Wednesday, February 26, 2014

“ ነውራቸው ክብራቸው ”

          
    “ ነውራቸው ክብራቸው ”
                                                 
                                                 
        

በዚህ ሰሞን ከረዳት ካፕቴን ኀይለመድህን አበራ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አስተያየቶች ሳነብና ሳዳምጥ ነበር።  ካነበብኩት መካከል  አንዱ ላይ ድንገት አይኔን አሳረፍኩኝ። በርግጥ  በወያኔ ካድሬዎች የተፃፈው ነበር። ረዳት ካፕቴን ኀይለመድህን አበራ  የኢትዩጵያን ክብር አዋረደ የሚል አስተያየት። ግን  ኢትዮጵያ የተዋረደችው እውን  በኀይለመድህን ወይስ  እራሱ ወያኔ መንግስት ነኝ ብሎ አገራችንን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነው???

ህውሀት በአገራች ላይ የማይቆጠር በደልና ውርደት የፈፀመ አምባገነን መንግስት ለመሆኑ የማይረሳ ቢሆንም የቅርብ ጊዜውን በኢትዩጵያዊያን ህሊና ከማይረሳው ክፉ ትዝታዎች መካከል እስቲ ጥቂቶቹን ላስታውሳቸው።  መቼም እነርሱ አድርገውና አጥፍተው እንዳልተደረገ ሆነው መቅረብ  ጠባያቸው ነው       “ ታሪክ ይቅር የማይለው ውርደት” ነው ።

Sunday, February 23, 2014

ውሽት ልማዳቸው

    ውሽት ልማዳቸው 


በየዘመናቱ የዘመን ክፍተት ሆነው ያለፍ በርካታ ጀግኖችን ከታሪክ ለማወቅ ችለናል በዘመናችንም ለማየት በቅተናል በአመዛኙ የታሪክ ተመልካች እንጂ በታሪክ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ የሚደፍርም ጥቂት ቢሆን ከሁሉ የከፉው ደግሞ ከነኝህ ጥቂቱ አሻራ አሳራፊ ውስጥ
ለስልጣናአቸው ማራዘሚያ ሲሉ የታሪክ ጀግኞችን ስራ ሲደብቁ ህልምና ራዕያቸውን ሲሸፍኑ ማየት ከምንም በላይ ያሳምማል።

አሁን ባለንበት ዘመን መተኪያ የሌላ ነፍሳቸው ገብረው ለዛውም ከነ ህይወታቸው ራሳቸውን
አቃጥለው ለህዝቤ ነፃነቱን ስጡ ብለው ራሳቸውን መሰዋት ሲያደርጉ አንባገነኞች ግን የተለመደውን ስም እየለጠፉ ሲላቸው የአይምሮ በሽተኛ ነው ብቻ ደስ ያላቸው ስም ለጥፈው ራሳቸው እንዳሻቸው በሚያሻሩት ሚዲያ የጀግናው ስራ አፈር ከድሜ ያበሉታል።

Saturday, February 8, 2014

ጩኸታችን ለማን ? ለሀገራችን ወይስ ለፓለቲካ ድርጅታችን?

ጩኸታችን ለማን ? ለሀገራችን ወይስ ለፓለቲካ ድርጅታችን?     
                                                                                 
                                                               
ደርግ ውድቀት በኋላ አቆጥቁጦ የነበረውን ያንን የሕዝብ ተስፋና እምነት መለስ ብለን ስንቃኘው፣ ያ ብዙ የተጠበቀበት ተስፋውና እምነቱ ፍሬ አፍርቶ የታየበት ሳይሆን ቀርቷል። ይልቁንም ትግሉ ለዲሞክራሲና ለነጻነት የሚካሄደው ትግል አፍዝ አደንግዝ የተጠናወተው ሆኖአል። ሕዝቡ ያለ አንድነትና ሕብረት ነፃነት ሊኖረ አይችልም እያለ ቢጣራም፣ የሚደርስለት በማጣቱ ራሱን በራሱ በምቸገረኝነትና በግዴለሽነት እራሱን በተስፋ መቁረጥ አዘቅት ውስጥ ሊጥል ተገዷል።

ስለዚህ፣ ዛሬ የኢትዮጵያን ሕዝብ ስቃይና መከራ መልሰን መላልሰን ማላዘን ሳይሆን ከግፍና ከመከራ ማዕበል የመውጫውን    ብልሃት ማመንጨትና መተግበር ላይ ማትኮር ግድ ይለናል። በተለይም ‘በፓለቲካው መሪነት ላይ ያሉት’ ምን ማድረግና ማከናውን እንዳለባቸው ራሳቸውን መልሰው በዝርዝርና በጥልቀት መመርመር ግድ ይላቸዋል። አማራጭ በማይገኝበት በህብረት ትግል ውስጥ ሆኖ የዘረኛውን የወያኔን ስርአት መጣል የውዴታ ግዴታችን ነው። አለመታደል ሆኖ ግን በፓለቲካ ድርጅት መካከል ህብረት ሳይሆን መለያየት፣በጋራ አገር ማሰብን ሳይሆን የእኔ ብቻ ባይነት፣መገፋፋትና መነቃቀፍ በመሃላችን ነግሶ ይታያል።