and elements of the urban youth , the new religious strain is becoming a significant force
ዶክተር ጥበበ ለምን ዓላማና በምን መረጃ militant ( ነውጠኛ) anti evangelical (ጸረ ወንጌል) እሰከማለት እንደደረሱ ባላውቅም እሳቸውም ግን ገና በ2009 ማኅበረ ቅዱሳን significant force ሆኖዋልና አስቡበት ሲሉ አስገንዝበው ነበር:: ምንም እንኳን ዶክተር ጥበበ እሸቴ በዚህ ጥናታዊ ጽሁፋቸው ላይ በርካታ አመኔታ የሚጎድላቸው ነጥቦችን ቢያስነብቡንም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ውስጥ፣ ቤተክርትስያኗን ወደ ሌላ እምነት ድርጅት ለመቀየር በስውር የሚሰሩ የተጠናከሩ ህቡዕ ቡድኖች እንዳሉና ተጽኗቸውም በሰንበት ትምህርት ቤቶች፣ በየማህበራቱ ፣ በየአጥቢያ ቤተክርትያንቱ እንዲሁም ገዳማቱን ሳይቀር መታየት መጀመሩን የውስጥ አዋቂ በሚመስል ሁኔታ እንዲህ በማለት ገልጸውታል::
Today, many underground movements are operating with in Ethiopian Orthodox Church, some with evangelical and others with Pentecostal convictions. ..Some of these movements exemplify attempts at religious innovation, though it is hard to plot their trajectories because of their hidden nature and complex character. Such developments are affecting wide ranging areas of the established structure of the Orthodox institutions, such as Sunday Schools, the mahibers, the monastic centers, and even the local churches in major cities.
የፕሮቴስታንቱ ዓለም ፓስተሮችም ከ34,000 የማያንሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አብያተ ክርትያናት ውስጥ ገብተው ቤተ ክርስትያኗን ወደ ፕሮቴስታንቱ ዓለም ለመገልበጥ አባላትን እየመለመሉና ስልጠና እየሰጡ እንደሆነ በጀብዱ መልክ በአደባባይ እየተናገሩ ነው::
The evangelist is hopeful that the seeds of revival are being planted and nurtured in the estimated 34,000 Orthodox churches in Ethiopia and abroad. So far more than 600 people have successfully completed the two-week course.
አልፎ ተርፎም ማኅበረ ቅዱሳንን ባይኖር የተሐድሶ እንቅስቃሴ ቤተክርትያኗን ሙሉ ለሙሉ ይቆጣጣራት እንደነበር በይፋ እየተጻፉ ነው:: ማኅበረ ቅዱሳንም ላይ ጥርሳቸውን የሚያገጫግጩት ለዚህ እኩይ ዓላማቸው እንቅፋት ስለሆነባቸው ነው ።ለዚህም ዓላማቸው ስኬት ማኅበረ ቅዱሳንን ሊያፈስርና ሊበትን የሚችል ዘርፈ ብዙ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ:: ቤተ ክህነቱ ውስጥ በገንዘብ የገዟቸው ቅጥረኞቻቸው ማኅበሩን ለማፍረስ የቻሉትን ያህል ሄደዋል::
ግን ከኪሳራ ውጭ ማኅበሩ ላይ ምንም ያመጣው ጉዳት አለመኖሩ ያሳሰባቸው አካላት አሁን ደግሞ ቤተ ክህነቱ ውስጥ ሰግስገው ላስገቧቸው ቅጥረኞቻቸውና በገንዘብ ለገዟቸው ይሁዳዎች የመጨረሻ ትንቅንቅ እንዲያደርጉ እንደላኳቸው በየቀኑ የምናየው ሃቅ እየሆነ ነው::
ዝነኛው ጋዜጠኛ ተመስገን ዘውዴ የማኅበረ ቅዱሳን የመጨረሻዎቹ ቀናት በሚል ርዕስ በቅርቡ ባስነበበን ግሩም ጽሁፍ ላይም የማኅበሩ ተቃዋሚዎች ቤተ ክህነት ውስጥ አዳራሽ ተፈቅዶላቸው ማድረጋቸውንና የአቋም መግለጫ እስከማውጣት መድረሳቸውን እንዲህ ሲል ነበር ያስነበበን
ለመጽሔቱ ዝግጅት ክፍል የደረሰው በድምፅ የተቀረፀ የውይይቱ ሙሉ ክፍል እንደሚያስረዳው፣ ተሰብሳቢዎቹ ማኅበሩን በተመለከተ ያወጡት የአቋም መግለጫ÷ የማኅበሩና የዋነኛ መሥራቾችናአባላት የባንክ አካውንት፣ ቀላልና ከባድ ተሸከርካሪዎች ጨምሮ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች፣ ት/ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት፣ የአክስዮን ተቋማት፣ የንዋያተ ቅድሳት ማምረቻዎችና ማከፋፈያዎች፣ከቀረጥ ነጻ የገቡና በመግባት ላይ ያሉ ዕቃዎች በሚመለከታቸው የመንግሥት መሥ/ቤቶች እንዲታገዱበቅ/ሲኖዶስ አማካይነት ደብዳቤ እንዲጻፍ፤ ከምእመናን በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ የሚቀበለውዓሥራት እየፈረጠመበት ስለኾነ እንዳይቀበል ይከልከል፤ የግቢ ጉባኤያት(የከፍተኛ ትምህርትተቋማት) እርሱ በሚቀርፀው ትምህርት እንዳይወሰዱብን በደንብ መሥራት፤ ተጠሪነቱ ከዋና ሥራአስኪያጅነቱ ሥር ወጥቶ በሰንበት ት/ቤቶች ማ/መምሪያ ውስጥ አንድ ንኡስ ክፍል ይኹን የሚሉናየመሳሰሉት ይገኙበታል፡
ይሄን የአቋም መግለጫ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው የተሰብሳቢዎቹ አንዱና ዋና እቅድ “የግቢጉባኤያት(የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) እርሱ በሚቀርፀው ትምህርት እንዳይወሰዱብን በደንብመሥራት፤ ” የሚል ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ለየግቢ ጉባ ኤያት ቀርጾ ያዘጋጀው ሥርዓተ ትምህርት እና መመርያ መጻሕፍቱ በሙሉ ይታወቃሉ። ቢጋሮቹም ፣ መጻሕፍቱም በሊቃውንቱ ታይተው የተመረመሩና የታረሙ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ናቸው። እርሱ በሚቀርጸው ትምህርት እንዳይወሰዱብን ማለት ትርጉሙ ምንድነው? ይሄ እንግዲህ እየተካሄደ ያለው ቤተ ክህነት አፍንጫ ና ብብት ስር ነው።
ማኅበረ ቅዱሳን የኔ ነው ! ያንተ ነው! ያንቺ ነው! የኛ ነው!
ምንም እንኳን ቤተ ክርስትያን ከፈተና ተለይታ ባታውቅም ቅድስት ቤተ ክርስትያናችን አሳሳቢ ፈተና ውስጥ ወድቃለች። ከአውሮፓና አሜሪካ ድረስ ሳይቀር ድርጎ የሚታሰብላቸው ሆድ አምላኪዎች የቤተ ክርስትያንን አባቶችን ክብር በማጉደፍ፣ የቤተ ክርስትያንን ትውፊትና ትምህርት በመገዝገዝ፣ ቤተ ክርስትያንን ወደ መናፍቃኑ ጎራ ለማስረከብ ሌት ተቀን እየሰሩ ይገኛሉ። በተለይም ራሳቸውን ተሐድሶ በሚል የሰየሙ ቡድኖች ቤተ ክርስትያኗን ለማፍረስ ቆርጠው ተነስተዋል። ለዚሁ እኩይ ዓላማቸው መሳካት ማኅበረ ቅዱሳን እንቅፋት ስለሆነባቸው ከምሁር እስከ ተርታው አባል ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ዘመቻ ከፍተዋል። የማኅበሩን ስም ለማጥፋት በርካታ ብሎጎች ሥራ ላይ ውለዋል። ብዙ ብር ወጥቶባቸው መጻሕፍት ታትመዋል።ህሊናቸውንና ሃይማኖታቸውን በብር በሸጡ ይሁዳ የቤተ ክህነት ሰዎችም ማኅበሩን ለመምታት ዘርፈ ብዙ ሙከራ ተደርጓል። አንዱም ማኅበሩን ለማፍረስ አቅም ባይኖረውም።አረቦቹ እንደሚተርቱት ውሾቹ ይጮሃሉ።ግመሉ ግን ይጓዛል።
እኛስ ለሃይማኖታችን የሚገደን ኦርቶክሳውያንስ ምን እያደረግን ነው? ማኅበረ ቅዱሳን የቤተክርስትያን እጅ ነው። የቤተ ክርስትያን አካል ነው።ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር የሚደረግ ትግል ሁሉ ቤተ ክርስትያንን ለመጣል የሚደረግ ሰይጣናዊ ትግል ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚታወጅ ጦርነት በሙሉ ቤተ ክርትያን ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው ።ማኀበረ ቅዱሳንንም ኢላማ ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ዋነኛ ምክንያት፣ ይሄ ትውልድ ስለ ኦርቶክሳዊ ማንነቱ የላቀ ግንዛቤ እንዲኖረው ማስተማሩና ከቤተ ክርስትያን ጎን መቆሙ ነው ። የማኅበረ ቅዱሳን ጥንካሬ የቤተ ክርስትያን ጥንካሬ ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚቀሰሩ ጣቶች በሙሉ ቤተ ክርስትያን ላይ የሚቀሰሩ ጣቶች ናቸው ።ስለዚህ ማኅበሩ ላይ የሚደረጉ ትንኮሳዎች ቤተ ክርስትያን ላይ እይሚደረጉ ትንኮሳዎች ናቸውና እያንዳንዳችን ኦርቶዶክሳውያን ቆመን ማሰብ አለብን አለብን።
ማኅበረ ቅዱሳን ይፈርሳል እንዴ ?
“ማኅበረ ቅዱሳን ይፈርሳል” ብለው ለሚቃዡ ሰዎችም እውነታውን አውቀውት ከወዲሁ እርማቸውን እንዲያወጡ ትንሽ ልበል። ዛሬ እኮ የትኛውም ዓለም ብትሄድ የማኅበረ ቅዱሳን ሴል (Cell) የሌለበት ክፍለ ዓለም የለም።ኢትዮጵያ ውስጥ እያንዳንዱ ቀበሌ ድረስ ” እምቢ ለቤተክርስትያኔ” የሚሉ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት አሉልህ።ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ እያንዳንዱ አብያተ ክርስትያናት ውስጥ ለቤተክርስትያን ሁለንተናዊ እድገት ነቅተው የሚሰሩ የማኅበሩ አባላት አሉ ። የማኅበሩ መመርያ እንደሚያዘው እያንዳንዱ የማኅበር አባል የሰንበት ትምህርት ቤት አባል ነው። የትኛውም ቤተ ክርስትያን ሰበካ ጉባኤ ውስጥ ቤተ ክርስትያንን ባላቸው አቅም ለማገልገል ቁርጥ አቋም ያላቸውየማኅበሩ አባላት አሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ የትኛውም የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅት ውስጥ የማኅበሩ አባል የሌለበት የለም ። እያንዳንዱ መስሪያ ቤት ያለ ተቀጣሪ የማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖና አሻራ የሌለበት የለም ። የማኅበሩ ቋሚ አባል ባይሆን እንኳን የማኅበሩ ግን ሙሉ ደጋፊ ነው ።ወይም በዘመኑ ቋንቋ ስትፍቀው ማኅበረ ቅዱሳናዊ ነውማኅበረ ቅዱሳን በየቀኑ ለቤተክርትስያንን ጉዳይ የሚንገበገብ ፣ የሚያስብ ትውልድ ፈጥሯል።ይህ ትውልድ ማኅበረ ቅዱሳናዊ ነው። ቢመረንም ፤ቢዋጠንም።
ከኢትዮጵያም ውጭ የማኅበሩ ቅርንጫፍ የሌለበት ቦታ የለም። በተለይ በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ። ዛሬ ዛሬ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ የሚደረጉ የማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤያት ከሀገር ውስጡ የማይተናነሱ እየሆኑ ነው። በዓረቡ ዓለምና በዕሥያ ያለው የማኅበሩ እድገትም ቀላል አይደለም። የትኛውም ክፍለ ዓለም ላይ የቤተ ክርስትያን ጉዳይ የሚገደው በቤተ ክርስትያን ጉዳይ ዝም የማይል የማኅበረ ቅዱሳን ሕዋስ አለ። ባጭሩ ማኅበሩ global ሆኗል። ወይ ደግሞ ነፋስ ሆኗል።አትይዘው አትጨብጠው። ነፋስ የማይነፍስበት ቦታ እንደሌለ ሁሉ ማኅበሩ የሌለበት ቦታ የለም።ማን ነበር ማኅበረ ቅዱሳን የሃሳብ መስመር ( Imaginary line) ሆኗል ያለው። ማኅበረ ቅዱሳንን ልዝጋው ብሎ የሚያስብ አላዊ እንኳን ቢመጣ አዲስ አበባና በየዞኑ ያለውን ጽፈት ቤት ሊዘጋ ይችል ይሆናል።ማኅበረ ቅዱሳንን ማጥፋት አይችልም:: ዋናው የማኅበሩ ሥራ የሚሰራው በያንዳንዷ ደብር ፣ በየሰበካ ጉባኤው ፣ በየሰንበት ትቤቱ ፣ በየ አባላቱ ቤት ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚያመጣው ለውጥ insignificant ነው። ሰሜን አሜሪካ ያለው ማዕከል ብቻውን አዲስ አበባ ያለው ማስተባበርያ የሚሰራውን ሥራ የምስራት አቅም አለው። እድሜ ለኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዛሬ አሜሪካ ሆነህ በያንዳንዱ ቀበሌ ፣በያንዳንዱ አጥቢያ ያለውን አባል ለቤተ ክርስትያን ሥራ ማስተባበር ከባድ አይደለም። It is a click or one call away. ማኅበሩ በአንድ የጸሎት ቋንቋ የሚናገሩ ፣ በአንድ የእምነት ልብ የሚመሩ ፤ እንደ አንድ ቃል ተናገሪ እንደ አንድ ልብ መስካሪ የሆኑ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኦርቶክሳውያን ስብስብ ነውና እንዲህ በቀላሉ እንደ አንቧይ ካብ አትንደውም።ብትሰረስረውም መሰረቱ ጠንካራ አለት ነውና አታፈርሰውም። ከሁሉም በላይ የማኅበሩ ጠባቂ እመብርሃን ናትና ገና ይሄ ማኅበር ያድጋል። ይሰፋ
No comments:
Post a Comment