Sunday, April 27, 2014

“እኛም ከሚሊዮኖቹ ውስጥ ነን”

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)
Ethiopian People's Congress for United Struggle (Shengo) www.ethioshengo.org shengo.derbiaber@gmail.com

“እኛም ከሚሊዮኖቹ ውስጥ ነን”

  ሚያዝያ 19፣ 2006
 (ኤፕሪል 27፣ 2014)

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)፣ በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እየተቀነባበረ በሚካሄደው “የሚሊዮኞች ድምፅ” ንቅናቄ ውስጥ “እኛም ከሚሊዮኞቹ ውስጥ ነን” በማለት ለተጀመረው እንቅስቃሴ ሙሉ ድጋፉን እንደሚሰጥ ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። በዚህም መሠረት የዚህ እንቅስቃሴ አካልነታችንን በተግባር ለመግለፅ በአዳማ (ናዝሬት) የሚካሄደውን እንቅስቃሴ በስፖንሰርነት ለመደገፍ እድሉ ስለገጠመን እጅግ ደስተኛ ነን።

ሸንጎ በተደጋጋሚ እንደገለጸው፣ በሀገራችን ውስጥ የሰፈነው የግፍ፣ የአድልዖና የከፋፋይነት ሥርዓት ማብቃት አለበት። ሥርዓቱ የሀገሪቱን ሕዝብና ሁሉንም የሀገሪቱን አካባቢ በከፍተኛ አደጋ ላይ ጥሏል። ኢትዮጵያን የባሕር በር የሌላት ከማድረግ ጀምሮ ዜጎቿን እርስ በርስ በጥርጣሬ እንዲተያዩ አልፎም እያንዳንዱ ዜጋ ያለፍትኅ እየተጎተተ የሚታሠርበት፣ የሚደበደብበት፣ ከሥራና ከንብረቱ የሚፈናቀልበት ሀገር እስከመሆን ደርሰናል። ገዥው ቡድንና ሥርዓቱ የሚመራበት ፖሊሲና ተግባሩ እንኳንስ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ፣ ለራሱ ለሥርዓቱ ደጋፊዎች የማይበጅ ኢንደሆነ ሁሉም የሚገነዘበው ነው።

Thursday, April 24, 2014

ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ

ከሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተላለፈ ጥሪ


ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ምሁራን መፍለቂያ ለመሆኗ አለም ይመሰክርላታል፡፡ አንቱ የተባሉ ምሁራንን በማፍራት ለዓለም አበርክታለች፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በአለም ካሉ ታላላቅ ዩንቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት እስከ አመራነት ድረስ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች መገኘታቸው ነው፡፡ እነዚህ ምሁራን በተሰማሩበት ስራ መስክ የሚያስመዘግቡት ውጤት እና በስራቸው ተሸላሚ መሆን ላነሳነው ሀሳብ ማጠናከሪያነት ያገለግለናል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነውና ልብ የሚሰብረው ግን ሀገራችን ከእነዚህ ውድ ልጆቿ ተገቢውን ዋጋ አለማግኘቷ ነው፡፡ ሀገራችን የወላድ መካን እየሆነች ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሆነ ተብሎ የሚቀነባበር ሴራ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡

Wednesday, April 23, 2014

ካልገደሉ አያቆሙንም – ሃብታሙ አያሌዉ (የአንድነት አመራር) ሰልፉን በተመለከተ

ካልገደሉ አያቆሙንም  (የአንድነት አመራር) ሰልፉን በተመለከተ

ሀገር የመገንጠል ዓላማ ይዞ የተነሳው የህወሓት ጁንታ፣ በስውር እና በአደባባይ የጫካ ልማዱን መሰረት አድርጎ ሲገድል መኖሩ አዲስ


ባይሆንም፣ ከሰሞኑ መረር ያለ እርምጃ ‹‹ግድያ›› ማሰቡን ከጓዳው የወጣ የወሬ ምንጭ ደረሰን፡፡
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ አስተዳደር ጽ/ቤት ተገኝቼ ነበር፡፡ የመገኘቴ ዓላማም የፊታችን እሁድ 

ሚያዚያ 26 የሚደረገውን

ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ የዕውቅና ደብዳቤውን ለመስጠት የተያዘውን ቀጠሮ በማክበር ነበር፡፡
የሰላማዊ ሰልፍ እውቅናን በተመለከተ ኃላፊ የሆኑት አቶ ማርቆስ ፎርም እንዲሞላ አዘዙ፤ የተባለውን ፎርም ሞላን፤ ያን ጊዜ የአቶ


በጎንደር 30 ሺህ ቤቶች እንደሚፈርሱ ታወቀ - ‹‹በከተማዋ ውጥረት ነግሷል››

በጎንደር 30 ሺህ ቤቶች እንደሚፈርሱ ታወቀ - ‹‹በከተማዋ ውጥረት ነግሷል››

Saturday, April 19, 2014

የኢሕአዴግ የደህንነት ሚ/ር አቶ ጌታቸው አሰፋ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር ሆነዋል * ዘረፋው ቀጥሏል

የኢሕአዴግ የደህንነት ሚ/ር አቶ ጌታቸው አሰፋ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር ሆነዋል * ዘረፋው ቀጥሏል

dollar
በኢትዮጵያ ውስጥ በከፍተኛ ስልጣን እርከን ላይ የተቀመጠ እና በሙስና አልተዘፈቀም የተባለ ቢኖር ደፍሮ ይህ ነው የሚል የለም። ከራሳቸው ስም ጀምሮ እስከ ዘመድ አዝማዶቻቸው ወዳጅ ጓደኞቻቸውን ሳይቀር በዘረፋ ውስጥ በማመሳጠር ያሰማሩት የወያኔ ባለስልጣናት ተቆጥረው አያልቁም። ከትንሽ የቀበሌ ካድሬ ጀምሮ ልከክልህ እከክልኝ ብላ እንብላ መውደቂያህን አሳምር ወዘተ እየተባለ የህዝብ ሃብቶች የሃገር ውስጥ እና የውጪ ባንኮችን አጨናንቀዋል።
የወያኔ ባለስልጣናት የሆኑና ከቤተሰቦቻቸው ከዘመድ ወዳጆቻቸው ጀርባ ሆነው ከፍተኛ የዘረፋ ስራ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የሚተገብሩ በአደባባይ ግን እንደ ንጹሃን ምንም እንዳሌለባቸው መታየት የሚፈልጉ ያሻቸውን ነገር በስልክ ቲዛዝ አሊያም በተላላኪ ደህነንቶች የሚያስፈጽሙ እንደ ደብረጺሆን ገ/ሚ ሳሞራ የኑስ አባይ ወልዱ በረከት ስምኦን ሃይለማርያም ደሳለኝ እና የተወሰኑ 3 % የሚሆኑ የሕወሓት አመራሮች ሃገሪቷን እየዘረፉ ይገኛሉ።
ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እና የሕወሓት አመራሮች በዘረፋ ስራ ላይ መሰማራታቸው ሳያንስ ከተለያዩ የዘረፋ ቡድኖች ጋር የተሳሰረ ግንኙነት /ኔትወርክ/ በምስራቅ አፍሪካ ዘርግተዋል ። ከአውሮፓ እና ከኢሽያ የሚነሱ የማፊያ ቡድኖች እና እጽ አዘዋዋሪዎች እና ህገወጥ ነጋዴዎች ጋር በመመሳጠር ሃገሪቷን የህገወጦች መተላለፊያ ከማድረጋቸውም በላይ ኮንትሮባንድን በህግ ሽፋን እየተገበሩ ሃገሪቷ ማግኘት ያለባትን እንዳታገኝ ለግል ጥቅማቸው በመሯሯጥ ዘረፋውን አጧጡፈውታል።

Tuesday, April 15, 2014

ያገር ጉዳይ ሲነሳ

                        ያገር ጉዳይ ሲነሳ        ከምናሴ መስፍን
                                                                                       almazmina@yahoo.com

«  ኢትዮጵያ አገሬ ሞኝነሽ ተላላ          
የሞተልሽ ቀርቶ  የገደለሽ በላ »
ቀኝ ጌታ  ዮፍታሄ ንጉሴ
(1887 1939)

የምድሪቷ ብእረኞች ቀድሞ የማየት አቅም ያላቸው ከአጥብያ  ኮኮብ ብርሃን የበለጠ ተወረውረው፣ ነገን አይተዋል ከሚባሉት ቀደምት ፈርጦች መካከል ተጠቃሹ ዮፍታሄ ንጉሤ አንዱ ነበሩ፡፡   ታሪክ ራሱን   ሲደግም ማየት አለመታደል በመሆኑ፣ እኒህን ጎምቱ ደራሲ የነገራችን መነሻ አደረኳቸው ።

ከሀገራችን የታሪክ ውቅያኖስ በማንኪያ ስንጨልፍለት ብዙ ያለፉ ዘመናት ክፉና በጎ ትዝታዎች ከፊታችን ድቅን ያላሉ፡፡ በኢትዮጵያና በፋሽስት ኢጣሊያ ጦርነት ወቅት የነበረውም እውነታ ላብነት ያህል የሚጠቀስ ነው፡፡ ይሄ ዘመን ከአገር ፍቅርና ጥቅም ይልቅ የግል ጥቅምና እራስ ወዳድነት ይቅደም የሚለው አስተሳሰብ በጉልህ ተንጸባርቆ የታየበት ክፉ ወቅት ስለነበረ ሁሌም ይታወሰናል፡፡ ነገርን ከስሩ ውሃን ከጥሩ እንዲሉ  በማይጨውና በተንቤን ኢትዮጵያውያን ተዋጊዎች ከመሶሎኒ  ታንክ ጋር በጎራዴ ተፋልመው በመርዝ ጋዝ  

Monday, April 14, 2014

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ ! ፪

ስለፍትህ ሲባል ስርዓቱ ይፍረስ! ፪ 

በዚህ ርዕስ ሥር ባለፈው ሳምንት በይደር ካቆየሁት ተከታይ ጽሑፍ በፊት አንድ እርምት የሚያሻው ጉዳይን በአዲስ መስመር ላስቀድም፡፡
ሬዲዮ ፋና እና “አምደኞቹ”
Temesgen-Desalegn4
ተመስገን ደሳለኝ
በ1988 ዓ.ም በኤፈርት ባለቤትነት ስርጭቱን አሀዱ ያለው “ሬዲዮ ፋና”፣ ከምስረታው አንስቶ ዛሬም ድረስ ልክ እንደ በረሃው ዘመን ሁሉ የሥርዓቱ ቀኝ እጅና የርካሽ ፕሮፓጋንዳው ማስተላለፊያ ቱቦ ሆኖ መዝለቁ ለወዳጅም ለጠላትም የማያከራክር ገሀድ የወጣ ሐቅ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተወሰኑ የግል ሚዲያዎች ላይ የርግማን ዘመቻ የታወጀ ይመስል ለተከታታይ ሳምንታት “ስመ-ጥር” ረጋሚዎችን ጣቢያው ድረስ ጋብዞ ማብጠልጠልና ማውገዙን ቀንደኛ ሥራው አድርጎ ይዞታል፡፡ በርግጥ ይህ ዘመቻ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የፕሬስ ድርጅት በኩል በ“ጥናት” ስም የወጣው ውንጀላ ቅጥያ ሲሆን፣ በቅርቡ ኢቲቪ ሰርቶ እንዳጠናቀቀው የሚነገርለት ዶክመንተሪ ፊልም ደግሞ “ሳልሳዊ” ዘመቻ ሆኖ ለጥቆ የሚቀርብ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

Sunday, April 13, 2014

አዎ ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠንቀቁ! ትልቁ ስጋት እሱ ነውና

አዎ ማኅበረ ቅዱሳንን ተጠንቀቁ! ትልቁ ስጋት እሱ ነው

መነሻ
ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ሰንደቅ ጋዜጣ በሚያዝያ 1/2006 ዓ.ም እትሙ ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ያወጣው ቃለ መጠይቅና ሀተታ ነው  :: ሶስቱም አስተያየት ሰጭዎች “ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ነው:: ስለዚህም መንግስት ሊያፈርሰው ነው ” የሚለው ወቅታዊ ዜና ምንጩ ከየት እንደሆነ ግልጽ እንዳልሆነ ጠቅሰዋል :: በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበበ ወርቁ ጉዳዩን “በሬ ወለደ ነው” ብለው ሲያጣጥሉት ፣ የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ ደግሞ ” የዚህ ወሬ ምንጩ ከየት እንደሆነ አናውቅም” ሲሉ ተመሳሳይ ነገር ተናግረዋል።Mahibere Kidusan EOTC
ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው እንዴ?
በ 1955 እ. ኤ. አ የተመሰረተውና መቀመጫውን በኔዘርላድና በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው  Open Doors : Serving Persecuted Christians Worldwide  የተሰኘው ግዙፍ ድርጅት 2013 እ. ኤ. ኣ ባወጣው World Watch List ላይ ክርስትያኖችን በማሰቃየት በ63 ነጥብ ኢትዮጵያ 15ተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝና ፣ ለዚህም ስቃይ ዋና ተዋናይ ከሆኑት አካላት አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ ጽፎ ፣ ሊስቱንም በመላው ዓለም በትኗል ። ይሄው በመላው ዓለም በድረ ገጽና በተለያዩ ኤለክትሮኒክ ሚድያዎች (hard and soft copy) የተበተነው ሪፖርት ከመስክ የመረጃ ሰራተኞቼ ፣ ከምሁራንና ከሰላዮቼ አገኘሁ ባለው መረጃ መሰረት አቶ መለስ ዜናዊን ሞት ቀደማቸው እንዲ ማኅበረ ቅዱሳንን እንክትክቱን ሊያወጡት አቅደው እንደነበረ ፣ ቀጣዩም ግዜ ማኅበረ ቅዱሳን የሚገንበት ግዜ እንደሚሆንና ይሄም ለተሐድሶዎች አስቸጋሪ ግዜ ስለሚሆን ከማኅበረ ቅዱሳንን እንዲጠበቁ እንዲህ በማለት ያትታል

ሕወሓት ከምርጫ 2007 በኋላ ጠቅላይ ሚ/ር ለመቀየር አስቧል – ሃይለማርያም ውጣ፤ ቴዎድሮስ ግባ?

ሕወሓት ከምርጫ 2007 በኋላ ጠቅላይ ሚ/ር ለመቀየር አስቧል – ሃይለማርያም ውጣ፤ ቴዎድሮስ ግባ?

ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም አቶ መለስን ለመምሰል ቢሞክሩም፤ በሕወሓቶች ዘንድ ግን ማስመሰላቸው ሊዋጥላቸው አልቻለም
ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም አቶ መለስን ለመምሰል ቢሞክሩም፤ በሕወሓቶች ዘንድ ግን ማስመሰላቸው ሊዋጥላቸው አልቻለም

በሃገር ቤት የሚታተመው አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ እንደዘገበው ገዢው ፓርቲ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በሙስና ስም የ“ማጥራት ዘመቻ” ማካሄዱን ተከትሎ በመንግሥት ሥልጣን ላይ በሚገኙ የፓርቲው አመራሮች መሐል ተከስቷል በተባለ አለመተማመንና መጠራጠር መስፈኑ ካድሬዎችን በእጀጉ እንዳስጨነቀ ተጠቆመ። ኢህአዴግን ለመሰናበት የሚፈልጉ በርካታ ካድሬዎች “ለምን” በሚል የሚቀርብላቸውን ጥያቄ ለመመለስ በመቸገራቸው ብቻ በፓርቲውን ውስጥ ለመቆየት መወሰናቸውንም ውስጥ አዋቂ ምንጮች ገልጸዋል።